TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ትግራይን በኢኮኖሚ የማዳከም አንድ አካል ነው!" - የትግራይ ክልል መንግስት

ያልታወቀ 'የፌደራል መንግስት' አካል የቻይና ሻንዢ ግዛት ባለስልጣናት እና ኢንቨስተሮች ወደ ትግራይ እንዳይጓዙ መከልከሉ የትግራይ ክልላዊ መንግስት አሳውቆ የጉዞ ክልከላው "ትግራይን በኢኮኖሚ የማዳከም አንድ አካል ነው" ሲል ገልፆታል፡፡

(DW)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትራፊክ አደጋ የ5 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በደቡብ ወሎ ዞን ከመካነ ሠላም ወደ ደሴ ሲጓዘ የነበረ አነስተኛ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በ5 ሰዎች ላይ የሞትና በሌሎች ቁጥራቸው ባልተገለጸ ተሳፋሪዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።

(AMMA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ESAT...

"ESAT የተባለው ሚዲያ የህዝብን ህገ - መንግስታዊ መብት ጥያቄን በማጠልሸት እንዲሁም በዎላይታ ብሄር ላይ ግልጽ የህዝብን ሞራል የሚነካ ጥላቻ ንግግር ማታ ዕለታዊ በተባለው ፕርግራም ላይ ማድረጋቸውን በዎላይታ ህዝብ ስም በግልፅ አወግዛለሁ። በተጨማሪም ጣቢያው እንዲታረምና ሰፊውን ህዝብ ይቅርታ እንዲጠይቅ ጉዳዩን ለብሮድካስት ባለስልጣን ድረስ እንወስዳለን" - አቶ ዳጋቶ ኩምቤ (የወላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrAbiyAhemedAli

"ዩኒቨርሲቲ የሚኬደው ለመገዳደል ሳይሆን ለመማር ነው። እነዚህን ወጣቶች ለግጭት የሚጠቀሙ አካላት አይጠፉም፤ በአሁኑ ወቅት በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች ጠንካራ ጥበቃ የማደራጀት ስራ ተከናውኗል በተጨማሪም በጥፋተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ ይወሰዳል።" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

በምስራቅ ጎጃም ዞን ሁለት እጁ እነሴ ወረዳ ሞጣ ከተማ አስተዳደር ዛሬ አመሻሽ ላይ (ከምሽቱ 1:30) ጀምሮ በከተማዋ በሚገኘው የታላቁ ጀሚዑል ኸይራት መስጂድና ሌሎች ሁለት መስጅዶች ላይ የማቃጠል ተግባር መፈፀሙ ተሰምቷል።

ይህ አስደንጋጭ ድርጊት ከመፈፀሙ ቀደም ብሎ ፈፃሚዎቹ እና ምክንያቱ በግልፅ ባይታወቅም በጥንታዊው ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያነጣጠረ የጥቃት ሙከራም ነበር ተብሏል።

በአሁን ሰዓት በከተማይቱ ውስጥ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማም ነው ከአካባቢው እየወጡ የሚገኙ መረጃዎች የሚጠቁሙት። የሱቆች ዝርፊያ እየተካሄደ እንደሆነና በሰዎች ላይም አደጋ መድረሱ እየተገለፀ ነው። የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ሁኔታው ከዚህ የከፋ አደጋ ከማድረሱ በፊት ሊያስቆሙና አጥፊዎችንም በመለየት ለህግ ሊያቀርቡ ይገባል።

ሞጣ ከተማ፦

ማህበረሰቡ ለእልፍ አመታት ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መልኩ፣ በሃይማኖት መቻቻል፣ በመከባበር፣ በመዋደድ የሚኖርባት ከተማ እንደሆነች ነው የሚነገርላት። መንግስት አጥፊዎች በአፋጣኝ ለፍርድ ማቅረብ እና ለህዝብ ማሳወቅ አለበት። አፋጣኝ የእርቅ መርሃ ግብርም ሊዘጋጅ፣ የተጎዱም ሊካሱ፣ የተቃጠሉ መስጊዶችም በአስቸኳይ ሊገነቡ ይገባል። ነዋሪዎችን የማያባራ ግጭት ውስጥ ለመክተት እየተደረጉ ያሉ አደገኛ እንቅስቃሴዎች በአስቸኳይ ሊቆሙ ይገባል።

ከኡስታዝ አቡበክር አህመድ👇
https://telegra.ph/TIKVAH-12-21

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#WALTA

ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ ኮርፖሬት ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካዔል ጋር በተያያዘ በተለቀቀው ሀሰተኛ መረጃ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸው አራት የተቋሙ ሰራተኞችን ከስራ አግዷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ATTENTION

የፌደራሉ እንዲሁም የክልሉ መንግስት በሞጣ አካባቢ ለተፈጠረው ችግር እጅግ አስቸኳይ የሆነ መፍትሄ ሊፈልጉ ይገባል። ህዝቡንም የማረጋጋት ስራ በአፋጣኝ ሁኔታ ሊሰራ ይገባል። ችግሮች አሁን ካሉበት ሳይባባሱ እንዲሁም ሳይዛመቱ መንግስት አስፈላጊውን ሁሉ ትኩረት ሊያደርግ እንደሚገባ እናሳስባለን። ልዩ ትኩሩት በሞጣ ከተማ ለተፈጠረው ችግር!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለሞባይል ስልክ ስክሪን ማጠንከሪያነት አገልግሎት ላይ የሚውለው ቴክኖሎጂ በተጠቃሚዎች ላይ የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ ተገለጸ!

ሰሞኑን በሃገራችን በስፋት መነጋገሪያ ሆኖ የሰነበተው በብዛት ከቻይና ወደ ሃገር ውስጥ የሚገባ የናኖ ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነው (Nano coating machine) ለሞባይል ስልክ ማጠንከሪያነት አገልግሎት ላይ በመዋል ላይ ይገኛል፡፡

ይህንን ተከትሎ ከተገልጋዮች እና የተለያዩ ሚዲያ አካላት በደረሰ መረጃና በቀረበው ጥያቄ መሰረት ወደ ሃገር እየገባ ባለው የዚህ ቴክኖሎጂ መሳሪያ ከጨረራ አንጻር ጤና ላይ ሊያስከትል የሚችለው ጠንቅ መኖሩና አለመኖሩን ለማጣራት የኢትዮጵያ ጨረራ መከላከያ ባለስልጣን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎ በመገኘት በመጋዘን ውስጥ ከሚገኙ (Nano coating machine) መሳሪያዎች ውስጥ ናሙና በመውሰድ ባደረገው የቁጥጥር እና ምርመራ ሥራ መሳሪያው የኢትዮጵያ ጨረራ መካላከያ ካስቀመጠው ጉዳት ከሚያስከትሉ የጨረራ መጠን ልኬት በታች የሆነ እና በህዝብ እና በአካባቢ ላይ የሚያስከትለው ጉዳት አለመኖሩን አረጋግጧል፡፡

አዮን ፈጣሪ ስላልሆኑ የጨረራ አይነቶች አዮን ፈጣሪ ያልሆኑ የጨረራ አይነቶች በርካታ ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ልዕለ ሀምራዊ ሞገድ (UV Radiation) ይገኝበታል።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-20

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የዕምነት ተቋማት ላይ የሚሰነዘሩ ጥቃቶች የክሽፈታችን መገለጫዎች ናቸው። ሌላው ሰው የሚያከብረውን፣ የሚያመልከውን፣ ተደፍቶ የሚጸልይበትን እና ከፈጣሪው ጋር የሚገኛኝበት ሥፍራ ማቃጠልና ማውደም እርስ በርሳችን አለመከባበራችንን ነው የሚያሳየው። እጅግ የኋላቀርነትም ምልክት ነው። በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በጋራ ልናወግዝ ይገባል። [ትናንት] በምስራቅ ጎጃም፣ ሞጣ አካባቢ በመስጊዶች ላይ የተፈጸመው ጥቃት እጅግ አስነዋሪ የወንጀል አድራጎት ነው። መንግስት ድርጊቱን የመጸሙትን ሰዎች ወደ ፍርድ በማቅረብ ተጠያቂ እንዲሆኑ ማድረግ አለበት። ለእምነት ተቋማትም በቂ ጥበቃ ሊደረግ ይገባል።" - ያሬድ ሀይለማርያም (የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት የሆነው AHRE ዋና ዳይሬክተር)
.
.
.
"የእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ለማውገዝ ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው። ሃይማኖትንና ብሔርን መሰረት ያደረጉ ግጭቶች ወደማያባሩ ቀውስ ውስጥ ሊከቱ እንደሚችሉ ይታወቃል። በመሆኑም በቤተክርስቲያን፣ በመስጅድ እና በተለያዩ የእምነት ተቋማት ላይ የሚደርሰውን የተቀነባበረ ሴራ በመገንዘብ ችግሩን በሰከነ መንፈስ ማክሸፍ ይገባል። አረመኔያዊ ድርጊት በመፈጸም የሚሳተፉ አካላትን ለይቶ ለህግ ማቅረብ ለነገ የማይተው ጉዳይ ነው።" - ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ (የትራንስፖርት ሚኒስትር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሞጣ ከተማ በሀይማኖት ተቋማት ላይ የደረሰውን ጥቃት የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) በጽኑ ያወግዛል!

በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ትላንት አርብ ታህሳስ 10 ቀን 2012 ዓ/ም ከምሽቱ 1 ሰዓት አካባቢ በጥንታዊና ታሪካዊው ሞጣ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ላይ ለጊዜው ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ የእሳት ቃጠሎ የተነሳ ሲሆን፣ በቤተ ክርስቲያኑ ላይ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ በከተማው ነዋሪ ርብርብ እሳቱ በቁጥጥር ስር ውሏል።

ይህንን ተከትሎ የተወሰኑ ወጣቶች በመስጊዶችና አንድ የንግድ ቤት ላይ የእሳት ቃጠሎ እንዲደርስ አድርገዋል። ሱቆችን የመዝረፍ ሙከራም ተካሂዷል። አብን በሞጣ ከተማ በሁለቱም የእምነት ተቋማትና በንብረት ላይ የተፈፀመውን ጥቃት በጥብቅ ያወግዛል።

ድርጊቱም በምንም አይነት መንገድ ጠንካራ ትስስር ያለውን የሞጣና አካባቢው ህዝበ ክርስቲያንና ህዝበ ሙስሊም የሚገልጽ ሳይሆን ጥቂት በስሜት የሚንቀሳቀሱ ግለሰቦች ድርጊት እንደሚሆን ይረዳል።

የአማራ ሕዝብ ለሺህ ዓመታት የተለያዩ ሀይማኖቶች ተከባብረው፣ሙስሊሙ አብያተ ክርስቲያን፣ ክርስቲያኑ መስጊዶች ሲገነቡ አብሮ እየገነባ፣በሰላም የሚኖሩበት ህዝብ ሲሆን፣ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በአማራ "ክልል" በተለይ በእስልምና እምነት ተቋማት ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች መጨመራቸው አሳሳቢ ነው። የእምነት ተቋማት ላይ የሚደረግ ጥቃት የአማራን ሕዝብ እሴት የማይወክል፣ ፍፁም ህገወጥና በአስቸኳይ ሊታረም የሚገባ ተግባር ነው ብሎ ንቅናቄያችን ያምናል።

የክልሉ መንግስት በህዝባችን የእምነት፣የትምህርትና የንግድ ተቋማት ላይ የሚደርሱ ተደጋጋሚ ጥቃቶችንም ሆነ የህዝባችን ሰላም ለማደፍረስ የሚንቀሳቀሱ ሰርጎ ገቦችን መቆጣጠር አለመቻሉ በጣም አሳዛኝና አስቸኳይ መፍትሄ የሚያሻው ነው።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-21

@tikvahethiopia
#IMF

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ( አይ ኤም ኤፍ) ለኢትዮጵያ የ2 ነጥብ 9 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ አፀደቀ፡፡ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሥራ አስፈፃሚ ቦርድ ያጸደቀው ይህ ድጋፍ የኢትዮጵያን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለመደገፍ  የሚውል  መሆኑ ተገልጿል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትዝብት...

እውነት እናተ የቲክቫህ ቤተሰብ ናችሁ?

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እጅግ በሚያስፈራ መልኩ መጥፎ ድርጊቶችን እንደማውገዝ የሚያፎካክሩ፣ የኔ ብቻ ይነገርልኝ ስለ ሰው ምን አገባኝ የሚሉ፣ ያለፈውን ነገር እያነሱ የሚያስተያዩ የሚያወዳድሩ፣ ባለፈው እንዲህ ሲሆን መች ቀረበ የሚሉ፣ የሰው ልጆችን ሞትና ስቃይ ሳይቀር የሚያወዳድሩ፣ አንዱን ጥፋት በሌላ ጥፋት ለመሸፈን የሚፈልጉ እየበዙ ነው። መጥፎ ድርጊትን እኩል ካላወገዝን ሀገራችን ለማጥፋት ቀዳሚዎቹ እኛ እንሆናለን።

አንዳንድ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት የሚመስሉ ነገር ግን ስለቤተሰባችን ዓላማ ምኑንም የማያውቁ ሰዎች የራሳቸው ጉዳይ ብቻ እስካልተነገር ድረስ በተለያዩ አቅጣጫዎች ሲፈልጉ ዘረኛ፣ ተላላኪ፣ አሽቃባጭ፣ እያሉ ስድባቸውን ጥላቻቸውን ያዘንቡብናል። እኛም በትዕግስት ወገኖቻችን ናቸውና ይህ ጥላቻ መጥፎ ነው የሚጎዳውም ራስን ነውና ይቅርባችሁ እያልን ክፉ ሳንናገር እያስረዳን ነው። ሚዛናዊ ነገር አታቀርቡም የሚሉ የቤተሰባችን አባላት ደግሞ ማስረጃችሁን አቅርቡ ሲባሉ ስድብ፣ የጥላቻ ንግግር ይልካሉ ወይም ችግሮችን ፈልገው ሊነግሩን ይጥራሉ። ሁሉም ነገር ገፁ ላይ ስላለህ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል።

እውነተኛ ትችት እና ቅሬታ ካላችሁ በማስረጃ ብቻ አቅርቡ፤ ያንን ማድረግ ካቃታችሁ የጥላቻ ንግግሮቻችሁን የምናስተናግድበት አቅም የለንም! የጥላቻ ንግግር የምትናገሩና ምንም ማስረጃ ሳይኖራችሁ የምትሳደቡ እንዲሁም የቤተሰቡን ስም የምታንቋሽሹ ሰዎችን ከቤተሰባችን ለመቀነስ እንገደዳለን፤ ማንም ሰው የተሰማውን መናገር ይችላል፣ ቅር ያለውን መግለፅ ይችላል ግን መረጃ፣ ማስረጃ ማቅረብ አለበት ያንን ሳያደርግ የሚሳደብ ግን ሆን ብሎ በህዝቦች መካከል እልቂት እንዲፈጠር የሚፈልግ ነውና እሱ የቤተሰባችን አባል መሆን አይችልም።

@tikvahethiopiaBot
ኢትዮጵያ፣ግብጽና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት እያካሄዱ ነው!

የሶስቱ ሀገራት ውሃ ሚኒስትሮች በካርቱም በግድቡ ውሃ አሞላል እና አለቃቀቅ ዙሪያ ትኩረት በማድረግ እንደሚወያዩ ተነግሯል፡፡ ይህ ውይይቱ በአለም ባንክ እና አሜሪካ ታዛቢነት ከሚካሄዱት አራት ስብሰባዎች ሶስተኛው መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ውይይት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ፣ ካይሮ እንዲሁም በዋሽንግተን መካሄዱ የሚታወስ ነው፡፡

(ፋና ብሮድካስቲንግ)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሞጣ ከተማ 'በሃይማኖት ተቋማት' ላይ በተፈጸመው ድርጊት ማዘኑንና ድርጊቱን እንደሚያወግዝ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ!

ዛሬ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸህ ሰኢድ አሕመድ በጽሕፈት ቤታቸው ትናንት በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈጸመውን የቃጠሎ ድርጊት አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

ታኅሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አጸያፊ ተግባር መፈጸሙን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል። በሞጣ ከተማ አስተዳደር የሚገኙ አራት መስጂዶች መቃጠላቸዉንና የሙስሊም ሱቆችና ድርጅቶች ላይ ዝርፊያ መፈጸሙን ገልጸዋል። ‹‹በተፈጸመው ድርጊት የተሰማንን ሐዘን እንገልጻለን፤ አስጸያፊ ድርጊቱንም እናወግዛለን›› ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ።

More👇
https://telegra.ph/ETH-12-21-2

(AMMA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE - ሲጠናቀቅ ደቡብ፣ ኦሮሚያና ጋምቤላን በአቋራጭ የሚያገናኘው የጎሬ - ማሻ - ቴፒ የ140 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ ተጀመረ። ጅማ ፣ ቦንጋ ፣ ሚዛን ቴፒ ፣ ጋምቤላ ፣ ጎሬ ፣ መቱ እና አዲስ አበባን በአጭር ርቀት የሚያገናኘው የጎሬ - ማሻ - ቴፒ መንገድ ግንባታ የፌዴራልና የክልል ባለስልጣናት በተገኙበት በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል፡፡ ይህ የአስፋልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታ በ4 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር እንደሚከናወን የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የኮሙኒኬሽን ዳይሬክቶሬት አስታውቋል፡፡

(SRTA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#MoSHE - የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ቀንድ ታሪክ በሚል ርዕስ "ለዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች' ማስተማሪያ እንዲሆን የተዘጋጀ ሞጁልን ይመለከታል!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(የገቢዎች ሚኒስቴር)

ባህር ዳር ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ምድረ ገነት ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሠራተኞች እና የፊደራል ፖሊስ አባላት በቅንጅት በጥናት ተለይቶ በነበረ ቀንደኛ ኮንትሮባንዴስት ቤት በደረሰ የህብረተሰብ ጥቆማ መሠረት በተደረገ ብርበራ /ኦፕሬሽን/በቀን 10/04/2012 ዓ.ም ብዛቱ 1288 የክላሽ ጥይት እና 414 የብሬን ጥይት በድምሩ 1702 ህገ ወጥ ጥይት በቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን ከጉዳዪ ጋር በተያያዘ 02 ተጠርጣሪ ተይዘው ጉዳያቸው በህግ አግባብ እየታየ ይገኛል።

(የገቢዎች ሚኒስቴር)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ለተማሪዎች ደህንነት እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚደረገው ጥበቃ ሊጠናከር ይገባዋል። እንደሚታወቀው ሀገሪቱ ለውጥ ውስጥ በመሆኗ ውስብስብ የሆነ የፖለቲካ ችግር አለ፤ ይሄም መፍትሄ ያሻል። ለረጅም ጊዜ ሲንከባለል የመጣው በብሄሮች መካከል ያለው ክፍፍልም በእርቅ እና በመተባበር በእኩልነት እንዲኖር ትልቅ ስራ መስራት ይፈልጋል። ሌላው የመንግስትንም አደረጃጀት ስናይ ችግሮች ሳይፈጠሩ መፍታት ሲፈጠሩም በፍጥነት ችግሩን ፈቶ ሊደርስ የነበረውን የአደጋ መጠን መቀነስ ላይ ትልቅ ችግር አለ። ይሄም መፈታት አለበት።" - ዶ/ር ሃሰን የሱፍ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ከዚህ በፊት በነበሩ ስርዓቶች በዜጎች ላይ የሚደርሰውን በደል ለማስቀረት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተቃውሞ አድርገዋል። ሆኖም በአሁኑ ወቅት በዩኒቨርሲዎች ውስጥ የሚስተዋሉት ተግባራት ከኢትዮጵያዊ ታሪክ፣ ባህልና እሴት ያፈነገጡ ናቸው። በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ከሚደረገው የሰላም መደፍረስ በተጨማሪ በአንዳንድ ክልሎች ያለው ግጭት ባለሀብቶች መዋእለ ንዋያቸውን እንዳያፈሱ የሚያግዳቸው ነው። ይህም አገሪቱንና አብዛኛውን ድሃ ህዝብ የሚጎዳ ነው። ከዚህም ሌላ የግል ፍላጎታቸውን ለማሳካት በሚፈልጉ ፖለቲከኞች ምክንያት አብዛኛው ድሃ ኢትዮጵያዊ ለግጭት እየተዳረገ በመሆኑ የሚመለከተው አካል የእርምት እርምጃ መውሰድ አለበት።"-አቶ ኤርሚያስ መኮንን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Jimma

ትላንት በሞጣ ከተማ የተፈፀመውን አፀያፊ ድርጊት የጅማ ከተማ ነዋሪዎች እንደሚያወግዙት አደባባይ በመውጣት ገልፀዋል። በእምነት ተቋማት ላይ የሚፈፀም ጥቃት እንዲቆም አሳስበዋል። መንግስት አጥፊዎችን በአስቸኳይ ለህግ እንዲቀርብ ጠይቀዋል።

(Abdulwahid Abdellah - Seid Miftah)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- ተጠርጣሪዎችን አፈላልጎ በመያዝ እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ!

በምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ አስተዳደር በቤተ እምነት ተቋማት ላይ የደረሰው የቃጠሎ አደጋ በተመለከተ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ታኀሣሥ 10 ቀን 2012 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡20 አካባቢ በሞጣ ከተማ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን የእሳት ቃጠሎ መከሰቱን ተከትሎ በሌሎችም የሃይማኖት ተቋማት ላይ የእሳት ቃጠሎ መፈጸሙን ከዞኑ ፖሊስ መምሪያ ያገኙትን መረጃ ጠቅሰው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል መምሪያ ኃላፊ ጀማል መኮንን ተናግረዋል፡፡ በቡድን በመሰባሰብ መስጂዶች ላይ ጥቃት እንደተፈፀመ ነው ኮማንደር ጀማል የተናገሩት፡፡

በድርጊቱ በሞጣ ከተማ አስተዳደር ቀበሌ 03 የሚገኝ መስጂድ ሙሉ በሙሉ ሲቃጠል፣ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን እና ቀበሌ 05 እና 06 የሚገኙ መስጂዶች ደግሞ በከፊል እንደተቃጠሉና አንድ የገበያ ማዕከል በቃጠሎና በመሰባበር ጉዳት እንደደረሰበት ኮማንደር ጀማል መኮንን ተናግረዋል፡፡

በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ሪፖርት እንዳልተደረገም አመላክተዋል፡፡ ፖሊስ ችግሩን በማስቆም የማረጋጋት ሥራ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡ በቀጣይ ተጠርጣሪዎችን አፈላልጎ በመያዝ እርምጃ እንደሚወሰድም አስታውቀዋል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች ሃይማኖትንና ማንነትን መሠረት አድረገው የሚነሱ ችግሮችን ኅብረተሰቡ ከማባባስ ይልቅ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር የማርገብና የማረጋጋት ልምድ ሊዳብር እንደሚገባ ኮማንደር ጀማል መኮንን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

https://telegra.ph/AMMA-12-21

#AMMA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia