TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.5K photos
1.48K videos
211 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ከሩስያ ጋር በዩክሬን አንዋጋም " - አሜሪካ

የአሜሪካ ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን በሰጡት መግለጫ #ዩክሬን ውስጥ ከሩስያ ጋር ወደ ውጊያ እንደማይገቡ ተናግረዋል።

ባይደን " ፑቲን ጠብ አጫሪ አጥቂ ናቸው ፤ ይህንን ጦርነት መርጠዋል። እሳቸው እና አገራቸው ውጤቱን ይሸከማሉ " ብለዋል።

በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሉን ባይደን አሳውቀዋል።

ጆ ባይደን ፥ " የእኛ ሃይሎች በዩክሬን ውስጥ ከሩሲያ ጋር ግጭት ውስጥ አይደሉም እንዲሁም አይገቡም " ያሉ ሲሆን " ሃይሎቻችን በዩክሬን አይዋጉም የኔቶ አጋሮቻችንን እና የኔቶ ግዛትን እያንዳንዱን ኢንች ግን እንከላከላለን " ሲሉ ተናግረዋል።

ተጨማሪ 7ሺ የአሜሪካ ወታደሮች ወደጀርመን እንደሚያመሩ አሳውቀዋል።

ፕሬዝዳንት ባይደን " ሩሲያ በኩባንያዎቻችን ወሳኝ መሠረተ ልማቶች ላይ የሳይበር ጥቃቶችን የምትቀጥል ከሆነ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ ነን " ሲሉ ዝተዋል።

@tikvahethiopia
#ስንዴ

#ዩክሬን እና በ #ሩስያ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በተለይ ከመካከለኛው ምስራቅ ብዙ ማይሎች ርቆ ነው። ነገር ግን ጦርነቱ በርካታ ሰዎችን ችግር ላይ ሊጥል ይችላል ተብሎ ተፈርቷል።

🌾 ሩሲያ እና ዩክሬን በድምሩ 29 በመቶውን የአለም ስንዴ ወደ ውጭ ይልካሉ። ሀገራቱ አሁን ከገቡበት ጦርነት ጋር ተያይዞ በ13 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የስንዴ ዋጋ ንሯል።

ይህ ጦርነት በዚህ ከቀጠለ በርካታ ሀገራት አስከፊ የሆነ ችግር የሚገጥማቸው ሲሆን በተለይም 3 ሀገራት ለከፍተኛ ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ ፤ እነዚህ 3 ሀገራት እነማን ናቸው ?

🇾🇪 የመን

🌾 በጦርነት የደቀቀችው ሀገር የመን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የምግብ ምርቶች ላይ ጥገኛ ናት ፤ ሀገሪቱ ቢያንስ 27 በመቶውን ስንዴ ከዩክሬን እና 8 በመቶውን ከሩሲያ በመግዛት ላይ ነው የምትገኘው።

🥖 በየመን ለ7 አመታት የዘለቀው ግጭት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ህዝቦቿን ለረሃብ ዳርጓል፤ አሁን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ችግሩን በአስከፊ ሁኔታ እያባባሰ ነው።

🇪🇬 ግብፅ

🌾 90 % የሚሆነው የግብፅ ስንዴ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ነው የሚገባው። ግጭቱ አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እያደረሰ ነው።

🌻 ሩሲያ እና ዩክሬን በግብፅ የሱፍ አበባ ዘይት ዋነኛዎቹ አቅራቢዎች ናቸው።

👨‍🍳 የዳቦ ጋጋሪዎች ከወዲሁ የዱቄት እና የምግብ ዘይት ዋጋ በጣም ውድ ሆነብን እያሉ ነው።

📈 አንድ ዳቦ ጋጋሪ በዱቄት ዋጋ ከ50% በላይ ጭማሪ እና የምግብ ዘይት ዋጋ ላይ አነስተኛ ጭማሪ በመታየቱ ንግዱ ተጎድቷል ብሏል።

🇱🇧 ሊባኖስ

🌾 ሊባኖስ ከዩክሬን 60 በመቶ የሚሆነውን የስንዴ ምርት ታስገባለች።

ሊባኖስ የዩክሬን የሩስያ ጦርነትን ተከትሎ አማራጭ የስንዴ አቅርቦትን እንደምትመለከት ገልፃለች።

🇷🇺 የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ሩሲያ ላይ እንደጉድ እየወረደ ባለው #ማዕቀብ የተነሳ ሩሲያውያን ላይ የከፋ ተፅእኖ ይዞ እየመጣ ነው። ዩክሬንም የጦር ሜዳ በመሆኗ ዜጎቿ ሀገር ጥለው እየተሰደዱ ነው።

ነገር ግን ቀውሱ ከሩሲያ እና ዩክሬን ባለፈ #የስንዴ_ዋጋን እንዲጨምር በማድረግ በመካከለኛው ምስራቅም ምግብ በጣም ውድ እንዲሆን እያደረገው ይገኛል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ነዳጅ📈 ብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዘይት በ10 % ወደ ' 107 ዶላር ' ከፍ ብሏል፤ ይህም እኤአ ከ2014 በኃላ ከፍተኛው እንደሆነ ነው የተነገረው። ከዩክሬን ጋር ጦርነት ላይ የምትገኘው ሩሲያ በዓለም ሦስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ የነዳጅ ዘይት አምራችና ሁለተኛዋ ከፍተኛ የነዳጅ ዘይት ላኪ ሀገር ነች። አጠቃላይ ሩሲያ በዓለም የነዳጅ ምርት 10 % ድርሻ አላት።  የዩክሬን እና የሩስያ ጦርነት፤ ጦርነቱን…
ነዳጅ📈

ዛሬ የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል #ከ110_ዶላር በላይ መድረሱን AFP ዘግቧል።

በአሜሪካ ነዳጅ ገበያ እንደመለኪያ በሚታየው ዌስት ቴክሳስ ኢንተርሚዴት የ1 በርሚል ነዳጅ ዋጋ በ5.06 በመቶ ጨምሮ 108.64 ዶላር ደርሷል።

ሁለቱም ላይ እንደእኤአ ከ2014 በኃላ የተመዘገበ ከፍተኛው ጭማሪ መሆኑ ተነግሯል።

የቀጠለው የ #ሩስያ እና #ዩክሬን ጦርነት መላው ዓለም ላይ ተፅእኖው በየዕለቱ እያየለ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ስውዲን እና ፊንላንድን የNATO አባል የማድረጉ ሂደት 'በፍጥነት' ይካሄዳል ብለን እንጠብቃለን " - የNATO ዋና ጸሐፊ ጄንስ ስቶለተንበርግ ከሩስያ ጋር 1300 ኪሎ ሜትር የሚረዝም ድንበር የምትጋራው ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል የአባልነት ጥያቄዋን የፊታችን እሁድ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል። ስውዲንም የአባልነት ጥያቄዋን በተመሳሳይ ቀን ታቀርባለች ተብሎ ነው የሚጠበቀው።…
#Update

የዩክሬን እና የፊንላንድ ፕሬዜዳንቶች በስልክ ተነጋገሩ።

በዋነኝነት NATOን ለመቀላቀል ባሳየችው ፍላጎት ሳቢያ ከሩስያ ጋር ዛሬም ድረስ መፍትሄ ያላገኘ አስከፊ ጦርነት ውስጥ የገባቸው #ዩክሬን እና NATOን ለመቀላቀል ጥያቄ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ የምትገኘው #ፊንላንድ ፕሬዜዳንቶች በስልክ ተነጋግረዋል።

የፊንላዱ ፕሬዜዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ፤ ከፕሬዜዳንት ቮልድሚር ዜሌንስኪ ጋር በነበራቸው ውይይት ሀገራቸው ለዩክሬን ያላትን ፅኑ ድጋፍ በድጋሜ እንዳረጋገጡላቸው ገልፀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፊንላንድ የNATO አባል ለመሆን እየሄደችበት ስላለው ሂደት እንዳሳወቋቸው ገልፀው የዩክሬኑ ፕሬዜዳንትም ያላቸውን ድጋፍ እንደገለፁለቸው በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፅፈዋል።

የዩክሬን ፕሬዜዳንት ዜሌንስኪ በበኩላቸው ከፊንላዱ ፕሬዜዳንት ጋር በነበራቸው የስልክ ውይይት ፊንላንድ ለNATO አባልነት ለማመልከት ያላትን ዝግጁነት አድንቀው አመስግነዋል ፤ በተጨማሪ ስለ ዩክሬን የአውሮፓ ውህደት በተመለከተ መነጋገራቸውን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ #1 ፦

