TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ኑ ትውልድ እንገንባ!

#ሰበታ የምትገኙ 0932540523/ያሬድ ለማ/ ፣ 0921421493/ያብስራ ካሳ/

#አዲስ_አበባ የምትገኙ 0970514616/ዮናስ ገ/መስቀል/፣ 0924140293/መባ/

#ድሬዳዋ የምትገኙ 0915034762/መሃሪ/

#አዳማ የምተገኙ 0949377735/ሰላም/

#ሀዋሳ የምትገኙ +251926429534/ተስፋ/፣ +251935932153/ብስራት/

በሁሉም የክልል፣ ዞን እና ወረዳ የሚገኙ አስተባባሪዎችን በየጊዜው ይፋ እናደርጋለን!! እርሶም የዚህ አካል በመሆን ማስተባበር ይችላሉ! @tsegabwolde 0919743630

የዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች በትልቁ አሻራችሁን እንደምታሳርፉ ምንም አንጠራጠርም!

5ኛው አመት የTIKVAH-ETH የመፅሃፍት ማሰባሰቢያ ዘመቻ!
#ድሬዳዋ

የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መስሪያ ቤት የድሬዳዋ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከህብረተሰቡ በደረሰ #ጥቆማ መሰረት ከፖሊስ አካላት ጋር በመተባበር በድሬዳዋ ከተማ አባይ በሚባል መድኃኒት ቤት ውስጥ እንዲሁም በአንድ ግለሰብ ሲዘዋወሩ የነበሩ መድሃኒቶችን ይዟል።

መድሃኒቶቹ 27 ሺህ 470 ብር የሚገመት ዋጋ ያላቸው ሲሆን፥ የመድኃኒት ቤቱ ባለቤት በፖሊስ በቁጥጥር ስር እንዲውል በማድረግ ህጋዊ እርምጃ እንደተወሰደበት ከባለስልጣኑ የተገኘው መረጃ ያመላክታል። ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ የቁጥጥሩ ባለቤት በመሆን ከማንኛውም ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ራሱን በመጠበቅ የቁጥጥር ስራውን እዲያግዝም ጥሪውን አቅርቧል።

መሰል ህገወጥ የምግብና የመድኃኒት ንግድና ዝውውር ድርጊቶች ሲፈጸሙ ለባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በነጻ የስልክ መስመር በ8482 ወይም በአካባቢው ለሚገኙ የፍትህ አካላትና የጤና ተቆጣጣሪዎች እንዲጠቁም ጠይቋል።

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አምቦ #ለኩ #ጅማ #ከሚሴ #ይርጋለም #ሃዋሳ #ሶዶ

ኑ ትውልድ እንገንባ!

#አዲስ_አበባ
0970514616/ዮናስ ገ/መስቀል/
0924140293/መባ/

#ሰበታ
0932540523/ያሬድ ለማ/
0921421493/ያብስራ ካሳ/

#መቐለ
0912178520/ኤርሚያስ ደጀኔ/
0923602445/ፊራኦል መስፍን/

#ራያ_ቆቦ
+251949256094/ሉላይ/

#ጅማ
0911670454/አሰፋ/

#ድሬዳዋ
0915034762/መሃሪ/

#አዳማ
0949377735/ሰላም/

#ሀዋሳ
+251926429534/ተስፋ/
+251935932153/ብስራት/

#ለኩ
0919687777/ዳዊት እንዳለ/

#ይርጋለም
0953804369-/አሸናፊ/
0964039768-ብርሀኑ/

#ከሚሴ
0915543171/ሁሴን/

#ወላይታሶዶ
+251913776084/Aso/
0926172318/Beza/

•ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ መደበኛ የመማሪያ እና አጋዥ መፅሃፍትን በመለገስ ለመጭው ትውልድ የተሻለች ኢትዮጵያን እናውርስ!!

📚የዘንድሮው አመት ተፈታኝ ተማሪዎች እና ወላጆች በዚህ ስራ ላይ በስፋት በመሳተፍ ለመጭው ትውልድ አርዓያ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እናቀርባለን!

5ኛው አመት የTIKVAH-ETHIOPIA የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ!

በዚህ ሀገራዊ ስራ መሳተፍ የምትፈልጉ የበጎ አድራጎት ማህበራትና ግለሰቦች @tsegabwolde

በሁሉም ከተሞች ያሉ አስተባባሪዎችን በየዕለቱ እናሳውቃለን!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እሁድን በበጎ ተግባር!

