#TakelUma "የኃይማኖት ተቋማት (ቤተክርስቲያን እና መስጅድ) ማቃጠልም ሆነ ማፍረስ የሞራል ውድቀት እና ኃላፊነት የጎደለው ተግባር ነው። በየትኛውም ሚዛን አግባብነትም ተቀባይነትም የለውም። የሚኮነን ድርጊት ነው።" - ኢ/ር ታከለ ኡማ (የአ/አ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈጸመው ጥቃት በአገሪቱ የሃይማኖት ግጭት ለመፍጠር የታሰበ ሴራ ነው" - የሃይማኖት ተቋማቱ
በአማራ ክልል በሞጣ አካባቢ በሃይማኖት ተቋማት ላይ የተፈጸመው ጥቃት ሙስሊሙንና ክርስቲያኑን ማህበረሰብ ለማጋጨት የተቀነባበረ ሴራ መሆኑ ታውቆ አጥፊዎች ለህግ እንዲቀርቡ የሃይማኖት ተቋማቱ ጥሪ አቀረቡ።
በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማ ምክር ቤት ዋና ፀሃፊ ሼክ ቃሲም ሙሃመድ ታጁዲን እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የብፁዕ ወቅዱስ ፓትሪያርክ ልዩ ፅህፈት ቤትና የውጭ ጉዳይ የበላይ ሃላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ዶክተር አቡነ አረጋዊ እንዳሉት በሞጣ የተፈፀመው ተግባር ማንንም የማይወክል፣ ከኢትዮጵያዊያን መልካም እሴቶች ያፈነገጠ እኩይ ዓላማ ያላቸው አካላት ሴራ ነው።
በኢትዮጵያ ሙስሊሙና የክርስቲያኑ ማህበረሰብ ለዘመናት አብሮ የኖረና በዝምድናና በደም የተሳሰረ ጭምር መሆኑን የሚናገሩት አባቶቹ ሞጣ ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት ግን በሃይማኖት ስም ህዝብን ከህዝብ በማጋጨት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚጥሩ አካላት ድርጊት በመሆኑ ሁሉም ሊያወግዘው ይገባል ሲሉም ገልፀዋል።
https://telegra.ph/ETH-12-21-3
(ENA)

በወቅታዊ ሁኔታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መግለጫ፦
በመላው ዓለም የምትገኙ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን!
በደረሰው ወቅታዊ እና ያልታሰበ ጉዳት በሐዘን ላይ የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናንና ምዕመናት: የኢትዮጵያ እስልምና ጠቅላይ ምክር ቤት እና የመጅሊስ አባላት የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች ወገኖቻችን፦
በአማራ ክልል በምሥራቅ ጎጃም ዞን በሞጣ ወረዳ በቤተ እምነቶች ላይ የቃጠሎ ጉዳት መድረሱን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች ሰምተናል። በጉዳቱም የተሰማንን ልባዊ ሐዘን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስም እንገልጻለን።
የተፈጸመው ድርጊት የሀገራችን ሰላም እና እድገት የማይጠቅም ለዘመናት የቆየ አብሮነት የመኖር ዕሴቶቻችን የሚንድ መሆኑን መላው ሕዝባችን ተረድቶ በተረጋጋ እና በሰከነ መንፈስ ጉዳዩ እስከሚጣራ በትእግስት እንድትጠባበቁ እናሳስባለን። ከዚሁም ጋር የሚመለከታችሁ የመንግሥት አካላት ለጉዳዩ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት አስፈላጊው ክትትል እንድታደርጉ እናሳስባለን።
ይኽንኑ ድርጊት አስመልክቶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሚመለከተው የመንግሥት የአስተዳደር : የሕግ እና የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን አጣርተን ይፋ የምናደርግ መሆኑን በአጽንዖት እንገልጻለን።
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን እና ሕዝቦቿን ይባርክ!!

አስቸኳይ መግለጫ!
በሙስሊም እምነት ተቋማት እና አማኞች ላይ እየደረሰ ያለውን ጥቃት አስመልክቶ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የወጣ መግለጫ፦

#AbiyAhemedAli
"በብልጽግና ጎዳና ላይ በምትገኘው ኢትዮጵያ የሀገራችንን የቆየ የሃይማኖቶችን የመቻቻልና አብሮ የመኖር ባህል የሚፃረሩ ጽንፈኛ አካሄዶች ቦታ የላቸውም። እንዲህ ያሉ የፈሪ አካሄዶችን አጥብቄ አወግዛለሁ። መላው ሰላም ወዳድ ኢትዮጵያውያንም የመከባበርና አብሮ የመኖር ጥልቅ ዕውቀታችሁን እንድታጋሩ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ከፋፋይ አጀንዳዎችን መረዳትና መጠየፍ የጋራ ዕድገታችንን ለማረጋገጥ ያስችላል።" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
@tikbahethiopiaBot @tikvahethiopia

#FDRE_Defense_Force
ሴት የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተልዕኮ የመፈፀም አቅማቸዉ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ!
ሴት የሰራዊት አባላቱ የተልዕኮ አፈፃፀም ብቃታቸዉ ከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝና አቅማቸዉ ይበልጥ ለማሳደግ ታከታይነት የለው የትምሕርትና ሥልጠና ተግባር በማከናወኑ ሁለንትናዊ ዝግጁነቱን የተሞላ እንዳደረገለት በ7ኛ ወጋገን ሜካናይዝድ ክፍለ ጦር የ2 ሞተራይዝድ ብርጌድ አዛዥ ኮሎኔል መካሽ ጀበሬ ገለጹ፡፡
በመከላከያ ሠራዊቱ ዉስጥ የሴቶች ተሳትፎ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደ ተቋም በከፍተኝ ትኩረት እየተሰራበት መሆኑን የጠቆሙት አዛዡ በብርጌዱ ዉስጥ የሚገኝ ሴት የሰራዊት አባላት እልሕና ወኔ በእጆጉ የሚያኮራ መሆኑን ተናግረዋል። በህክምና በመገናኛና ኢንፎርሜሽን እንዲሁም በበርካታ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሆነዉ አኩሪ ዉጤት ያስመዘገቡ አባላት መኖራቸዉናን በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡

በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የተሰጠ መግለጫ፦
- የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቻይና ሻንሲ ግዛት ልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኢንቨስትመንት፣ ትምህርት፣ መአድን ልማት እና የሁለትየሽ ግንኝነት ዙርያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት ለማድረግ እየመጣ መሆኑን በግልፅ ደብዳቤ ለክልሉ መንግስት መፃፉ ይታወቃል፡፡ ሆኖም የትግራይ ክልል መንግስት እንግዶቹን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ በመጠበቅ ላይ እያለ ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ጉዞኣቸው እነዲስተጓጎል እና እንዳይመጡ ተደርጓል፡፡
በመሆኑም የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የቻይና ሻንሲ ግዛት ልኡካን ቡድን ወደ ትግራይ እንዳይመጡ መከልከላቸው አግባብነት የሌለው መሆኑ በመግለፅ፤ ይህ ተግባር በትግራይ ክልል ውስጥ የሚደረጉትን የኢንቨስትመንትና ተዛማጅ የልማት እንቅስቃሴዎች በይፋ የሚገታና የህዝብ ለህዝብ መልካም ግንኙነት እንዳይጠናከር የማድረግ ተግባር የተፈፀመበትን ምክንያት በወቅቱ በቂ ማብራርያ እንዲሰጥበት የጠየቅን ቢሆንም እስካሁን በይፋ የተሰጠ ማብራርያ ባለመኖሩ በድጋሚ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጠው ይጠይቃል፡፡
የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ
መቐለ፡ ታህሳስ11 2012 ዓ/ም

ህዝቡ የተቃጠሉ ቤተ-እምነቶችን መልሶ በጋራ በመገንባት የቆየውን አብሮነት ለማጎልበት እንዲሰራ ጥሪ ቀረበ!
መላው ህዝብ በአማራ ክልል ሞጣ ከተማ የተቃጠሉ ቤተ-እምነቶችን መልሶ በጋራ በመገንባት የቆየውን አብሮ የመኖር እሴት የበለጠ ለማጎልበት እንዲሰራ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጥሪ አቀረበ።
የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሞጣ ከተማ ቤተ እምነቶች ላይ የደረሰውን ቃጠሎ በማስመልከት ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል።
በኢትዮጵያውያን መካከል ለዘመናት የኖረው ተባብሮና ተፈቃቅሮ የመኖር እሴት እንዲናድ፣ ግጭትና ጥላቻ እንዲፈጠር ለማድረግ ቤተ እምነቶችን በማቃጠል የሃማኖት ግጭት ለመፍጠር በሚንቀሳቀሱ አላካት ላይ መንግስት አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድም ጉባኤው ጠይቋል።
https://telegra.ph/ETH-12-21-4

"እምነት ያለው ሰው አዛኝ፣ አሳቢ፤ ለሌሎች የሚጨነቅ ነው። ይሁን እንጂ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ እምነት ተቋማት፣ አማኒያንና ንብረታቸው ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ከሃይማኖታዊ አስተሳሰብም ሆነ ከሰብዓዊነት የወጣ እኩይ ተግባር ነው፤ በመሆኑም መላው ኢትዮጵያዊያን ተከባብሮና ተቻችሎ በመኖር ካዳበርነው እሴቶቻችን በተቃራኒ የሚፈጸሙ ተግባራት በምድር ወንጀል፤ በሰማይ ቤት ደግሞ ሃጥያት መሆናቸውን በመገንዘብ ይገቱ ዘንድ መስራት አለብን። በአሁኑ ወቅት የእምነት አባቶች የሚናገሩት ሰሚ እያጣ ነው፤ ወጣቶች ለአባቶቻቸው ክብር መስጠትና ምክራቸውን መስማት አለባቸው። መንግስትም ከህዝቡ ጋር በመተባበር በዚህ የጥፋት ተግባር በተሰማሩ አካላት ላይ እርምጃ ሊወስድ ይገባል።" - ሼህ መሀመድ ሲራጅ (የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስራ አስፈፃሚ ቦርድ አባል)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Semera
የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በዛሬው ዕለት በአገር አቀፍ ደረጃ የሚከበረውን የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ቀን ለማክበር ሰመራ ከተማ ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቷ ከክልሉ አመራሮች፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ ከአገር ሽማግሌዎችና ከፌዴራል ባለድርሻ አካላት ጋር እንደሚመክሩም ይጠበቃል።
በከተማው በሚኖራቸው ቆይታ በሰመራ ዩኒቨርስቲ ከሴት ተማሪዎችና አመራሮች ተሳትፎና ከስርዓተ-ጾታ ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩም ተመልክቷል። ከዚህ ጎን ለጎን የዱብቲ ሪፈራል ሆስፒታልን የሥራ እንቅስቃሴ ይጎበኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በተጨማሪም በሰመራ ዩኒቨርስቲና በተመረጡ የከተማው አካባቢዎች ችግኝ ይተክላሉ ተብሎም ይጠበቃል። ፕሬዝዳንቷ ብሔራዊ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ምክር ቤት ሰብሳቢ መሆናቸው ይታወቃል።
ምንጭ፡- ኢዜአ

የሸገር ዳቦ ፋብሪካ የሲቪል ስራው ተጠናቀቀ!
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት እና ሌሎች ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ከ6 ወራት በፊት ግንባታው የተጀመረውን በሰዓት 80 ሺህ ዳቦ የሚያመርተው የዳቦ ፋብሪካ ግንባታ ያለበትን ደረጃ በቦታው በመገኘት ተመልክተዋል፡፡
በከተማዋ ያለውን የዳቦ አቅርቦት ከፍ የሚያደርገውና የዋጋ ንረቱንም በተጨባጭ መልኩ እንደሚያረጋጋ የሚጠበቀው ይህ ግዙፍ የዳቦ ፋብሪካ በአሁኑ ወቅት የሲቪል ስራው ሙሉ በሙሉ መጠናቀቁ በጉብኝቱ ወቅት ተጠቅሷል፡፡
በሀገራችን በዓይነቱ የመጀመርያ የሆነው ይህ የዱቄትና የዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የማሽን ተከላው በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ እና በሁለት ወራት ጊዜ ውስጥ ወደ ምርት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
(Mayor Office of AA)

አንድ ፓድ ለእህቴ!
የወሎ ዩኒቨርስቲ ሴቶች ክበብ አባላት ለሶስት ቀን የሚቆይ "አንድ ፓድ ለእህቴ" የሞዴስ ማሰባሰብ ስራ እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡ ሞዴሱ ተሰብስቦ የሚሠጠው ለሴት ታራሚዎች እና ግቢ ውስጥ ላሉ የተቸገሩ ሴት ተማሪዎች እንደሆነ ነው የተገለፀልን፡፡
አንድ ፓድ ለእህቴ!
- በዚህ መልካም ስራ ላይ እየተሳተፋችሁ ለምትገኙ ወጣቶች በሙሉ በቲክቫህ ኢትዮጵየ ስም ያለንን ትልቅ አክብሮት ለመግለፅ እንወዳለን!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia

በሞጣ ከተማ 15 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በሞጣ ከተማ በተፈጠረው የእምነት ተቋማት ቃጠሎና የንብረት መውደም እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 15 ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። እስካሁን ከተያዙት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ሞጣ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷ እየተነገረ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሞጣ ከተማ በተፈጠረው የእምነት ተቋማት ቃጠሎና የንብረት መውደም እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 15 ግለሰቦችን ፖሊስ በቁጥጥር ስር መዋሉን ገልጿል። እስካሁን ከተያዙት ተጠርጣሪዎች በተጨማሪ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ለማዋል እየሰራ መሆኑን ፖሊስ ገልጿል። ሞጣ ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ መመለሷ እየተነገረ ነው።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መረጃ ስለ ኤክሳይዝ ታክስ!
ኤክሳይዝ ታክስ /excise tax/ የቅንጦት ዕቃዎች ሆነው ዋጋቸው ጨመረም አልጨመረ መሠረታዊ በመሆናቸው ምክንያት የገበያ ተፈላጊነታቸው በማይቀንስ ዕቃዎች ላይ እንዲሁም የኅብረተሰቡን ጤና የሚጎዱ እና ማህበራዊ ችግሮችን የሚያስከትሉ ዕቃዎችን አጠቃቀም ለመቀነስ ሲባል የሚጣል ነው፡፡
https://telegra.ph/ETH-12-22
#MinistryofRevenuesofEthiopia

የኤክሳይዝ ታክስ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው!
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት ቀርቦ ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የኤክሳዝ ታክስ ማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ እያወዛገበ ነው። አዋጁ በመሠረታዊ የፍጆታ ዕቃዎች ላይ ሳይቀር ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚያሳድርና የአምራች ኩባንያዎችን ህልውና የሚፈታተን ነው ተብሏል፡፡
በአሁኑ ወቅት በሥራ ላይ የሚገኘው የኤክሳይዝ ታክስ አዋጅ 307/1995 ያሉበትን ክፍተቶች ለማሟላትና ለመንግሥትም ከፍተኛ ገቢ ለማስገኘት ያስችላል ተብሎ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውይይት የቀረበውና ለገቢዎች በጀትና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች የተመራው የማሻሻያ ረቂቅ አዋጅ፤ በአገር ውስጥ በሚመረቱና ከውጪ አገር በሚገቡ የተለያዩ ምርቶች ላይ ተጨማሪ ታክስ የሚጥል ነው፡፡
በማሻሻያ ረቂቅ አዋጁ የቅንጦት ዕቃዎች ተብለው የተለዩትና ተጨማሪ የኤክሳይዝ ታክስ ከተጣለባቸው ምርቶች መካከል ዘይት፣ ስኳር፣ ጨው፣ ጣፋጭና ጨዋማ ምግቦች የአልኮል መጠጦች፣ የትምባሆ ምርቶች፣ የተሰፉ ልብሶች፣ የታሸጉና ጋዝ ያላቸው ውሃዎችን የለስላሳ መጠጦች፣ ይገኙበታል፡፡
https://telegra.ph/ETH-12-22-2
#AddisAdmas