TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 4,675 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ መቶ አርባ አንድ (141) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5175 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 81 ወንድ እና 60 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ2 ወር - 87 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 139 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 2 የውጭ ዜጋ ናቸው።

113 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 15 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል ፣ 6 ሰዎች ከሐረሪ ክልል፣ 3 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 2 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 1 ሰው ከድሬዳዋ ከተማ እና 1 ሰው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 18 (4 ከጤና ተቋም እና 14 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን የኮሮና ቫይረስ የተገኝበት ናሙና የለም።

ከዚህ ባለፈ ሶስት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል።

ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ52 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

2. የ72 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

3. የ62 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበሩ።

በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 81 ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል በትላንትናው ዕለት 58 ሰዎች (44 ከአዲስ አበባ፣ 8 ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1,544 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

በኢትዮጵያ እስካሁን የተደረገው የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የላብራቶሪ ምርመራ 232,050 ደርሷል።

5,175 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል ፤ 81 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ህይወታቸው አልፏል፤ 1,544 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት ቫይረሱ ያለባቸው 3,548 ሰዎች ሲሆኑ 30 ሰዎች በፀና ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Oromia

ባለፉት 24 ሰዓት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቀጥሎ ከፍተኛው የኮቪድ-19 ኬዝ የተመዘገበው በኦሮሚያ ክልል ነው።

በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ 9 ሰዎች ከጅማ ዞን (3 ወንድና 6 ሴት) ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ18-60 ነው፤ ሁሉም የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ የላቸውም።

ከዘጠኙ መካከል አራቱ (4) ከማህበረሰቡ የተገኙ ሲሆን የቀሩት አምስቱ (5) ደግሞ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ ያላቸው ናቸው።

በጅማ ከተማ 3 ኬዝ ተመዝግቧል ፤ ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ከማህበረሰቡ የተገኙ ናቸው።

በተጨማሪ ከቦረና 1 ሰው (የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያለው - ኬንያ) ፣ 1 ሰው ከሰበታ (ከማህበረሰቡ የተገኘ) እና 1 ሰው ከቡራዩ (ከማህበረሰቡ የተገኘ) ተገኝቶባቸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Diredawa

በድሬዳዋ ከተማ ከተደረገው 85 የላብራቶሪ ምርመራ የ84 ዓመት አዛውንት (ሴት) በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። እኚህ አዛውንት ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክክ ያላቸውና ከለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበሩ ናቸው።

#COVID19Gambella

ባለፉት 24 ሰዓት በክልሉ በተደረገው 93 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 15 ደርሷል።

#COVID19Harari

በክልሉ ከተደረገው 69 የላብራቶሪ ምርመራ 6 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 3 ወንድና 3 ሴት ናቸው ፤ ነዋሪነታቸው 1 ሰው ሐረሪ ክልል ሃኪም ወረዳ ፣ 2 ሰዎች ድሬዳዋ ከተማ (ለስራ ወደ ሀረር የመጡ)፣ 3 ሰዎች ኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ጎሎ ኦዳ፣ ጉርሱም እና ሐሮማያ ወረዳ (ለህክምና ሐረር የመጡ) ናቸው።

#COVID19BenishangulGumuz

በክልሉ በተደረገው 96 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በኮቪድ-19 መያዙ ተረጋግጧል። ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ሰኔ-17-2012 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ በተደረገው በረራ በአሶሳ ህዳሴ ኤርፖርት በተወሰደው የናሙና ምርመራ የተገኘ ሲሆን ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ ከአዲስ አባባ የመጣ ነዉ፡፡ ከግለሰቡ ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎችን የመለየት ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 3,434 ደርሷል። ባለፉት 24 ሰዓት ቫይረሱ የተገኘባቸው 111 ሰዎች (2 የውጭ ዜጎች አሉበት) ሲሆኑ ከነዚህ መካከል የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው 2 ሰዎች ፣ 19 ሰዎች በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን የቀሩት 92 ሰዎች የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክም ሆነ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌላቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በ7 ቀናት ውስጥ 16 ሰዎች ሞተዋል!

ሀገራችን ኢትዮጵያ በየዕለቱ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎችን ከመቁጠር ተሻግራ በቀን ምን ያህል ሰው ሞተ ወደሚለው እየገባች ነው።

ከሰኔ 12/2012 ዓ/ም- ሰኔ 18/2012 ዓ/ም ባሉት 7 ቀናት ውስጥ አስራ ስድስት (16) ሰዎች ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ ህይወታቸው አልፏል።

መዘናጋቱ ፣ ቸልተኝነቱ ፣ ወጣት ስለሆንኩ ብያዝም እድናለሁ የሚለው የተሳሳተ አመለካከታችን ትልቅ ዋጋ ሊያስከፍለን ይችላል።

ይህ ወረርሽኝ ትዕግስትን የሚፈታተን ፣ የሚያደክም እና የሚያሰልች ቢሆንም ለአንዲት ህይወታችን ስንል መፍትሄ እስኪገኝ ድረስ በንቃት እራሳችንን መጠበቅ አለብን።

ዛሬም በሜክሲኮ፣ አሜሪካ፣ ብራዚል በሌሎችም ሀገራት በየዕለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እየረገፉ ነው ፤ በሺዎች ሆስፒታል እየተኙ ነው ፤ መሰላቸትና መዘናጋት ፍፅሞ ልንወጣው የማንችለው አዘቅት ውስጥ ሊከተን ይችላል።

#TIKVAH
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ1 ወር በታች የሆኑ ጨቅላ ህፃናት ከኮቪድ-19 አገገሙ!

በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል በኮቪድ-19 ተይዘው ከታከሙ ህፃናት ሁለት ዕድሜአቸው ከአንድ ወር በታች የሆኑ ጨቅላ ህፃናት ሙሉ በሙሉ አገግመው ከሆስፒታሉ ማውጣታቸውን ዶ/ር ያሬድ አግደው አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

በአምቦ ዩኒቨርስቲ የተቋቋመው የኮሮና ቫይረስ ምርመራ ማእከል ተመርቆ ስራ ጀምሯል። ይህ ላብራቶሪ በቀን እስከ 1 ሺህ ናሙናዎችን መመርመር እንደሚችል ተገልጿል።

በተጨማሪ የአርባ ምንጭ የኮቪድ-19 ምርመራ ማዕከል ምርመራ ጀምሯል። ማዕከሉ በቀን እስከ 400 የሚደርሱ ናሙናዎችን የመመርመር አቅም አለው። ማዕከሉ ለጋሞ፣ ጎፋ፣ ደቡብ ኦሞ፣ ኮንሶ ፣ እና ከደራሼ ዞኖች፣ ቡርጂ፣ አማሮ እና አሌ ልዩ ወረዳዎች ለሚመጡ ናሙናዎች የ24 ሰዓታት የምርመራ አገልግሎት ይሰጣል - #FBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሚዲያዎቹ ተፅእኖ!

ከሰሞኑን ቢቢሲ ትግርኛ፣ ቢቢሲ አማርኛ፣ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎክ (OMN) እና አውሎ ሚዲያ በነጀነራል ሰዓረ ጉዳይ ባለቤታቸውን ኮሎኔል ፅጌ አለማየሁን አነጋግረው ያለውን ሁኔታ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያውቀው አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ስለተፈጠረው ሁኔታ፣ ስለ ፍርድ ሂደቱ ፣ የጀነራል ሰዓረ ቤተሰቦች በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ በግልፅ ሳያውቅ ከአንድ ዓመት በላይ ተቆጥሯል።

ኮሎኔል ፅጌ አለማየሁ ትላትን ምሽት በOMN በተሰራጨ ልዩ ዝግጅት ላይ ስለጉዳዩ ልክ እንደሌላው ሰው በፌስቡክ እና ዩትዩብ እንደሚከታተሉ ይፋ አድርገዋል፤ ይህ ብዙዎችን አስደንግጧል አሳዝኗልም።

ኮሎኔል ፅጌ የባለቤታቸው ደም በከንቱ መፍሰሱ፣ ያለፍትህ ከዓመት በላይ መቆየታቸው፣ ስለ ሀገር መሪው፤ ስለጀግናው ፤ ለኢትዮጵያ ህዝብ ደህንነት ሲል ስለተሰዋው ባለቤታቸው ጠያቂ ማጣታቸው ፣ ለጉዳዩ ትኩረት መነፈጉ አሁንም ድረስ እንደሚያንገበግባቸው እያለቀሱ ተናግረዋል።

ከላይ የተጠቀሱት ሚዲያዎች ኮሎኔል ፅጌን በማነጋገር ከሰሩት ስራ በኃላ ዛሬ ጥዋት የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በጀነራል ሰዓረ እና የሜጀር ጀነራል ገዛኢ አበራ ግድያ ወንጀል ሲካሄድ የነበረው የክርክር ሂደት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጻል።

የችሎት ክርክሩ ከሰኔ 23/2012 ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት የተጎጂ ቤተሰቦች ጉዳዩን መከታተል የሚፈልጉ ውስን ሚዲያዎች ወይም ግለሰቦች ባሉበት ይቀጥላል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ350 ሺህ አለፉ!

በመላው አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 351,367 ከነዚህ መካከል 9,115 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 168,933 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ከፍተኛ የኮቪድ-19 ኬዝ ከተመዘገበባቸው የአፍሪካ ሀገራት መካከል ደቡብ አፍሪካ፣ ግብፅ እና ናይጄሪያ በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ናቸው።

በደቡብ አፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ 118,375 ሲሆኑ 2,292 ሰዎች ሞተዋል ፤ 59,974 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በግብፅ በቫይረሱ የተያዙ 61,130 የደረሱ ሲሆን 2,533 ሰዎች ሞተዋል ፤ 16,338 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል።

በናይጄሪያ በቫይረሱ የተያዙ 22,614 ሲሆኑ ከነዚህ መካከል 549 ሰዎች ሞተዋል፤ 7,822 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 250 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ8 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,414 የላብራቶሪ ምርመራ 250 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5425 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 158 ወንድ እና 92 ሴት ሲሆኑ የእድሜ ክልላቸው ከ3 ወር - 90 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት 240 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 10 የውጭ ዜጋ ናቸው።

177 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 21 ሰዎች ከትግራይ ክልል ፣ 20 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 18 ሰዎች ከጋምቤላ ክልል፣ 8 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 1 ሰው ከድራዴዋ ከተማ እና 1 ሰው ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርምራ ውስጥ 32 (11 ከጤና ተቋም እና 21 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርምራ ሲሆን 6 ናሙናዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል።

ከዚህ ባለፈ ሁለት በህክምና ማዕከል ውስጥ በህክምና ላይ የነበሩ ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸው እና ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር 89 ደርሷል፡፡

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት 144 ሰዎች (123 ከአዲስ አበባ፣ 7 ከአማራ ክልል፣ 7 ከትግራይ ክልል፣ 5 ከሶማሊ ክልል፣ እና 2 ከኦሮሚያ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1688 ነው።

@tikvahethiopia
ህይወታቸው ያለፈ 8 ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ40 ዓመት ወንድ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

2. የ26 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

3. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበሩ።

4. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

5. የ27 ዓመት ሴር የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠ።

6. የ65 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

7. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

8. የ60 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Tigray

ከአዲስ አበባ በመቀጠል ባለፉት 24 ሰዓት በትግራይ ክልል ከፍተኛው የኮቪድ-19 ኬዝ ተመዝግቧል።

በክልሉ ከተደረገው 246 የላብራቶሪ ምርመራ 21 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ከሃያ አንዱ (21) መካከል ሃያዎቹ (20) የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው ሲሆን 1 ሰው የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌለው ነው።

በአጠቃላይ በትግራይ ክልል በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 204 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 42 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Amhara

ባለፉት 24 ሰዓት 483 የላብራቶሪ ምርመራ የተካነወነ ሲሆን 20 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። 16 ሰዎች ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሚገኙ ለይቶ ማቆያ ማዕከላት ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩና የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ያላቸው፤ 1 ዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ዞን ሰቆጣ ለይቶ ማቆያ፤ 1 ከኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን ባቲ አውቶብስ መናኸሪያ በተደረገ የናሙና ምርመራ፣ 1 ከሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ አውቶብስ መናኸሪያ ናቸው።

#COVID19Diredawa

በድሬዳዋ ከተማ ከተደረገው 55 የላብራቶሪ ምርመራ የ23 ዓመት ወጣት (ወንድ) በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። ወጣሩ ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ የነበረውና ከለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረው ነው።

#COVID19Gambella

ባለፉት 24 ሰዓት በክልሉ በተደረገው 274 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በክልሉ በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 33 ደርሷል።

#COVID19Somali

በክልሉ ከተደረገው 103 የላብራቶሪ ምርመራ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከጅግጅጋ ሲሆኑ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው ናቸው።

#COVID19BenishangulGumuz

በክልሉ በተደረገው 380 የላብራቶሪ ምርመራ 1 ሰው በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል። በዛሬዉ እለት ቫይረሱ የተገኘባት ግለሰብ ሰኔ-18-2012 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ አሶሳ በህዝብ ማመላለሻ ትራንስፖርት (በገዳ ባስ) ከአዲስ አባባ የመጣች ስትሆን ከዳቡስ ኬላ ላይ ከተሳፋሪዎች ላይ በተወሰደዉ የናሙና ምርመራ ነዉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia