#Update
የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር የፀጥታ ኃይሉን ወደሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል እንደሚያሰማራ አስታወቀ።
ከተማ አስተደሩ የልዩ ሀይል አባላቱ ዛሬ ሽኝት ይደረግላቸዋል ብሏል።
እስካሁን ድረስ የደቡብ እና ሲዳማ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተንቀሳቀሱ ሲሆን ኦሮሚያ እንዲሁም ሱማሌ ክልል የፀጥታ ኃይላቸውን እንደሚያሰማሩ መግለፃቸው ይታወቃል።
Photo Credit : Dire Police
@tikvahethiopia

#EHRC
ኢሰመኮ ሃምሌ 3 እና 4 /2013 ዓ/ም መተከል ዞን ቡለን ወረዳ በምትገኘው ኢማንጅ ቀበሌ በተከሰተ ግጭት ቢያንስ 16 ሰዎች መገደላቸውን መረጃ እንደደረሰው አሳውቋል።
ኮሚሽኑ መረጃው ከደረሰው ጀምሮ ክትትል ሲያደርግና ከአካባቢ የፀጥታ እና አስተዳደር ኃላፊዎች ጋር ሲነጋገር መቆየቱን ገልጿል።
ሃምሌ 4 ከአንድ ቀን አስቀድሞ በታጠቁ ኃይሎች ስለመገደላቸው በሚነገር አንድ የኢማንጅ ቀበሌ ነዋሪ የቀብር ስነስርኣት ወቅት በተከሰተና የአፀፋ ስለመሆኑ በሚነገር ጥቃት 15 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
በተጨማሪም ከማሽ ዞን በምንጅጋ ወረዳ ሃምሌ 8 በደምቤ ቀበሌ ሌሎች 8 ነዋሪዎች በታጠቁ ኃይሎች ከተገደሉ በኃላ ስጋት ያደረባቸው ከ4 ሺህ ያላነሱ የቀበሌው ነዋሪዎች ተፈናቅለው ምጅንጋ /በሎይጂንጋፎይ/ ወረዳ ተጠልለው እንደሚገኙ ኢሰመኮ ገልጿል።
ኢሰመኮ መግለጫውን እስካወጣበት ሰዓት ድረስ የመሳሪያ ድምፅ ይሰማ እንደነበርና የፀጥታ ኃይሎችም ወደቦታው እንዳልደረሱ አሳውቋል፤ በምጅንጋ ተጠልለው ለሚገኙ ነዋሪዎች ጥበቃ እንዲደረግ አሳስቧል።
ኮሚሽኑ የክልሉ ሰላም እንዲሁም ደህንነት በዘላቂነት ለመመለስ አጥፊዎችን በአፋጣኝ ለህግ ማቅረብ ፣ የነዋሪዎችን ሰላም እና ደህንነት በተሟላ መልኩ ማረጋገጥ አስፈላጊ እንደሆነም አሳስቧል።

#Ethiopia
ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 5,787 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 93 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሁለት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 31 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

"ፎቶው ለምርጫ 2013 ያነሳሁት ነው" - አማኑኤል ስለሺ
ከሰሞኑን በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ #የትግራይ_ተወላጆች ያለ ምንም አግባብ ለእንግልትና ማንነትን መሰረት ላደረገ እስር እየተዳረጉ መሆኑን ለቲክቫህ ቤተሰቦች ሪፖርት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ፖሊስ ስለጉዳዩ የሰጠውን ምላሽንም ሰምተናል።
ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አምነስቲ ኢንተርናሽናል አንድሪፖርት ዛሬ ይፋ አድርጎ ነበር።
አምነስቲ በሪፖርቱ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ የትግራይ ተወላጆችን ከሕግ አግባብ ውጪ በሆነ መልኩ አስሯል ብሏል።
የትግራይ ተወላጆች ለእስር የተዳረጉት የትግራይ ኃይሎች መቐለ ከገቡ በኋላ ነው ያለ ሲሆን እስሩም ማንነትን መሠረት ያደረገ ይመስላል ሲልም ይገልጻል።
የፌደራሉ መንግስት በሰብዓዊነት ላይ ያተኮረ የተናጠል የተኩስ አቁም አውጆ ከትግራይ መውጣቱን ተከትሎ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የትግራይ ተወላጆች መታሰራቸውን ድርጅቱ በሪፖርቱ አምልክቷል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ ያለ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግሥት ከሕግ አግባብ ውጪ የሆነ እስርን እንዲያቆም እንዲሁም ከሕግ አግባብ ውጪ የታሰሩ በአፋጣኝ ከእስር እንዲለቅ ጠይቋል።
አምነስቲ በዚህ ሪፖርቱ አንድ ፎቶ ያያዘ ሲሆን ፎቶው ግን ከሪፖርቱ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ለማረጋገጥ ችለናል።
የዚህ ፎቶ ባለቤት ፎቶግራፈር አማኑኤል ስለሺ ሲሆን ፤ የፎቶ ባለሞያው ለAFP ነው የሚሰራው ፤ አምነስቲ የተጠቀመው ፎቶግራፍ ለምርጫ 2013 የተነሳ እንጂ ከእስሩ ጋር የተያያዘ አይደለም።
አማኑኤል ስለሺ ፥ "አምነስቲ ኢንተርናሽናል የተጠቀመው ፎቶ ለምርጫ ያነሳሁትን ነው፤ ድርጊቱ ስህተት ነው" ሲል የቲክቫህ ቤተሰቦች እወቁልኝ ብሏል። አምነስቲ በአስቸኳይ ፎቶውን እንዲያወርድም ጠይቋል።

ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው ..
- ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ፣
- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ
- የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ
- ወልዲያ
- ሪፍትቫሊ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት እያስመረቁ ነው።
#ባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 363 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።
ተማሪዎቹ በመደበኛ፣ በተከታታይ እና በክረምት መርሐ-ግብሮች፤ በመጀመሪያ ዲግሪ፣ በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሶስተኛ ዲግሪ እና የስፔሻሊቲ ህክምና የሰለጠኑ ናቸው።
#አሶሳ_ዩኒቨርሲቲ
የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 2 ሺህ 237 ተማሪዎችን ነው በማስመረቅ ላይ የሚገኘው።
ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ተማሪዎችን ሲያስመርቅ ለ8ተኛ ጊዜ ሲሆን የዛሬዎቹ ተመራቂዎች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
#የኢትዮጵያ_ሲቪል_ሰርቪስ_ዩኒቨርሲቲ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲም በተለያየ የትምህርት መስኮች በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ-ግብሮች ያሰለጠናቸውን ከ2 ሺህ 500 በላይ ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።
ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ ሁለተኛ ዲግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ የተማሩ ናቸው።
ከእለቱ ተመራቂዎች ውስጥ 153 የሚሆኑት ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመሆን በውጭ ግንኙነት ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት የሰለጠኑ እጩ ዲፕሎማቶች ናቸው።
#ወልዲያ_ዩኒቨርሲቲ
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 2,537 ተማሪዎችን አስመርቋል።
#ሪፍትቫሊ_ዩኒቨርስቲ
የሪፍትቫሊ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 16, 967 ተማሪዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም አስመርቋል።
መረጃው የetv ነው።

#ኢትዮጵያ🇪🇹 #ኤርትራ🇪🇷
የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ቡድን ከኤርትራ አቻቸው ጋር ዛሬ ከ ቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ የምድብ የመጀመሪያ ጨዋታውን የሚያካሂስ ይሆናል።
ከጨዋታው አስቀድሞ ልዩ የመክፈቻ ስነ- ስርዓት እንደሚኖር የተገለፀ ሲሆን፤ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንደሚታደሙበት ይጠበቃል።
More : @tikvahethsport

የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከአዛም ቲቪ ጋር በመተባበር የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ውድድር የመክፈቻ ጨዋታ ከ8:30 ጀምሮ በአማራ ቴሌቪዥን በቀጥታ እንደሚተለላፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አሳውቋል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update
በወቅታዊ የሀገራቸው ሁኔታ ላይ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ሲሪል ራማፎሳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።
በቀጥታ ስርጭት ለህዝባቸው ገለፃ ያደረጉት የደቡብ አፍሪካው ፕሬዘዳንት ሲሪል ራማፎሳ ፥ "በሀገሪቱ የተነሳው አመፅ መንግስት ፣ ፖሊስና ሌሎች የፀጥታ አካላት ዝግጁ ባልሆኑበት ሆኔታ"/እንደሆነ ተናግረዋል ፡፡
በጋውቴንግ እና በ KZN ክልሎች ውስጥ በመቶዎች የሚቆጠሩ የግብይት ማዕከሎች ወድመዋል ፣ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።
Video credit : eNCAnews
Faya ( Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

#AstraZeneca
- በማላዊ፣
- በደቡብ ሱዳን፣
- በላይቤሪያ፣
- በሞሪታንያ፣
- በጋምቢያ፣
- በሴራ ሊዮን፣
- በጊኒ፣
- በኮሞሮስ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በድምሩ 450,000 የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ጥቅም ላይ ሳይውሉ መወገዳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።
ምክንያት ? የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ የበሽታ መከላከል ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ሪቻርድ ሚሂጎ እንዳሉት ፥ ወደ አፍሪካ የተላኩ የአስትራዜኒካ ክትባቶች ቶሎ አለመድረሳቸው ጥቅም ላይ ሳይውሉ ለመወገዳቸው ዋናው ምክንያት ነው።
አስትራዜኒካ በአፍሪካ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ክትባት ነው።
1.2 ቢሊዮን ከሚሆኑ የአህጉሪቱ ነዋሪዎች መካከል አስካሁን ክትባት ያገኙት 8 ሚሊዮኑ ብቻ ናቸው።
መረጃው የቢቢሲ ነው።

የአፋር ክልል "ህወሓት" ጦርነት ከፈተብኝ አለ።
የአፋር ክልላዊ መንግስት ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው 'ህወሓት' ፥ "የሽብር ድርጊቱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል" ሲል ገልጿል።
ክልሉ "ህወሓት" ጦርነት ከፈተብኝ ያለው በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ነው።
አፋር ክልል በመግለጫው ላይ ፥ "ይህ እኩይ ቡድን በዳር ድንበር አስከባሪው በኢትዮጵያዊነቱ የማይደራደረው ጀግናው የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል የከፈተውን ጦርነት መንግስት ከህዝባችን ጋር በመተባበር ይመክታል" ሲል አስፍሯል።
"ሰላማዊ የሆነው ክልላችንን ለማተራመስ ህወሓት የለኮሰው ጦርነት በአጭሩ እንዲገታ አርብቶ አደር ህዝባችንም አስፈላጊውን ሁሉ ጥረት ማድረግ የሚጠበቅ ነው" የሚለው የክልሉ መንግስት መግለጫ "ህዝቡ አካባቢውን በንቃት ሊጠብቅ ይገባል" ብሏል።
የክልሉ ሚሊሺያ እና አጠቃላይ የፀጥታ ሀይሉ በህዝቡ ላይ የተሠነዘረውን ጥቃት የመከላከል ስራ በቁርጠኝነት የሚተገብር ይሆናል ሲልም አክሏል።
ከሰሞኑ በአማራ ክልል እና ትግራይ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ላይ ውጥረት ማየሉን ተከትሎ የክልል መንግስታት የፀጥታ ኃይሎቻቸውን ወደአካባቢው ማሰማራታቸው ይታወቃል።
አሁንደግሞ የአፋር ክልል መንግስት ይፋ ባደረገው መረጃ በያሎ ወረዳ በኩል ጦርነት መቀስቀሱ ተሰምቷል።

የሰላም ዋጋ በሞቃዲሾ !
የሱማሊያ ዋና ከተማ ሞቃዲሾ ስታዲየም ለዓመታት ስፖርታዊ/የእግር ኳስ ጨዋታዎችን አያስተናግድም ነበር።
በሀገሪቱ በነበረው የእርስ በእርስ ጦርነት ፣ የሽብር ጥቃት የሱማሊያ የስፖርት እንቅስቃሴ ተደክሞ ነበር ፤ ታድክሞ ብቻ ሳይሆን ሞቶም ጭምር ነበር።
ከቅርብ አመታት ወዲህ ግን ሀገሪቱ በአንፃራዊነት እየተረጋጋች ፣ ሰላሟም እየተመለሰ ፤ ከእርስ በእስር ጦርነቱ እያገገመች ስትመጣ የስፖርት እንቅስቃሴው መነቃቃት ጀምሯል።
የአሚሶም ወታደሮች መቀመጫ የነበረው የሞቃዲሾ ስታዲየም አሁን ላይ እድሳት ተደርጎለት ጨዋታዎችን በማስተናገድ ላይ ይገኛል።
ትላንት 65 ሺህ ህዝብ የታደመበት ታሪካዊ ጨዋታ ሞቃዲሾ ስታዲየም አስተናግዳል።
ጨዋታው በሶማሊያ ፕሪሚየር ሪግ የሆርሴድ ክለብ እና የሞቃዲሾ ከተማ ክለብ መካከል የተደረገ ሲሆን ያለ ግብ በአቻ ውጤት ነው የተጠናቀቀው።
በሀገሪቱ ፕሪምየር ሊግ ግርጌ ላይ የሚገኙ ሁለቱ ክለቦች በሶማሊያ በርካታ ደጋፊዎች ያላቸው ናቸው።
በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው በርካታ ቁጥር ያለው ህዝብ ወደ ሞቃዲሾ ስታድዮም በመግባት ጨዋታውን የታደመው እንደአስታን ስፖርት መረጃ።
ለጦርነት እና ለሽብር ጥቃት ከማንም ቀድመው የሚደርሱ፣ የሚዘግቡ ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ይህን በጎ ዜና ለዓለም ህዝብ አልማድረሳቸው እንዳሳዘናቸው አንዳንድ የሱማሊያ ዜጎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲፅፉ ተመልክተናል።