TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደህንነታቸው የተጠበቀ የዓለማችን ሀገራት...

“ግሎባል ፋይናንስ” የተሰኘው ዓለም አቀፍ ተቋም የፈረንጆች 2021 ዓመት የዓለማችንን አገራት ደህንነት ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

በተቋሙ ዓመታዊ ሪፖርት መሰረት ፦

- አይስላንድ፣
- የተባበሩት አረብ ኢምሬት (UAE)
- ኳታር
- ሲንጋፖር እና ፊንላንድ ከዓለማችን 134 አገራት አስተማማኝ ደህንነት ያለባቸው ቀዳሚዎቹ አገራት ናቸው ብሏል።

- ፊሊፒንስ፣
- ኮሎምቢያ፣
- ጓቲማላ፣
- ናይጀሪያ እንዲሁም ቦስኒያ እና ሄርዞጎቪና በዓለማችን ደህንነታቸው #ያልተረጋገጠባቸው አገራት መሆናቸውን ተቋሙ ገልጿል።

ከአፍሪካ ሞሮኮ ፣ ሞሪሺየስ እንዲሁም ቦትስዋና በአንጻራዊነት የተሻለ ደህንነት ያለባቸው አገራት እንደሆኑ ሪፖርቱ ያስረዳል።

በ2020 የ 'ግሎባል ፋይናንስ' ሪፖርት ከ163 የዓለም ሀገራት 139ኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ ዘንድሮ ደረጃዋን አሻሽላ 83ኛ ሆናለች፡፡

ድርጅቱ በዚህ ዓመት በኮሮና ቫይረስ እና በሌሎች ምክንያቶች በሪፖርቱ ያካተታቸው አገራት ዝርዝር ወደ 134 ዝቅ ማለቱን አስታውቋል።

መመዘኛው ምንድነው ?

ተቋሙ የአገራቱን ደህንነት ለመመዘን ከተጠቀመባቸው መስፈርቶች መካከል ፦
• በአገራቱ ያሉ ግጭቶች፣
• የኮሮና ቫይረስ ጉዳት፣
• የፖለቲካ መረጋጋት፣
• ለሽብር ቡድኖች ጥቃት የመጋለጥ እድል፣
• ዓመታዊ የወታደራዊ በጀት እና የቤት ውስጥ ጥቃቶች መጠን ዋነኞቹ ናቸው።

ግሎባል ፋይናስን ማነው ?

ግሎባል ፋይናንስ ዋና መቀመጫውን አሜሪካ ኒዮርክ ያደረገ ዓለም አቀፍ የግል ተቋም ሲሆን ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ ጥናቶችን በማካሄድ ለአገራት እና የቢዝነስ ተቋማት የውሳኔ ግብዓት የሚሆኑ ሪፖርቶችን የሚያወጣ ተቋም ነው።

መረጃው የአል ዓይን ኒውስ ነው።

@tikvahethiopia
#Update

የፖሊስ መልስ !

በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የሀገራችን ከተሞች የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች እንግልት እየደረሰባቸው እንደሆነ ያለህግ አግባብ ቤታቸው እንደሚበረበር፣ ማንነትን መሰረት በማድረግ ብቻ ለእስር እየተዳረጉ መሆኑ በተደጋጋሚ ሪፖርት አድርገዋል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል ስለዚህ ጉዳይ ትላንት ሪፖርት ማውጣቱ ይታወቃል።

ኢሰመኮ ከቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ በትግራይ ከቀጠለው ግጭት ጋር በተያያዘ በሲቨል ዜጎች ላይ እንግልትና እስር፣ እንዲሁም የንግድ ቤት መዝጋት የሚገልፁ መረጃው እንደሚያሳስበው ገልጾ ነበር።

ከትግራይ ተወላጆች ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም በይፋ ስለወጡት መረጃዎች የአ/አ ፖሊስ እንዲሁም ፌዴራል ፖሊስ በኮሚኒኬሽናቸው ክፍል ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም።

ዛሬ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ጌቱ አርጋው ከኢ.ቲ.ቪ. ጋር ቃለምምልስ አድርገው ነበር ፤ በዚሁ ወቅት ከሰሞኑ ሲነሱ ስለነበሩት አቤቱታዎች፣ ክሶች እና ቅሬታ ምላሽ ሰጠተዋል።

• ሽብረተኛ ነው ተብሎ የተፈረጀውን #የህወሃት_ቡድን_በመደገፍ በተለያዩ የተግባር እንቅስቃሴዎች ተሰማርተዋል በሚል ወንጀል የተጠረጠሩ 323 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው ነው ብለዋል።

• ተጠርጣሪዎቹ በብሔራቸው ምክንያት በህግ ቁጥጥር ስር አልዋሉም ብለዋል ፤ የትግራይ ተወላጆች በብሄራቸው ምክንያት እየታሰሩ ነው የሚሉ ሪፖርቶችንም ውድቅ አድርገዋል። ከተጠርጣሪዎች መካከል ከትግራይ ብሔር ውጪ የሆኑ የሌላ ብሔረሰብ አባላት ይገኙበታል ሲሉ ተናግረዋል።

• ግለሰቦቹ የተጠረጠሩባቸው ወንጀሎች ብለው ኮሚሽነሩ የዘረዘሩት፦
- ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን የህወሀት ድርጅትን መደገፍ፣
- የጦር መሳሪያ ይዞ መገኘት፣
- ሕገመንግስቱን ማንቋሸሽ፣
- ሰንደቅ ዓላማን ማዋረድ፣
- ሃሺሽ ማጨስ እና ቁማር መጫወት ይገኙበታል።

• በወንጀሎች ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሰቦች መኖሪያ ቤት በፍርድ ቤት ፍቃድ በተደረገ ፍተሻ የህወሀት ልዩ ኃይል አልባሳት፣ ሽጉጦች፣ ክላሾች እና ጥይቶችን ጨምሮ የተለያዩ የጦር መሳሪያዎች ተገኝቷል ብለዋል።

• ከወንጀሎች ነፃ የሆኑት በርካታ የትግራይ ተወላጆች በነፃነት በአዲስ አበባ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

• የአ/አ የጥፋት ቀጠና ለማድረግ ሽብርተኛ ተብሎ ያተፈረጀውን የህወሓት ቡድን በመደገፍ የአገርን ሰላም ለማናጋት የሚያስቡ ካሉ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Addis-Ababa-Police-07-17
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 4,645 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 79 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሁለት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 28 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#WFP

የዓለም ምግብ ፕሮግራም ለትግራይ ክልል ሰብዓዊ ዕርዳታ ለማቅረብ ዛሬ ወደ መቐለ በረራ ጀምሯል።

ተቋሙ በረራውን ያደረገው ያቀረበው ጥያቄ በመንግስት ተቀባይነት አግኝቶ መሆኑ ነው የተገለፀው።

ከአዲስ አበባ ስድስት ሰዎችን ይዞ ወደ መቐለ የበረረው አውሮፕላን ንብረትነቱ የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም ነው።

ከአዲስ አበባ ወደ መቐለ የተደረገው በረራ ድጋፉ በምግብ እና ስነ-ምግብ አቅርቦት የሚሳተፉ በክልሉ በ21 ወረዳዎች ለሚሰሩ ሰራተኞች ደመወዝ፣ ለስራ ማስኬጃ፣ ለምግብ ቁሳቁስ መጫኛና ማውረጃ የሚውል ገንዘብ መሆኑ ተጠቁሟል።

አውሮፕላኑ በዛሬው እለት መቐለ ደርሶ ወደ አዲስ አበባ መመለሱ ተገልጿል።

መንግስት የሰብዓዊ ድጋፉ በአውሮፕላን ማከናወን ለሚፈልጉ አካላት ሲወጡም ሆነ ሲገቡ የቦሌ አውሮፕላን ማረፊያን ብቻ እንዲጠቀሙ መመሪያ ማውጣቱ አይዘነጋም። #ENA