➡️ #ሴኔጋል ፦ በምዕራብ ሴኔጋል ፤ ቲቫዋን በምትሰኝ ከተማ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰ ቃጠሎ 11 አዲስ የተወለዱ ህጻናት መሞታቸውን ፕሬዝዳንት ማኪ ሳል ተናግረዋል።

➡️ #አፍጋኒስታን ፦ በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል እና ሰሜናዊ ከተማ ማዛር ኢ ሻሪፍ ከተከታታይ በደረሱ ፍንዳታዎች ቢያንስ 14 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል። ዳኢሽ ለጥቃቱ ኃላፊነት መውሰዱን ሮይተርስ ዘግቧል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ለሚያካሂዱት ኦፕሬሽን ወታደሮቻቸውን ወደ ሀገሪቱ ከላኩ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ዩክሬን ውስጥ በወታደራዊ ዘመቻው ከቆሰሉ ወታደሮች ጋር ተገናኝተዋል። በሌላ የሩስያ ጉዳይ ፤ ሀገሪቱ ያለባትን የውጭ ሀገራት እዳ በራሷ መገበያያ ገንዘብ “ሩብል” ለመክፈል ወስናለች ፤ እዚ ውሳኔ ላይ የደረሰችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ከቀናት በፊት በሩሲያ በአሜሪካ ባንኮች በኩል የምትፈጽመውን የውጭ ዕዳ ክፍያ ፍቃድ መሰረዙን ተከትሎ ነው።

➡️ #ዩክሬን ፦ ወደ ሰቨሮዶንስክ ከተማ የሚወስደውን አውራ ጎዳና ለመቆጣጠር በሩስያ እና ዩክሬን ኃያሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት እየተደረገ ነው። ሩሲያ ይህን ከተማ ለመቆጣጠር ተቃርቢያለሁ ብትልም አንድ ከፍተኛ የዩክሬን ባለሥልጣን ነገሩን አስተባብለዋል። ይህ ጎዳና ዩክሬን የምትቆጣጠራቸውን ከተሞች ሩሲያ ከያዘቻቸው ከተሞች ጋር የሚያገናኝ ከፍ ያለ ወታደራዊ ዋጋ ያለው ነው።

➡️ #ጋምቢያ ፦ የጋምቢያ መንግስት የቀድሞ ፕሬዝዳንት ያህያ ጃሜህ ከ20 አመታት በላይ በዘለቀው የስልጣን ዘመናቸው ተፈጽመዋል በተባሉ ግድያ፣ አስገድዶ መድፈር፣ ማሰቃየት እና ሌሎች ወንጀሎች ላይ ክስ እንደሚመሰርት አስታውቋል።

#አልጀዚራ #ቲአርቲወርልድ #ስፑትኪን #ሮይተርስ

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 🌍

➡️ #ሶማሊያ ፦ በሶማሊያ እየተባባሰ ያለው የድርቅ ሁኔታ ለምግብ እጦት እና ለውሃ እጥረት የተጋለጠው ህዝብ ቁጥር 8 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው ድርቅ በገጠር 66 ወረዳዎችና ሰፊ አካባቢዎች ክፉኛ መቷል።

➡️ #ዩክሬንዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት 243 ህጻናት መሞታቸውን እና 444 ህፃናት መቁሰላቸውን አረጋግጫለሁ ስትል አስታውቃለች።

➡️ #ግብፅ ፦ የግብፅ ፍርድ ቤት በቀድሞው የፕሬዚዳንት እጩ አብደል ሞኒም አቡል ፎቱህ እና በሙስሊም ወንድማማች ቡድን ውስጥ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦችን " የሀሰት ዜና በማሰራጨት " እና መንግስትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል በእስራት እንዲቀጡ ወስኗል። አቡል ፎቱህ 70 ዓመታቸው ሲሆን የ15 አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ መሐመድ አል-ካሳስ የአቡል ፎቱህ " Strong Egypt Party " ምክትል ኃላፊ የ10 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ እንዲሁም የ15 አመት እስራት የተፈረደባቸው የወንድማማችነት የቀድሞ የበላይ መሪ ማህሙድ ኢዛት ሲሆኑ እሳቸው ቀደም ሲልም በሌሎች ክሶች የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ነበር።

➡️ #ሱዳን ፦ የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጥቅምት 25 የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን አሳውቀዋል። ቡርሃን " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአገር አቀፍ ደረጃ ተነስቷል " ብለዋል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የዩክሬን #ዶንባስ ግዛትን ነፃ ማውጣት ለሞስኮ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ግዛቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን ለራሳቸው መወሰን አለባቸው ብለዋል።

#ቲአርቲ #AJ #ኤፒ #SNTV

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ 📣

➡️ #ካሜሮን፦ በካሜሩን መገንጠልን አላማቸው አድርገው ይንቀሳቀሳሉ የተባሉ ታጣቂዎች ናይጄሪያ ድንበር አቅራቢያ በሚገኝ መንደር በፈጸሙት ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎችን መግደላቸው ተሰምቷል። ጥቃቱ ባሳለፍነው እሁድ በደ/ምዕራብ የካሜሩን ክፍል ኦቦኒ ሁለት በተሰኘ መንደር የተፈፀመ ሲሆን ከሞቱ ሰዎች ባሻገር ከ60 በላይ ሰዎች ቆስለዋል። ታጣቂዎቹ ነዋሪዎቹ በየወሩ ገንዘብ እንዲከፍሏቸው ይፈልጋሉ፤ ነዋሪዎቹ ደግሞ ፍቃደኛ አልሆኑም። ለዚህም ነው ጥቃት ያደረሱባቸው ተብሏል።

➡️ #ሜክሲኮ ፦ በደቡባዊ ሜክሲኮ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተትና የጎርፍ አደጋ በትንሹ 10 ሰዎች ሲሞቱ በርካቶች የገቡበትን ማወቅ እንዳልተቻለ ተሰምቷል።

➡️ #ቻይና ፦ የሻንጋይ ነዋሪዎች ከሁለት ወር በኃላ የኮቪድ-19 የእንቅስቃሴ ገደብ መነሳቱን ተከትሎ ነፃ ሆነዋል። ነዋሪዎች ባለፉት 2 ወር ኮቪድ-19ኝን ለመከላከል በተጣለ የእንቅስቃሴ ገደብ ምክንያት ከእንቅስቃሴ ርቀው ቆይተዋል።

➡️ #ዩክሬን ፦ የየክሬን ኬርሰን ግዛት በሩስያ ቁጥጥር ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሀገሪቱ ባለስልጣናት ሁሉንም የግንኙነት መስመሮች እንዲዘጉ ማድረጋቸው ተነግሯል።

➡️ #አሜሪካ ፦ የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ጆ ባይደን ሀገራቸው ለዩክሬን 'ቁልፍ ኢላማዎችን' ለመምታት የሚያስችላትን እጅግ የዘመኑ ሮኬቶችን እንደምትልክ አሳውቀዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ ወደ ባይዶዋ እንደሚሄዱ የተነገረላቸው አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፕሬዝዳንት ከሶማሊያ ደቡብ ምዕራብ ግዛት መሪ አብዲአዚዝ ሀሰን ሞሀመድ እና ከባህላዊ የሀገር ሽማግሌዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል። ፕሬዜዳንቱ ወደ ባይዶዋ ያደረጉት ጉዞ ዳግም ፕሬዜዳንት ሆነው ከተመረጡ በኃላ የመጀመሪያቸው ነው።

#ቲአርቲ #ቢቢሲ #ፍራንስ24 #ሲጂቲኤን

@tikvahethiopia
የሩስያ ፕሬዜዳንት ፑቲን ቻይና ገብተዋል።

ፕሬዜዳንት ቭላድሚር ፑቲን በቻይና የስራ ጉብኝት ለማድረግ እንዲሁም " የቤልት ኤንድ ሮድ " ዓለም አቀፍ ትብብር መድረክ ላይ ለመሳተፍ ቻይና ገብተዋል።

በሁለት ቀን የቻይና ቆይታቸው ወቅት ከሀገሪቱ ፕሬዜዳንት እና ከሌሎች ሀገራት መሪዎች ጋር ይመክራሉ ተብሏል።

ፑቲን በተለይ ሀገራቸው ከ #ዩክሬን ጋር ወደ ጦርነት ከገባች በኃላ እምብዛም ከሀገር ሲወጡ እንዳልነበር ይታወቃል።

@tikvahethiopia