TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
58.1K photos
1.45K videos
208 files
4.02K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ስንዴ

#ዩክሬን እና በ #ሩስያ መካከል እየተካሄደ ያለው ጦርነት በተለይ ከመካከለኛው ምስራቅ ብዙ ማይሎች ርቆ ነው። ነገር ግን ጦርነቱ በርካታ ሰዎችን ችግር ላይ ሊጥል ይችላል ተብሎ ተፈርቷል።

🌾 ሩሲያ እና ዩክሬን በድምሩ 29 በመቶውን የአለም ስንዴ ወደ ውጭ ይልካሉ። ሀገራቱ አሁን ከገቡበት ጦርነት ጋር ተያይዞ በ13 ዓመታት ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የስንዴ ዋጋ ንሯል።

ይህ ጦርነት በዚህ ከቀጠለ በርካታ ሀገራት አስከፊ የሆነ ችግር የሚገጥማቸው ሲሆን በተለይም 3 ሀገራት ለከፍተኛ ችግር ሊዳረጉ ይችላሉ ፤ እነዚህ 3 ሀገራት እነማን ናቸው ?

🇾🇪 የመን

🌾 በጦርነት የደቀቀችው ሀገር የመን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ የምግብ ምርቶች ላይ ጥገኛ ናት ፤ ሀገሪቱ ቢያንስ 27 በመቶውን ስንዴ ከዩክሬን እና 8 በመቶውን ከሩሲያ በመግዛት ላይ ነው የምትገኘው።

🥖 በየመን ለ7 አመታት የዘለቀው ግጭት ከግማሽ በላይ የሚሆነውን ህዝቦቿን ለረሃብ ዳርጓል፤ አሁን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ችግሩን በአስከፊ ሁኔታ እያባባሰ ነው።

🇪🇬 ግብፅ

🌾 90 % የሚሆነው የግብፅ ስንዴ ከዩክሬን እና ከሩሲያ ነው የሚገባው። ግጭቱ አሁን ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት እያደረሰ ነው።

🌻 ሩሲያ እና ዩክሬን በግብፅ የሱፍ አበባ ዘይት ዋነኛዎቹ አቅራቢዎች ናቸው።

👨‍🍳 የዳቦ ጋጋሪዎች ከወዲሁ የዱቄት እና የምግብ ዘይት ዋጋ በጣም ውድ ሆነብን እያሉ ነው።

📈 አንድ ዳቦ ጋጋሪ በዱቄት ዋጋ ከ50% በላይ ጭማሪ እና የምግብ ዘይት ዋጋ ላይ አነስተኛ ጭማሪ በመታየቱ ንግዱ ተጎድቷል ብሏል።

🇱🇧 ሊባኖስ

🌾 ሊባኖስ ከዩክሬን 60 በመቶ የሚሆነውን የስንዴ ምርት ታስገባለች።

ሊባኖስ የዩክሬን የሩስያ ጦርነትን ተከትሎ አማራጭ የስንዴ አቅርቦትን እንደምትመለከት ገልፃለች።

🇷🇺 የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን ተከትሎ ሩሲያ ላይ እንደጉድ እየወረደ ባለው #ማዕቀብ የተነሳ ሩሲያውያን ላይ የከፋ ተፅእኖ ይዞ እየመጣ ነው። ዩክሬንም የጦር ሜዳ በመሆኗ ዜጎቿ ሀገር ጥለው እየተሰደዱ ነው።

ነገር ግን ቀውሱ ከሩሲያ እና ዩክሬን ባለፈ #የስንዴ_ዋጋን እንዲጨምር በማድረግ በመካከለኛው ምስራቅም ምግብ በጣም ውድ እንዲሆን እያደረገው ይገኛል።

@tikvahethiopia