TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ድሬፖሊስ : በዛሬው ዕለት የድሬዳዋ ፖሊስ ከዚህ ቁም ይጠቀምበት የነበረውን የደንብ ልብስ በአዲስ የደንብ ልብስ መቀየሩን በይፋ አስተዋውቋል።

አዲሱ የደንብ ልብስ ፦
- የተቋሙን ቁመና በሚገልፅ መልኩ በጥናት የቀለም (ከለር) ልዩነት የተደረገበት
- አዲሱ የተቋሙ አርማ ያረፈበት
- ቀደም ብሎ አባላት ያነሱት የነበረውን የጥራትና ተያያዥ ችግሮችን የፈታ እንደሆነ ተገልጿል።

የፎቶ ባለቤት : ድሬ ፖሊስ

@tikvahethiopia
#ድሬ

በድሬዳዋ ከተማ ትላንት በደረሰ የእሳት አደጋ የዋጋ ግምቱ 46 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወደመ።

" ለጊዜው  ምክንያቱ ባልታወቀ  ሁኔታ  በተነሳ የእሳት ቃጠሎ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር የሚገመት ንብረት ውድሟል " ሲል የድሬድዋ ፖሊስ አሳውቋል።

ፖሊስ እንደገለፀው አደጋው የደረሰው ትላንት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም ቀበሌ 02 ልዩ ቦታው ኢንዱስትሪ መንደር ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ንብረትነቱ " የሮያል ፎም ፍራሽ እና ፕላስቲክ ፋብሪካ " ላይ ነው፡፡

ከቀኑ 5 ሰአት ገደማ በተነሳው የእሳት ቃጠሎ የፋብሪካው ንብረት የሆኑ ፦

👉 አንድ ትልቅ የምርት ማከማቻ መጋዘን፤
👉 አንድ  ቦንድድ ማሽን፤
👉 በርካታ የተጠናቀቁ የስፖንጅ ፍራሽ ምርቶች እንዲሁም ሁለት ሆዝ የእሳት ማጥፊያ በአጠቃላይ የዋጋ ግምቱ አርባ ስድስት (46) ሚሊዬን ብር ንብረት ወድሟል።

አደጋው እንደደረሰ የድሬዳዋ ፖሊስ የእሳት እና ድንገተኛ ዲቪዥን እና የድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ የእሳት አደጋ ተከላካይ ቡድን በቦታው ላይ በመድረስ እሳቱ ወደ ሌላ ቦታ እንዳይዛመት ከፍተኛ ርብርብ አድርገዋል። አደጋውን ለመከላከል አርባ ስምንት ሺ ሊትር ውሃ እና አንድ መቶ ሊትር ፎም መጠቀማቸው ተገልጿል።

በደረሰው የእሳት አደጋ ከንብረት ጉዳት ውጪ በሰው ላይ ምንም አይነት አደጋ ያልደረሰ መሆኑን የገለፀው የድሬዳዋ ፖሊስ በአሁኑ ወቅት የአደጋውን መንስኤ በማጣራት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

ምንጭ፡ #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
#ድሬ

ትላንት ምሽቱን በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቀው ፤ በቀበሌ 07 አፈተ-ኢሳ / አሸዋ ሰልባጅ ተራ / ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጎርፍ መውረጃ አሸዋ ውስጥ ተኝቶ የነበረው የ55 አመት ጎልማሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን የሰልባጅ ልብስ መሸጫ ቦታው ላይ ጉዳት ደርሷል።

የ55 አመቱ ጎልማሳ በአካባቢው ላይ የቀን ስራ እየሰራ ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ግለሰብ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኳል ብሏል።

ከመጋቢት 7 - መጋቢት መጨረሻ ድረስ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የሜትዮሮሎጂ ትንበያ መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የድሬዳዋ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳሬክቶሬት መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።

በሌላ ዜና ፦ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ገደማ ቀበሌ 09 " ገንደ ገመቹ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የገባ #ከርከሮ በቤቱ ባለቤት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በድልጮራ ሪፈራ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ ዳርቻ የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢውን #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
#ድሬ

የድሬዳዋ ፖሊስ ፤ በአሽከርካሪነት ተመድቦ ከሚሰራበት ድርጅት እንዲያሽከረክር የተሠጠውን መኪና ሰርቆ በ290 ሺህ ብር የሸጠው ተጠርጣሪ ግለሰብን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገለፀ።

ተጠርጣሪው ግለሰብ CCECC በተሰኘ የመንገድ ስራ ድርጅት ተቀጥሮ በማገልገል ላይ ነበር።

የካቲት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከምሽቱ ሶስት ሠዓት ላይ የድርጅቱን የስራ ኃላፊዎች ወደቤታቸው ካስገባቸው በኋላ ያለማንም ፍቃድ ተሸከርካሪውን ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር በመሆን ወደ አዲስ አበባ በመውሰድ 4 ሚሊዮን ብር የሚገመተውን ተሸከርካሪ ለአንድ ግለሰብ በ290 (ሁለት መቶ ዘጠና ሺ) ብር ሽጧጣ።

የወንጀል ድርጊቱ ከተፈፀመ ከሁለት ቀን በኋላ ከድርጅቱ መኪና እንደጠፋ ሪፖርት የደረሰው ፖሊስ ከተጠርጣሪው አድራሻ በመነሳት ባደረገው ክትትል ተሽከርካሪውን በሌላ ሰው እጅ በአዳማ ከተማ ሲሽከረከር በቁጥጥር ስር ሊያውለው መቻሉ አሳውቋል።

በአሁኑ ወቅት ተሽከርካሪውን ሰርቆ የሸጠውን አሽከርካሪ እና የገዛውን ግለሰብ ጨምሮ 5 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያጣራ መሆኑን ድሬ ፖሊስ ገልጿል።

የድሬ ፖሊስ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ለንብረታቸው ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንዳለባቸው መልእክት አስተለልፏል።

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድሬዳዋ❤️

የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው።

ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ በከባድ ዝናብ ውስጥ ሆነው ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለነበሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላቶች የማበረታቻ የብር ሽልማት ተበረከተላቸው።

ሽልማቱን ያበረከቱት የትራፊክ ፖሊስ አባላቱን ተግባር በማህበራዊ ሚድያ የተመለከቱ የድሬዳዋ ወጣቶች ናቸው።

የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ የትራፊክ አደጋ እንዳይደርስ ሲያከናውኑት የነበረው ስራ ለሌሎችም ትምህርት ሆኖ ያለፈ ነው። #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia