TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AstraZeneca

ብሪታንያ በአስትራዜኔካ ኩባኒያ የተሰራውን የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠት ዛሬ ታህሳስ 26 ጀምራለች ፥ የኩላሊት እጥበት ታካሚ የሆኖ የሰማኒያ ሁለት ዓመት አረጋዊ ይህን ክትባት ለመከተብ የመጀመሪያ ሆነዋል።

ግማሽ ሚሊዮን የአስትራዜኔካ ክትባቶች ዝግጁ ሆነዋል ሲሉ የሀገሪቱ የጤና ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

ይሄኛው ክትባት በፋይዘር ባዮንቴክ ከተቀመመው ክትባት ዋጋው ረከስ እንደሚል ደግሞም እጅግ ከባድ ቅዝቃዜ ባለው ማቀዝቀዣ መቀመጥ ያለበት ባለመሆኑ ለማጓጓዣ ቀለል ያለ መሆኑ መገለፁን ቪኦኤ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBot
#AstraZeneca አጫጭር መረጃዎች ፦

- WHO የክትባት ደህንነት አማካሪ ኮሚቴ የአስታራዜኔካ ክትባት ተጠቂነትን ለመከላከል፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሞትን ይቀንሳል ብለዋል። አማካሪ ኮሚቴው እንዳለው ተገኘው መረጃ የደም መርጋት መጨመርን አያሳይም ብሏል፡፡

- የአውሮፓ የመድሃት ኤጀንስ ክትባቱ እንደተባለው የጎላ የደም ማርጋት ችግር እንደሌለበት እና ክትባቱ ወረርሽኙን በመከላከል ረገድ ውጤታማነት እንደሆነ አሳውቋል።

- ጣልያን፣ ፈረንሳይ፣ ኔዘርላንድስ፣ ፖርቹጋል፣ ስፔን እና ጀርመን ያቋረጡትን የአስትራዜኔካ ክትባት መስጠት እንደሚቀጥሉ አሳውቀዋል።

- የብሪታኒያው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ትላንት አርብ የአስትራዜኔካ የመጀመሪያውን ዙር ክትባት ተከትበዋል።

- የ55 ዓመቱ የፈረንሳይ ጠ/ሚ ዣን ካስቴክስ የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባት ትላንት ተከትበዋል፤ ፈረንሳይ 55 እና ከዛ በላይ እድሜ ላላቸው ዜጎቿ ክትባቱን መስጠት እንደምትቀጥልም ተገልጿል።

- Africa CDC የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት የአስትራዜኔካ የኮቪድ-19 ክትባትን መስጠት እንዲቀጥሉ ብሏል።

Source : France 24, Sky News , Al Ain, Africa CDC, WHO

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#AstraZeneca

- በማላዊ፣
- በደቡብ ሱዳን፣
- በላይቤሪያ፣
- በሞሪታንያ፣
- በጋምቢያ፣
- በሴራ ሊዮን፣
- በጊኒ፣
- በኮሞሮስ እና ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በድምሩ 450,000 የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ጥቅም ላይ ሳይውሉ መወገዳቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል።

ምክንያት ? የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ የበሽታ መከላከል ፕሮግራም ኃላፊ ዶ/ር ሪቻርድ ሚሂጎ እንዳሉት ፥ ወደ አፍሪካ የተላኩ የአስትራዜኒካ ክትባቶች ቶሎ አለመድረሳቸው ጥቅም ላይ ሳይውሉ ለመወገዳቸው ዋናው ምክንያት ነው።

አስትራዜኒካ በአፍሪካ በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘው ክትባት ነው።

1.2 ቢሊዮን ከሚሆኑ የአህጉሪቱ ነዋሪዎች መካከል አስካሁን ክትባት ያገኙት 8 ሚሊዮኑ ብቻ ናቸው።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

@tikvahethiopia