TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከኮቪድ-19 ያገገሙ ታካሚዎች ወደቤታቸው ተሸኙ!

በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማዕከል የኮቪድ 19 ህክምና ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸውን ሆስፒታሉ አስታውቋል።

በኮቪድ-19 ፓዘቲቭ ሆነው ወደ ሆስፒታሉ የገቡት በአጠቃላይ 178 ነበሩ፡፡ በመጀመሪያ ዙር 44 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸው የሚታወቅ ሲሆን በሁለቱ ዙር አጠቃላይ 81 ሰዎች አገግመው ወጥተዋል።

በሆስፒታሉ የኮቪድ 19 ቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ሰዎች 205 ሲሆኑ ከነዚህ ውስጥ 144 ሰዎች ነጻ ተብለው ወደ ቤታቸው መሄዳቸውን ሆስፒታሉ በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ114 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ከኮቪድ-19 አገገሙ!

የ114 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ ከኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ከኮሮና ቫይረስ ሙሉ በሙሉ አገግመው መውጣታቸውን ዶ/ር ያሬድ አግደው አሳውቀዋል።

ከኮቪድ-19 ያገገሙት አዛውንት ለተጨማሪ ህክምና የካቲት 12 ሆስፒታል የሚገኙ ሲሆን ፤ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ዶ/ር ያሬድ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አንሱ ሶኒ ሆስፒታል መግባታቸው ተሰማ!

የላይቤሪያው ትምህርት ሚኒስትር በኮቪድ-19 ምክንያት ሆስፒታል መግባታቸው ተሰምቷል።

የላይቤሪያ ትምህርት ሚኒስቴር በሚቀጥለው ሳምንት ትምህር ቤቶች እንዲከፈቱ ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት ሚኒስትሩ ሆስፒታል የገቡት።

ሚኒስትር አንሱ ሶኒ ብቻ ሳይሆን ምክትላቸው ላቲም ዳ - ቶንግም ሆስፒታል ገብተዋል። ፍሮንት ፔጅ አፍሪካ የተሰኘው የላይቤሪያ ጋዜጣ ሚኒስትር ዴኤታው ሕመማቸው ሲፀና ወደ ጋና ሄደው እንዲታከሙ መደረጋቸውን ዘግቧል።

የላይቤሪያ መረጃ ሚኒስትር ሌን ዩጂን ናግቤ ለጋዜጣው እንደተናገሩት ዴኤታው ጤናቸው ሰላም ነው ፤ ዋና ሚኒስትሩም ወደ ጋና ለሕክምና ሄደዋል የሚባለው ውሸት ነው ሲሉ አስተባብለዋል።

በላይቤሪያ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና ይዘጋጁ ዘንድ በሚቀጥለው ሳምንት ትምህርት ይከፈታል ተብሎ ይጠበቃል - #BBC

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኒው ዮርክ ማራቶን በኮቪድ-19 ምክንያት ተሰረዘ!

በኮቪድ-19 ስጋት ምክንያት የኒው ዮርክ ከተማ ማራቶን ውድድር መሰረዙን ዛሬ አዘጋጆቹ ይፋ ማድረጋቸውን #ቪኦኤ ዘግቧል።

የኒው ዮርክ ማራቶን በመጪው ኅዳር ወር 50ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ዝግጅት ላይ ሃምሳ ሺህ ሯጮች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተመልካቾች እና 10 ሺህ በጎ ፈቃደኞች ያሰባሰባል ተብሎ ተጠብቆ ነበር።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ኮሮና ቫይረስ በአሳሳቢ ደረጃ እየተዛመተ መሆኑንና ከበጋው በኋላ በሚመጡት ወራት 2ኛ ዙር ወረርሽኝ ይከተላል የሚል ሥጋት በመኖሩ ነው ውድድሩ የተሰረዘው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrTsigeredaKifle

በኢትዮጵያ እና ጅቡቲ ድንበር የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል የተቋቋመው የደወሌ አስገዳጅ ለይቶ ማቆያና የህክምና መከታተያ ማዕከል ለአገልግሎቶ ብቁ ባለመሆኑ #መዘጋቱን የፌደራል መንግስት አስታውቋል።

ይህንኑ አገልግሎት የሚሰጥ የማቆያ እና ህክምና ማዕከል በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ እና በፌደራል ጉምሩክ በተገነባው አዲስ ጣቢያ መዘጋጀቱን በጤና ሚንስቴር የተቋቋመው የክልሎች የኮቪድ መከላከልና ዝግጁነት ምላሽ አስተባባሪ ዶክተር ፅጌረዳ ክፍሌ ለDW ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የታላቁ ህዳሴ ግድብን ለመገንባት ማንንም እንዳልጠየቅን ሁሉ ለመሙላትም የማንንም ፈቃድ #አንጠይቅም ፤ ሆኖም ግን ኢትዮጵያ ኃላፊነት እንደሚሰማት ታላቅ ሀገር በእውነትና በእውቀት ላይ ተመስርታ እንደምትሰራ ለዓለም እናስረዳለን" - ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢንቨስትመንት ላይ ያለው ተጽዕኖ እና የመንግስት ምላሽ - #PMO

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በሀብታችን የመጠቀም ሙሉ መብት አለን። የአባይ ውሀ ምንጭ 85 በመቶ ኢትዮጵያ ናት።ይህም ሆኖ ተፈጥሮ በጋራ እንድንጠቀምበት የሰጠንን ጸጋ በሰላም አብረን እንጠቀም" - ጄነራል ብርሃኑ ጁላ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MackySall

የሴኔጋሉ ፕሬዝደንት ኮሮናቫይረስ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ ስለነበራቸው ራሳቸውን ማግለላቸው ተነገረ።

ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ለሚቀጥሉት ሁለት ሳምንት ራሳቸውን አግልለው የጤናቸውን ሁኔታ እንደሚከታተሉ #BBC ዘግቧል።

ፕሬዝደንት ማኪ ሳል ለጊዜው ተመርምረው ከቫይረሱ ነፃ ናቸው ቢባልም ከ2 ሳምንት በኋላ ድጋሚ እንደሚመረመሩ ታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ የትምህርት ሚኒስቴር ከአጋሮቹ ከዩኒሴፍ እና ከሕፃናት አድን ድርጅት ጋር በመሆን ትምህርታዊ ዝግጅቶችን በኢትዮሳት የቴሌቪዥን መድረክ ማስተላለፍ ጀመሩን #SavetheChildren በላከልን መግለጫ አሳውቋል።

ለትምህርት ማሰራጫነት የታለመው የመጀመሪያው የሳተላይት መድረክ ኢትዮሳት በኮቪድ-19 ምክንያት የተቋረጠውን የትምህርት ቤቶች የትምህርት ተግባር ለማሰቀጠል እንዲቻል ዘጠኝ ትምህርታዊ ቻነሎችን በስርጭቱ ሥርዓት ውስጥ እንዲካተቱ አድርጓል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
የቤት ለቤት ልየታ በአዲስ አበባ!

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ የቤት ለቤት ልየታና ግንዛቤ ማስጨበጥ መርሐ ግብር በሁለት ዙር ከአምስት ሚሊዮን በላይ ግለሰቦችን ተደራሽ ማድረጉን ኢፕድ ዘግቧል። በሁለት ዙር በተከናወነው ልየታም በምርመራ 13 ግለሰቦች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ቢሮው አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የትራምፕ ደህንነት አባላት ኮቪድ-19 ተገኘባቸው!

ባለፈው ቅዳሜ ቱልሳ ውስጥ የተካሄደው የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ የተገኙ የደኅንነት አባላት ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተሰምቷል።

የደህንነት አባላቱ ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡት ከመካከላቸው የተወሰኑት የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስለተገኘባቸው መሆኑ ተገልጿል።

መረጃውን መጀመሪያ ያወጣው ዋሽንግተን ፖስት ሲሆን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፖሊስ ባለሥልጣን ደግሞ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት በጣት የሚቆጠሩ አባላት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከምርጫ ቅስቀሳው በፊት የፕሬዝደንት ትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን አባላትና ሁለት የደኅንነት ሰዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተዘግቦ ነበር።

ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ባልተገታባት ኦክላሆማ ግዛት የምርጫ ቅስቀሳ አደርጋለሁ ሲሉ ብዙ ወቀሳ ገጥሟቸው ነበር።

በስብሰባው ቦታ የተገኙት ታዳሚዎችም ሙቀታቸው ተልክቶ እንዲሁም የእጅ ማፅጃ ፈሳሽ ተሰጥቷቸው ቢገቡም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ አልነበረም።

የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አንድ ሚሊዮን ሰዎች ለመታደም ቃል ገብተዋል ብለው የነበረ ቢሆንም 19 ሺህ ሰው በሚይዘው ስታደየም የተገኙት 6,200 ሰዎች ብቻ ነበሩ ሲል #BBC አስነብቧል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
ኮቪድ-19 ባለፋት 24 ሰዓት በአሜሪካና ብራዚል!

እንደ #worldometers መረጃ ባለፉት 24 ሰዓት በአሜሪካ 38,386 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ808 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በብራዚል ደግሞ 40,995 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ሲረጋገጥ የ1,103 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ5,106 ተጠባባቂዎች ቅጥር እንደሚፈፀም ተገልጿል!

የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ኃብት ልማት ቢሮ በተጠባባቂ ተይዘው ከነበሩት ተወዳዳሪዎች ለ5,106 ቅጥር እደሚፈፀም ገልጿል።

በህዳር ወር 2012 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ተፈትነው የማለፊያ ውጤት ካገኙት በየካቲት ወር ላይ ለ8,094 ያህሉ በውጤታቸው መሰረት ቅጥር መፈፀሙ ይታወሳል።

በተጠባባቂ ተይዘውት ከነበሩት መካከልም ለ5,106 ተወዳዳሪዎች ቅጥር እንደሚፈፀም የቢሮው ኃላፊ የሆኑት አቶ ኃይሉ ሉሌ ትላንት በሰጡት መግለጫ ተናገረዋል።

የቅጥር ሂደቱ ተወዳዳሪዎች WWW.ADDIS.GOV.ET የዌብሳይት አድራሻ ላይ የተመደቡበት ተቋም ወይም ክፍለ ከተማ ከቅዳሜ ሰኔ 20 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ማየት ይችላሉ ተብሏል።

ከሰኞ ሰኔ 22 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በየተመደቡበት ሂደው የኮቪድ-19 ቅድመ መከላከልን መሰረት ባደረገ ሂደት ሪፖርት እንዲያደርጉና የቅጥር ፎርማሊቲ እንዲያሟሉ መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

በትላንትናው ዕለት በሶማሌ ክልል የአይሻ ወረዳ ፣ ደወንሌ ኮሪደር በሚገኝ ኬላ ከጅቡቲ ለሚገቡ አሽከርካሪዎች ኮቪድ-19 ለመመርመር የሚያስችል ናሙና መውሰድ ተጀምሯል።

ናሙናውን ለመውሰድ የሚያስችል እና ለማቆያ የሚያገለግል የድንኳን አልጋ በማዘጋጀት ነው ስራው መጀመሩን #SRTV የዘገበው።

የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ናሙና ምርመራው ኮንቴኔር በሚጭኑ አሽከርካሪዎች ላይ ነው የተጀመረው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NEBE የትግራይ ክልል ምክር ቤት ምርጫን አስመልክቶ የሰጠውን ውሳኔ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲያውቅለትና ምርጫ እንዲያስፈፅምለት ያቀረበውን ጥያቄ ቦርዱ እንዳልተቀበለው አስታወቀ። ምርጫ ቦርድ የተጠየቀውን የሰው ሀይል፣ የሎጄስቲክስ እና የቁሳቁስ አቅርቦት የምሰጥበት የህግ አግባብ የለም ሲል ዛሬ ባወጣው መግለጫ ገልጿል - @tikvahethmagazine @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ትግራይ ምርጫውን ለማካሄድ በቂ ዝግጅት አድርጋለች" - አቶ ሩፋኤል ሽፋረ

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በትግራይ ክልል ምርጫውን ለማካሄድ ፍቃደኛ ባይሆንም 6ኛው ክልላዊ ምርጫ በክልሉ እንደሚካሄድ የትግራይ ክልል ምክር ቤት አስታውቋል፡፡

የትግራይ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባዔ የሆኑት አቶ ሩፋኤል ሽፋረ እንደገለጹት ትግራይ ምርጫውን ለማካሄድ በቂ ዝግጅት አድርጋለች ብለዋል - @tikvahethmagazine

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 141 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ3 ሰዎች ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia