TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ICRC በሰሜን ኢትዮጵያ እያደረገ ያለው ድጋፍ :

የዓለም አቀፉ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ዛሬ መግለጫ አውጥቷል፤ በመግለጫው በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል እያደረገ ያለውን ድጋፍ በዝርዝር ገልጿል።

IRCR እደረገ ያለው ድጋፍ ፦

- በትግራይ እና በአማራ ክልል ለሚገኙ አምስት ሆስፒታሎች የተለያዩ ድጋፎችን አድርጓል። ድጋፍ ያደረገው ለሰቆጣ እና ላሊበላ አጠቃላይ ሆስፒታሎች፣ ለጎንደር እና አይደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች እንዲሁም ለአይከል የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ነው። ድጋፉ 250 በጽኑ የተጎዱ ወይም 900 መካከለኛ ጉዳት ያጋጠማቸውን ሰዎች መርዳት ያስችላል።

- የመቐለ አጠቃላይ ሆስፒታል የኮቪድ-19 ክፍልን ለመደገፍ የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል ፤ በሸራሮ የሚገኘውን ሆስፒታል መልሶ ለማቋቋም ሥራ ጀምሯል።

- ለአይደር፣ ሁመራ፣ ዳንሻ እና ማይካድራ ሆስፒታሎች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ ነው።

- በትግራይ ክልል የስልክ እና የኢንተርኔት ግንኙነት መቋረጡን ተከትሎ፤ በግጭቱ ምክንያት ከቤተሰባቸው ጋር ተቆራርጠው የሚገኙ ሰዎችን ለማገናኘት የስልክ ጥሪ እና የጽሑፍ መልዕክት አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል፤ ከዚህ አገልግሎት ተጠቃሚዎች መካከል የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ይገኙበታል።

- ከኢትየጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ጋር በመተባበር ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር ተጋላጭ ለሆነው የማኅብረሰብ ክፍል በውሃ ቦቴ ተሸካሚ ተሽከርካሪዎች ውሃ እያቀረበ ነው።

- የክረምት ወቅት ውሃ ወለድ በሽታዎች እንዳይከሰቱ እና የንጹህ ውሃ አቅርቦትን ለማረጋገጥ የኬሚካል ድጋፍ ማድረግ ቀጥሏል።

@tikvahethiopia
"...በትግራይ የምግብና የሸቀጦች ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል" - ICRC

ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ማኅበር /ICRC/ በትግራይ የመሠረታዊ ሸቀጦች እና የምግብ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን አስታውቋል።

ICRC ዛሬ ባወጣው መግለጫ በተለይ ባለፉት 2 ሳምንታት የምግብ ዋጋ በከፍተኛ መጠን መጨመሩን አስታውቋል።

በመላው ትግራይ ክልል ባንኮች ዝግ በመሆናቸው ምክንያት ሰዎች መሠረታዊ ግብይቶችን ለመፈጸም የጥሬ ገንዘብ እጥረት አጋጥሟቸዋል ብሏል።

ICRC ፥ "ፋብሪካዎች ተጎድተው ቀርተዋል / እንዲወድሙ ተደርገዋል። በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል። በዚህም ምክንያት በርካቶች ከሥራ ውጪ ሆነዋል። ይህም የጤና አገልግሎት ጨምሮ መሠረታዊ ቁሶች እና አገልግሎቶች እንዳይገኙ አድርጓል" ሲል ገልጿል።

አብዛኛው የጤናና የመጠጥ ውሃ ማጣሪያ ተቋማት ኃይል የሚያገኙት ከጄነሬተር በሚመነጭ የኤሌክትሪክ ኃይል መሆኑን በመጥቀስ፤ በአሁኑ ወቅት በክልሉ ቋሚ የኤሌክትሪክ ኃይል እና የነዳጅ አቅርቦት አለመኖሩን ቀይ መስቀል ገልጿል።

መረጃው የተገኘው ከ #ICRC መግለጫ ሲሆን የፅሁፍ ዝግጅት ቢቢሲ ድረገፅ ነው።

@tikvahethiopia
#Tokyo2020

በዓለም ህዝብ ዘንድ በእጅጉ የሚናፈቀው እና በጉጉት የሚጠበቀው የቶክዮ ኦሎምፒክ ሊጀምር ተቃርቧል።

ሀገራትም ወደ ስፍራው መጓዝ ጀምረዋል።

የደቡብ አፍሪካው የአትሌቲክስ ቡድን ደግሞ ወደስፍራው ለመጓዝ የኢትዮጵያ ኩራት የሆነውን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ምርጫው አድርጓል።

የደቡብ አፍሪካ የመጀመሪያው ዙር የአትሌቲክስ ቡድን ዛሬ ከሰዓት በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ ለመሳተፍ ወደ ስፍራው የኢትዮጵያ አየር መንገድን ምርጫው አድርጎ ተጉዟል።

በዚህም አየር መንገዱ ኩራት እንደተሰማው ገልጿል።

Photo Credit : የኢትዮጵያ አየር መንገድ

@tikvahethiopia
#ኢሰመኮ

EHRC / ኢሰመኮ #በትግራይ_ክልል ከቀጠለው ግጭት ጋር ተያይዞ በሲቪል ሰዎች ላይ እንግልት እና እስር ፣ የንግድ ቤት መዘጋት ፣ ብሎም በሲቪል ሰዎች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መከሰቱንና ሕይወት መጥፋቱን፣ እንዲሁም በታሳሪዎችና በምርኮኞች ላይ የሚደርስ ኢሰብአዊ አያያዝ፣ በስደተኞች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችና ሕጻናትን ለውትድርና መጠቀም የሚያመላክቱ መረጃዎች እጅግ የሚያሳስበው መሆኑን ገልጿል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia😷

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት 5,591 የኮቪድ-19 ላብራቶሪ ምርመራ ያከናወነች ሲሆን 125 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተግኝተዋል፤ አንድ ሰው ህይወቱ ያለፈ ሲሆን 39 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia
#Update

የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ የተዘረፉ ንብረቶችን በቤት ለቤት ፍተሻ የማስመለስ ዘመቻ ጀምሯል።

ከሰሞኑን በቀድሞው የደ/ አፍሪካ ፕሬዘዳንት ጃኮብ ዙማ ደጋፊዎች የተነሳው አመፅን ተከትሎ በተለያዩ ተቋማት ላይ ዝርፊያ ሲፈፀም እንደነበር የሚታወስ ነው።

የደ/አፍሪካ መንግስት ይህን ዘረፋ እና አመፅ ለመግታት የመከላከያ ሰራዊቱን ያሰማራ ሲሆን በዛሬው እለት አመፅ እና ዝርፊያ በነበረባቸው ቦታዎች ላይ ተሳትፈው ከተለያዩ ተቋማት ዘርፈው በቤታቸው ውስጥ የደበቁትን ንብረት ቤት ለቤት አሰሳ እያደረገ እያስመለሰ ይገኛል። ይህ ተግባር በሚቀጥሉት ቀናት በተለያዩ ቦታዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተሰምቷል።

አመፅ እና ረብሻው በረድ ባለባቸው የተለያዩ ቦታዎች አካባቢ የማፅዳት ስራ በደቡብ አፍሪካ የታክሲ ማህበርተኞች አቀናጅነት እየተካሄደ ይገኛል።

በጆሀንስበርግ ከተማ ከሌላው ቀን በአንፃሩ ሰላማዊ ዉሎ ነበር። አንዳንድ የንግድ ተቋማት ተከፍተው ስራ ጀምሯል።

Faya (Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
አዲስ ስታንዳርድ በጊዜያዊነት ታግዷል፤ ለምን ?

አዲስ ስታንዳርድ ትላንት በፌስቡክ ገፁ ላይ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ለጃከን አሳታሚ የተሰጠውን ፈቃድ በጊዜያዊነት ማገዱን ገልጿል።

ባለሥልጣን መ/ቤቱ ፈቃዱን ያገደበት ምክንያት አላብራራም ብሏል ፤ የሚዲያ ሥራዎቹንም ከሐምሌ 8/2013 ጀምሮ በጊዜያዊነት ማቆሙን የጃከን አሳታሚ አሳውቋል።

ኩባንያው በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት ላይ በሰፈረው መሰረት የፕሬስ ነፃነት መከበሩን ለማረጋገጥ ያሉትን መንገዶች ሁሉ እንደሚጠቀም አስታውቋል።

AS ይህን ካለ ከሰዓታት በኃላ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ባወጣው መግለጫ በኢንተርኔት ላይ ሚድያነት የተመዘገበውን አዲስ ስታንዳርድን ማገዱን አረጋግጧል።

ግንቦት 20/2013 የተመዘገበውን አዲስ ስታንዳርድን በጊዜያዊነት ያገደበትን ምክንያት ሲናገር “በደረሱት ቅሬታዎችና እራሱም ባደረገው ክትትል አሳሳቢ አካሄድ በማስተዋሉ” መሆኑን ገልጿል።

“ሚድያው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተላለፈ ውሣኔን ባለማክበር አንድን የሽብር ቡድን “የመከላከያ ኃይል” ብሎ እውቅና እስከመስጠት በደረሰ ሁኔታ የሽብር ቡድኑ አጀንዳ ማራመጃ መድረክ መሆኑን አውቀናል” ብሏል።

አክሎም “እነዚህ እና ሌሎች ተያያዥ የሥነ ምግባር ግድፈቶች ጥልቅ ምርመራ ይደረግባቸዋል፤ ሌሎች እርምጃዎችም ይወሰዳሉ” ብሏል።

ባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ለፕሬስ ነፃነት እና ሙያዊና በሥነ ምግባር የሚገዛ ጋዜጠኛነትን ለማበረታታት ያለውን ቁርጠኛነት በድጋሚ እንደሚያረጋግጥ የገለፀ ሲሆን "ነፃነት የሚመጣው ከኃላፊነትና ከተጠያቂነት ጋር መሆኑንም በተቆጣጣሪ አካልነቱ አጉልቶ ማስገንዘብ እንደሚፈልግ" አመክልቷል።

ሁሉም መገናኛ ብዙኃን የህግ የበላይነትን እንዲያከብሩና በኃላፊነት ስሜት እንዲሠሩ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#Update

የሱማሌ ክልል የፀጥታ ኃይሉን ወደሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል እንደሚያሰማራ አስታወቀ።

የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ለኢ.ፕ.ድ. በሰጡት ቃል "አገር ለማፍረስ የመጣን ኃይል በጋራ ከመታገል ውጪ ምንም አማራጭ የለም።" ብለዋል።

አክለው ፥ "የሽብር ቡድኑን ጥቃት ለማምከን በሚደረገው እንቅስቃሴ የሱማሌ ክልል የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት የጸጥታ ኃይል ወደ ቦታው ለማስመራት ዝግጅት እያደረገ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም የኦሮሚያ ክልል እንዲሁም የሲዳማ ክልል መንግስታት የፀጥታ ኃይላቸውን ወደሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል እንደሚያሰማሩ መግለፃቸው ይታወቃል (የሲዳማ ክልል የፀጥታ ኃይሎች ዛሬ ደብረማርቆስ መድረሳቸው ተነግሯል) ፤ የደቡብ ክልል መንግስትም የፀጥታ ኃይሎቹ "ግዳጅ ቀጠና" ደርሰዋል ማለቱ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
ቱርክ ለኢትዮጵያ ወታደራዊ ዘመቻ ድሮን ሰጥታለች ?

በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ ፥ ቱርክ ለኢትዮጵያ ሰራዊት ግልጋሎት ይውላሉ የተባሉ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን /ድሮኖች/ እያቀረበች ነው #ሀሰት ሲል አስተባበለ።

ሰሞኑን የኢትዮጵያ መንግስት ለወታደራዊ ዘመቻ የሚሆኑ ቱርክ ሰራሽ ድሮኖች ወደ አገር ውስጥ አስገብቷል የሚሉ ሪፖርቶች በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ተሰራጭቶ ነበር።

ይህን ተከትሎ ነው ኤምባሲው ምላሽ የሰጠው።

በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ ፥ "በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ ቱርክ ለኢትዮጵያ መንግሥት ድሮኖችን እያቀረበች ነው በሚል የሚሰራጨው መረጃ የሐሰት ነው" ብሏል።

በኢትዮጵያ ቱርክ አምባሳደር የሆኑት ያፕራክ አልፕ ፥ "በአሁኑ ሰዓት ምንም አይነት የቱርክ ሰዉ አልባ አዉሮፕላን ወይንም ድሮኖች በኢትዮጵያ የሉም።" ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
#Update

ፕርቶሪያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በደቡብ አፍሪካ ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ በደቡብ አፍሪካ ከሚገኙ የኢትዮጵያውያን ሚዲያ ተቋማት ጋር ተወያይቷል።

በኳዙሉ ናታል እና ሀውቴን ፕሮቬንሶች በዋናነት በደርባን እና በጆሃንስበርግ እንዲሁም በዙሪያቸው በሚገኙ ከተሞች ለሚገኙ ኢትዮያውያን መልዕክት አስተላልፈዋል።

* መልዕክቱን እና ሙሉ መግለጫውን ከላይ ይመልከቱ።

Faya (Tikvah-Family)
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia
5 ዓመት የቱርክ መፈንቅለ መንግስት ከከሸፈ ...

እአአ ጁላይ 15/2016 ተሞክሮ የከሸፈው የቱርክ መፈንቅለ መንግስት ትላንት 5 ዓመት ደፍኗል። በወቅቱ የቱርክ ህዝብ ታንክን ጨምሮ ከባባድ መሳሪያዎችን በባዶ እጁ ፊት ለፊት በመጋፈጥ እጅግ በተጠና ሁኔታ የተደራጀውን ሙከራ ያከሸፈው።

ተሞክሮ በከሸፈው መፈንቅለ መንግስት ወቅት ለሀገራቸው ዘብ ቆመው ህወታቸውን ያጡ የቱርክ ዜጎች ትላንት በመላው ቱርክ ታስበዋል።

ከቱርክ ውጭ በሚገኙም የቱርክ ኤምባሲዎችም ዕለቱ ታስቦ ውሏል።

#በኢትዮጵያ የቱርክ ኤምባሲ አባላት ዕለቱን (ጁላይ 15) እና በዕለቱ ህይወታቸው ያለፈውን 251 ዜጎች በማስታወስ 15 ችግኞችን በአዲስ አበባ ተክለዋል።

የሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን መንግስት ላይ በ2016 በተሞከረው መፈንቅለ መንግስት ሙከራ ወቅት 251 ዜጎች ሲሞቱ 2,200 ሰዎች መጎዳታቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#Update

የተቃውሞ ሰልፍ በሊምፖፖ ...

የደ/አፍሪካ ግዛት በሆነችው LIMPOPO ዋና ከተማ በሆነችው POLOKWANE የታክሲ ማህበርተኞች ( ባለንብረቶች ) አካባቢያቸውን በአካባቢው ካሉ ደቡብ አፍሪካውያን እና የንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመሆን እየጠበቁ ይገኛሉ።

መረጃ መለዋወጫ የዋትሳፕ ግሩፕ ፈጥረው ግጭቱ ወደ ክልላቸው እንዳይገባ በጥምረት ክሕግ አካላት ጋር እንቅስቃሴ ማድረግ ከጀመሩ ቆይተዋል።

በዛሬው እለት የክልሉ ነዋሪዎች ከፖሊስ ፣ ከአካባቢው የታክሲ ማህበርተኞች እና የንግዱ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በደቡብ አፍሪካ በተለያዩ አካባቢዎች የተነፃውን አመፅ እና ያለውን ዝርፊያ #ተቃውመው አደባባይ ወጥተዋል።

ይህ ግጭት ያልተዛመተባቸው የደቡብ አፍሪካ ግዛቶች አሁንም ሰላማዊ የሆነ እንቅስቃሴ እንደቀጠለ ነው። ግጭት ተነስቶባቸው የነበሩ አካባቢዎችም አንፃራዊ ሰላም እያገኙ የንግድ ተቋማትም እየተከፈቱ ይገኛሉ።

እንዲሁም ተዘግቶ ሰንብቶ የነበረዉ ኤን 3 መንገድ ሙሉ በሙሉ ተከፍቷል ወደ ሲድሪ፣ ሄድል በርግ፣ ኩዋዙሉ ናታል እና ሀዉተን የሚወስዱ መንገዶች አሁን ክፍት ናቸዉ። ምን አልባት የመንገድ መጨናነቅና መዘግየት ሊኖር እንደሚችል ፖሊስ ጠቁሟል።

በተጨማሪ የህግ አካላቶች የ24 ሰአት ጥበቃ እያደረጉ ሲሆን በኤን 3 መንገድ ምንም አይነት ጥርጣሬ ከገጠሞ 0800 63 43 57 ይህን ስልክ በመጠቀም ጥቆማ ማድረስ ይችላል።

Video :- 14.4 MB

Faya ( Tikvah-family )
Limpopo
South Africa

@tikvahethiopia