TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.8K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የዛሬ የህዳር 10/2012 ዓ/ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልት እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሰባሰበ መረጃ👇
https://telegra.ph/ETH-11-20-4

(TIKVAH-ETHIOPIA)

#ድሬዳዋ #ሀረማያ #ወልዲያ #መቱ #ASTU
#መደወላቡ #ባህርዳር #ደባርቅ #ደብረታቦር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ነው።

#ጎንደር_ዩኒቨርሲቲ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 6 ሺህ 574 ተማሪዎችን ዛሬ እያስመረቀ ይገኛል፡፡

በ87 የመጀመሪያ እንዲሁም በ67 የድህረ ምረቃ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ነው የሚያስመርቀው፡፡

በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ የውኃ መስኖ እና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ተገኝተዋል፡፡

#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በተለያየ የትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው ለስምንተኛው ዙር ነው ተማሪዎቹን እያስመረቀ የሚገኘው።

#ቦንጋ_ዩኒቨርሲቲ

የቦንጋ ዩኒቨርሲቲ 2ኛ Batch ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል።

#ደብረብርሃን_ዩኒቨርሲቲ

የደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ13ኛ ዙር በተለያዩ መርሃ ግብሮች ያስተማራቸውን በ2ኛ ዲግሪ 231 ተማሪዎችን እና በ3ኛ ዲግሪ አንድ ተማሪ እያስመረቀ ነው።

#ኮተቤ_ሜትርፓሊታን_ዩኒቨርሲቲ

የኮተቤ ሜትርፖሊታን በተለያየ የትምህርት ክፍሎች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ዩንቨርሲቲው በዛሬው እለት ያስመረቃቸው በመጀመሪያና ሁለተኛ ድግሪ ወንድ 448 ሴት 135 በድምሩ 583 ተማሪዎች ናቸው።

#ቅድስተ_ማርያም_ዩኒቨርሲቲ

የቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 636 ተማሪዎችን በኦሮሞ ባህል ማዕከል አስመርቋል።

አጠቃላይ ከተመረቁት ውስጥ 322 ወንዶች 314 ደግሞ ሴቶች ናቸው።

#ሀራምቤ_ዩኒቨርሲቲ

ሀራምቤ ዩኒቨርሲቲ በተለያየ ትምህርት መስክ ያሰለጠናቸውን 3683 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነዉ።

ዩኒቨርሲቲው ለ18ኛ ዙር ነው ተማሪዎችን እስመረቀ የሚገኘው።

ምንጭ፦ ኢፕድ፣ ዋልታ፣ አሚኮ፣ የዩኒቨርሲቲዎች ገፅ

@tikvahuniversity
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ ፦ በደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፤ " የጋፋት የህዋ ምህንድስ እና ልማት ማዕከል " ከ20 ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ መጓዝ የሚችል ሮኬት አስወንጭፏል።

ዩኒቨርሲቲው " አፄ ቴዎድሮስ 2015 " የሚል ስያሜ የተሰጣትን ሮኬት ከ20 ሺህ ጫማ ከፍታ በላይ በማስወንጨፍ ስኬታማ ሙከራ ማድረጉን አሳውቋል።

" የጋፋት የህዋ ምህንድስና ልማት ማዕከል " ከዚህ ቀደምም ተመሳሳይ ሙክራ ያደረገ ሲሆን ይኸኛው ሙከራ ግን ከዚህ በፊት ከተደረጉ ሙከራዎች የተሻለ ምርምር የተደረገበት መሆኑን አሳውቋል።

ቪድዮ ፦ አሚኮ

#ደብረታቦር_ዩኒቨርሲቲ #አፄቴዎድሮስ2015

Via @tikvahuniversity
TIKVAH-ETHIOPIA
#ተጨማሪ የባህር ዳር ፣ ጎንደርና ሸዋሮቢት ነዋሪዎች ምን አሉ ? የባህር ዳር ፣ ጎንደር ፣ ሸዋሮቢት ከተማ ነዋሪዎች ከተማቸው በመከላከያ ሰራዊት ስር እንደሚገኝና ዛሬ ተኩስ እንዳልነበር ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ በሰጡት ቃል ተናግረዋል። #ባህርዳር ነዋሪ 1 " ከትለንት ከግማሽ ለሊት በኃላ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። ተኩስም የለም፤ መከላከያው ተቆጣጥሮታል። አንፃራዊ ሰላም አለ። መከላከያው…
የአማራ ክልል ከተሞች እንዴት ዋሉ ?

በአማራ ክልል በትልልቆቹ ከተሞች በዛሬው ዕለትም ተኩስ ሳይሰማባቸው መዋላቸውን ፤ ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ እንዳልተጀመረ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ነዋሪዎች ምን አሉ ?

#ባሕርዳር

ዛሬ  የተኩስ ድምጽ አለመሰማቱን ፤ ግጭትም ይሁን ውጊያ እንዳልነበር ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። ነገር ግን መደበኛ እንቅስቃሴ አልጀመረም።

የንግድና የተለያዩ ቋማት በአብዛኛው ባለመከፈታቸው ከተማዋ ጭር ብላ ነው የዋለችው።

የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ መኪኖች እና ባጃጆች ወደ ሥራ ባለመመለሳቸው የነዋሪው እንቅስቃሴ ተገትቶ ውሏል።

ተቋርጦ የነበረው የ ' ኢትዮጵያ  አየር መንገድ በረራ ' ወደ ባሕር ዳር መጀመሩን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ነገር ግን ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ ከተማ የሚወስድ ትራንስፖርት ስለሌለ ተሳፋሪዎች በእግራቸው ለመጓዝ ተገደዋል።

አሁንም የተወሰኑ መንገዶች በትላልቅ ቋጥኖች እና ድንጋዮች እንደተዘጉ ስለሆኑ ለትራንስፖርት አስቸጋሪ ነው።

ከተማዋ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ ባትመለስም አንዳንድ ነዋሪዎች በእግራቸው ሲንቀሳቀሱ ውለዋል።

#ደብረ_ማርቆስ

በደብረ ማርቆስ ከተማ ትራንስፖርትም ሆነ የንግድ መደብሮች ወደ ስራ እንዳልተመለሱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

" ሱቅ፣ ሆቴል ዝግ ነው። " ያሉ አንድ ነዋሪ " ምንም እንኳን በአይኔ ባላይም ጥዋት አንድ ባስ ከማርቆስ ወጥቶ ወደ አ/አ ሄዷል የሚባል ነገር አለ ፤ ከአዲስ አበባ መስመር ግን አንድ ሁለት ባሶች ማርቆስ ገብተዋል። " ሲሉ ገልጸዋል።

በደብረ ማርቆስ ወደ ጎንደር፣ ወደሌሎችም ቦታዎች የሚሄዱ ተሽከርካሪዎች እንደቆሙ ናቸው ፤ መደበኛ እንቅስቃሴም አልተጀመረም።

#ደጀን

ከተማዋ አሁን ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ ብትሆንም ሰሞኑን ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ አገልግሎቶች ተስተጓጉለዋል።

የውሃ እንዲሁም መብራት አገልግሎት ከተቋረጠ ቀናት እንደተቆጠሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ፤ በብቸና መስመር ወደ ሞጣ የሚያልፍ በርካታ የመከላከያ ኃይል እንደተመለከቱ ገልጸዋል።

ብቸና ላይ ግጭት እንደነበር የሚጠርጥሩት ነዋሪው ሥፍራው ከደጀን ከ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ ቢሆንም የከባድ ተኩስ ድምፅ ግን ይሰማ እንደነበር ጠቁመዋል።

#ጎንደር

ከትላንት #ረቡዕ ጀምሮ ተኩስ እንደማይሰማና አሁን ላይ ሰላም መሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ሰዎች በእግር ይንቀሳቀሱ እንጂ፣ ተሽከርካሪ የለም።  በብዛት ሱቆች እና ወፍጮ ቤቶች አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።

በከተማው የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት እንዲከፈቱ ቢታዘዙም ሁሉም ሙሉ በሙሉ እንዳልተከፈቱ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

በጎንደር የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና ታንኮች በተለይ ደግሞ አድማ በታኞች በስፋት እንደሚታዩ ተነግሯል።

ዛሬ ወደ ጎንደር ከተማ በረራ ይጀመራል ቢባልም ወደ ከተማው አውሮፕላን እንዳልገባ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

#ደብረብርሃን

በደብረ ብርሃን ሱቆች እና ትራንስፖርት ሙሉ በሙሉ ባይሆንም ወደ አገልግሎት እየተመለሱ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

አንድ አስተያየት ሰጪ ከትላንት ከሰዓት ጀምሮ ባጃጅ መንቀሳቀስ መጀመሩን ጠቁመዋል። ዛሬ ደግሞ ሱቆች መከፈታቸውንና አገልግሎት ሰጪ ተቋማትም ስራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።

የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ፍተሻ እያደረጉ መሆኑ ተመላክቷል።

#ላሊበላ

" ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ባይሆንም " የመንግስት ሰራተኞች ወደ ስራ መግባታቸው ፣ ተቋማት እና ተሽከርካሪዎች በተወሰነ ደረጃ ስራ እንደጀመሩ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ከወትሮው የተለየ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ እንዳልታየ የገለፁት ነዋሪዎች የአውሮፕላን በረራ እንዳልተጀመረና የበረራው መጀመር እየተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል።

በላሊበላ በረራ ለመጀመር ቀናት ሊፈለግ እንደሚችል ተነግሯል።

#ደብረታቦር

የከተማዋ እንቅስቃሴ በጣም ቀዝቃዛ ነው። ነዋሪው በጊዜ  ነው ወደ ቤቱ እየገባ ያለው።

አሁን ላይ በከተማዋ ፤ ምንም ዓይነት የተኩስ ድምፅ ባይሰማም  በከተማዋ የጦር መሣሪያም ሆነ ስለት ያለው ቁስ ይዞ መንቀሳቀስም ሆነ መገኘት አደጋ እንደሆነ ነዋሪዎች ገልጻዋል። ይህን ይዞ የተገኘ ሰው እርምጃ ይወስድበታል ብለዋል።

ሆቴሎችና ባንኮች ዝግ እንደሆኑ ይገኛሉ።

ምንም እንኳን በከተማው ላይ የተረጋጋ ሁኔታ ቢኖርም 800 መቶ ብር የነበረ የምግብ ዘይት እስለ 1500 ብር ድረስ እየተሸጠ እንዳለ ፤ ይሄም ቢሆን ሱቆች አሁንም ዝግ ስለሆኑ በሰው በሰው የሚገኝ እንደሆነ ተጠቁሟል።

መረጃው ከኤኤፍፒ፣ ዶቼቨለ፣ ቢቢሲ የተሰባሰበ ነው።

NB. የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ፦
- በባህር ዳር ፣
- በደብረ ማርቆስ፣
- በደብረ ብርሃን፣
- በላሊበላ ፣
- በጎንደር ፣
- በሸዋሮቢት ከባጃጆችና ከሞተር ሳይክሎች በስተቀር ሌሎች የከተማ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች ከነሐሴ 4 ጀምሮ ወደ ሥራ የመመለስ እና አገልግሎት የመስጠት #ግዴታ_እንደተጣለባቸው ማሳወቁ ይታወሳል።

ከዚህም በተጨማሪ ፤ የሕዝብ የአገልግሎት ሰጪ ፣ የመንግሥት፣ የማኅበረሰብና የንግድ ተቋማት ከነሐሴ 4/2015 ጀምሮ ክፍት እንዲሆኑ ማዘዙ አይዘነጋም።

@tikvahethiopia