TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የቅዱስ ሲኖዶስ የሰላም ጥሪና ፀሎተ ምህላ አዋጅ!

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ለኢትዮጵያዊያን የሰላም ጥሪ አቀረበ። ቅዱስ ሲኖዶስ በጥቅምት 13 ቀን 2012 አስቸኳይ መገለጫው ኢትዮጵያዊያን የአገራቸው ሰላም እንዲያስጠብቁ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ሲኖዶሱ ከጥቅምት 13 ጀምሮ ለ3 ቀናት የጾምና ጸሎት ምህላን አውጇል፡፡ በዚህም መላው ኢትዮጵያዊያዊያን እንደየእምነታቸው ስለ አገራቸው ሰላም በጾም፣ በጸሎትና በሀዘን በአንድ ልብ ሆነው ጥሪያቸውን ለፈጣሪ እንዲያቀርቡ ጠይቋል፡፡

Via AHDU RADIO
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

በድሬዳዋ ከተማ ያለው ሁኔታ መልኩን እየቀየረ እንደመጣ የድሬዳዌ ቲክቫህ ቤተሰቦች ገልፀዋል። መንግስት ሁኔታዎች ወደከፋ ደረጃ ሳይደርሱ መፍትሄ እንዲፈልግ ጥሩ ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethioia
#attention

"አዳማ ላይ አሁን ችግር አለ፤ ይህ 11 ቀበሌ ያለ መንገድ ነው። ሌሎች አከባቢ ላይም ተመሳሳይ የመሣሪያ ትኩስ እና መንገድ መዝጋት አለ። ሰው እንቅስቃሴ ከማድረግ በፊት ጥጥንቃቄ ያድርጉ።" ኢብሮ/ቲክቫህ ቤተሰብ አዳማ/

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention | ወለቴ አካባቢ ያለው አለመረጋጋት በዛሬው ዕለትም ቀጥሏል። ሁኔታዎች ወደከፋ ደረጃ እንዳይደርሱ አስገላጊው ትኩረት ሊሰጥ እንደሚገባ የወለቴ ቲክቫህ ቤተሰቦች አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NewsAlert

ግብፅ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ልዩነት በውይይት ለመፍታት ተስማማች!

ግብፅና ኢትዮጵያ በህዳሴው ግድብ ዙሪያ ያላቸውን ልዩነት በንግግር ለመፍታት መስማማታቸውን ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚነስትርና የግብፁ ፕሬዝዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ በሩሲያ ሶቹ ከተማ ተገናኝተው ውይይት አድርገዋል፡፡

ግብፅ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ደረጃዎች ኢትዮጵያና ሱዳን ያሉበትን በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲደረግ የነበረውን ድርድር ማቋረጧን ተከትሎ ኢትዮጵያም ከንግግር ውጭ የውስጥ ጥቅሜን አሳልፌ አልሰጥም ማለቷ ይታወቃል፡፡ ግብፅም በአደራዳሪነት ሶስተኛ ወገን እንነጋገር የሚለውን ሀሳብ በኢትዮጵያም በኩል ተቀባይነት ሳያገኝ ቀርቷል፡፡

ሁለቱ መሪዎች ታዲያ ከሩሲያ- አፍሪካው የጋራ የኢኮኖሚ ፎረም የጎንዮሽ መድረክ ላይ ዛሬ ረፋድ ባደረጉት ውይይት ግብፅ ወደ ቀድሞው የድርድር መድረክ እንደምትመለስ ፕሬዝዳንት ሲሲ እንዳረጋገጡላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለኢቲቪ ተናግረዋል፡፡ የአገራቱን ግንኙነት እያሻከረ ያለው የግብፅ ሚዲያዎች ዘገባ በመሆኑ ሁለቱ መሪዎች በጉዳዩ ላይም መክረውበታል፡፡

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ላይ ከዚህ ቀደም የነበረው የሶስቱ አገራት ቴክኒካል ኮሚቴ መድረክም ተጠናክሮ እንዲቀጥልና ፖለቲካዊ መፍትሄ የሚያሻቸው ጉዳዮችን ደግሞ በፖለቲካዊ ውይይት ለመፍታት ከስምምነት መድረሳቸውን መሪዎቹ ተናግረዋል፡፡ ሁለቱ አገራት የአባይን ወንዝ በፍትሃዊነትና በአስተማማኝ ሁኔታ ለመጠቀም የአካባቢ ጥበቃ ስራዎችን አጠናክሮ ለመስራትም ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

Via EBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት እየቀዘቀዘ መምጣቱ ተነገረ!

ከሃያ አመታት በኋላ ወደ ወዳጅነት ተመልሶ የነበረው የኢትዮጵያና ኤርትራ ግንኙነት ከአራት ወራት በላይ ሳይዘልቅ እየተቀዛቀዘ መምጣቱን ምሁራን ተናገሩ፡፡ ዛሬ በአዘማን ሆቴል “ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ” ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ጥናታቸውን ካቀረቡት ምሁራን አንዱ የሆኑት አምባሳደር ህሩይ አማኑኤል የቅርብና አስቸጋሪ የሆነው የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት ከአራት ወራት በላይ መጀመሪያ በነበረው ስሜት መቀጠል አልቻለም ብለዋል፡፡

ይህ እንዲሆን ካደረጉ ምክንያቶች ውስጥ የኢጋድ ጉባኤ ላይ አለመሳተፏ፣ የቀይ ባህር ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ሚና አለመለየቱ፣ የድንበር አከፋፈት ላይ ስምምነት አለመኖሩና በሱዳን ጉዳይ ላይ ተመሳሳይ አቋም አለመያዝ የሚጠቀሱ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡

https://telegra.ph/ETH-10-24-2

Via Sheger FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Attention

በባሌ ሮቤ ከተማ ያለው ሁኔታ አሳሳቢ በመሆኑ ትኩረት እንዲሰጠው በከተማው የሚኖሩ የቲክቫህ ቤተሰቦች ጠቁመዋል። በሌላ በኩል በነጌሌ አርሲ ያለው ሁኔታ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ በከተማይቱ የሚገኙ የቤተሰባችን አባላት አሳስበዋል።

ዛሬ በበርካታ አካባቢዎች መንገዶች እንደተዘጉ ነው!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Attention

በባሌ ጎባ ውጥረት አለ፤ የንግድ እንቅስቃሴ ተቋርጧል መንገድም እንደተዘጋ ነው። የአዲስ አበባ ባስ ሳይወጣ ሁለት ቀን ቀርቷል። ተማሪ ወደ ተመደበበት ሀገር ሊሄድ አልቻለም። ነገሮች እየተባባሱ ወደ ከረረ ነገር እየሄደ ነው ስለሆነ መንግስት ልዩ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ልዩ ትኩረት ትፈልጋለች፤ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሁኔታዎችን ለመቆጣጣር ጥረት እያደረገ ይገኛል። በአንዳንድ አካባቢዎች ያለው አለመረጋጋት ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዳይሰፋ ወጣቱ ለሰላም ቅድሚያ እንዲሰጥ የድሬ ቲክቫህ ቤተሰቦች ተማፅነዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#AMBO

በአምቦ ከተማ ዛሬም አለመራጋጋት ተስተውሏል፤ መንገዶች ተዘጋግተዋል። የሀገር ሽማግሌዎች ወጣቶችን ለማረጋጋት እና ሰላም ለማስፈን ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛል። የከተማው መውጫና መግቢያ እንደተዘጋ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

#ሱሉልታ ከተማ ዛሬም አለመረጋጋት ይታያል። መንገዶች ተዘግተዋል። በየአስፓልቱ የሚቃጠል ጎማዎችም ይታያሉ። መንግስት ለከተማይቱ ትኩረት እንዲሰጥ የቲክቫህ ሱሉልታ ቤተሰቦች አሳስበዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Bishoftu

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በከተማይቱ ከትላንት ጀምሮ የተፈጠረውን አለመረጋጋት ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል። በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት በቢሾፍቱ ከተማ የሰው ህይወት ላይ ጉዳት ደርሷል። ዝርዝር መረጃዎችን ስናገኝ የምን ቅርብ ይሆናል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ #የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ኃይለማርያም በስልጣን ዘመናቸው የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናገሩ!