#አዲስ_አበባ

💫የአንድ እሽግ ለአንድ ልጅ የሙዚቃ ድግስ ነገ እሁድ ነሃሴ 26 በጌትፋም ሆቴል ይደረጋል። መግቢያ: 12 ደብተር - 2 እስክርቢቶ - 2 እርሳስ - 2 መቅረጫ እና 2 ላጲስ - የTIKVAH-ETH የአ/አ ቤተሰቦች እንዳትቀሩ! #onepackforonechild

💫Rotaract Ethiopia በጎ ስራ ላይ የተሰማራ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ሲሆን ለአዲሱ አመት #አልባሳት እያሰባሰበ ነው እናተም ተሳተፉ ያላችሁበት መጥተው ይወስዳሉ ደውሉላቸው Rotaract club of Atrons President Yeabsera --- +251922175164. (Or Natnael -@Natysf +251923594536, Sofonias - @SophoDarik +251 92 453 9140

#ወላይታ_ሶዶ

💫"አለን ኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበር ወላይታ ሶዶ ቅርንጫፍ" ላለፉት ሁለት ቀናት ለ800 ተማሪዎች ለትምህርት የሚሆናቸውን ቁሳቁስ እያሰባሰበ ነው። በተጨማሪ የደም ልገሳ እየተደረገ ይገኛል። ነገም ለ3ኛ ቀን ይቀጥላል። ወላይታ ሶዶ ያላችሁ የTIKVAH-ETH ተከታዮችም እሁዳችሁን ከነሱ ጋር ማሳለፍ ትችላላችሁ። ስልክ +251913776084፣ 0926172318

#ሻሸመኔ

💫የሻሸመኔ ወጣቶች ነገ የይደግ በጎ አድራጎት ማእከልን ይጎበኛሉ እንዲሁም ግቢውን ያፀዳሉ። የሻሸመኔ የTIKVAH-ETH ቤተሰቦች ኑ እሁድን በመልካም ስራ እናሳልፍ ከሰአት 8:00 ሰአት ላይ CDI እንገናኝ ብለዋችኃል!! ስልክ፦0926940304

#ለኩ
💫በለኩ ከተማ የሚገኙ "እኔም ለወገን" የበጎ አድራጎት ማህበር አባላት የሻይ ቡና ፕሮግራም አዘጋጅተዋል። የለኩ ቤተሰቦቻችን እሁድን አብራችሁ!0986241726

💫"ነገ በለኩ ፉርቃን የአበባ እና የችግኝ መተከል ስነ ስርአት ስለሚኖረን የቻላችሁ ከጥዋቱ 3 ሰአት በለኩ ፉርቃን ግቢ በመገኘት አሻራችሁን እንድታሳርፉ ጀመአችን ጥሪውን ያስተላልፋል" ቢላል የለኩ ሙስሊም በጎ አድራጎት ጀመአ

#ድሬዳዋ

💫"የድሬዳዋ ስካውት ካውንስል አባላት ነን በከተማችን የሚገኙ መንገዶች በግራና በቀኝ ያሉ ጠርዞችን ነጭ እና ጥቁር ቀለም በመቀባት ለመንገዱ ውበት እንዲሁም በምሽት ለአሽከርካሪዎች በቀላሉ እንዲታይ በማድረግ የትራፊክ አደጋን ከመቀነስ አንፃር የበኩላችንን እየተወጣን ነው ። ስራው ገና አልተጠናቀቀም ነገም እለተ ሰንበት ይቀጥላል።"

#ወሊሶ

💫ወገኔን ለማስተማር እሮጣለሁ በከተማችን ቅን ወጣቶች የተቋቋመው የ" we are one" የበጎ አድራጎት ማህበር ባሳለፍነው አመት "ወገኔን ለማስተማር እኔም እሮጣለሁ" በሚል መሪ ቃል ታላቅ የእሩጫ ዉድድር ማሰናዳቱ የሚታወስ ነዉ። በዘንድሮ አመትም በተመሳሳይ መሪ ቃል በአይነቱ ልዩ በሆነ ሩጫ ዝግጅቱን አጠናቆ እርሶን እየጠበቀ ይገኛል ታድያ እርሶም የሩጫ ቲሸርት በመግዛት ከአላማችን ጎን ይሰለፉ። የቲሸርቱ ዋጋ 100 ብር የቲሸርቱ መገኛ ቦታ: ፓስታ ቤት፣የኛ ህንፃ ፣ክርኪስ እናም ሁሉም ቦታ አዙረው በመሸጥ ላይ ከሚገኙ አባላቶች

በሌሎች አካባቢዎች ያሉ እንቅስቃሴዎችን እንደደረሰኝ አቀርባለሁ!
#ድሬዳዋ

የጤና ሚኒስትር ዶክትር አሚር አማን በድሬ ዳዋ ከተማ አስተዳደር የችጉንጉንያ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር በሚኒስቴሩ እና በከተማ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ጎበኙ፡፡ የጤና ሚኒስትሩ በዚሁ ጉብኝታቸው ሚኒስቴሩ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባባር ወረርሽኙን ለመቆጣጠር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ተግረዋል፡፡

Via #FBC
@tsegabwolde @tikvahiopia @tikvahethmagazine
ነገ ጳጉሜ 2 በስራ ገበታው ላይ ያልተገኘ ሰራተኛ ስራውን በገዛ ፈቃዱ እንደለቀቀ ተቆጥሮ ድርጅቱ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ገልጿል። #DIREDAWA

#ድሬዳዋ_ናሽናል_ሲሚንቶ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#New⬆️ "...ወደ ክቡር ስራችሁ ትመለሱ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን!!" #ድሬዳዋ_ናሽናል_ሲሚንቶ #DIREDAWA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ድሬዳዋ | ዛሬ ጥዋት በድሬዳዋ ከተማ መጋላና አዲስ ከተማ ለሰዓታትም ቢሆን አለመረጋጋት ተፈጥሮ እንደነበር የድሬዳዋ ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንደማያውቁ የገለፁት ቤተሰቦቻችን ከተለያየ አቅጣጫ የመጡ የተደራጁ ወጣቶች ከሰፈር ወጣቶች ጋር ግጭት ፈጥረ ነበር ብለዋል። የድንጋይ መወራወር ነበር በዚህም በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል፤ ሆስፒታልም የተወሰዱ ሰዎች ነበሩ፤ በአንድ የታገ ውሃ ማሸጫ ሱቅ ላይም ውድመት ደርሷል፤ መከላከያ ሲገባ ግን ሁሉም ነገር ወደነበረባት ሊመለስ ችሏል ሲሉ ገልፀዋል። አስተያየቷን የሰጠች መጋላ አካባቢ የምትኖር የቤተሰባችን አባል ሁኔታው የተፈጠረው በሰፈሩ የነበሩ የመከላከያ አባላት በመውጣታቸው ሳይሆን እንደማይቀር ገልፃ የአካባቢው ነዋሪዎችም ለከተማው ዘላቂ መፍትሄ ሳይገኝ የመከላከያ ሰራዊቱ ከተማውን ለቆ መውጣት እንደሌለበት ገልጻለች።

ከዚህ ቀደም በቀላሉ መቆጣጠር የሚቻል ጉዳይ አድጎ ከፍተኛ ቀውስ መፍጠሩ አይዘነጋምና መንግስት አሁንም ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዛሬ የህዳር 10/2012 ዓ/ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልት እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሰባሰበ መረጃ👇
https://telegra.ph/ETH-11-20-4

(TIKVAH-ETHIOPIA)

#ድሬዳዋ #ሀረማያ #ወልዲያ #መቱ #ASTU
#መደወላቡ #ባህርዳር #ደባርቅ #ደብረታቦር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሀዋሳ #ድሬዳዋ #ባህርዳር

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አዲስ የማለዳ በረራ ጀመረ።

አየር መንገዱ ከሀዋሳ ፣ ከድሬዳዋ እና ከባህር ዳር ወደ አዲስ አበባ ማለዳ 1:00 የሚነሱ እለታዊ በረራዎች መጀመሩን አሳውቋል።

#EthiopianAirlines

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሳፋሪኮም ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በድሬዳዋ ከተማ ጀምሯል። ይህ የደንበኞች የሙከራ ምዕራፍ ኩባንያው በአገር አቀፍ ደረጃ አገልግሎቱን ለመስጠት ከሚዘጋጅበት ጊዜ አስቀድሞ በተለያዩ ክልሎች እና ከተሞች የኔትወርክ እና የአገልግሎት ጥራቱን በተጠናከረ ሁኔታ የሚፈትሽበት ወቅት ነው። በድሬዳዋ ከተማ የደንበኞች የኔትወርክ ሙከራ በ2G፣ 3G እና 4G ኔትወርኮች…
#DireDawa #SafaricomEthiopia

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ የደንበኞች አገልግሎት በ " 700 " ላይ በመደወል ማግኝት ይቻላል።

ዛሬ ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በድሬዳዋ ከተማ መጠነ ሰፊ የደንበኞች የኔትዎርክ ሙከራ ጀምሯል።

ደንበኞች ለማንኛውም የደንበኞች ድጋፍ አገልግሎቶች በጥሪ ማዕከሉ በተለያዩ ቋንቋዎች ማለትም ፦
- በአማርኛ
- በአፋን ኦሮሞ
- በሱማሊኛ
- በትግርኛ እንዲሁም እንግሊዝኛ የማግኘት አማራጭ የሚኖራቸው ሲሆን የደንበኞች አገልግሎት ሠራተኞችን " 700 "  ላይ በመደወል ማናገር ይችላሉ።

* ማስታወሻ

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ሽያጭ ማዕከሎች ለሲም ካርድ ሽያጭ ምዝገባ ፣ ለስልክ ቀፎዎች ግዢ እና ልዩ ልዩ የደንበኞች ድጋፍ ለመስጠት ክፍት ናቸው። የሽያጭ ማዕከሎቹ የሚገኙት ፦
- #ከዚራ
- #መስቀለኛ
- #ኮርኔል ነው።

#SafaricomEthiopia #ድሬዳዋ #DireDawa

@tikvahethiopia
#ድሬዳዋ

" ልክ እንደሚገዛ ሰው ዙሪያውን እየተሽከረከርክ ' ሊሾ ነው ሊሾ አይደለም ' እያልክ አተካራ ውስጥ መግባት የትራንስፖርት ሂደቱን ማደናቀፍ ነው " - ኮሚሽነር አለሙ መግራ

አሁን ላይ ከሀገሪቱ ከተሞች አስተማማኝ ደህንነት እና ሰላም ያለባት #ድሬዳዋ በየዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የከባድ ጭነት ተሽከርካሪዎችን ታስተናግዳለች።

የከተማው ፖሊስ የትራፊክ ፅህፈት ቤት እንዚህ የደረቅም ይሁን ፍሳሽ ጭነት ተሽከርካሪዎች ጉዟቸው የተሳለጠ እንዲሆን የሚያስተዳደርበት የራሱ መንገድ አለው።

የድሬዳዋ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዋና አዛዥ ኮሚሽነር አለሙ መግራ የከባድ ተሽከርካሪዎችን በተመለከተ በሰጡት ገለፀ ፤ ከተማይቱ በየቀኑ ከ1 ሺህ በላይ የደረቅ እና ፍሳሽ ጭነት የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ታስተናግዳለች።

ኮሚሽነሩ ፤ " እነኚህ መኪናዎች በአደጋ መጠን እዚህ ግባ የሚባል ነገር የላቸውም ፤ ህግ እና ስርዓትን መተላለፍ ላይም ያን ያህል ችግር የለም።

ለምሳሌ ፦ ከጅቡቲ የሚመጡ ትላልቅ መኪናዎች ክብደት ከሆነ በሚዛን ነው የሚመዘኑት አንድ የትራፊክ ተቆጣጣሪ ይሄንን ክብደት ትርፍ ጭነሃል ማለት አይችልም። የመቆጣጠሪያ ቦታ አለ። ፍጥነትም ከሆነ የሚፈጥኑበት እድል የለም ከተማ ውስጥ ፣ መንጃ ፍቃድም ሳይዝ ጎረቤት ሀገር መግባት አይችልም ብዙ ነገር አሟልቶ ነው የሚመጣው።

ብዙ ነገሮች አሟልቶ የሚገኝ መኪናን መንገድ ላይ አስቁመህ ዙሪያውን እየተሽከረከርክ እንደሚገዛ ሰው ሊሾ ነው ሊሾ አይደለም፣ እንዲህ ነው እንደዛ አይደለም እያልክ አተካራ ውስጥ መግባት በራሱ የትራንስፖርት ሂደቱን ማደናቀፍ ነው " ብለዋል።

የከተማው ፖሊስ ፣ ትራፊክም እነዚህን መኪናዎች የሚያስተዳድርበት የራሱን ሲስተም ዘርግቶ እየተጠቀመ መሆኑን ገልጸዋል።

" መኪናዎቹ ከተማ ከገቡ በኃላ ሊሳሳቱ የሚችሉት መንገድ ነው " ያሉት ኮሚሽነሩ " መንገድ ሲሳሳቱ ምልክቶችን ሊጥሱ ይችላሉ ስለዚህ እነዚህ እንግዶች ስለሆኑ መንገድ የማሳየት ስራ መስራት ከመቅጣት ባለፍ " እንደሚገባ ጠቁመዋል።

" እነዚህ ተሽከርካሪዎች በአደጋ ላይ ያን ያህል ተሳትፎ ስለሌላቸው በሆነው ባልሆነው ሰብሰብ ፈልገህ የምትቀጣ ከሆነ ችግሩ ለመቅጣት ሳይሆን ሌላ የዲሲፕሊን ችግር ስለሆነ ይሄ ድሬዳዋ ፖሊስ ትራፊክ ውስጥ NO / አይሆንም ተብሎ አንድም የጅቡቲ መኪና ፤ ትላልቅ ከባድ መኪናዎች ከተማችን ሲገቡ harass የሚያደርግ ፣ የሚቀጣ፣ የሚከስ ነገር የለም " ሲሉ አስረድተዋል።

ይህ በመሆኑ እነዚህ ተሽከርካሪዎች ያለምንም መደናቀፍ ፤ ለአንድ ደቂቃ ሳይቆሙ በተሳለጠ መንገድ እንዲሄዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

ይህ እየተደረገ ያለውም የከባድ ተሽከርካሪዎቹ የሀገር የጀርባ አጥንት በመሆናቸው ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ይህ በ #ድሬዳዋ ያለ አሰራር ለሌሎችም ቦታዎች ማስተማሪ የሚሆን ነው። በተለያዩ አካባቢዎች የትራፊክ ፖሊሶች በሆነው ባልሆነው ተሽከርከሪ እያስቆሙ የሚቀጡበት፣ ሲያሻቸው የሚሳደቡበት ፣ ሲያሻቸው ገንዘብ የሚቀበሉበት ሁኔታ አለ፤ ስለዚህ ይህን ከስርዓት የወጣ ተግባር ሁሉም በየደረጀው ማረም ይገባዋል።

@tikvahethiopia
የዘወትሯ ኢትዮጵያ የፎቶግራፊ አውደርዕይ !

የአዲስ አበባ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ማህበር (አአፎባማ) ከግራር የጠቢባን መነሃሪያ እንዲሁም ከUSAID ጋር በመተባበር የዘወትሯ ኢትዮጵያ የተሰኘ ተጓዥ የፎቶግራፍ አውደርዕይ አዘጋጅቷል።

ይህ አውደርዕይ በሚካኤል ጸጋዬ ዋና አዘጋጅነት የቀረበ ነው።

የመጀመርያ ዙር ቆይታውን በባህርዳር ያደረገው የዘወትሯ ኢትዮጵያ ተጓዥ የፎቶግራፍ አውደርዕይ አሁን ወደ #ድሬዳዋ አቅንቷል።

ከነሃሴ 30 ጀምሮ እስከ ጳጉሜ 4 ለአምስት ቀናት በሚቆየው በዚህ የፎቶግራፍ አውደርዕይ ላይ 15 የሚሆኑ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች በአጠቃላይ ከ90 በላይ በስራዎቻቸውን ያቀርባሉ። በቀጣይ ሐዋሳ ላይ ከመስከረም 3 - 7/2016 መዳረሻውን ያደርጋል።

በተዘረሩት ቀናት ላይ በፎቶ አውደርዕዩ ላይ በመገኘት የዘወትሯን ኢትዮጵያ አብረውን ይቃኙ! ኑ! የአንድነታችንን ውበት በጋራ እናድንቅ!
#ድሬዳዋ

🔹" የትውልድን ስነምግባር የምትቀርጽ እና በይዞታዋም ህጋዊ የሆነችን ቤተክርስቲያን  አፍርሶ ሆቴል መስራት አግባብነት የለውም " - ቤተክርስቲያን

🔸" ቦታውን ለልማት ተፈልጎ ነው ፤ ካቢኔው የልማት ጥያቄዎችን የማስተናገድ ሃላፊነት አለበት " - የድሬዳዋ ከንቲባ ጽ/ቤት

የድሬደዋ መካነ-ኢየሱስ ቤተክርስቲያን የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ቤተክርስቲያኗ ካለችበት ቦታ እንድትነሳ የሚል ደብዳቤ እንደላከላት አስታውቃለች።

ቤተክርስቲያኗ የከተማው አስተዳደር ውሳኔውን በ2 ቀን ውስጥ እንዲያስተካክል ጠይቃለች።

ቤተክርስቲያኗ ፤ ለ40 አመታት በስፍራው የቆየች እና ህጋዊ ይዞታ እንዳላት የገለፀች ሲሆን የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጽ/ቤት ግን ለሆቴል ስራ በሚል በአንድ ወር ውስጥ ከቦታው እንድትነሳ ደብዳቤ መላኩን አስረድታለች።

የቤተክርስቲያኗ ዋና ሰብሳቢ ቄስ በላቸው አምባሮ ፤ " የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት ለቤትክረስቲያኗ በላከው ደብደቤ እንዳስቀመጠው ቦታው ለሆቴል ቱሪዝም መፈለጉን የሚገልፅ ነው " ብለዋል።

ነገር ግን የትውልድን ስነምግባር የምትቀርጽ እና በይዞታዋም ህጋዊ የሆነችን ቤተክርስቲያን  አፍርሶ ሆቴል መስራት አግባብነት የሌለው እና በምዕመን መካከል ሁከትን መፍጠር እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

" ከዚህ በፊት ቤተክርስቲያኗ ለከተማዋ መንገድ ስራ በሚል ተባበሪ በመሆን የተወሰኑ ሜትሮችን ወደ ውስጥ ተጠግታለች " ያሉት ቄስ በላቸው፣ " ይህ ግን በህልውናዋ ላይ የመጣ ነው " ብለዋል፡፡

ስለሆነም የከተማዋ ከንቲባ ጽ/ቤት ካቢኔ የወሰነውን ውሳኔ በሁለት ቀን ውስጥ እንዲያስተካክል የጠየቁ ሲሆን ይህ ካልሆነ ግን ቤተክርስቲያኗ ሌሎች ህጋዊ አማራጮችን እንደምትጠቀም አስገንዝበዋል።

የድሬደዋ ከተማ ከንቲባ ጸህፈት ቤት በበኩሉ ቤተክርስቲያኗ እንድትናሳ ካቢኔው ወስኖ ለቤተክርስቲያኗ ደብዳቤ መላኩን አረጋግጧል።

የጽ/ቤቱ  ሃላፊ አቶ ገበየሁ ጥላሁን  ፤ " ቦታው ለልማት ተፈልጎ ነው ፤ ካቢኔው የልማት ጥያቄዎችን የማስተናገድ ሃላፊነት አለበት " ብለዋል።

ነገር ግን ቤተክርስቲያኗ ጉዳዩን ተቃውማ ደብዳቤ ከመላክ ውጭ ከጽ/ቤቱ ጋር አልተነጋገረችም ያሉ ሲሆን ሁሉም ነገር የሚፈታው በንግግር ነው ብለዋል።

ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ድሬዳዋ

" ለከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የምንሰጠው #ክብር ትልቅ ነው " - ድሬዳዋ

በመላው ኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች ለእንግድነትም ሆነ እዛው በከተማዋ እየሰሩ ለመኖር አስተማማኝ የሰላም እና ፀጥታ ደህንነት ካለባቸው ከተሞች አንዷ ድሬዳዋ ናት።

ከተማይቱ በአንድ ወቅት አጋጥሟት ከነበረው የፀጥታ መንገጫገጭ ከወጣች በኃላ ላለፉት ዓመታት እጅግ አስተማማኝ ደህንነቷና ሰላሟን አስጠብቃ ትገኛለች።

በማታም ሆነ በቀን በከተማዋ ውስጥ ለመንቀሳቀስ እንዲሁም ሰርቶ ለመግባት ያማታሰጋ ሆና ተሰርታለች።

ከዚህ ባለፈም ፤ #የኢትዮጵያ የጀርባ አጥንት በሆነው ዋና መንገድ ላይ በመገኘቷ በርካታ አሸክርካሪዎች በየዕለቱ ታስተናግዳለች።

ብዙ ርቀት በአስቸጋሪ የአየር ፀባይ የሚጓዙ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅና ፤ በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚስተዋለው የተንዛዛ የትራፊክ ፖሊስ ጭቅጭቅ እንዳይኖርም እያደረገች ትገኛለች።

የድሬዳዋ ከተማ የትራፊክ ፖሊስም ረጅም መንገድ በረሃና አስቸጋሪ የአየር ንብረት በመቋቋም የሀገሪቱን ገቢ እና ወጪ ንግድ ለሚያፋጥኑ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች የሚሰጠው #ክብር ትልቅ መሆኑን የሚገልፅ ሲሆን ማንኛውም አሽከርካሪ በከተማው ውስጥ ሆኖ ችግር ከገጠመው ለማስተካከል ዘውትር ዝግጁ ነኝ ብሏል።

#ቪድዮ፦ ከወር በፊት የከተማይቱ አመራሮች ረጅም ርቀት ተጉዘው ድሬዳዋ ከተማ የደረሱ የከባድ መኪና አሽከርካሪዎችን ለማክበር የታሸገ ውሃ ሲሰጧቸው የሚያሳይ ነው።

@tikvahethiopia
#ኦዲት

#ለተከታታይ_ዓመታት ለተገኘበት በርከት ያለ የኦዲት ክፍተት ማስተካከያ ማድረግ እንደተሳነው የተገለፀው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ከአመራር መቀያየር ባለፈ ጥብቅ ሪፎርም እንደሚስፈልገው የፌደራል ዋና ኦዲተር አስታውቋል።

ይህንን ያስታወቀው፤ የሕ/ተ/ምክር ቤት የመንግሥት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በ2014 / 15 በጀት ዓመት ሒሳብ ኦዲት ላይ የዋና ኦዲተር መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ውይይት ሲደረግ ነው፡፡

መስሪያ ቤቱ ምን አለ ?

ኮሚሽኑ ፦
📄ለሚፈጽማቸው ክፈያዎች ደረሰኝ ባለማቅረብ፣
📄ኮፒ ደረሰኝ መጠቀም፣
📃በኮፒ ደረሰኝ ሂሳብ ማወራረድ፣
📄ያልተፈቀደ ክፈያ በመፈጸም፣
📄ለተከፈለ ገንዘብ ማስረጃ ባለማቅረብ፣ እንዲሁም #በቢሊዮኖች ብር የሚቆጠር ተከፋይ እና ተሰብሳቢ ውዝፍ የኦዲት ሪፖርት ተገኝቷል።

- ከሳዑዲ ከስደት ለተመለሱ 102 ሺህ ኢትዮጵያውያን ለኪስ አበል እንዲሁም ለቤት ኪራይ 5.2 ሚሊዮን ብር ማስረጃ ሳይቀርብ ተከፍሏል። ተከፈለ ለተባለው ለዚህ ገንዘብ ሰነድ ማግኘት ባለመቻሉ ትክክለኛነቱን ማረጋገጥ አልታቻለም።

- ለምግብ ዝግጅት ድርጅት ተብሎ የተከፈለና በወጪ የተመዘገበ 2.9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም ዋጋው ከ65.3 ሚሊዮን ብር በላይ የሆነ 14 ሺህ ኩንታል ዱቄት " ናህሊ ዱቄት ፋብሪካ " ለተስኘ ድርጅት የተከፈለ ተብሎ የቀረበ ቢሆንም የቀረበው ደረሰኝ ግን ኮፒ ነው።

- በወጪ ሒሳብ ለተመዘገበ 79 ሚሊዮን ብር ለኦዲት ሥራ የሚፈለጉ የወጪ ማስመስከሪያዎች (ቫውቸሮች) ከደጋፊ ሰነዶች ጋር እንዲቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ማስረጃ ሊቀርብ አልቻለም።

- ያልተወራረደ 881.5 ሚሊዮን ብር ተሰብሳቢ ሒሳብ መኖሩ በኦዲት ሪፖርት ቢረጋገጥም፣ ከኦዲት ግኝት በኋላ የተወሰደ ማስተካከያ የለም።

➡️ በወቅቱ ያልተወራረደ 39.7 ሚሊዮን ብር ተከፋይ ሒሳብና ያልተከፈለ ሲሆን ከኮሚሽኑ መደበኛ በጀት 37.6 ሚሊዮን ብር በሥራ ላይ አልዋለም።

በተጨማሪም ፦

* ውኃ የሚያስገቡ እና ጣሪያቸው የሚያፈሱ መጋዘኖች ተገኝተዋል።

* በቆይታ ብዛት የተበላሸ ብስኩት ሳይወገድ በግምጃ ቤት ተገኝቷል።

* የቆይታ ጊዜያቸው የማይታወቅና በውስጣቸው ምን እንዳለ የማይታወቅ የታሸጉ 9 ኮንቴነሮች በመጋዘን ግቢ ውስጥ ተገኝቷል።

* የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈ ፦
🔹ሴሪላክ የዱቄት ወተት፣
🔹የወይራ ዘይት፣
🔹የምግብ ዘይት፣
🔹ብዛት ያላቸውና ጊዜያቸው ያለፈባቸው ቴምሮች፣
🔹የንፅህና መጠበቂያ ሞዴስ ተገኝቷል።

* በእህል መጋዘኖች ውስጥ የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ሊያልፍ #ሁለት እና #ሦስት ወራት የቀራቸው አልሚ ምግቦች፣ ሳሙናዎችና እህሎች ተገኝቷል።

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ተ/ማርያም የኦዲት ሪፖርት ላይ ለመምክር በተጠራው ውይይት አለመገኘታቸው ቋሚ ኮሚቴውን አስቆጥቷል።

በወቅቱ ውይይቱ ላይ የተገኙት ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ኮሚሸነሩ የቀሩት ሌላ ተልዕኮ ስለነበራቸው እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ወይዘሮ መሠረት ዳምጤ ምን አሉ ?

° ኮሚሽኑ ኃላፊዎችን #ከመቀያየር ባለፈ መሠረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ያስፈልገዋል።

° በ2014 ዓ/ም የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት ኦዲተሮች ለጊዜያዊ የኦዲት ሥራ የተረከቡትን ቢሮ ኦዲት አድርገው በሚወጡበት ጊዜ የኮሚሽኑ ሠራተኞች በመግባት #ሰነድ እያወጡ መሆኑን መረጃ አለኝ።

° ይህ ኮሚሽን ለፈጸማቸው ክፍያዎች ሰነድ ማቅረብ አለመቻሉ መሠረታዊ ችግሩ ነው።

° ከዚህ በፊት የበላይ ኃላፊው ቢታሰሩም ኮሚሽኑ ግን አሁንም ሰንኮፉ አልተነቀለም፣ በመሠረታዊነት ችግሩ አልተቀረፈም።

° በመጋዘኖች ውስጥ በሚገኙ ንብረቶች ከፍተኛ ችግር አለ። ገንዘቡ አንዴት እንደሚመጣ እናውቀዋለን ነገር ግን እዚህ ያለው ሥራ የተዝረከረከ ነው፡፡

° በ2013 ዓ.ም. #ድሬዳዋ እና #ሻሸመኔ በሚገኙ መጋዘኖች ከታዩ ችግሮች በመነሳት የኦዲት አስተያየት የተሰጠንባቸው ጉዳዮች በ2014 ዓ.ም በድጋሚ ኦዲት ሲደረግ በነበሩበት እንጂ ተስተካክለው አልተገኙም።

° " ደመወዝ የምንበላበት ተቋም ነው፣ ስለዚህ እዚያ ያለውንም ሥራ ልክ እንደ ቤታችን ማየት አለብን፡፡ ይህ ሁሉ ቁሳቁስ የሚገዛው በብድር ነው እናውቃለን፡፡ እዚህ አምጥተን በአግባቡ የማይውል ከሆነ፣ መሬት ላይ የሚደፋና ከጋዝ ጋር ተቀላቅሎ የሚበላሽ ከሆነ ሥራው ትርጉም አልባ ነው "

° በዚህ ውይይት ላይ ያልተገኙት #ኮሚሽነሩ የቀሩት ዕርዳታ ለማፈላለግ ሊሆን ይችላል ፤ ነገር ግን ተቋሙ የተገኘውን ንብረት በተገቢው መንገድ ማስተዳደር ካልተቻለ፣ ዕርዳታ ማፈላለጉ ብቻ ትርጉም የሌለውና በቀዳዳ በርሜል ውኃ እንደመሙላት የሚቆጠር ነው።

የገንዘብ ሚኒስቴር ፤ የኢንስፔክሽን መምርያ ኮሚሽኑ በኮፒ ደረሰኝ ሒሳብ እንደሚያወራረድ በተደጋጋሚ ቢነገርም ሊስተካከል ባለመቻሉ ይህንን ያደረገ ኃላፊ መጠየቅ አለበት ብሏል።

More - https://telegra.ph/Reporter-12-14-2

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህ መረጃ ባለቤትነቱ የ "ሪፖርተር ጋዜጣ " መሆኑን ያሳውቃል።

@tikvahethiopia
በሀገራችን አንዳንድ መልካም የስራ ስነምግባር የጎደላቸው ፣ ከአሸከርካሪዎች ጉቦ ካልተቀበሉ ቀኑ መሽቶ የማይነጋ የሚመስላቸው ፣ አንዳንዴም ሆን ብለው ምክንያት ፈልገው የቅጣት ወረቀት ለመፃፍ በኃላም #ጉቦ ለመቀበል የማይፈነቅሉት ድንጋይ የሌላቸው ፣ ፀሀዩ በረታብኝ ፥ ዝናቡም አካፍብኝ ብለው የሚጠለሉ የትራፊክ የፖሊስ አባላት እንዳሉት ሁሉ ፦
- ለስራቸው ታማኝ
- ህግን አክባሪ
- ቅን አገልጋይ
- ፀሀይ ፣ ዝናብ ሳይሉ ህዝብን አክብረው የሚሰሩ በርካታ የትራፊክ ፖሊስ አባላት አሉ።

ለእነዚህ አይነት ህዝብን አክብረው ምንም አይነት ሁኔታ ሳይገድባቸው ለሚሰሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላት #ምስጋና ይገባል።

በሀገራችን ካሉ ከተሞች አንዷ በሆነችው የሰላም ተምሳሌቷ #ድሬዳዋ ❤️ የትራፊክ ፖሊስ አባላቶቿ በተለያየ ጊዜ በመልካም ስነምግባራቸው ስማቸው ተደጋግሞ ይነሳል።

ትላንትና በከተማው ከባድ ዘናብ ዘንቦ በነበረበት ወቅት የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት አንድ የትራፊክ ፖሊስ አባል በዝናብ ውስጥ ሆኖ ስራውን ሲያከናውን የሚያሳይ የተቀረጹ ቪድዮዎች እና ፎቶዎች ብዙዎች በማህበራዊ ሚዲያ ሲያጋሩት ውለዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ድሬዳዋ❤️

የማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበረከተላቸው።

ከሰሞኑን በድሬዳዋ ከተማ በከባድ ዝናብ ውስጥ ሆነው ኃላፊነታቸውን ሲወጡ ለነበሩ የትራፊክ ፖሊስ አባላቶች የማበረታቻ የብር ሽልማት ተበረከተላቸው።

ሽልማቱን ያበረከቱት የትራፊክ ፖሊስ አባላቱን ተግባር በማህበራዊ ሚድያ የተመለከቱ የድሬዳዋ ወጣቶች ናቸው።

የድሬ ትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ከፍተኛ ዝናብ እየጣለ የትራፊክ አደጋ እንዳይደርስ ሲያከናውኑት የነበረው ስራ ለሌሎችም ትምህርት ሆኖ ያለፈ ነው። #ድሬፖሊስ

@tikvahethiopia