TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከዓለም ዙሪያ 🌍

➡️ #ሶማሊያ ፦ በሶማሊያ እየተባባሰ ያለው የድርቅ ሁኔታ ለምግብ እጦት እና ለውሃ እጥረት የተጋለጠው ህዝብ ቁጥር 8 ሚሊየን ሊደርስ ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋትን ፈጥሯል። አሁን ላይ በሀገሪቱ ያለው ድርቅ በገጠር 66 ወረዳዎችና ሰፊ አካባቢዎች ክፉኛ መቷል።

➡️ #ዩክሬን ፦ ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት 243 ህጻናት መሞታቸውን እና 444 ህፃናት መቁሰላቸውን አረጋግጫለሁ ስትል አስታውቃለች።

➡️ #ግብፅ ፦ የግብፅ ፍርድ ቤት በቀድሞው የፕሬዚዳንት እጩ አብደል ሞኒም አቡል ፎቱህ እና በሙስሊም ወንድማማች ቡድን ውስጥ ያሉ ታዋቂ ግለሰቦችን " የሀሰት ዜና በማሰራጨት " እና መንግስትን ለመገልበጥ አሲረዋል በሚል በእስራት እንዲቀጡ ወስኗል። አቡል ፎቱህ 70 ዓመታቸው ሲሆን የ15 አመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ መሐመድ አል-ካሳስ የአቡል ፎቱህ " Strong Egypt Party " ምክትል ኃላፊ የ10 ዓመት እስራት ተፈርዶባቸዋል፣ እንዲሁም የ15 አመት እስራት የተፈረደባቸው የወንድማማችነት የቀድሞ የበላይ መሪ ማህሙድ ኢዛት ሲሆኑ እሳቸው ቀደም ሲልም በሌሎች ክሶች የእድሜ ልክ እስራት ተፈርዶባቸው ነበር።

➡️ #ሱዳን ፦ የሱዳኑ ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብደል ፈታህ አል ቡርሃን ጥቅምት 25 የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት ተከትሎ ተጥሎ የነበረውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መነሳቱን አሳውቀዋል። ቡርሃን " የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በአገር አቀፍ ደረጃ ተነስቷል " ብለዋል።

➡️ #ሩስያ ፦ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ የዩክሬን #ዶንባስ ግዛትን ነፃ ማውጣት ለሞስኮ ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ገልፀው ሌሎች ግዛቶች የወደፊት ዕጣ ፈንታቸውን ለራሳቸው መወሰን አለባቸው ብለዋል።

#ቲአርቲ #AJ #ኤፒ #SNTV

@tikvahethiopia
ከዓለም ዙሪያ ፦

#ካናዳ ፦ የካናዳው ጠ/ሚ ጀስቲን ትሩዶ አነስተኛ የእጅ ሽጉጥ መግዛትም ሆነ መታጠቅ እንዲከለከል ጠይቀዋል። የትሩዶ መንግሥት በጠቅላላው የእጅ ሽጉጥ መግዛት ሆነ ቤት ማስቀመጥ በሕግ እንዲያስቀጣ ረቂቅ እያወጣ ነው። ረቂቁ እንደሚለው ካናዳዊያን የእጅ ሽጉጦቻቸውን ባይነጠቁም ከዚህ በኋላ አዲስ መግዛት ግን አይችሉም። ትሩዶ ይህን ሐሳብ ያፈለቁት በአሜሪካዋ ቴክሳስ ግዛት አንድ አፍላ ታጣቂ 19 ሕፃናትን ተኩሶ ከገደለ በኋላ ነው።

➡️ #እስራኤል #UAE ፦ እስራኤል እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የነፃ ንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል ፤ ይህ እስራኤል ከአረብ ሀገር ጋር ያደረገችው የመጀመሪው ትልቅ ስምምነት ነው።

➡️ #ሴኔጋል ፦ የሴኔጋል ፖሊስ በአንድ ሆስፒታል ውስጥ በደረሰው እና የ11 ህጻናት ህይወት ከቀጠፈው የእሳት አደጋ ጋር በተያያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉ ተሰምቷል።

➡️ #ሩስያ ፦ በያዝነው ዓመት 70ኛ ዓመታቸውን የሚደፍኑት የሩስያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በጤና እክል ምናልባትም በካንሰር ህመም እየተሰቃዩ ሳይሆን አይቀርም የሚሉ ያልተረጋገጡ የመገናኛ ብዙኃን ሪፖርቶች እየወጡ ናቸው። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ግን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ታመዋል መባሉን ሀሰት ሲሉ አስተባበሉ። ላቭሮቭ ፕሬዚዳንት ፑቲን በየቀኑ በአደባባይ እንደሚታዩ እና እንደማኛውም ጤነኛ ሰው የህመም ምልክት አያታይባቸውም ብለዋል።

➡️ #ሶማሊያ ፦ የሶማሊያ ባይዶዋ ከተማ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነች። ከተማዋ ፕሬዝዳንቱ ፈርማጆን አሸንፈው ዳግም የፕሬዜዳንትነት መንበሩን ከተረከቡ በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኟት ከተማ ትሆናለች።

#ቢቢሲ #ቲአርቲ #ሲጂቲኤን #SNTV

@tikvahethiopia
የሀያት ሆቴል ኦፕሬሽን !

በጎረቤታችን ሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በሚገኘው " ሀያት ሆቴል " ባለፈው ዓርብ " አልሸባብ " ጥቃት ፈፅሞ ፤ ህይወት አጥፍቶ ፣ ንብረት አውድሞ በሆቴል ውስጥ የነበሩ ሰዎች አግቶ ለሰዓታት ቆይቷል።

በኃላም የሶማሊያ ጦር በካሄደው ኦፕሬሽን ሆቴሉን ከአልሸባብ ታጣቂዎች ነፃ ማድረግ ችሏል።

በሆቴል ሀያት ምን ተፈጠረ ?

የአልሸባብ ታጣቂዎች " ሀያት ሆቴል " ውጭ ላይ ሁለት ፈንጂ ያፈነዱና ወደ ሆቴሉ ሕንጻ በመግባት ተኩስ ይከፍታሉ።

በዚህ ጥቃት ብቻ በሰዓቱ 12 ሰላማዊ ሰዎችን እንደገደሉ ተገነግሯል (ቁጥሩ ከፍ ሊል ይችላል)።

የ "አልሸባብ" ታጣቂዎች የሽብር ድርጊት በዚህ አላበቃም ወደ ሆቴሉ ከገቡ ከሰዓታት በኋላ በሕንጻው የመጨረሻ ፎቅ ላይ መሽገው ይቆያሉ፤ ሆቴሉንም ይቆጣጠራሉ።

ይህ ሁሉ በሚሆን ሰዓት በሆቴሉ ውስጥ ታግተው የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች ነበሩ።

የሶማሊያ ጦር 30 ሰዓታት ከወሰደ ኦፕሬሽን በኃላ ታጣቂዎቹን በመግደል ሆቴሉን ነፃ ማድረግ እንደቻለ ተነግሯል።

ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች አግተው የነበሩት የአልሸባብ ታጣቂዎች መተለላፊያ ደረጃዎችን በቦምብ በማፍረሳቸው የጸጥታ ሃይሎች ለሰዓታት ያህል እንግዶች ያሉበት ስፍራ ለመድረስ ሲቸገሩ ነበር።

የሶማሊያ ጦር ታጣቂዎቹ ሆቴሉን ከያዙበት ሰዓት አንስቶ ባካሄደው ኦፕሬሽን በርካታ የሆቴሉ እንግዶች እና ሠራተኞችን ከታጣቂዎቹ ማትረፍ ችሏል።

ከሶማሊያ ብሄራዊ ቴሌቪዥን በተገኘ መረጃ 106 ሰዎችን ከሽብር ጥቃቱ ማትረፍ ተችሏል።

ዓርብ አንስቶ ነበረ ጥቃት ትክክለኛ ቁጥራቸው እስካሁን ያልታወቀ ሰዎች ተገድለዋል፣ ቆስለዋል።

የሶማሊያ መንግስት በሽብር ጥቃቱ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት ያሳውቃል ተብሎ እየተጠበቀ ነው።

#SNTV #BBC
Video Credit : SM

@tikvahethiopia