የቀድሞው የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በዶይቼ ቬለ (DW) ቴሌቪዥን ጣቢያ ከሚተላለፈው “ኮንፍሊክት ዞን” ከተባለ ፕሮግራም ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ “አምባገነን ተብዬ ልጠራ አይገባኝም” አሉ።የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር በእርሳቸው የስልጣን ዘመን ስለተፈጸሙ ግድያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እና የሙስና ወንጀሎች ተጠይቀው ምላሽ ሰጥተዋል።

እነዚህን ጉዳዮች በተመለከተ የደህንነት ባለስልጣኖቻቸው በወቅቱ በቂ መረጃ ይሰጧቸው እንዳልነበር ተናግረዋል።
በኢትዮጵያ አሁን ያለው ለውጥ እንዲመጣ የራሴን ድርሻ ተወጥቻለሁ” ያሉት የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር፤ “እኔን አምባገነን አድርጎ መሳል ትክክል አይደለም” ብለዋል።

Via DW/ኢፕድ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል በምትገኘው የባሌ ሮቤ ከተማ ለጀዋር መሐመድ ድጋፍ ከተደረገ ሰልፍ በኋላ በተቀሰቀሰ ግጭት ቁጥራቸው በወል ያልታወቀ ሰዎች መሞታቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። የባሌ ሮቤ ነዋሪዎች የሐይማኖት መልክ ይዟል ባሉት ግጭት ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች እና ሻይ ቤቶች መቃጠላቸውን የዐይን እማኞች ለጀርመን ራድዮ ተናግረዋል።

የጀርመን ሬድዮ ያነጋገራቸው ሶስት የከተማዋ ነዋሪዎች ከትናንት አመሻሽ ጀምሮ ባሌ ሮቤን ከሌሎች አካባቢዎች የሚያገናኙ መንገዶች፣ የግብይት መደብሮች፣ የመንግሥት እና ማኅበራዊ ተቋማት መዘጋታቸውን አስረድተዋል። ጀዋር መሐመድ በማኅበራዊ ድረ-ገፆች ካሰራጨው መልዕክት በኋላ ትናንት ጠዋት በአብዛኛው ወጣቶች የተሳተፉበት ሰልፍ መካሔዱን የገለጹት ነዋሪዎች በሒደት መልኩን እየቀየረ ወደ ግጭት እና ጥቃት መቀየሩን ተናግረዋል።

https://telegra.ph/ETH-10-24-3

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SHASHEMENE

በሻሸመኔ ከተማ ተዘግተው የነበሩ መንገዶች በመክፈት ላይ ይገኛሉ። የትራንስፖርት እንቅስቃሴም አልፎ አልፎ ይታያል። ንግድ ቤቶችም መከፈት ጀምረዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከትላንት ጀምሮ ተዘግተው የነበሩት የሻሸመኔ መንገዶች እየተከፈቱ ነው። ተሽከርካሪዎችም እየተንቀሳቀሱ ይገኛል። የወትሮዋና ደማቋ ሻሸመኔ ባትመስልም ነገሮች እየተረጋጉ እና እየረገቡ ነው።

ከየከተሞቹ ያሉ ሁኔታዎችን ቤተሰቦቻችን ማሳወቅ ትችላላችሁ፤ እንደሁል ጊዜው በፎቶ ማስደገፍ እንዳትረሱ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ሻሸመኔ | የትራንስፖርት እንቅስቃሴው ተጀምሯል። መንገድ ላይ የነበሩ ድንጋዮችም እየተነሱ ነው። የንግድ ሰዎችም ወደ ስራቸው እንዲመለሱ መልዕክት እየተላለፈላቸው ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አወዳይ ከተማ መንገድ እየተከፈተ ይገኛል። በየአስፓልቱ የተጣሉ ድንጋዮችም እየተነሱ ይገኛሉ። አስፓልቱ በከተማው ነዋሪዎች እየፀዳ ነው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሱሉልታ ከተማ ላይ ተዘግቶ የነበረው መንገድ አሁን ክፍት ሆኗል። ተሽከርካሪዎችም እየተንቀሳቀሱ ይገኛሉ። #ETH

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#SEBETA የሰበታ ከተማ ነዋሪ ቲክቫህ ቤተሰቦች የሰበታን እንቅስቃሴ አሳውቀውናል፤ መንገዶች ተከፍተዋል። የትራንስፖርት እንቅስቃሴም እየተጀመረ እንደሆነ ገልፀዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia