#update የኤሌክትሪክ አገልግሎት በፈረቃ ሊሆን የቻለበትን ምክንያት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል አገልግሎት ገለፀ። የአገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ግድቦች የማመንጨት አቅም 4,300 ሜጋ ዋት የደረሰ ቢሆንም የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የማመንጨት አቅም የሚወሰነው ግድቦቻቸው በሚይዙት የውሀ መጠን ነው፡፡ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ከሁሉም የሃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ከ1,400 ሜጋ ዋት በላይ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት አይቻልም፡፡ ይህ የኤሌክትሪክ ሃይል መጠን ከፍላጎቱ ጋር ሲነጻጸር 60% የሚሆነውን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኛ ብቻ ቢያስተናግድ ነው፡፡
ሁሉም ኃይል ማመንጫ ግድቦች በየደረጃቸው አስተዋጽኦ ቢኖራቸውም ከፍተኛ ሃይል የማመነጨት አቅም ያለው የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ ነው፡፡ የግልገል ጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ግድብ የማመንጨት አቅም በውሃ ላይ የተመሰረተ በመሆኑ የበልጉ ወቅት ሲዘገይና የውሃው መጠን እየቀነሰ በሄደ ቁጥር ማመንጨት የነበረበትን ያህል የኤሌክትሪክ ሃይል ማመንጨት አልቻለም፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የሃይል ማመንጫ ግድቡ አዲስ በመሆኑ መያዝ የሚችለውን ያህል ውሀ ሙሉ በሙሉ ማጠራቀም አልቻለም፡፡
ይባስ ብሎ ካለፈው አመት ከነበረው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የዘንድሮው የውሀ መጠን ከፍታ በ15 ሜትር ዝቅ ብሏል፡፡ ባለፈው አመት ተመሳሳይ ወቅት የግድቡ ውሃ ከባህር ጠለል በላይ 834 ሜትር ላይ የነበረ ሲሆን በዚህ አመት ተመሳሳይ ጊዜ 818 ሜትር ላይ ደርሷል፡፡
ለክረምቱ መዳረሻ ከመጋቢት ወር ጀምሮ በአገሪቱ የምስራቅና ደቡብ ምስራቅ አካባቢዎች ከበልግ ዝናብ ይገኛል ተብሎ የተገመተው የውሀ መጠን በታሰበው ልክ አለመገኘቱና የቀጣዩ ክረምት ዝናብ ወደ ግድቦቹ እስኪገባ ደግሞ ከዚህ በኃላ ቢያንስ ለሰባት ሳምንታት ያህል ጊዜ መጠየቁ የኃይል አቅርቦቱን ጊዚያዊ ችግር እንዲያስተናግድ አስገድዶታል፡፡
በአጭር አገላለፅ በቀጣዮቹ 6 ሳምንታት ለአገሪቱ የሚያስፈልገው የኤሌክትሪክ ኃይል መጠንና በግድቦቹ ያለው የውሀ ከፍታ ሊያስገኝ የሚችለው የኃይል መጠን ሲሰላ ከፍላጎቱ አንጻር በቂ አይደለም፡፡
አሁን ያለው ውሃ ያለ ቁጠባ ጥቅም ላይ ቢውል ደግሞ ክረምቱ ሳይደርስ ማመንጫወቹ ውሀ አልባ ይሆናሉ፡፡ለዚህ ያለው አማራጭ ውሀውን በቁጠባ መጠቀም ብቻ ነው፡፡ ይህን ለማድረግ ደግሞ በየቀኑ ካለው የኃይል ፍላጎት በአማካይ እስከ ከ700 እስከ 900 ሜጋ ዋት የሚያመነጭ የውሃ መጠንን መቆጠብ ያስፈልጋል ማለት ነው፡፡ የውሃ ቁጠባው ቀጥታ በሀይል ስርጭት ቅነሳ ተግባራዊ የሚደረግ ነው፡፡
ግንቦት 9/2011 ዓ.ም በውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስቴር በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የአዲስ አበባ የፈረቃ ፕሮግራም በሶስት ምድብ ተከፍሎ እንደሚከናወን የተገለፀ ቢሆንም በጋዜጣዊ መግለጫው የተነገረው የፈረቃ ፕሮግራም ለደንበኞችም በቂ ጊዜ የማይሰጥ፣ ለአሰራር አመቺ ባለመሆኑ እና የሚቋረጥበት ሰዓት አጭር በመሆኑ ኔትዎርኩ ላይ ጫና በመፍጠር ለተጨማሪ የኃይል መቆራረጥ ምክንያት ስለሚሆን እንደገና ተሻሽሎ በሁለት ፈረቃ እንዲሆን ተወስኗል፡፡
ለደንበኞችም በየዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት ከሚሆን ይልቅ የጠዋትና የምሽት ሰዓታትን መሰረት ባደረገ መልኩ አንድ ቀን ጠዋት ከጠፋ ሌላ ቀን ከሰዓት ወይም ምሽት ላይ እንዲሆን በማድረግ መርሃ ግብር ተዘጋጅቶ ወደ ትግበራ ተገብቷል፡፡
#እንደገና ተሻሽሎ በቀረበው የፈረቃ ፕሮግራም መሰረት በአዲሰ አበባ ከተማ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚቋረጠው ከንጋቱ 11፡00 እስከ ቀኑ 8፡00 እና ከቀኑ 8፡00 እስከ ምሽቱ 4፡00 ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም ሁሉም የዝቅተኛ መስመር (የቤት ተጠቃሚዎች) ከምሽቱ 4፡00 ጀምሮ እስከ ንጋቱ 11፡00 የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
በዚህ የኃይል ቅነሳ መርሃ ግብር የድንጋይ ወፍጮዎች እስከ ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓም ሙሉ በሙሉ ሀይል እንዳይጠቀሙ፣ በውጭ ምንዛሪ ግኝት የተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ሙሉ በሙሉ ሀይል #እንዳማይቋረጥባቸው፣ የሲሚንቶ ፋብሪካዎች 15 ቀን ተጠቅመው በቀጣዩ 15 ቀን እንዳይጠቀሙ፣ በኤክስፖርት መስክ ከተሰማሩ ውጭ ያሉ አምራች ኢንዱስትሪዎች አንድ ቀን ከተጠቀሙ በኋላ በቀጣዩ አንድ ቀን እንዳይጠቀሙ በቀጥታ መስመር ኃይል የተገናኘላቸው (dedicated line) የጤና፣ የውሃ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፈረቃ ውጭ እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡
በሌሎች የሃገሪቱ ከልሎች ተግባራዊ የሚደረገው የፈረቃ መርሃ-ግብር በክልል፣ በዲስትሪክትና በአገልግሎት መስጫ ማዕከላት አማካኝነት የሚገለፅ ሲሆን ክቡራን ደንበኞቻችን የፈረቃ መርሃ-ግብሩ እስከ ሰኔ 30 ሊቀጥል የሚችል ስለሆነ የተፈጠረውን ጊዜያዊ ችግር በመረዳት በትዕግስት እንድትጠብቁን እየጠየቅን የፈረቃ መርሃ-ግብሩን ዝርዝር መረጃ በተለያዩ የኮሙኒዩኬሽን አግባቦች የምናሳውቅ ይሆናል ሲል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ገልጿል።
Via #walta
@tsegabwolde @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ማንኛውም ዓይነት ሞተር ሳይክል ማሽከርከር የሚከለክለውን መመሪያ ተከትሎ የተለያዩ አስተያየቶች እየተሰጡ ይገኛሉ። በሞተር ብስክሌት ከሚተዳደሩ ዜጎች የወጣት ጥላሁነ ታደሰ አጭር ታሪክ በሚከተለው መልኩ ተዘጋጅቷል።
Via #walta
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethipia
Via #walta
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethipia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በምሽት እጄን ጠምዝዞ 6700 ብር የያዘ ቦርሳየን የቀማኝ ሞተር ሳይክል ታርጋ አልነበረውም - በምሽት በሞተር ብስክሌት ዘረፋ የተፈፀመባት ወጣት ታሪክ፤
Via #walta
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #walta
🗞ቀን 15/10/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ምርጫ2012? 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ በተያዘለት ጊዜ “ይካሄድ” “አይካሄድ” በሚል በአዲስ አበባ ከተማ ውይይት ተካሄደ፡፡
Via #walta
🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Via #walta
🗞ቀን ሰኔ 29/2011 ዓ/ም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
🤔#WALTA ምን ነካው??
የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥን አስመልክቶ የሀዋሳ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ አሉ ተብሎ የተሰራጨው መረጃ እርሳቸው ያላሉት ነው!
"በሀዋሳ ከተማ ድምጽ ለመስጠት ከተመዘገበዉ መራጭ ዉስጥ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ ሰጥቷል"- ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ
.
.
ትናትና በተካሄደዉ የሲዳማ ህዝበ ውሳኔ የድምጽ አሰጣጥ በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የነበረዉ ሂደት በሰላም መጠናቀቁን የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥራቱ በየነ ገለጹ፡፡
በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ድምጽ ለመስጠት በመራጭነት ከተመዘገበዉ ህዝብ ከ90 በመቶ በላይ ድምጽ መስጠቱን በየምርጫ ጣቢያዎች እየወጣ ያለው ውጤት እንደሚያሳይም ምክትል ከንቲባው ተናግረዋል፡፡
በድምፅ መስጫው ቀን እንዲቋረጡ ተደርገዉ የነበሩ መንግስታዊ አገልግሎቶችና የንግድ እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ተግባራቸዉ መመለሳቸዉንም ተናግረዋል፡፡
የሲዳማ ህዝበ ዉሳኔ በሀገሪቱ ለታየዉ የዴሞክራሲ ሂደት ማሳያ ተደርጎ ሊወሰድ የሚችል መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ “ውጤቱ ምንም ይሁን ምን ቀድሞ የነበረውን አንድነታችንን በማጠናከር ከድህነት ለመዉጣት መተባበር ይኖርብናል” ብለዋል ምክትል ከንቲባው፡፡
(EBC)
ትክክለኛው መረጃ የፋና ብሮድካስቲንግ እና የEBC ነው!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

#WALTA
ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽ ኮርፖሬት ከትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካዔል ጋር በተያያዘ በተለቀቀው ሀሰተኛ መረጃ ከጉዳዩ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አላቸው ብሎ የጠረጠራቸው አራት የተቋሙ ሰራተኞችን ከስራ አግዷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Walta
በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የወንጀል ምርምራ ቢሮ የተደራጁና ልዩ ልዩ ወንጀሎች ምርምራ ዳይሬክተር የሆኑት ኮማንደር አበራ ቡሊና ዛሬ ከተናገሩት የተወሰደ፦
- በወንጀሉ የሚያስጠረጥር መረጃ የተገኘባቸው ሰባት የተቋሙ ሰራተኞች ላይ ምርምራ ተጀምሯል።
- ምርምራ የሚደረግባቸው የዋልታ ቴሌቪዥንን የፌስቡክ ገጽ የይለፍ ቃል የሚጠቀሙ፤ ከድርጊቱ ጋር ቅርበት ያላቸው ናቸው። ከእነዚህ ተጠርጣሪዎች እውቅና ውጭ ድርጊቱ ሊፈፀም የማይችል መሆኑንና ግለሰቦቹ ሃላፊነት ቦታ ላይ ያሉ መሆናቸው በድርጊቱ ያስጠረጥራቸዋል። የምርምራ ሂደቱ ተጀመረ እንጂ አላለቀም፤ ምርምራው ውስብስብ በመሆኑ በቀጣይ በጥልቀት ማየትን ይጠይቃል።
- አንድ ተጠርጣሪ በስሙ የይለፍ ቃል በመጠቀም መረጃው የተላለፈ መሆኑ በምርምራ ተረጋግጧል፤ ነገር ግን መረጃውን እርሱ ይልቀቀው ወይስ ሌሎች የይለፍ ቃል ያላቸው ወይም በሌላ በሳይበር ተጠልፎ የተለቀቀ የሚለው በዝርዝር የሚታይ ነው።
- በድርጊቱ የተጠረጠሩት አካላት ተቋሙ ከሰጠው ጥቆማ በተጨማሪ ለድርጊቱ ቅርበት ያላቸውና ተጠርጣሪ ሊያስብላቸው የሚያስችል መረጃ የተገኘባቸው ናቸው።
- በእስካሁኑ ምርምራ ማን ምን ሲያደርግ እንደነበረ የሚያመላክቱ ቴክኒካዊ የሆኑ መረጃዎች ተገኝተዋል። በቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሳይበር ወንጀልና ሌሎች ውጫዊ ጉዳዮች መኖር ስለአለመኖራቸው ለማጣራት ምርምራው ይቀጥላል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#Walta💻
ከ864 ሺህ በላይ ተከታይ ያለው የዋልታ የፌስቡክ ገፅ መጠለፉን ለመመልከት ተችሏል።
የፌስቡክ ገፁ በክሪፕቶ ከረንሲ ጠላፊዎች እጅ እንደገባ የሚፃፉት ኮዶች እንደሚያመላክቱ የዘርፉን ባለሞያ ዋቢ አድርጎ ኢትዮጵያ ቼክ አስነብቧል።
የአክስዮን እና ክሪፕቶ ከረንሲ የሚገበያይ ነጋዴ የሆነው አብነት ተፈራ፥ " እየጠየቁ ያሉት የክሪፕቶ ከረንሲ ቲተር (Tether) ነው። ቴተር ማለት ወደ አሜሪካ ዶላር የሚመነዘር እና የሚተመን መጠን ያለው ሲሆን ስሌቱም 1 $. 5000 USDT = 5000$ ነው። " ብሏል።
አክሎም " በስተመጨረሻ የሚታየው ረጅም ቁጥር ደግሞ ኤተሪየም ዋሌት (Ethereum wallet) አድራሻ ነው፣ በህግ አስከባሪዎች እንዳይታወቁ ደግሞ አድራሻውን እየቁያየሩት ይገኛል" ሲል ለ ኢትዮጵያ ቼክ አስረድቷል።
ገፁን በቁጥጥር ስር ያዋሉት ጠላፊዎች የገፁን አድራሻ የቀየሩት ሲሆን የተለያዩ መልዕክቶችንም እያስተላለፉ ይገኛሉ። የገፁ ፕሮፋይል ፒክቸርም ተነስቷል።
ዋልታ ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ኮርፖሬት በበኩሉ ሕጋዊ የፌስቡክ ገጹ የቴክኒክ ችግር እንደገጠመው ገልጿል።
ድርጅቱ በፌስቡክ ገፁ ላይ የገጠመውን የቴክኒክ ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መሆኑን በመግለፅ ችግሩ መፈታቱን አስከሚያስታውቅ ድረስ በፌስቡክ ገፁ የሚለጠፉ ማናቸውም መልዕክቶች ከተቋሙ ዕውቅና ውጭ መሆናቸውን አሳውቋል።
@tikvahethiopia