TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.07K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ድሬ

ትላንት ምሽቱን በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በጎርፍ የአንድ ሰው ህይወት ያለፈ ሲሆን በንብረትም ላይ ጉዳት ደርሷል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ እንዳሳወቀው ፤ በቀበሌ 07 አፈተ-ኢሳ / አሸዋ ሰልባጅ ተራ / ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ በጎርፍ መውረጃ አሸዋ ውስጥ ተኝቶ የነበረው የ55 አመት ጎልማሳ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ በተኛበት ህይወቱ አልፎ የተገኘ ሲሆን የሰልባጅ ልብስ መሸጫ ቦታው ላይ ጉዳት ደርሷል።

የ55 አመቱ ጎልማሳ በአካባቢው ላይ የቀን ስራ እየሰራ ራሱን እና ቤተሰቡን የሚያስተዳድር ግለሰብ መሆኑን የገለጸው ፖሊስ ለተጨማሪ ምርመራ አስክሬኑ ወደ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል ተልኳል ብሏል።

ከመጋቢት 7 - መጋቢት መጨረሻ ድረስ መደበኛ እና ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊዘንብ እንደሚችል የሜትዮሮሎጂ ትንበያ መረጃ የሚያመለክት ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር ለጎርፍ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ ያሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የድሬዳዋ የአደጋ ስጋት ኮሚሽን የቅድመ ማስጠንቀቂያ ዳሬክቶሬት መረጃ ሲሰጥ ቆይቷል ተብሏል።

በሌላ ዜና ፦ መጋቢት 18 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ ዘጠኝ ሰአት ገደማ ቀበሌ 09 " ገንደ ገመቹ " ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት የገባ #ከርከሮ በቤቱ ባለቤት ላይ ከባድ የአካል ጉዳት አድርሷል።

በአሁኑ ወቅት ግለሰቡ በድልጮራ ሪፈራ ሆስፒታል በህክምና ላይ የሚገኝ ሲሆን በድሬዳዋ ከተማ ዳርቻ የሚኖሩ የህብረተሰቡ ክፍሎች ተገቢውን #ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ፖሊስ አሳስቧል፡፡

#ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia