TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.9K photos
1.5K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ማስጠንቀቂያ

" ሲሪስ አፕል ጁይስ " 100% የተሰኘው ጭማቂ በውስጡ ጎጂ የሆነ ከሻጋታ የመነጨ መርዛማ ኬሚካል ስለተገኘበት ምርቱን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ማሳሰቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

በፍራፍሬዎች ላይ የሚከሰት ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በሲሪስ አፕል ጁይስ ውስጥ 100% ስለተገኘ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማስጠንቀቂያ ተላልፏል።

ምርቱ የዓለም አቀፍ የምግብ ደህንነት ማስጠንቀቂያ በዓለም አቀፍ ደረጃ ምርቱ ጥቅም ላይ እንዳይውል ባለስልጣን መ/ቤቱ ያስጠነቀቀ ሲሆን፥ በተመሳሳይ የሲሪስ አፕል ጁይስ አምራች የሆነው የደቡብ አፍሪካ የምግብና የመጠጥ አምራች ምርቱ ማይኮቶክሲን የተሰኘው ከሻጋታ የሚመነጭ መርዛማ ኬሚካል በውስጡ በእንዳለ በመግለጽ ህብረተሰቡ እንዳይጠቀመው ነው ያሳሰበው፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድሃኒት ባለስልጣን ፥ ህብረተሰቡ የሲሪስ አፕል ጁይስ 100% ምርት በሀገራች ገበያ ውስጥ እንዳለ በመገንዘብ ምርቱን እንዳይጠቀም አስጠንቅቆ ÷ ምርቱን በማንኛውም አጋጣሚ ገበያ ላይ ሲገኝ በፌዴራል ደረጃ በነጻ ስልክ መስመር በ8482 እንዲሁም በአቅራቢያ ለሚገኙ የክልል ተቆጣጣሪ አካላት ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት ማስተላልፏል።

#ሼር #Share

@tikvahethiopia
#Puratos : ፑራቶስ የኢትዮጵያን ገበያ ተቀላቀለ።

ፑራቶስ ኢትዮጵያ ዛሬ በአዲስ አበባ የገነባውን ልዩ የፈጠራ ማዕክል ማስመሩቁን ለቲክቫህ በላከው መልዕክት አሳውቋል።

ፑራቶስ ኢትዮጵያ ዛሬ ያስመረቀው ወሎ ሰፈር አካባቢ ያስገነባውን የዳቦ፣ ኬክና ሸኮሌት ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካ እና ልዩ የምግብ ፈጠራ ማዕከል ነው።

የኩባንያው ዋና ስራ አፈፃሚ ዶሚኒክ ኤድዋርዶ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር በዓለም ላይ የታወቀው "ፑራቶስ የንግድ ስያሜ (brand) የኢትዮጵያን ገበያ በመቀላቀሉ ደስታ እና ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አዲሱ ፋብሪካ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የፈጠራ ማዕከል እያደገ የመጣውን የደንበኞችን የጥራት ፍላጎት ለማሟላት ቁልፍ ነው ብለዋል።

ፑሩቶስ ኢትዮጵያ ሀገር ውስጥ ያሉ የኬክና ዳቦ ባለሞያዎች፣ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች ፣ ሱፐር ማርኬቶች እና ሬስቶራንቶችን የሚያገለግል ሲሆን በተጨማሪ የጅቡቲ ፣ ሱዳን ፣ ሱማሊያ እና ኤርትራ ሃገራትን ፍላጎት ለማሟላት ዕቅድ እንዳለው ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

ፑሩቶስ በእኤአ 1919 ቤልጂየም ውስጥ የተቋቋመ ባለቤትነቱ የቤልጂየም የሆነ የምግብ አቀናባሪ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ከ100 በሚበልጡ ሀገራት ውስጥ ቅርንጫፍ አለው፤ በአሁን ሰዓት በአፍሪካ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ደ/አፍሪካ እና አይቮሪኮስት ውስጥ እየሰራ ይገኛል።

@tikvahethiopia
#USA : ከሰዓታት በኃላ የአሜሪካ ፕሬዚዳን ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዋይት ሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ፡፡

ፕሬዝዳንት ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኃባ አንድን የአፍሪካ አገር መሪ ተቀብለው ሲያነጋግሩ ይህ የመጀመሪያቸው ይሆናል፡፡

ጄን ሳኪ (የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ) ሁለቱ መሪዎች “ዴሞክራሲንና የሰብአዊ መብቶችን በመክላከል ሰላምና ደህንነትን ማስከበርና የምጣኔ ሀብት እድገትን በማምጣት እንዲሁ የከባቢ አየር ለውጥ” ዙሪያ ይነጋገራሉ ብለዋል፡፡

ኬኒያ የተመድ የጸጥታው ምክር ቤት የወቅቱ ተረኛ ፕሬዚዳንት ነች፡፡

ሁለቱ አገሮች የሚገናኙት አሜሪካ በሰሜን ኢትዮጵያ ባለው ግጭት ተሳታፊ በሆኑ ወገኖች ላይ ማእቀብ ለመጣል እያጤነች ባለበት ጊዜ መሆኑም የአሜሪካ ድምፅ ዘገባ አመልክቷል።

@tikvahethiopia
" ከ5 ዓመት በላይ በወሰን ማስከበር ምክንያት ሳይፈርሱ የቀሩ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወስዷል " - የቦሌ ወረዳ 14

ከገርጂ ሮባ እስከ መብራት ሀይል ከ5 ዓመት በላይ በወሰን ማስከበር ምክንያት ሳይፈርሱ የቀሩ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 አስተዳደር አስታወቀ።

ከገርጂ ሮባ-መብራት ሀይል ያለው የመንገድ ስራ ባለመጠናቀቁ ነዋሪዎች ለረጅም ጊዜ ጥያቄዎችን ሲያነሱ ቆይተዋል ያለው ወረዳው በዛሬው ዕለት ግን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት እርምጃ ተወስዷል ሲል አሳውቋል።

ግንባታዎቹ ከገርጂ ሮባ ዳቦ እስከ መብራት ኃይል ላለው የመንገድ ግንባታ በታቀደለት ጊዜ ላለመጠናቀቅ እንቅፋት ሆነው መቆየታቸውን ወረዳው ገልጿል።

@tikvahethiopia
#ETHIOPIA😷

ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 ተጨማሪ 38 ዜጎችን በኮቪድ-19 ሳቢያ አጥታለች።

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የጤና ሚኒስቴር ይፋ ባደረገው ሪፖርት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 38 ሰዎች ሲሞቱ ከተደረገው 8,253 የላብራቶሪ ምርመራ ደግሞ 778 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል።

የዛሬው ሪፖርት እንደሚያሳየን 650 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#ጥንቃቄ 😷 #TikvahFamily

@tikvahethiopia
#Turkey : ቱርክ ተዋጊ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ እና ለሞሮኮ ለመሸጥ መስማማቷን 4 የመረጃ ምንጮች ገለፁልኝ ሲል ሮይተርስ ዘግቧል።

አንድ ስማቸው ያልተገለፀ የቱርክ ባለልስጣን ለሮይተርስ በሰጡት ቃል፥ ኢትዮጵያ እና ምርኮ የመለዋወጫ አቅርቦትና ስልጠናን ባካተተ ስምምነት " ባይራክታር TB 2 " የተባሉ የጦር አውሮፕላኖችን ለመግዛት መጠየቃቸውን ተናግረዋል።

ስማንቸው እንዲገለፅ የልፈለጉ አንድ ዲፕሎማት ደግሞ ሞሮኮ ግንቦት ወር ላይ ያዘዘቻቸውን ተዋጊ አውሮፕላኖችን መረከቧን አሳውቀዋል።

ዲፕሎማቱ ፥ ኢትዮጵያም የሰው አልባ አውሮፕላኖችን ከቱርክ ለመግዛት ጥያቄ አቅርባ ትእዛዙን ምን ደረጃ ላይ እንዳለ አይታወቅም ብለዋል።

ኢትዮጵያ፣ ሞሮኮ፣ ቱርክ ስለስምምነቱ ምንም ያሉት ነገር ባይኖርም ሮይተርስ ግን ስምምነቱን በደንብ ከሚያውቁ የመረጃ ምንጮች ዝርዝር መረጃ እንዳገኘ ዘግቧል።

2 የግብፅ የፀጥታ ምንጮች አሜሪካ እና አውሮፓ ህብረት ሽያጩን ለማስቆም ሀገራቸው መጠየቋን ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ሌላ ምንጭ ደግሞ የሽያጩ ስምምነት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማደስ ጥረት እያደረጉ ያሉት ግብፅና ቱርክ ውይይት ሊደረግበት ይገባል ብለዋል።

ቱርክ ለኢትዮጵያና ሞሮኮ የምትሸጣቸው የመከላከያ እና የአቪዬሽን ቁሳቁሶች ባለፉት 2 ወራት መጨመሩን ይፋዊ መረጃዎች ቢያሳዩም ስለ ድሮን የቀረበ መረጃ የለም።

የቱርክ የወጪ ንግድ ምክር ቤት መረጃ እንደሚያሳየው እኤአ 2021 የመጀመሪያ 3 ወራት 51 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የመከላከያ እና አቪዬሽን ቁሳቁስ ሸመታለች።

ግብይቱ በነሃሴ እና መስከረም ከፍተኛ ጭማሪ ማሳየቱን ሮይተርስ ገልጿል።

የዜና ወኪሉ፤ ከመከላከያና ከጠ/ሚ ፅ/ቤት በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት ጥረት እንዳደረገ ነገር ግን እንዳልተሳካለት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ENDF : ዛሬ ምሽት የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው ፥ " አሸባሪው ህወሀት የጀመረውን ማጥቃት ፤ በማያዳግም ሁኔታ እንቀለብሳለን " ብሏል።

ሚኒስቴሩ ከ3 ቀናት በፊት TPLF ጦርነት አውጆ በሁሉም ግንባር ውጊያ መክፈቱን ይህንንም በራሱ አባላት አንደበት መግለፁን ፤ እራሱ በከፈተው ውጊያም እየተቀጠቀጠ መሆኑን በመግለጫው ላይ ገልጿል።

መከላከያ ሚኒስቴር፤ ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀው ህወሓት ከሠኞ ጀምሮ ውጊያ መክፈቱንና እራሱ በጀመረውም ውጊያ አይቀጡ ቅጣት እየደረሰበት መሆኑንም አክሏል።

ሰራዊቱ ዛሬ ባወጣው መግለጫ የህወሓትን ጥቃት የመመከት ውጊያ እያካሄደ መሆኑን ገልጾ ፥ የጠላትን ወራሪ ሀይል መመከት ብቻ ሳይሆን እየደመሰሰ የኢትዮጵያን ደህንነት እና ህልውና የማስከበር ታሪካዊ ሀላፊነቱን እየተወጣ በጠላትም ላይ ከባድ ኪሳራ እያደረሰና ሽንፈት እያከናናበ መሆኑ አሳውቋል። ይህንንም ገድል አጠናክሬ ቀጥላለሁ ብሏል።

* ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Masha በማሻ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ።

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን የመቅደላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳውቋል።

ገደቡ የተጣለው የሀገሪቱን እና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ለህዝቡ ደህንነት ሲባል መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ የእንቅስቃሴ ገደቡን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ በማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሞተርና ባጃጅ ከምሽቱ 1 ሰዓት በኃላ እንዲሁም ማንኛውም ሰው ከ2 ሰዓት በኃላ መንቀሳቀስ እንደማይችል አሳስቧል።

የእንቅስቃሴ ገደቡ ከደሴ-ማሻ የሚሰሩ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን አይጨምርም ተብሏል።

ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት እንዲሁም በድንገተኛ ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የእንቅስቃሴ ገደቡን የሚተላለፍ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ፖሊስ አስጠንቅቆ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
ለአካል ጉዳተኞች በአይነቱ ለመጀመርያ ጊዜ በተከታታይ ለሶስት ቀን ሲሰጥ የነበረው የፈጠራ አቅም ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

ከጥቅምት 1 እስከ 3/2014 በተከታታይ ለሶስት ቀን ለአካል ጉዳተኞች (PWD) እንደ አገር በፈጠራ ሥራዎች እንዲሰማሩ የሚያግዝ ሁሉን አቀፍ የፈጠራ ፖሊሲ እንዲኖራቸው ለገበያ የሚቀርቡ ክህሎቶችን እና የግል ብራንዲንግን ለፖሊሲ ተሟጋችነት ለማሳደግ የሚያስችል በአይነቱ የመጀመርያ የሆን ስልጠና በሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች (Indigenous Innovation -I2) የበጎ አድራጎት ድርጅት ከCIPE ጋር በመተባበር ተሰጥቷል።

በስልጠናው መጨረሻ ላይ የስልጠና ተሳታፊዎቹ ድርጅቶቹ በስልጠናው ቀጣይነት ላይ እንዲሰሩ እና በኢትዮጵያ የኢኖቬሽን የፖሊሲ ማሻሻያ አካል ጉዳተኞችን ያካተተ እንዲደረግ ለአካል ጉዳተኞች ፍትሃዊ ተሳትፎ በመሟገት አምባሳደር ለመሆን ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#USA : ከሰዓታት በኃላ የአሜሪካ ፕሬዚዳን ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ በዋይት ሀውስ ተቀብለው ያነጋግራሉ፡፡ ፕሬዝዳንት ባይደን የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ከሆኑ በኃባ አንድን የአፍሪካ አገር መሪ ተቀብለው ሲያነጋግሩ ይህ የመጀመሪያቸው ይሆናል፡፡ ጄን ሳኪ (የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ) ሁለቱ መሪዎች “ዴሞክራሲንና የሰብአዊ መብቶችን በመክላከል ሰላምና ደህንነትን ማስከበርና የምጣኔ ሀብት…
ባይዳን እና ኬንያታ ምን ተወያዩ ?

ትላንት ለሊት የአሜሪካው ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የኬንያውን ፕሬዝደንት ኡሁሩ ኬንያታን በዋይት ሐውስ ተቀብለው አነጋግረዋል።

ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በወጣው መረጃ ሁለቱ መሪዎች በአሜሪካ እና በኬንያ መካከል ባለው ጠንካራ የተባለ ወዳጅነት ዙሪያ ተወያይተዋል።

በውይይታቸው በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ ውስጥ ላሉ ግጭቶች ሰላማዊ መፍትሄ መገኘት አለበት በሚለው ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተነጋግረዋል።

ሁለቱ መሪዎች ዲሞክራሲ እና የሰብዓዊ መብቶች ጥበቃ እንዲሁም አህጉራዊ ሰላም እና ደኅንነት በማስጠበቅ ዙሪያ ሁለቱ አገራት በጋራ በሚያከናውኗቸው ተግባራት ዙሪያ ተነጋግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፕሬዝደንቶቹ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በጋራ ለመግታት የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ለማምረት ሊያደርጉ ስለሚችሉት ትብብሮች ተወያይተዋል።

ፕሬዝደንት ባይደን ለአፍሪካ ሕብረት አገራት የጆንሰን ኤንድ ጆንስን ምርት የሆነው 17 ሚሊዮን ክትባት እንደሚሰጡ አስታውቋል።

Credit : BBC

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ

ከትላንትና በስቲያ በደቡብ አፍሪካ ግዛት በሆነቸው Port Elizabeth በሶማሊያ ዜጎች እና በደቡብ አፍሪካ የPort Elizabeth የታክሲ ባለንብረቶች መካከል ግጭት ተነስቷል።

በተፈጠረው ግጭት እስካሁን በሰው ሕይወት የደረሰ ጉዳት እንዳለ ባይታወቅም በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

የግጭቱ መነሻ በአካባቢው ያሉ የታክሲ ባለንብረቶች ከሶማሊያዊ የሱቅ ባለቤት ጋር በተፈጠረው አለመግባባት እንደሆነ በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ገልፀዋል።

በዜጋቸው ላይ የደረሰውን በደል የሰሙ በተለያየ ቦታ የሚገኙ የሶማሊያ ተወላጆች ግጭት ወዳለበት ስፍራ እንዳቀኑ እና በቦታው ካሉ የታክሲ ባለንብረቶች ጋር ግጭት ውስጥ እንደገቡ የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ።

ያለው ውጥረት ረገብ እስኪል ድረስ በአካባቢው የምትኖሩት (የTikvah-Ethiopia ቤተሰቦች ) ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እራሳችሁን እንድትጠብቁ እና ጥንቃቄ እንድታደርጉ ለማለት እንወዳለን

Faya (Tikvah-family)
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia