TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ላይቤሪያ የ2 ሰዎችን ሞት ሪፖርት አደረገች!

በላይቤሪያ ባለፉት 24 ሰዓት የ2 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። ከሟቾቹ አንዱ የጤና ባለሞያ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። ከዚህ ቀደም ሪፖርት ከተደረገው ሞት ጋር አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 3 ደርሷል።

በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ 3 በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም አስራ ሶስት (13) ደርሰዋል።

#SamiraSawlani
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጣልያን የ24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

ባለፉት 24 ሰዓት በጣልያ የ525 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። ቁጥሩ ባለፉት 5 ቀናት ሪፖርት ከተደረጉት #ዝቅተኛ ነው። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 15,887 ደርሷል።

በተጨማሪ በ24 ሰዓት 4,316 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር ወደ 128,948 ከፍ ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ የሚስፋፋበትን ፍጥነት ተመልከቱ ፦

• ጥር 27/2012 ዓ/ም አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር - 28,000

• የካቲት 27/2012 ዓ/ም አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር - 98,500

• ዛሬስ ? ዛሬ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር - 1,245,207

ቁጥራዊ መረጃው ዓለም አቀፍ ሁኔታን የሚመለከት ነው!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኢትዮጵያ ሁለተኛው ሞት ተመዘገበ!

በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በሀገራችን በዛሬው እለት ሁለተኛ ሰው ህይወት ማለፉን ስገልጽ በከፍተኛ ሀዘን ነው። ታማሚው በለይቶ ማቆያ ከመጋቢት 24 ጀምሮ ህክምና ሲደረግላቸው የነበርና ከገቡበት ቀን ጀምሮ በጽኑ ህሙማን ክፍል ክትትል ላይ የነበሩ ናቸው። በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸውና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

(የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ሁለተኛው (2) ሟች የ56 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆኑ መጋቢት 24/2012 ዓ/ም የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] እንደተገኘባቸው ተረጋግጦ በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነበር።

ግለሰቡ ወደለይቶ ማቆያ ከገቡበት ዕለት ጀምሮ በፅኑ ህክምና ላይ አስፈላጊው ክትትል ሲደረግላቸው የነበሩ ሲሆን በዛሬው ዕለት ከቀኑ 12:00 ሰዓት ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሩዋንዳ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 104 ደረሱ!

የሩዋንዳ ጤና ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ሁለት አዲስ ኬዞችን ሪፖርት አድርጓል። በሀገሪቱ ያሉ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ታማሚዎች ቁጥርም 104 ደርሰዋል።

የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- ሁለቱም (2) በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ከዚህ ቀደም በቫይረሱ ከተያዙ ግለሰቦች ጋር ንክኪ የነበራቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሩዋንዳ አራት በኮሮና ቫይረስ ተይዘው የነበሩ ሰዎች ከበሽታው አገግመው ከህክምና ማዕከል ወጥተዋል።

ምንጭ፦ የሩዋንዳ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሱዳን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 12 ደረሱ!

ሱዳን በዛሬው እለት ሁለት ተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ኬዞችን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 12 ደርሰዋል። በሱዳን ሁለት ሰው ከቫይረሱ ያገገመ ሲሆን ከዚህ ቀደም የሁለት (2) ሰዎች ሞት ሪፖርት መደረጉ አይዘነጋም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ዛሬ ሪፖርት በተደረገው የሁለተኛው ኢትዮጵያዊ ሞት ዙሪያ የሰጡትን መግለጫ በዚህ አጭር ቪድዮ መከታተል ትችላላችሁ።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማስታወሻ!

- ነገ 28/07/2012 ዓ/ም በወላይታ ሶዶ ከተማ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የጸረ-ተዋሲያን ኬሚካል ርጭት በዋና ዋና መንገዶች ይካሄዳል። ርጭቱ ጠዋት ከ12፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 5፡00 ሰዓት ይቆያል። ርጭት የሚደረግባቸውን ቦታዎች በ @tikvahethmagazine ማግኘት ትችላላችሁ።

- ከመጋቢት 28/2012 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ በመላው የአገራችን ክፍል የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ በቤታቸው ሆነው በጸሎት የፈጣሪን ምህረት የሚለምኑበት ጊዜ እንዲሆን የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ በዚህም መሠረት በነገው ዕለት በሶስት የተመረጡ ቦታዎች የጸሎት መርሃ ግብሩ የማስጀመርያ ፕሮግራም የኃይማኖት አባቶችን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ኃላፊዎችና ወጣቶች ተሳታፊ በሚሆኑበት ይከናወናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እንደምን አደራችሁ ?

ትላንት 27/2012 ለሊት ባስቀመጥንላችሁ መልእክት @tikvahethmagazine ከ100,000 ከላይ ሰዎች ሀሳባችሁን አጋርታችኃል፣ ጥያቄ ጠይቃችኃል፣ ስጋታችሁን ገልፃችኃል።

- አንዳንዴ በተሳሳተ አረዳድ መመሪያዎችን ላለማክበር የሚቀርብ ሀሳብም እንዳለ ታዝበናል። 'ከቤት አትውጡ' ሲባል እስካሁን የዕለት ጉርሱን አግኝቶ የሚያድረውን አይደለም። ሀገራችን ላይ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ወጣት ተማሪዎች አሉ የእነሱ አርፎ መቀመጥ የቫይረሱን ስርጭት እጅግ በጣም ይቀንሰዋል። ምን ያህል ተማሪ ነው የግድ ከቤት ወጥቶ ሰርቶ ገብቶ ቤተሰቡን የሚያስተዳደረው?

- በተጨማሪ ቤታችሁ ሆናችሁ ስሩ የተባሉ አንዳንድ ሰዎችም ዘመድ ጥየቃ ላይ እንደሆኑ ሰምተናል፤ ታዝበናል። አንዳንዴ መመሪያዎችን ላለማክበር የምንሰጠው ምክንያት ተገቢ አይደለም።

- ጥሩ ስራ እየሰሩ ያሉ ሰዎች እንዳሉት ሁሉ እጅግ በጣም በሚያሳዝን መልኩ በዚህ የጭንቅ ሰዓት የቤት ኪራይ የሚጨምሩ፣ ተከራዮቻቸውን የሚያንገላቱ፣ ቤት እንዲለቁ የሚጠይቁም እንዳሉ ስንሰማ አዝነናል።

- ከዚህ ቀደም ቫይረሱ ከአ/አ አይወጣም የሚል እሳቤ ነበር፤ አሁን ደግሞ የክልል ትልልቅ ከተሞች ላይ ሲገኝ 'ኧረ እዛው ነው የሚቀረው እኛ ጋር አይደርስም' በሚል እሳቤ ህይወት በመደበኛ መልኩ ቀጥሏል። ይህ እጅግ ዋጋ ያስከፍላል።

- እጅ ታጠቡ፤እጅ ታጠቡ ! በምን እንታጠብ ? ይሄ የሺዎች ጥያቄ ነው በተለይ ከአዲስ አበባ ነዋሪዎች፤ መንግስት መፍትሄ እንዲፈልግም ተጠይቋል።

- በርካቶች ኢትዮ ቴሌኮም የህዝቡን የኢንተርኔት ፍላጎት ተመልክቶ ይህ ወቅት እስኪያልፍ ድረስ ዋጋ ላይ ማስተካከያ በማድረግ ይበልጥ ህዝቡ እንዲጠቀም እንዲያደርግም ሀሳብ ተነስቷል።

እንቀጥላለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቀጠለ...

- የለሊት ህገወጥ ጉዞ እጅግ በጣም አሳሳቢ ሆኗል። ይህን ጉዳይ ማስቀረት ካልተቻለ ዋጋ ያስከፍለናል።

- ባንክ ቤት የሚሰሩ ወንድም እህቶቻችንን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነት የሁላችንም ነው። የሞባይል ባንኪንግ፣ ATM ሌሎች አማራጮችን መጠቀም እየቻልን ባንክ ቤቶችን ከማጨናነቅ ብንቆጠብ ምናለበት?

- እቃዎችን በማመላለስ ላይ የተሰማሩ ሹፌሮች ለወረርሽኙ መከላከያ ሳኒታይዘር፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ለማግኘት እንደተቸገሩ አንስተዋል። የኛም ጉዳይ ትኩረት ይሻል ብለዋል።

- ከተሞች ላይ አሁንም የንፅህና መጠበቂያ መገልገያዎች ሳኒታይዘር፣ ማስክ ፣ የመሳሰሉት እንደልብ አይገኙም ፤ በዚህም ከርካታ የጤና ባለሞያዎች እራሳቸውን ለአደጋ እያጋለጡ ነው።

- ዛሬም የኢንዱስትሪ ፓርክ ሰራተኞች ሁኔታ መፍትሄ የላገኘ ነው። ሲወጡ እና ሲገቡ ያለው መጨናነቅ ምንም ያልተፈጠረ ተደርጎ

- ወላጆችን የትምህርት ቤት ክፍያ ካላመጣችሁ እያሉ የሚያስጨንቁ የትምህርት ተቋማት እንዳሉም ተነግሮናል፤ ምነው በዚህ የጭንቅ ጊዜ እንኳን ብንተዛዘን ?

- እራሳቸውን ለመከላከል ሰዎች በሚወስዱት እርምጃ ማሸማቀቅ ፣ መቀለድ ፍፁም ተገቢ አይደለም። ይህን የምታደርጉ ካላችሁ ብታቆሙ ጥሩ ነው። እራሳችሁን የምትጠብቁ ግን በሌላ አለማወቅ እና መዘንጋት ዋጋ መክፈል ስለሌለባችሁ አጠንክራችሁ ቀጥሉ።

- ይህ ቫይረስ ጭራሽ እንደሌለ ተደርጎ የሚታሰብበት እና መደበኛው ህይወት ያልቆመባቸው ቦታዎች ጊዜው ሳይረፍድ ቶሎ መፍትሄ ቢፈለግላቸው መልካም ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ኅብረተሰቡ አቅም ለሌላቸው ወገኖች ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል!

የጎዳና ተዳዳሪዎች እንዲሁም አቅመ ደካማ ወገኖች ለርሃብ እንዳይጋለጡ ኅብረተሰቡ በሚችለው ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዶክተር መሐሪ ታደሰ ጥሪ አቅርበዋል።

የመኝታ ፍራሽና ብርድ ልብስ ፣ አልባሳት ፣ እንደ ማካሮኒ ፣ ፓስታ ፣ ዱቄት ፣ ሩዝ ያሉ የምግብ ዓይነቶችን 'ሙሉ ዓለም የባሕል ማዕከል' በሚገኘው ጊዜያዊ የድጋፍ ማሰባሰቢያ ቦታ ማድረስ ይቻላል።

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በወላይታ ሶዶ ከተማ ዋና ዋና መንገዶች ላይ የፀረ-ተዋስያን የኬሚካል ርጭት እየተካሄደ ይገኛል። መረጃው ከወላይታ ዞን አስተዳደር ነው የተገኘው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#JackMa

የኢለባባ ኩባንያ ዋን ስራ አስፈፃሚ ጃክ ማ ሁለተኛ (2) ዙር የኮሮና ቫይርስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለአፍሪካ ሀገራት መላካቸውን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸድ አስታውቀዋል።

#ኤፍቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማስታወቂያ!

የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ላይ ለመሰማራት ለተመዘገባችው ጤና ባለሙያዎች በመሉ!

የCOVID-19 ወረርሺኝን ለመግታት መጋቢት 24/2012 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር ድረ- ገጽ ላይ በወጣው ማስታወቂያ የተመዘገባችሁ ባለሙያዎችን ወደ ስራ ለማሰማራት በቅድሚያ ከስራው ጋር የተያያዘ እውቀት፣ ክህሎት ብሎም አመለካከት ለማሳደግ ከዚህ በታች በተመለከተው መሰረት በ online course እንድትወሰዱ እያሳሰብን ስልጠናውን እንደጨረሳችሁ ማጠናቀቃችሁን የሚገልጽ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀቱ በቀጣይ ለሚኖረው ተግባር ስለሚፈለግ ከሲስተሙ ፕሪንት በማድረግ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡

ወደ covid19-IPC Online course ለመግባት በሚከተለው አድራሻ (ሊንክ) ይጠቀሙ

www.moh.gov.et/covid19-courses/

User Name በሚለው ቦታ በምዝገባ ወቅት የጻፋችሁትን የኢሜይል አድራሻ (email address መጻፍ

የይለፍ ቃል (Password): changeme - ማስገባት

ከላይ በተጠቀሰው መሰረት በመግባት ስልጠናውን መከታተል የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

[ጤና ሚኒስቴር - ኢትዮጵያ]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዩጋንዳ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 52 ደረሱ!

ትላንት ለሊት የዩጋንዳ ጤና ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በ24 ሰዓት ውስጥ 300 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በዩጋንዳ ያሉ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 52 ደርሰዋል።

የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- የ22 ዓመት ዩጋንዳዊ MARCH 22 ከዱባይ ወደ ዩጋንዳ የገባ

- የ66 ዓመት ዩጋንዳዊት MARCH 22 ከዱባይ ወደ ዩጋንዳ የገባች

- የ65 ዓመት ዩጋንዳዊት March 22 ከዱባይ ወደ ዩጋንዳ የገባች

- የ26 ዓመት ዩጋንዳዊ MARCH 22 ከዱባይ ወደ ዩጋንዳ የገባ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ አገልግሎት የሚሰጡ ታክሲዎች የሰው መቀራረብን ለመቀነስ ከመጫን አቅማቸው ግማሽ ብቻ እንዲጭኑ ተወስኗል። ይህን ተከትሎም ተሳፋሪዎች እጥፍ እንዲከፍሉ መወሰኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

የአንበሳ አውቶብስ እና ሸገር አውቶብስ ደግሞ ያለምንም የዋጋ ጭማሪ 30 ሰው ብቻ እንዲጭኑ መወሰኑንም ነው ያስታወቀው። ውሳኔው ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን በጉዳዩ ላይ ዝርዝር መረጃ የሚሰጥ ይሆናል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ12ሺ በላይ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው!

የደቡብ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በመደበኛና በልዩ ሁኔታ ከተለያዩ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች 12,553 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል።

በመደበኛ መንገድ የይቅርታ ተጠቃሚዎችን መረጣና ምልመላ መስፈርት መሰረት ባደረገ መልኩ በአግባቡ የታረሙ ፣ መልካም ስነ ምግባር ያሳዩ 3,519 ወንድና 119 ሴት እንዲሁም 4 የእስራት ቅነሳ የተረገላቸው በድምሩ 3,642 ታራሚዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ 8,601 ወንድና 310 ሴት በድምሩ 8,911 ታራሚዎች እንዲፈቱ ተደርጓል።

በተለይም ደግሞ ነፍሰ ጡሮች ፣ ህጻናት ያላቸው ፣ ልዩ ልዩ ህመም ያለባቸው፣ እድሜያቸው የገፋ፣ ከ18 አመት በታች የሆኑና አመክሯቸው የተቃረበ ግለሰቦች እንዲወጡ ተደርጓል።

ምንጭ፦ የደቡብ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመግታት በምትሰራው ስራ በእጅጉ እየተደነቀች የምትገኘው ደቡብ ኮሪያ ባለፉት 24 ሰዓት 47 ኬዝ ብቻ ሪፖርት አድርጋለች። ከ50 በታች ሆኖ የተመዘገበው ይህ ሪፖርት ከየካቲት 21 በኃላ የመጀመሪያው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia