TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Puratos : ፑራቶስ የኢትዮጵያን ገበያ ተቀላቀለ።

ፑራቶስ ኢትዮጵያ ዛሬ በአዲስ አበባ የገነባውን ልዩ የፈጠራ ማዕክል ማስመሩቁን ለቲክቫህ በላከው መልዕክት አሳውቋል።

ፑራቶስ ኢትዮጵያ ዛሬ ያስመረቀው ወሎ ሰፈር አካባቢ ያስገነባውን የዳቦ፣ ኬክና ሸኮሌት ግብዓት ማምረቻ ፋብሪካ እና ልዩ የምግብ ፈጠራ ማዕከል ነው።

የኩባንያው ዋና ስራ አፈፃሚ ዶሚኒክ ኤድዋርዶ በምረቃ ስነስርዓቱ ላይ ባሰሙት ንግግር በዓለም ላይ የታወቀው "ፑራቶስ የንግድ ስያሜ (brand) የኢትዮጵያን ገበያ በመቀላቀሉ ደስታ እና ኩራት እንደተሰማቸው ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አዲሱ ፋብሪካ እና ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተገጠመለት የፈጠራ ማዕከል እያደገ የመጣውን የደንበኞችን የጥራት ፍላጎት ለማሟላት ቁልፍ ነው ብለዋል።

ፑሩቶስ ኢትዮጵያ ሀገር ውስጥ ያሉ የኬክና ዳቦ ባለሞያዎች፣ ዓለም አቀፍ ሆቴሎች ፣ ሱፐር ማርኬቶች እና ሬስቶራንቶችን የሚያገለግል ሲሆን በተጨማሪ የጅቡቲ ፣ ሱዳን ፣ ሱማሊያ እና ኤርትራ ሃገራትን ፍላጎት ለማሟላት ዕቅድ እንዳለው ዋና ስራ አስፈፃሚው ገልፀዋል።

ፑሩቶስ በእኤአ 1919 ቤልጂየም ውስጥ የተቋቋመ ባለቤትነቱ የቤልጂየም የሆነ የምግብ አቀናባሪ ሲሆን በዓለም ዙሪያ ከ100 በሚበልጡ ሀገራት ውስጥ ቅርንጫፍ አለው፤ በአሁን ሰዓት በአፍሪካ ኬንያ፣ ናይጄሪያ፣ ደ/አፍሪካ እና አይቮሪኮስት ውስጥ እየሰራ ይገኛል።

@tikvahethiopia