#CHINA
በቻይና ያሉ ተማሪዎችና ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መከላከያ የሚውል 452 ሺህ 589 ዩዋን ድጋፍ መደረጉን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎችና አቶ አስቻለው በላይ ከተባሉ የቤጅንግ ነዋሪ በድምሩ 101 ሺህ 189 ዩዋን ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በሌላ በኩል በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች 9 ሺህ 500 ዩዋን ፣ ከተለያዩ የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች አባላት ማለትም ከጓንዦ 3 ሺህ ዩዋን ፣ ከሻንሃይ 5 ሺህ 200 ዩዋን ፣ ከክችንችን 211 ሺህ ዩዋን ሲሰበሰብ በጓንዦ ከተማ ዳያስፖራ አባላት ደግሞ 120 ሺህ ዩዋን ድጋፍ ተገኝቷል።
ከዚህም ውስጥ 351 ሺህ 400 ዩዋን በቀጥታ ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በኢትዮጵያ ለተቋቋመው ብሔራዊ ሀብት አሰባሳቢ ግብረ ኃይል መላኩን ኤምባሲው ገልጿል።
ቀሪው ከተማሪዎች እና አቶ አስቻለው በላይ ከተባሉት የቤጂነግ ነዋሪ ኢትዮጵያዊ የተገኘው 101 ሺህ 189 ዩዋን ደግሞ የህክምና መሳሪያዎችን ገዝቶ ለመላክ ምርቶችን በማፈላለግ ላይ መሆኑን ኤምሳቢው አስታውቋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

በአሰላ ከተማ በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተጠርጥረው በሃሊላ ጤና ጣቢያ በተዘጋጀው የለይቶ ሕክምና መስጫ እንክብካቤ ሲደረግላቸው የነበሩት ሶስቱም (3) ሰዎች በተደረገላቸው ምርመራ ከቫይረሱ ነጻ መሆናቸውን የአሰላ ቲቺንግ እና ሪፈራያል ሆስፒታል ገልጿል።
ምንጭ፦ አርሲ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምንጭ፦ አርሲ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዊ ብሄረሰብ አስተዳደር ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ #ቲሊሊ ከተማ አስፓልት መንገድ ትላንት መጋቢት 27 ቀን 2012 ዓ/ም የኬሚካል ርጭት ተካሂዷል። ኬሚካል ርጭቱ ከችማ ስላሴ እስከ ካክስት በር የሚደርስ እንደሆነ ነው ከአዊ ኮሚዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ የሚያሳየው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DireDawa
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከተገኙት ሁለት (2) የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ውጭ ተጨማሪ ታማሚ አለመገኘቱ የአስተዳደሩ ጤና ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።
ከዛሬው መግለጫ የተወሰዱ ዋና ዋና ነጥቦች፦
- በአስተዳደሩ ቀደም ባሉት ቀናት ሁለት የኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው 4 ሰዎች ናሙና ተወስዶ በተደረገ ምርመራ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል።
- በአጠቃላይ 13 ተጠርጣሪዎችን ምርመራ ከተደረገላቸው 2 ታማሚዎች ብቻ መኖራቸው የተመጠቆመ ሲሆን ታማሚዎቹ የጤንነታቸው ሁኔታም እየተሻሻለ ነው።
- ከታማሚዎች ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው ዘመድ ፣ ጓደኛና የህክምና ባለሙያዎች ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡ በአጠቃላይ 36 ተጠርጣሪ ሰዎች የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው። በሀገር አቀፍ በተቀመጠው አሠራር መሠረት ናሙና በመላክ ውጤቱንም ለህብረተሰቡ ይገለፃል።
- ቀደም ሲል ናሙና ወደ አዲስ አበባ በመላክ ምርመራ ይደረግ የነበረው ወደ ሀረማያ ዩኒቨርስቲ መቀየሩን እና በቀጣይም በአስተዳደሩ ምርመራ እንዲደረግ ለድሬዳዋ ቅድሚያ እንዲሰጣት ተጠይቋል።
ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር

በድሬዳዋ ከተማ ከነገ መጋቢት 29/2012 ዓ/ም ጀምሮ በጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች 'የቤት ለቤት የህክምና' አገልግሎት በሳባ ምች ፣ በጉንፋንና ተመሳሳይ ምልክት የሚያሳዩ ታማሚዎች ወደ ጤና ተቋማት ሄደው ምርመራ እንዲደረግላቸው እንቅስቃሴ ይጀመራል። ስራው የተሳካ እንዲሆን ህብረተሰቡ ድጋፍ በማድረግ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።
ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ምንጭ፦ የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 44 ደረሱ!
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት የላቦራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው 164 ሰዎች ውስጥ አንድ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት፤ በ24 ሰዓታት ውስጥ ምርመራ ከተደረገላቸው ሰዎች መካካል 26ቱ በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋር ንክኪ አላቸው ተብለው የተጠረጠሩ ናቸው።
ቀሪዎቹ ደግሞ ለቫይረሱ ተጋላጭ ከሆኑ ማህበረሰቦች ናቸው ተብለው የተመረመሩ መሆናቸውን ነው የገለጹት።
በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ግለሰቦች ቁጥር 44 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ መካከል አንድ ግለሰብ በጽኑ ህሙማን ማቆያ ይገኛሉ።

የታማሚ ሁኔታ ፦
- ዛሬ በኮሮና ቫይረስ የተያዙት ግለሰብ የ65 ዓመት ሴት ኢትዮጵያዊት ሲሆኑ የዱከም ከተማ ነዋሪና የውጭ አገር የጉዞ ታሪክ #የሌላቸው ናቸው።
- ግለሰቧ ተጓዳኝ ለሆነ በሽታ ወደ ህክምና ተቋም ከሄዱ በኋላ የቫይረሱን ምልክት በማሳየታቸው ነው ምርመራ የተደረገላቸው። በምርመራው የኮሮና ቫይረስ እንዳለባቸው ተረጋግጧል።

#DrLiaTadesse
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 164
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 1
• በቫይረሱ ተይዘው በለይት ህክምና ውስጥ ያሉ - 36
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• ያገገሙ - 4
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 44
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ፦
• በ24 ሰዓት የተከናወነ ላብራቶሪ ምርመራ - 164
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 1
• በቫይረሱ ተይዘው በለይት ህክምና ውስጥ ያሉ - 36
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 1
• ያገገሙ - 4
• በበሽታው ህይወታቸው ያለፈ - 2
• ወደሀገራቸው የተመለሱ - 2
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 44
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጋና በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 214 ደረሱ!
ባለፉት 24 ሰዓት ጋና ተጨማሪ ዘጠኝ (9) ኬዞችን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 214 ደርሰዋል።
ሪፖርት ከተደረጉት 9 ኬዞች መካከል አንዲት የ37 ዓመት ሴት ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ የሌላት እና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋርም ግንኙነት የሌላት መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ጋና ተጨማሪ ዘጠኝ (9) ኬዞችን ሪፖርት አድርጋለች። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችም 214 ደርሰዋል።
ሪፖርት ከተደረጉት 9 ኬዞች መካከል አንዲት የ37 ዓመት ሴት ምንም አይነት የጉዞ ታሪክ የሌላት እና በቫይረሱ ከተያዙ ሰዎች ጋርም ግንኙነት የሌላት መሆኑ ለማወቅ ተችሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጋና መንግስት ለ3 ወር የውሃ ክፍያ ሸፍናለሁ ብሏል!
የጋና መንግስት ለቀጣይ 3 ወር የሁሉንም ዜጎች የውሃ ክፍያ እንደሚሸፍን አሳውቋል። በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚያተውን የውሃ እጥረትም መመቅረፍ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጋና መንግስት ለቀጣይ 3 ወር የሁሉንም ዜጎች የውሃ ክፍያ እንደሚሸፍን አሳውቋል። በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የሚያተውን የውሃ እጥረትም መመቅረፍ ስራዎች እየተሰሩ ነው ብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጋና ጤና ባለሞያዎች ለ3 ወር ከታክስ ነፃ ሆኑ!
የጋና ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሕሙማንን የሚንከባከቡ እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጦርነቱን ከፊት መስመር ሆነው ለሚመሩት የጤና ባለሙያዎች ወርሃዊ ደሞዛቸው ላይ #ጭማሪ እንደሚኖር ግልፀዋል። በተጨማሪ በጋና ውስጥ ያሉ ሁሉም ጤና ሰራተኞች ለሶስት (3) ወራት ከታክስ ነጻ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጋና ፕሬዝዳንት ናና አኩፎ አዶ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ሕሙማንን የሚንከባከቡ እንዲሁም የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት ጦርነቱን ከፊት መስመር ሆነው ለሚመሩት የጤና ባለሙያዎች ወርሃዊ ደሞዛቸው ላይ #ጭማሪ እንደሚኖር ግልፀዋል። በተጨማሪ በጋና ውስጥ ያሉ ሁሉም ጤና ሰራተኞች ለሶስት (3) ወራት ከታክስ ነጻ እንደሚሆኑ አስታውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የስፔን የ24 ሰዓት ሪፖርት ፦
በስፔን በ24 ሰዓት የ637 ሰዎች ሞት ተመዝግቧል። ቁጥሩ ባለፉት 2 ሳምታት ከተመዘገበው ዝቅተኛው ነው። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ከ13,000 በልጧል።
በተጨማሪ ባለፉት 24 ሰዓት 4,373 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ቁጥር ባለፉት ቀናት ከተመዘገበው ዝቅተኛ ነው (ቅዳሜ - 7,000 , እሁድ - 6,000) ጥብቅ የሆነ የአካላዊ ርቀት ውጤት እያመጣ ነው ተብሏል።

በኬንያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 158 ደረሱ!
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ። በሀገሪቱ ተጨማሪ አስራ ስድስት (16) ሰዎች በቫይረሱ በመያዛቸው አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 158 መድረሳቸውን አሳውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ መግለጫ እየሰጡ ይገኛሉ። በሀገሪቱ ተጨማሪ አስራ ስድስት (16) ሰዎች በቫይረሱ በመያዛቸው አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 158 መድረሳቸውን አሳውቀዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE
በኬንያ ሁለት ተጨማሪ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መሞታቸውን ፕሬዘዳንት ኡሁሩ ኬንያታ እየሰጡት በሚገኘው መግለጫ ላይ ተናግረዋል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 6 ደርሷል።

ኬንያ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 441 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል፤ ከእነዚህ ውስጥ ነው 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዛቸው የተረጋገጠው። በአጠቃላይ እስካሁን ድረስ 4,277 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጓል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 90 ደረሱ!
በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 513 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 31 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች 90 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 513 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 31 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች 90 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኬንያ ከመዲናዋ ናይሮቢም ሆነ ወደ መዲናዋ የሚደረግ ጉዞ ከለከለች!
ኬንያ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ለመግታት ከመዲናዋም ሆነ ወደ መዲናዋ ናይሮቢ የጉዞ እገዳ መጣሉን ፕሬዚደንት ኡሁሩ ኬንያታ አስታወቁ።
የጉዞ እገዳው ከዛሬ መጋቢት 28 ቀን 2012 ዓ.ም ምሽት 1፡00 ሰዓት (April 6, 2020 7:00 PM) ጀምሮ ለመጭዎቹ 21ቀናት የሚዘልቅ ነው።
ከናይሮቢ በተጨማሪም በሌሎች ሦስት የባህር ዳርቻ ከተሞች፤ ሞምባሳ፣ ክሊፍ እና ኪዋሌ እገዳው ተጥሏል።
ምንጭ፡- Ethiopian Embassy in Kenya

TIKVAH-ETHIOPIA
በጅቡቲ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 90 ደረሱ! በጅቡቲ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 513 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 31 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። በሀገሪቱ ያሉ አጠቃላይ የቫይረሱ ተጠቂዎች 90 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ በጅቡቲ ሪፖርት ከተደረጉት 31 ኬዞች ሀያ አምስቱ (25) ጅቡቲ ከሚገኘው ከAl-Rahma ሆስፒታል ጋር የተገናኘ ነው።
ሁለት (2) የህክምና ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው መረጋገጡን ተከትሎ በዶክተሮቹ የታከሙ እና ንክኪ ያላቸው ሁሉ ለመንግስት በአስቸኳይ ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
ከመጋቢት 7/2012 ዓ/ም ጀምሮ ከዚህ በታች ስማቸው ከተጠቀሱት ዶክተሮች ጋር ንክኪ ያለው ግለሰብ ለመንግስት ሪፖርት ያድርግ ተብሏል ፦
- Dr. Abdoulalim Saad Mohamed Abdelrehim [Cardiologist]
- Dr. Hazem Fawzi Moustapha Abdoulrahaman [Emergency and Resuscitation Service]

የጃንሜዳው አትክልት ተራ ነገ ስራ ይጀምራል!
አትክልት ተራ ሲሰጥ የነበረው የግብይት አገልግሎት ወደ ጃንሜዳ እንዲዛወር የከተማ አስተዳደሩ በወሰነው መሠረት ጃንሜዳን የማዘጋጀት ሥራው መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ገልፀዋል።
በዚሁ መሠረት የአትክልት ተራ ከነገ መጋቢት 29/2012 ዓ/ም ጀምሮ እንደሚዘጋ እና በጃንሜዳ የተዘጋጀው የአትክልት ግብይት ቦታ ሥራ እንደሚጀምር ያስታወቁት ምክትል ከንቲባው ነጋዴዎች እና በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ ዜጎች የኅብረተሰቡን ጤና ለመጠበቅ የተወሰነውን ይህን ውሳኔ ማክበር እንደሚኖርባቸውም አሳስበዋል።
#MayorofficeAA #EBC