TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Masha በማሻ ከተማ የእንቅስቃሴ ገደብ ተጣለ።

በደቡብ ወሎ ዞን መቅደላ ወረዳ ማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የእንቅስቃሴ ገደብ መጣሉን የመቅደላ ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት አሳውቋል።

ገደቡ የተጣለው የሀገሪቱን እና የክልሉን ወቅታዊ ሁኔታ መነሻ በማድረግ ለህዝቡ ደህንነት ሲባል መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

ፖሊስ የእንቅስቃሴ ገደቡን በተመለከተ በሰጠው ማብራሪያ በማሻ ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ሞተርና ባጃጅ ከምሽቱ 1 ሰዓት በኃላ እንዲሁም ማንኛውም ሰው ከ2 ሰዓት በኃላ መንቀሳቀስ እንደማይችል አሳስቧል።

የእንቅስቃሴ ገደቡ ከደሴ-ማሻ የሚሰሩ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችን አይጨምርም ተብሏል።

ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት እንዲሁም በድንገተኛ ችግር ምክንያት ካልሆነ በስተቀር የእንቅስቃሴ ገደቡን የሚተላለፍ ማንኛውም አካል ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ፖሊስ አስጠንቅቆ ማህበረሰቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopia