TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.5K photos
1.55K videos
215 files
4.26K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Bahirdar : የባህርዳር ከተማ ትምህርት መምሪያ መመሪያን ተከትለው ያልሰሩ የግል ትምህርት ቤቶችን አስጠነቀቀ።

መምሪያው በከተማው ላሉ ትምህርት ቤቶች በፃፈው ደብዳቤ ከዚህ ቀደም በትምህርት ቤት ክፍያ ጉዳይ ተከታታይ ውይይት መደረጉን አስታውሷል።

መስከረም 7/2014 ዓ/ም ትምህርት ቤቶቹ የተማሪ ወላጆችን ሰብስበው በክፍያ ዙሪያ ከወላጅ ጋር ተግባብተው በመመሪያው መሰረት ወላጅ ያመነበትን ክፍያ እንዲያስከፍሉና ወላጆችን ያወያዩበት ቃለጉባኤ የተሳታፊዎችን ፊርማ እና በቪድዮ የተደገፈ ማስረጃ ለትምህርት መምሪያው መረጃ አደራጅተው እንዲያሳውቁ በተሰጠ አቅጣጫ መሰረት ተቋማቱ ዕድሉን እንዳልተጠቀሙበት ትምህርት መምሪያው በደብዳቤው ላይ ገልጿል።

አሁን ላይ ወላጆች የት/ቤት ክፍያ እንደተጨመረባቸው ይህ የተጨመረው ጭማሪም ወላጆች ያላመኑበት መሆን ለመምሪያው ቅሬታ እያቀረቡ እንደሚኙ ገልጿል።

ትምህርት መምሪያው ፥ ትምህርት ቤቶች የጨመሩት ክፍያ ከተማሪ ወላጆች ስምምነት ውጭና ተገቢነት የሌለው በመሆኑ ከመስከረም 2014 ጀምሮ የተከፈለ ክፍያ ለቀጣይ ወራት ታሳቢ ተደርጎ በ2013 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ቤቶች ሲያስከፍሉ የነበረውን ክፍያ እንዲያስከፍሉ አሳስቧል።

ት/ቤቶቹ ይህንን ውሳኔ ተግባራዊ የማያደርጉ ከሆነ በቀጣይ የማስተማር ፍቃዳቸው እንደሚነሳ ፤ ከ2ኛ ሴሚኒስተር በኃላ ምንም አይነት ተማሪ በተቋማቸው የማይማርና ተቋማቱም እንደሚዘጋ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
#AGOA : ኢትዮጵያ በ "AGOA" በኩል ያላት ተጠቃሚነት ላይ አሜሪካ በቅርቡ ውሳኔ ላይ እንደምትደርስ ካትሪን ታይ (የንግድ ተወካይ) ተናግረዋል።

ኃላፊዋ በይፋዊ መንገድ እና በግብረሰናይ ድርጅቶች በኩል የሚደርሱን መረጃዎች አበረታች አይደሉም፤ በኢትዮጵያ እየታየ ያለው ሰብዓዊ ቀውስ ነው ማለታቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የጠ/ሚ ፅ/ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያ ቢልለኔ ስዩም፥ የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ፣ አማራ እና አፋር ክልሎች የተፈጠረውን ሰብዓዊ ቀውስ በአፋጣኝ መፍትሄ እንዲያገኝ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀዋል።

ቢልለኔ፥ " ሰብዓዊ ቀውስ AGOA እድል ከፈጠረላቸው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ሴቶች የስራ እድል በመንጠቅ አይገታም እንደውም ያባብሰዋል" ብለዋል።

ባለፈው ነሃሴ ወር ላይ አሜሪካ፥ በኢትዮጵያ እየተፈፀሙ ነው ያለችው የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፍትሄ የማያገኙ ከሆነ በAGOA ያለቀረጥ ምርቶቿን ለአሜሪካ ገበያ የማቅረብ እድሏን እንደምታጣ ገልፃ ነበር።

ሮይተርስ ኢትዮጵያ በ2020 (እኤአ) 237 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጡ ሸቀጦችን ያለቀረጥ በAGOA በኩል ለአሜሪካ ገበያ ማቅረቧን የሀገሪቱ መንግስት መረጃ ያሳያል ብሏል።

የጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ ከፍተኛ አማካሪ እና የኢትዮጵያ የንግድ ተደራዳሪ የሆኑት ማሞ ምህረቱ ኢትዮጵያን በAGOA በኩል ያላትን እድል ማሳጣት ማለት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰራተኞች እንደሚጎዳ ለፎርየን ፖሊሲ በፃፉት የግል አስተያየት ላይ ገልፀዋል።

AGOA ምንድነው?

African Growth and Opportunity Act (AGOA) የግብይት ስርዓት ነው፤ ይህ የግብይት ስርዓት የተወሰኑ የብቃት መስፈርቶችን የሚያሟሉ ከሳሃራ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት ሸቀጦችን ያለቀረጥ ለአሜሪካ ገበያ እንዲሸጡ የሚፈቅድ ነው። #DW

@tikvahethiopia
አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መሞቱ ተገለፀ።

የናይጄሪያ ጦር ፤ የምዕራብ አፍሪካ የISIL ከፍተኛ መሪ መሞቱን አስታወቀ።

የናይጄሪያ ጦር ኃይል ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት ጄኔራል ላኪ ኢራቦር ለጋዜጠኞች በሰጡት ቃል ፥ " አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መሞቱን አረጋግጥላችኃለሁ ፤ ሞቷል እንደ ሞተም ይቀራል" ብለዋል።

ጄኔራሉ ፤ አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ መቼ እና እንዴት እንደሞተ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

የምዕራብ አፍሪካ የISIL ከፍተኛ መሪ የሆነው አቡ ሙሳብ አል-ባርናዊ በ2009 የተገደለው የናይጄሪያው ቦኮ ሃራም የታጠቀ ቡድን መስራች መሀመድ የሱፍ ልጅ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Masha በማሻ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ። በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን የመቅደላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳውቋል። ገደቡ የተጣለው የሀገሪቱን እና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ለህዝቡ ደህንነት ሲባል መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ፖሊስ የእንቅስቃሴ ገደቡን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ በማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሞተርና ባጃጅ…
#Kombolcha : በኮምቦልቻ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሏል።

ኮምቦልቻ ከተማ አስተደደር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ባወጣው መግለጫ ፥ ለከተማው ህዝብ ሁለንተናዊ ደህንነት እና በህወሓት ቡድን ከቤት ቀያቸው ተፈናቅለው በከተማው ለሚገኙ ወገኖች አጠቃላይ ደህንነት ሲባል እንቅስቃሴዎች በሰዓት እንዲገደቡ መወሰኑን አሳውቋል።

በዚህ መሰረት ፦

1ኛ. ከምሽቱ 2:00 ጀምሮ ከፀጥታ አስከባሪዎች ውጭ የትኛውም ዓይነት የግለሰቦች እንቅስቃሴ ተከልክሏል።

2ኛ. ለወቅታዊ ሰራ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ ተቋማትና የጤና ተቋማት ተሽከርካሪዎች ውጭ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ እንቅስቃሴአቸው እንዲገደብ ተወስኗል።

3ኛ. የፋብሪካ ሰርቪስ በመስጠት የሚያገለግሉ ተሽከርካሪዎች ከሚያገለግሉበት ተቋም የመውጫ እና የመግቢያ ስዓት በተቋሙ ህጋዊ ደብዳቤ ለሰላምና ደህንነት ጽ/ቤት ማሳወቅ ይጠበቅባቸዋል ተብሏል።

መላው የኮምቦልቻ ነዋሪዎች ለሁሉን አቀፍ ትብብር እራሳቸውን ዝግጁ እንዲያዲያደርጉ የኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia
#Gedo : በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሸዋ ዞን በጨሊያ ወረዳ ጌዶ ከተማ በህገወጥ መንገድ ሲጓጓዝወ የነበረ ከ3 ሺህ 850 በላይ የክላሽ ተተኳስ ጥይቶች በቁጥጥር ስር ማዋሉን የከተማው ፖሊስ መመሪያ አስታውቋል።

ፖሊስ እንዳሳወቀው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3/59736 የሆነ ተሸከርካሪ ላይ በተደረገ ፍተሸ ከ3 ሺህ 850 በላይ የክለሽ ተተኳስ ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

ጥይቶቱ በቁጥጥር ስር የዋሉት በህብረተሰቡ ጥቆማ ነው ብለዋል፡፡

የመኪናው አሽከርካሪ እና የንብረቱ ባለቤት በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል።

ጥይቱን ለመውሰድ የመጣ ግለሰብም ትላንት በቁጥጥር ስር መዋሉ የከተማው ፖሊስ አክሎ መግለፁ የኦሮሚያ ክልል ኮሙዩኒኬሽን አሳውቋል።

Credit : Oromia Communication

@tikvahethiopia
#Majete : በሰ/ሸዋ ዞን የኤፍራታና ግድም ወረዳ የማጀቴ ቀጣና አንቃር ኮበኮብና አግላ ማጀቴ ቆላ ባሳለፍነው ዕሮብ ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ የ15 አምስት አርሶ አደሮች በማሳ ላይ እየተሰበሰበ ያለ የጤፍ ሰብል መቃጠሉን የኤፍራታና ግድም ወረዳ አሳውቋል።

ወረዳው ፥ የጤፍ ሰብሉ የተቃጠለው በአጥፊ ኃይሎች ነው ሲል ገልጿል።

ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ፦
- የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ፀጥታ አመራሮች
- የሰ/ሸዋ ዞን የፀጥታ አመራሮች፣
- የኤፍራታና ግድም ወረዳ አመራሮች
- የአርጡማ ፉርሲ ወረዳ አመራሮች
- የጨፋ ሮቢት ከተማ አስተዳደር አመራሮች፣ - የአገር መከላከያ ሰራዊት
- የፌደራል ፖሊስ አካባቢው የሚገኙ የፀጥታ ሃሎች እና የሰላም ኮሚቴን ጨምሮ የችግሩን ጠንሳሽ ለማጣራት እየሰሩ መሆኑን የኤፍራታና ግድም ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ተናግረዋል።

ከሁለቱም አጎራባች ወረዳዎች የተውጣጣ የምርመራ ቡድንም ተዋቅሮ ጉዳዩ እየተጣራ መሆኑን ዋና አስተዳዳሪው አስረድተዋል።

የተቃጠለው የጤፍ ሰብል 95 ኩንታል የተገመተ ሲሆን 4 መቶ 27 ሺህ 5 መቶ ብር የተተመነ መሆኑን ገልፀዋል።

የተቋቋመው የምርመራ ቡድን ጉዳዩን አጣርቶ ለአርሶ አደሮቹ ይከፈላልም ብለዋል።

ዋና አስተዳዳሪው ፥ በተደጋጋሚ ቀጣናው ወደ አልተፈለገ ችግር ውስጥ ለማስገባት የሚሰሩ የፀረ ሰላም ሃሎችን ከዕኩይ ተግባራቸው እንዲታቀቡ ያሳሰቡ ሲሆን ህብረተሰቡ ከፀጥታ ኃይሉ ጎን በመሆን በቅንጅት መስራት አለበት ብለዋል።

Credit : ኤፍራታና ግድም ወረዳ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#AU : የአፍሪካ ህብረት ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት እየተሳተፉ የሚገኙ አካላት በመጨረሻ ወደ ጠረጴዛ ይመጣሉ የሚል ከፍተኛ ተስፋ እንዳለው አስታወቀ።

አፍሪካ ህብረት ይህን ያስታወቀው ፥ በህብረቱ የፖለቲካ ጉዳዮች እንዲሁም የሰላምና ደህንነት ኮሚሽነር ባንኮሌ አዶየ በኩል ነው።

ኮሚሽነሩ ለአል-ዐይን ኒውስ በሰጡት ቃል ፥ " በሰሜን ኢትዮጵያ ያለውን ግጭት መቋጫ እንዲያገኝ በህብረቱ በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ነው " ብለዋል።

የአፍሪካ ህብረት ከመጀመርያው አንስቶ ግጭቱን በትኩረት ሲከታተለው የነበረ ጉዳይ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ የግጭቱን መጠን ከግምት ውስጥ በማስገባት “በቅርቡ የቀድሞ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንት ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ ተደርገው መሾማቸው” ህብረቱ ለጉዳዩ የሰጠውን ትኩረት የሚያመላክት ነው ብለዋል።

ህብረቱ በከፍተኛ ተወካዩ ኦሊሴጉን ኦባሳንጆ አማካኝነት የሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት መፍትሄ እንዲያገኝ የኢትዮጵያ መንግስትን ጨምሮ ከተለያዩ አካላት ጋር እየመከረ መሆኑንም አሳውቀዋል።

እስካሁን እየተደረጉ ባሉ ጥረቶች መሰረት “ሁሉም የግጭቱ ተዋናዮች በመጨረሻ ወደ ጠረጴዛ እንደሚመጡ ትልቅ ተስፋ አለን” ሲሉም ተናግረዋል።

የአፍሪካ ህብረት የሰሜን ኢትዮጵያን ግጭት እንዲፈታ በሶስት ቁልፍ ጉዳዮች እየመከረና በግጭቱ እየተሳተፉ ካሉ ኃይሎች ጋር እየተወያየ አንደሆነ ኮሚሽነሩ ጠቅሰዋል።

“ግጭቱን ማቆም፣ ያልተገደበ የሰብዓዊ እርዳታ ተደራሽነት እንዲኖር ማድረግ እና ዘላቂ የሆነ ፖለቲካ መፍትሄ ማባጀት” የሚሉ ዓበይት ነጥቦች ህብረቱ በኢትዮጵያ የተከሰተውን ግጭት እንዲቆም በተደጋጋሚ እና በቀጣይነት እየሰራባቸው የሚገኙ ጉዳዮች ናቸው ሲሉ ነው ኮሚሽነሩ የገለፁት።

Credit : አል ዐይን ኒውስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#BORENA • "... በዝናብ መጥፋት 4164 ከብቶች ከ1916 አባወራዎች ሞተዋል ፤ ከ9 ሺ በላይ የቀንድ ከብቶች በሞት አፋፍ ላይ ናቸው " - ዶ/ር ቃሲም ጉዮ (የቦረና ዞን የእንስሳት ሀብት ቢሮ ኃላፊ) • "... የሳር ግዢው በቀናት ውስጥ ይጠናቀቃል ፤ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ለአርብቶ አደሮች ይደርሳል " - ዶ/ር አሚና አብዱራህማን (የክልሉ እንስሳት እና ዓሳ ሃብት ኤጀንሲ ኃላፊ) በቦረና ዞን…
#BORENA : የቦረና ዞን ነዋሪዎች በዝናብ እጥረት ምክንያት በተከሰተ ድርቅ ለውሀ፣ ለምግብና ለጤና ችግር ተጋልጠዋል።

የቦረና ዞን አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሬባ ኦዳ ለኤፍ ቢ ሲ በሰጡት ቃል፤ በዞኑ በ2013 ዓ.ም የበልግ ዝናብ በቂ አለመሆኑና የ2014 ዓ.ም የመኸር ዝናብ በወቅቱ ባለመዝነቡ ምክንያት በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ገልፀዋል።

በደረሰው ድርቅ 539 ሺህ 679 የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች የውሀ እጥረት እንዳጋጠማቸው የገለፁት ኃላፊው ከዚህ ውስጥ 177 ሺህ 553 ለሚሆኑት ብቻ በቦቴ ውሀ እንዲያገኙ ማድረግ መቻሉን አንስተዋል።

እስካሁን በደረሰው የምግብ እጥረትም 6 ሺህ 398 ህፃናት ፣9 ሺህ 78 እናቶችና 2 ሺህ 226 አዛውንቶች ላይ የጤና ችግር መታየቱ ገልፀዋል።

እስካሁንም ለ118 ሺ 864 ሰዎች የምግብ እርዳታ የተደረገ መሆኑን የገለፁት ሀላፊው 166 ሺህ 136 የሚሆኑት ደግሞ ተጨማሪ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አንስተዋል።

በተከሰተው ድርቅም 7 ሺህ 540 ከብቶች የሞቱ ሲሆን ÷13 ሺህ 641 የሚሆኑት ደግሞ በሰው ድጋፍ የሚንቀሳቀሱ መሆኑ ተገልጿል።

እንስሳቶቹን ከአደጋው ለማትረፍም 2 ሚሊየን 463 ሺህ 214 ቤል ሳር ከመንግስት የተጠየቀ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የደረሰ ነገር እንደሌለ ተነስቷል።

አሁን ላይ በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች እየተደረጉ ያሉ ድጋፎች እንደቀጠሉ ቢሆንም ከችግሩ ስፋት እና አሳሳቢነት አንፃር ግን በቂ ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል ሁሉ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ መቅረቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

Credit : FBC

@tikvahethiopia