@tikvahethiopia
#Update

ደቡብ አፍሪካ ለምትገኙ የቲክቫህ አባላት :

በደ/አፍሪካ ሰሞኑን አመፅ የነበረባቸው ቦታዎች በአንፃራዊ ሁኔታ መረጋጋት እየታየ ይገኛል።

የኩዋዙሉ - ናታል አስተዳደር (Town of KwaNongoma) በተፈፀመዉ ጥፋት ምክንያት የንግድ ተቋማት አለመከፈታቸዉን አስታዉቋል።

የህግ አካላቶች በማንኛዉንም የትራንስፖርት መንገዶች በፒተርማርስበርግ ፍተሻ እያደረጉ ሲሆን በበርገር መንገድ ዘራፊዎችን ከነ መረጃ ማሠራቸዉን ገልፀዋል።

ከመንገድ ትራንስፖርት ባገኘነዉ መረጃ በፑማላንጋ R40 የማርሼ (R40 to Marite area.) መንገድ ላይ በሚያልፋ መኪናዎች ላይ ድንጋይ እየተወረወረ ስለሚገኝ ባትጠቀሙ ይከመራል።

በዚያዉ አካባቢ ሀዚቪዉ አቀጣጫም ቡሽባክ እሪጅ ተመሳሳይ ችግር እንዳለ ከስፍራዉ የሚወጡ መረጃዎች ያሳያሉ።

ከቅዳሜ ጠዋት ጀምሮ በዘረፋዉ በብርቱ ተሳትፈዋል ከሚባሉት በጆርጅ ጎሽ ሆስፒታል ጆሐንስበርግ (George Goch Hostel) አካባቢ የህግ አካላቶች ተደራጅተዉ የቤት ለቤት አሰሳ አድርገዉ የነበረ ቢሆንም አንድም ሰዉ እንኳን አለማግኘታዉ አግርሞትን የፈጠረ ሲሆን ማምሻዉን በድጋሚ በተከናወነ ፍተሻ ፖሊስ 20 ተጠርጣሪዎችን ማሠሩን ከኤስ.ኤ.ቢ.ሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Faya (Tikvah-Family)
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
"...ሰዎቹን በህይወት የማግኘት እድሉ ጠባብ ነው" - ፖሊስ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ ደንቢያ ወረዳ 13 የሚደርሱ ሰዎችን አሳፍራ በጣና ሃይቅ ጉዞ የጀመረች አነስተኛ ጀልባ ተሰወረች።

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ምክትል ኮማንደር ቸርነት አስማረ ጀልባዋ የተሰወረችው በወረዳው አዲሰጌ ድንጌ ተብሎ ከሚጠራ ቀበሌ አባን ላይ ጎጥ መነሻቸውን በማድረግ ወደ ጎርጎራ ወደብ ጉዞ ከጀመረች በኋላ ነው ብለዋል።

ተጓዥቹ ሐምሌ 9 ቀን 2013 ዓም ለሊት ድንች ጭነው ጉዞ መጀመራቸውን ከቤተሰቦቻቸው መረጃው ለፖሊስ መድረሱን ገልፀዋል።

ተሳፋሪዎቹ ከ10 እስከ 13 እንደሚደርሱና አብዛኞቹም በስም ዝርዝር መለየታቸውን የገለፁት ምክትል ኮማንደሩ ተሳፋሪዎቹ ከመዳረሻው ጎርጎራ ወደብ እንዳልደረሱ መረጋገጡን ተናግረዋል።

ከትናንት እኩለ ቀን ጀምሮ በሁለት ቡድን የተዋቀረ የፖሊስና የባለሙያዎች ቡድን ፍለጋ እያካሄደ መሆኑን አመልክተው እስካሁን ምንም አይነት ፍንጭ ማግኘት እንዳልተቻለ አስታውቀዋል።

በዛሬው እለት ፍለጋው መቀጠሉን ጠቁመው ተጓዦቹ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ወይ በማዕበል ተወስደዋል፤ አለበለዚያም ከአቅም በላይ በሆነ ጭነት ጀልባዋ ሰምጣለች የሚል ድምዳሜ ላይ መደረሱን አብራርተዋል።

ተጓዦቹ የተነሱበት ሰዓት ለሊት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፍለጋውን አስቸጋሪ እንዳደረገው ጠቅሰው ከዚህ በኋላ ሰዎችን በህይወት የማግኘት እድሉ ጠባብ እንደሆነም አመልክተዋል።

ከመነሻው እስከ መዳረሻው ድረስ ያለው የውሀ ላይ ጉዞ የ15 ኪሎ ሜትር ርቀት እንዳለው አመልክትው በፍለጋው የሚገኘውን ዝርዝር ውጤት በቀጣይ ህዝቡ እንዲያውቀው እንደሚደረግ አስታውቀዋል። #ኢዜአ

@tikvahethiopia
#EMA

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን (ኢመብባ) በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ሁሉም መገናኛ ብዙሃን የሀገሪቱን ሉዓላዊ ግዛት ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ ስያሜዎችን ከመጠቀም እንዲቆጠቡ አሳሰበ።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል የሚደረገውን ኦፕሬሽን ጋር ተያይዞ በመደበኛም ሆነ በበየነመረብ የሚሰሩ ዜናዎች እና ፕሮግራሞች ላይ ክትትል ማድረጉን የገለፀ ሲሆን በክትትሉ ወቅት ህግን ያላከበሩ አዘጋገቦችን ተመልክቻለሁ ብሏል።

በዋነኝነት በኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ የተፈረጀውን ህወሓትን የትግራይ መከላከያ ሰራዊት / ኃይል / የሚል ስያሜ መጠቀም መሆኑን አንስቷል።

በክልል ደረጃ "የመከለከያ ሰራዊት" የሚባል ኃይል አለመኖሩን የገለፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ እንዲህ አይነት ስያሜ የኢትዮጵያን ሉዓላዊ ግዛት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ የሀገር ደህንነትን እና የኢትዮጵያን ህዝብ ጥቅም የሚጎዳ ነው ብሏል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት ጥቅምት 2013 ዓ/ም የቀድሞው የትግራይ ክልል መንግስት በህገ - መንግስት ሽሮ አዲሱን ግዚያዊ አስተዳደር አቋቁሟል ሲል ያስታወሰው ኢመብባ ምርጫ ቦርድ በክልሉ ምርጫ አካሂዱ ክልሉን የሚያስተዳድረው አካል እስኪመረጥ ድረስ በአንዳንድ ሚዲያዎች ዘገባ ውስጥ እምደሚታየው "የትግራይ ክልል መንግስት" የሚባል አካል የለም ብሏል።

በክልሉ ምርጫ እስኪካሄደ ድረስ ትግራይን እንዲመራ ስልጣን የተሰጠው ጊዜያዊ አስተዳደሩ ነው ሲልም አክሏል።

የኢመብባ ፥ መደበኛ ሆኑ የበየነ መረብ ሚዲያዎች "የትግራይ መከላከያ ሰራዊት/ኃይል/" እንዲሁም "የትግራይ ክልል መንግስት" የሚል ስያሜ ከመጠቀም ተቆጠቡ ሲል አሳስቧል።

መ/ ቤቱ ስያሜዎቹን ሲጠቀም በተገኘ የመገናኛ ብዙሃን ተቋም ላይ ጠንካራ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Update

ደ/አፍሪካ ነዋሪ ለሆናችሁ የቲክቫህ አባላት :

በፕሪቶሪያ #ሞሬሌታ_ፖርክ የሚገኘዉ ፕላስቲክ ቪዉ ድርጅት ለሊቱን በተነሳ እሳት ዉድመት ደርሶበታል።

ፓርክ ቪው ሰሞኑን በደ/አፍሪካ በነበረው አመፅ እና ዘረፋ ጉዳት ያልደረሰበት አካባቢ ነበር። ሆኖም በአሳዛኝ ሁኔታ ምክንያቱ ባልታወቀ መነሻ ትላንት ለሊቱን በእሳት አደጋ ጉዳት ደርሶበታል።

በቃጠሎዉ የተነሳ ሰዎች ላይም ጉዳት መድረሱን ከአካባቢዉ የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ።

በአካባቢው የምትገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች ጥንቃቄ አይለያቹ።

በሌላ በኩል በደ/አፍሪካ ፍትህ ሚኒስቴር ዘረፋዉ ላይ የተሳተፉ ግለሠቦችን ለመዳኘት የሚያስችል ከመደበኛዉ የሕግ ስርዓት በተለየ የሚሰራ ፍርድ ቤት እና የፍርድ አሠጣጥ ህግ በኩዋዙሉ ናታል ተግባራዊ አድርጓል።

Video credit : Ek media

Faya (Tikvah-Family)
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
#TokyoOlympics2020

የቶኪዮ ኦሊምፒክስ ከመጀመሩ ከ5 ቀናት በፊት በአትሌቶች መንደር ውስጥ 2 ስፖርተኞቸ ኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው።

ስፖርተኞቹ ለቫይረሱ ታጋላጭ የሆኑ የመጀመሪያዎቹ ተወዳዳሪዎች ሆነዋል፡፡

2ቱ ስፖርተኞች ቅዳሜ ዕለት ተመርምረው ቫይረሱ ከተገኘባቸው ባለሥልጣን ጋር በተመሳሳይ ቡድንና ስፖርት ዘርፍ የሚገኙ ናቸው ሲሉ አዘጋጆቹ አሳውቀዋል።

ሌሎች የቡድኑ አባላት በክፍላቸው ተለይተው እንዲቀመጡ ተደርጓል።

በመንደሩ ቫይረሱ የተገኘባቸው #የመጀመሪያዎቹ ስፖርተኞቹ ሲሆኑ ሌላ ቦታ አንድ ተጨማሪ ስፖርተኛ እሑድ ዕለት በተመሳሳይ ቫይረሱ ተገኝቶበታል፡፡

በአጠቃላይ እሁድ ዕለት ጋዜጠኞች፣ ተባባሪ አካላትን እና ሌሎች ሠራተኞችን ጨምሮ ከኦሎምፒክ ጋር የተገናኙ 10 አዳዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች አዘጋጆቹ ሪፖርት አድርገዋል፡፡

በቶኪዮ የቫይረሱ ስርጭት መጠን እየጨመረ ሲሆን ለአራት ተከታታይ ቀናት ከ 1 ሺህ በላይ አዳዲስ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ተመዝግበዋል፡፡

ብዙ ጃፓናዊያን በዚህ ወቅት ይህ ውድድር መካሄዱን እንደሚቃወሙ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩ ቢቢሲ በድረገፁ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#Update

ሁሉም ክልሎች በሚባል ደረጃ (የድሬዳዋ ከተማን ጨምሮ) የፀጥታ ኃይላቸውን ወደሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል እያሰማሩ ይገኛሉ።

የጋምቤላ፣ ሀረሪ እና ሱማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሎች የተመደበላቸውን የግዳጅ ቀጠና መነቅሳቀሳቸው ታውቋል።

የየክልሉ ልዩ ኃይሎች ወደግዳጅ ቀጠና ከመሄዳቸው ቀደም ብሎ በየክልላቸው መንግስት የሽኝት መርሃግብር ተደርጎላቸው።

የኢትዮጵያ የፌዴራል መንግስት እንደሳወቀው ከሆነ የፌዴራሉ ፀጥታ ኃይሎች እንዲሁም የክልል የፀጥታ ኃይሎች በተመደቡበት ቦታ ቦታቸውን እየያዙ ናቸው።

@tikvahethiopia
ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ በችግር ላይ ላሉና ለአቅመ ደካሞች ድጋፍ አደረጉ።

#ኢትዮጵያዊው ባለሃብት ሼይኽ መሐመድ ሁሴን አሊ አል አሙዲ ለመጪው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በወሎ በተለያዩ አካባቢዎች በችግር ላይ ላሉ እና በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካሞች የሚከፋፈል 106 በሬዎችን እና 100 በግ እና ፍየሎችን ለኡዱሂያ ድጋፍ አድርገዋል።

ሼይኽ መሀመድ አል አሙዲ ለኡዲሂያ እንዲሆን በማሰብ ድጋፍ ያደረጓቸው በሬዎች ፣በጎች እና ፍየሎች በወሎ በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች እና በአዲስ አበባ ለሚገኙ አቅመ ደካሞችም በተለያዩ መስጂዶች እና ተቋማት በኩል እንዲከፋፈል መደረጉ ተገልጿል።

መረጃው የተገኘው ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 4,102 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 81 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ ሶስት ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 49 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የአፋር ክልል "ህወሓት" ጦርነት ከፈተብኝ አለ። የአፋር ክልላዊ መንግስት ከደቂቃዎች በፊት ባወጣው መግለጫ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው 'ህወሓት' ፥ "የሽብር ድርጊቱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ ጦርነት ከፍቷል" ሲል ገልጿል። ክልሉ "ህወሓት" ጦርነት ከፈተብኝ ያለው በፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ነው። አፋር ክልል በመግለጫው ላይ ፥…
#Afar

ትላንት የአፋር ክልላዊ መንግስት በህ/ተ/ምክር ቤት ሽብርተኛ ድርጅት ተብሎ የተፈረጀው 'ህወሓት'፥ "የሽብር ድርጊቱን ወደ አፋር በማስፋት የአፋር አርብቶ አደር ህዝብ ላይ #ጦርነት ከፍቷል" ማለቱ ይታወሳል።

ክልሉ 'ህወሓት' ጦርነት ከፈተብኝ ያለው ፈንቲ ረሱ ዞን ያሎ ወረዳ በኩል ነው ፤ የክልሉ መንግስት የተከፈተበትን ጦርነት ከህዝብ ጋር በመተባበር እንደሚመክት መግለፁ አይዘነጋም።

የአፋር ክልል ሰላም እና አስተዳደር ቢሮም ትላንት ጧቱ 2 ሰአት ጀምሮ "ህወሓት" በያሎ ወረዳ በንጹሃን አርብቶአደሮች ላይ በከፈተዉ ድንገተኛ ጥቃት በሰዉና ንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱን ሪፖርት አድርጓል።

ቢሮው፥ ህጻናትና ሴቶችን ጨምሮ አርብቶ አደሮች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ያሳወቀ ሲሆን ቡድኑ የተለያዩ የግለሰብ ቤቶችን ላይ ዝርፊያ መፈፀሙን ገልጿል።

ህወሓት የከፈተውን ጥቃት ተከትሎ ወደስፋራዉ የደረሰዉ የአፋር ልዩ ሃይልና የአካባቢዉ ህብረተሰብ የመከላከል እርምጃዎችን በመውሰድ የቡድኑን አላማ ማክሸፍ መቻሉን አስረድቷል።

'ህወሓት' በአፋር ክልል በከፈተው ጥቃት ወደክልሉ ይጓጓዝ የነበረው የሰብዓዊ ድጋፍ ተስተጓጉሏል።

የህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ብሎ የፈረጀው 'ህወሓት' አፋር ውስጥ ጥቃት መፈፀሙን አምኗል። ቡድኑ ጥቃት ፈፅመኩኝ ያለው የመንግሥት ደጋፊ ወታደሮች ላይ ነው።

አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ ለAFP በሰጡት ቃል አፋር ክልል ውስጥ ጥቃት መፈፀማቸውን ገልፀው ጥቃቱ "ውስን ርምጃ ነበር" ብለዋል።

ጥቃቱ ያነጣጠረው በትግራይ እና አፋር ድንበር አካባቢ ተሰባስበው የነበሩ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ላይ ነበር ያሉት አቶ ጌታቸው፥ "ርምጃውን የወሰድነው እነዚህን ሃይሎች ወደ ኦሮሚያ እንዲመለሱ ለማድረግ ነበር፤ ይህም ተሳክቶልናል" ብለዋል።

telegra.ph/Afar-07-18

@tikvahethiopia