TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] በሽታ ምላሽ አሰጣጥን (የኮቪድ-19) አስመልክቶ የተዘጋጀ መግለጫ!

በኢትዮጵያ በ24 ሰዓት ውስጥ 59 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ነው አምስት (5) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተርረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የታማሚዎች ሁኔታ ፦

- ሶስቱ ታማሚዎች ኢትዮጵያውያን ናቸው። አንደኛው ታማሚ ኤርትራዊ፤ ሌላኛው ታማሚ ደግሞ ሊቢያዊ ነው።

- ታማሚ አንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪኩ እንደሚያሳየው ከዱባይ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- ታማሚ ሁለት የ60 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሲሆን የኮንጎ የጉዞ ታሪክ ያለውና በለይቶ ማቆይ ውስጥ የነበረ ነው።

- ታማሚ ሶስት #ለጉብኝት አዲስ አበባ የመጣ የ45 ዓመት ወንድ ከካናዳ የመጣና በለይቶ ማቆያ የነበረ ነው።

- ታማሚ አራት የ27 ዓመት ሴት ስትሆን ከዩናይትድ ኪንግደም፣ ሌስተር ሲቲ የመጣችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ የነበረች ናት።

- ታማሚ አምስት የአዲስ አበባ ነዋሪ የ30 ዓመት ወንድ ሲሆን ከበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያለው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ ፦

• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 1843
• ባለፉት 24 ሰዓት የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 59
• ዛሬ በበሽታው የተያዙ ታማሚዎች - 5
• በአሁን ጊዜ በለይቶ ማቆያ ያሉ ታማሚዎች - 37
• ፅኑ ህሙማን - 1
• ህይወታቸው ያለፈ - 0
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 4
• በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ድምር - 43

ማስታወሻ፦ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጡ 2 ታማሚዎች ወደሀገራቸው ተመልሰዋል።

#EPHI

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

እስካሁን ድረስ ምንም የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝ ሳይመዘገብባት የቆየችው ደቡብ ሱዳን ዛሬ የመጀመሪያውን የቫይረሱን ታማሚ ሪፖርት አድርጋለች።

የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተገኘባት ግለሰብ የ29 ዓመት ወጣት ስትሆን FEBRUARY 28 ከኢትዮጵያ ወደ ደቡብ ሱዳን የገባችና በለይቶ ማቆያ ውስጥ ክትትል ሲደርገላት የነበረች እንደሆነ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሮይተርስ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RepublicOfSouthSudan

የደቡብ ሱዳን ምክትል ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ዛሬ መጋቢት 27/2012 ዓ/ም ያወጣው መግለጫ እንዳመለከተው የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተገኘባት የ29 ዓመት ወጣት ከአንድ ወር በፊት በአዲስ አበባ (ኢትዮጵያ) በኩል ከኔዘርላንድ ወደ ደቡብ ሱዳን የገባች ናት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት በኢትዮጵያ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

አንዲት የ60 ዓመት ታማሚ መጋቢት 19 ፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ታይቶባቸው በለይቶ ማከሚያ ገብተው የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው የነበረ ሲሆን በመጋቢት 22፣ 2012 ዓ.ም በኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው መረጋገጡ ይታወሳል፡፡

ይሁንና ከመጋቢት 22 አንስቶ ላለፉት ስድስት ቀናት በፅኑ ህክምና ላይ የነበሩ ሲሆን በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡

የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በህልፈተ ህይወታቸው የተሰማውን ሀዘን ገልጾ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን ተመኝቷል፡፡

#MoH #EPHI #EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 59 ደረሱ!

በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 252 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች 59 ደርሰዋል።

በተጨማሪ አንድ (1) ሌላ በቫይረሱ የተያዘ ሰው ከበሽታው ማገገሙን የጅቡቲ የጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። በዚህም አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 9 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhemedAli

በኮቪድ-19 ሕይወቷ ላለፈው ኢትዮጵያዊት ቤተሰብ እና ወዳጆች ከልቤ መጽናናትን እመኛለሁ። ነፍሷ ዘላለማዊ ረፍትን ታግኝ።

ዜናውን የሰማችሁ ሁሉ #እንድትረጋጉ እና የወጡትን መመሪያዎች በጥብቅ እንድትከተሉ አሳስባለሁ።

የሚገጥመንን ሁኔታ በጋራ ለማስተናገድ በምንዘጋጅበት በዚህ ጊዜ፣ በእምነት ጸንተን ቫይረሱ በማኅበረሰባችን መካከል እንዳይሠራጭ በትጋት ልንሠራ ያስፈልጋል።

አካላዊ ርቀታችሁን ጠብቁ። እጆቻችሁን በሚገባ ታጠቡ። በምትችሉት መንገድ ሁሉ ለሌሎች ድጋፍ አድርጉ።

(የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ አሊ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

ከጤና ሚኒስቴር የተሰጠ የሀዘን መግለጫ፦

በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ በሽታ ምክንያት በሀገራችን የአንድ ሰው ህይወት ሊያልፍ ችሏል። ታማሚዋ በኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ለይቶ ማቆያ ህክምና ሲደረግላቸው ነበር።

ከቀናት በፊት ወደ ጽኑ ህሙማን ክፍል ተዛውረው ጥብቅ ክትትል ሲደረግላቸው የነበረ ቢሆንም በዛሬው እለት ህይወታቸው አልፏል።

በዚህም የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን በእራሴና በጤና ሚንስቴር ስም እየገለጽኩ ለቤተሰቦቻቸው እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልባዊ መጽናናትን እመኛለሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TikurAnbessaSpecializedHospital

ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ክትትል የሚፈልጉ ተመላላሽ ታካሚዎቹ ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጋላጭ እንዳይሆኑ በማሰብ ባሉበት አገልግሎት እንዲያገኙ ማድረግ መጀመሩን አስታውቋል።

የሆስፒታሉ የሕክምና ባለሙያዎች በተመላላሽ ታካሚዎቹ ሞባይል ስልኮች ላይ በመደወል ማማከርን ጨምሮ አስፈላጊውን አገልግሎት እየሰጧቸው መሆኑን ሆስፒታሉ ገልጿል።

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ዙሪያ የሰጡትን መግለጫ በዚህ አጭር ቪድዮ መከታተል ትችላላችሁ። ቪድዮ ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የተገኘ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 142 ደረሱ!

የኬንያ ጤና ሚንስቴር መግለጫ እየሰጠ ይገኛል። ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ አስራ ስድስት (16) ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMercyMwangangi

በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጠ አስራ ስድስት (16) ሰዎች ውስጥ አስራ አምስቱ (15) ኬንያውያን ሲሆኑ አንደኛው (1) ናይጄሪያዊ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrMercyMwangangi

በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት 530 የላብራቶሪ ምርመራ የተደርገ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ነው 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው። እስካሁን ኬንያ ውስጥ በአጠቃላይ 3,836 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoH_KENYA

ትላንት ኬንያ ውስጥ ተጨማሪ አራት (4) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በመረጋገጡ የትላንትናውን ሪፖርት ጨምሮ አሁን ሪፖርት ከተደረገው ጋር አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 142 መድረሳቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። የኬንያ ጤና ሚኒስቴርም ቀደም ብሎ ያወጣውን የ138 ሰዎች ኬዝ ሪፖርት በማስተካከል 142 አድርጎታል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦

• በቫይረሱ የተያዙ ታማሚዎች ብዛት - 142
• ከበሽታው ሙሉ በሙሉ ያገገሙ - 4
• ህይወታቸው ያለፈ - 4

ምንጭ፦ የኬንያ ጤና ሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦

• በኬንያ 530 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 16 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በጅቡቲ 252 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 8 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኢትዮጵያ 59 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 5 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia