TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
61.8K photos
1.56K videos
216 files
4.28K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ትናንት ምሽት በአክቲቪስት ጃዋር መሃመድ ላይ የተፈጸመው ተግባር ተቀባይነት የሌለውና ስህተት ነው" – አቶ ሽመልስ

የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ም/ፕሬዝዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በአክቲቪስት ጀዋር መሐመድ ላይ የተከሰተውን ጉዳይ አስመልክቶ ከሰጡት መግለጫ የተወሰዱ አንኳር ነጥቦች:-

• ትናንት ማታ የተፈጸመው ድርጊት ስህተት ነው፤ ስህተቱን ማን እንደፈጸመው፣ ለምን ጉዳዩን ምሽት ላይ ማድረግ እንደተፈለገ አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል፡፡

• ዛሬ ለሞቱት ወገኖች በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ስም የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል፡፡

• ዛሬ በተደረገው ሰልፍ ላይ ኦሮሚያን የግጭት አውድማ ለማድረግ የሚፈልጉ ኃይሎች ሰልፉ ላይ አስነዋሪ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡

• እነዚህ ኃይሎች ጉዳዩ የሃይማኖትና የብሔር መልክ እንዲይዝ ጥረት እያደረጉ ነው፡፡

• የተለያዩ አካላት ለውጡ ዘላቂነት እንዳይኖረው የተለያዩ ሙከራዎች ሲያደርጉ ነበር፡፡

• ዛሬ የተፈጸመው መሆን የሌለበት ነገር ነው፡፡

• መንግስት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችን ለመከላከል ነው ለወንድማችን ጀዋርና ለሌሎች ከውጭ ለገቡ ሰዎች ጥበቃ የሚያደርገው፡፡

👉https://telegra.ph/ETH-10-23-7

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

ዛሬ ነውጥ ካስተናገዱ ከተሞች አንዷ አዳማ ስትሆን የ2 ሰው ህይወት አልፏል። በንብረት ላይም ጉዳት የደረሰ ሲሆን፣ ንብረትነቱ የAfrica PLC. የሆነ የምግብ ነክ ምርቶች ፋብሪካ ጉዳት ደርሶበታል። የብራዘርስ ብስኩት ፋብሪካም ጉዳት ደርሶበታል።

Via ELU
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#BATI

ከአማራ ክልል በባቲ ወረዳ የተሰባሰቡ 92 ታዳጊ ህጻናትና ወጣቶችን በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር ለማስወጣት የሞከሩ ሁለት ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

በፌዴራል ፖሊስ የ3ኛ ሻምበል ዋና አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ሞገስ ከበደ እንደገለጹት ግለሰቦቹ የተያዙት በሕገ ወጥ መንገድ ሰዎቹን ጭነው ወደ መካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ለማሸጋገር ሲሞክሩ ነው።

በወንጀል የተጠረጠሩት ግለሰቦች ለማምለጥ ሙከራ ቢያደርጉም፤ ኅብረተሰቡ ባደረገው ትብብር ዋና አዘዋዋሪውና ረዳት አሽከርካሪው መያዛቸውን ተናግረዋል።

መንገደኞቹ የተሰባሰቡት ከሰሜንና ደቡብ ወሎ፣ ሰሜን ሸዋ፣ ዋግ ኸምራ ብሄረሰብና ኦሮሞ ብሄረሰብ ዞኖች መሆኑንም አስረድተዋል። ወጣቶቹ  ሲጓጓዙ የነበሩት የጅቡቲ ሰሌዳ  844 ዲ64 የጭነት መኪና እንደነበርም ዋና አዛዡ ገልጸዋል።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Activist #Jawar_Mohammed tells Al Jazeera English he is seriously considering running in May election.

Via Robyn Lee Kriel

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ጠቅላይ ሚንስትሩን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር፣ የደህንነት ኃይሎች በአጽንኦት የተናገሩት 'ብዙ ባላንጣዎች ስላለህ ጥቃት ቢሰነዘርብህ በሃገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል ስለዚህ የደህንነት ጥበቃ ሊኖርህ ይገባል' ነው የተባልኩት..." ጃዋር መሃመድ
.
.
ትናንት ሌሊት በአክቲቪስት ጃዋር መሐመድ መኖሪያ ቤት አጋጠመ የተባለውን ክስተት ተከትሎ በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች በተካሄዱ የተቃውሞ ሰልፎች በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት እንደደረሰ ተነግሯል።

ጀዋር ከቢቢሲ ጋር በነበረው ቆይታ ትናንት እኩለ ለሊት ላይ በመኖሪያ ቤቱ ተፈጽሟል ስላለው ጉዳይ እና ምልከታውን ለቢቢሲ አጋርቷል።

ጃዋር እኩለ ሊሊት ላይ የተፈጸመውን ሲያስረዳ "ተኝቼ ነበር፤ በፌደራል ፖሊስ ተመድበውልኝ የነበሩት ጠባቂዎች 'በአስቸኳይ መሳሪያችሁን ይዛችሁ ውጡ' ተባሉ። ይህ ከፍተኛ ድንጋጤን ፈጠረ" ይላል።

ድንጋጤ የፈጠረበትን ምክንያት ሲያስረዳ፤ "አንደኛ እኩለ ለሊት ነው። ሁለተኛው ደግሞ 'ጀዋር ሳይሰማ ውጡ' ነው የተባሉት። በዚያ ላይ የሚተኩ ጠባቂዎች የሉም" ይላል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-23-9

Via BBC

@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#BBC | "እኔን #ማሰረ ከተፈለገ በፈለጋቸው ጊዜ ቢጠሩኝ የምገኝላቸው ሰው ነኝ። 'ና ታሰር' ቢሉኝ እንኳ ክሱ አሳማኝ እስከሆነ ድረስ እምቢ የምልበት ምክያት የለም፤ በውድቅት ለሊት በጣም አጣራጣሪ በሆነ መልኩ የተሞከረው ምን እንደሆነ አልገባኝም። የእስርም አይመስለኝም። ከውስጥ እንደምሰማው ሰሞኑን የነበረን ክርክር እየጦፈ ስለመጣ ሴኪሪቲውን በማስነሳት እንዲፈራ እና እንዲሸማቀቅ እናደርጋለን' የሚል የውስጥ ንግግር እንደነበረ፤ ከዚያም በገፋ መልኩ በዱርዬዎች ቤቴ ላይ ጥቃት በማድረስ ለማሳበብ እንደታሰበ ነው ያሉኝ መረጃዎች የሚያሰዩት" አክቲቪስት ጃዋር መሃመድ

📹11 MB
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«በጸሎት ሁሉም ቢደግፍ ጥሩ ነው። ዋናው ግን የመንግሥት ሥራ ነው» ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል

የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል በወቅታዊ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ምክትል ርእሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ከኤርትራ ጋር በተያያዘ ባነሱት ነጥብ የክልሉ መንግስት የተጀመረው የሰላም ሂደት ምሉእ እንዲሆን እንደሚሻ ገልፀዋል፡፡ የትግራይ ክልል መንግስት «ተከበናል የሚል መንፈስ በህዝብ ዘንድ እየፈጠረ፣ ለጦርነት እየተዘጋጀ ነው የሚሉ ጉዳዮች ይነሱበታል» ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄም ዶክተር ደብረፅዮን ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡

📹3.3 MB

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጅማ እንዴት አመሸች?

ጅማ ከተማ በዛሬው ዕለት ከተካሄደ ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ቦታዎች ላይ የንግድ እንቅስቃሴ ለተወሰነ ሰዓት ቆሞ ነበር፤ የትራንስፖርት እንቅስቃሴም ተቋርጦ እንደነበር ቅድም ገልፀንላችኃል፤ አመሻሹን ግን ከተማዋ ወደ መረጋጋት በመመለሷ የትራንስፖርት አገልግሎት ጀምሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Wollega

ዛሬ በሁሉም የቄለም ወለጋ ዞን ወረዳዎች ትምህርት ቤቶችና ሌሎችም የመንግስት ተቋማትና የግል አገልግሎት ሰጪዎች መደበኛ ስራቸውን ሲያከናውኑ ነው የዋሉት። በምዕራብ ወለጋ ዞንም ዛሬ በተመሳሳይ ያጋጠመ ችግር አልነበረም ሰላም ነው የዋለው። በምስራቅና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞኖችም እንዲሁ ዛሬ ሰላም ነው የዋለው።

Via ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FICHE | በዛሬው ዕለት በፍቼ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ መካሄዱን ተከትሎ የንግድ ሱቆች፣ መንገድና የመንግስት መስሪያ ቤቶች አገልግሎታቸውን ለተወሰኑ ሰዓታት አቋርጠው ነበር። በሂደቱም በሰውና ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ አዛዥ ከማንደር ካሳዬ ነጋሽ ገልጸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በገብረ ጉረቻ አለልቱና ሃቢሶ ከተሞች ዛሬ ዕለት የተቃውሞ ሰልፎች ተካሂደዋል። ሰልፎቹ በሰላም መጠናቀቃቸው እንዲሁም በአሁኑ ወቅት የከተሞቹ እንቅስቃሴ ወደ ቀድሞ መረጋጋት መመለሱን ለመስማት ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
•ሁለት ሰው ሞቷል
•ከ50 በላይ ሰዎች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል


በአዳማ ከተማ ዛሬ በተከሰተው የፀጥታ ችግር የ2 ሰዎች ህይወት ማለፉንና በ50 ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት መድረሱን ፖሊስ አስታውቋል። የአዳማ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር ደረጀ ሙለታ ለኢዜአ እንዳሉት በከተማዋ ዛሬ ጠዋት ላይ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ ከተለያዩ አቅጣጫዎች የተሽከርካሪ መተላለፊያ መንገድ ሲዘጋ ነበር።

በዚህም ተሳትፎ የነበራቸው ግለሰቦች ድንጋይ መወርወር፣ ንብረት ላይ ጉዳት ማድረስና የተለያዩ የንግድ ተቋማትን የመዝጋት ችግር እንደፈጠሩ ተናግረዋል። የከተማው ፖሊስ አባላት የሰው ህይወት እንዳይጠፋና ንብረት እንዳይወድም ለመከላከል ጥረት ማድረጋቸውን አስረድተዋል።

ሆኖም ከተከሰተው የጸጥታ ችግር ተያይዞ በተፈጠረው ግርግር የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉን ኮማንደሩ አስታውቀዋል። 50 ሰዎች ደግሞ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአዳማ ሪፈራል ሆስፒታልና ሜዲካል ኮሌጅ የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን አመልከተዋል።

“በአሁኑ ወቅት ከተማዋን የፀጥታው ሁኔታ ወደ ነበረበት ለመመለስ የተለያዩ የፀጥታ አካላት ገብተው በጋራ እየሰሩ ነው “ብለዋል።

“ሁሉም ዜጋ ለሰላም፣ ዘብ መቆም አለበት ያሉት ኮማንደሩ ማንኛውም ጥያቄ ቢኖር በሰላማዊ መንገድ ብቻ በመጠየቅ የከተማዋን መልካም ስም ለማስጠበቅ ነዋሪው የድርሻውን እንዲወጣም ጠይቀዋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
•በሀረር ከተማ 3 ሰዎች ሞተዋል
•ከ50 የሚበልጡ ሰዎች ቆስለዋል


በሀረር ከተማ በነበረው #የተቃውሞ_ሰልፍ ላይ ከአጎራባች የምስራቅ ሃረርጌ ወረዳዎች ወደ ከተማዋ የመጡ ወጣቶች የጥቃቱ ሰለባ መሆናቸውን አንዲት የአይን እማኝ ለጀርመን ድምፅ ራድዮ ጣቢያ አስረድተዋል። በጥቃቱም ሶስት ሰዎች ተገድለው ከሃምሳ የሚልቁት መቁሰላቸውን በአይኔ አይቻለሁ ብለዋል። 

«ልጆች ሰልፍ ወጥተው ተሰልፈው እየሄዱ ነበር፤ በኮምቦልቻ ወረዳ በኩል የገቡት ተመተዋል፤ ከፈዲስ ወረዳ በኩል የመጡትም ተመተዋል፤ ሶስት ሰዎች ሞተዋል።

በአጠቃላይ በኦፕሬሽን ውስጥ ያሉና እና በአይናችን ያየናቸው ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሃምሳ ይሆናሉ። አሁን እንግዲህ ወጣቶቹን አንድ በአንድ ለመያዝ እየሞከሩ ነው፤ ወደ እስር ቤት ያስገቧቸውም አሉ። ጉዳት ደርሶባቸው አሁንም ወደ ሃኪም ቤት እየመጡ ያሉ አሉ። በዱላ እየደበደቧቸው ነዉ፤ የቦምብ ውርወራም ነበር።» 

የሀረሪ ክልል አስተዳደርና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ ናስር ዩያ በከተማዋ ከጥዋት ጀምሮ ሲካሄድ በነበረው የተቃዉሞ ሰልፍ በተፈጠረ ግጭት የሁለት ሰዎች ህይወት ማለፉንና አራት ሰዎች መቁሰላቸውን ለጀርመን ድምፅ ራድዮ አረጋግጠዋል። ተጨማሪ የማጣራት ስራዎችንም እየሰሩ ስለመሆኑ አስረድተዋል። 

«ጥዋት ላይ ሰላም ነበር ፤ ነገር ግን በአንድ ቀበሌ በተፈጠረ ግጭት ሶስት ሰዎች ተዳክመዋል። ከእነርሱ ውስጥ ሁለቱ ሞተዋል። ነገሩን አሁን እግር በእግር እየተከታተልነው ነው። ጥበቃ ላይ የነበሩ የመከላከያ ወታደሮች ናቸው የሚሉ አሉ። በእኛ በኩል ያሰማራነው የጸጥታ አካል የለንም ። ህዝቡ በሰላም ድምጹን አሰምቶ እንዲመለስ ነበር ፍላጎታችን፤ ለምን ይህ እንደሆነ እያየን ነው።» ብለዋል።

Via የጀርመን ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ሂደት አሜሪካ እንደምትደግፍ በአሜሪካ የአለም የንግድ ድርጅት የንግድና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ምክትል ተወካይ አረጋገጡ፡፡

የፋይናንስ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ በአሜሪካ የአለም የንግድ ድርጅት የንግድና የባለብዙ ወገን ጉዳዮች ምክትል ተወካይ ካራ ሞሮው ጋር ተወያይተዋል፡፡

የሁለቱን አገራት የንግድና ኢንቨስትመንት በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ ጠቃሚ ሃሰቦችን ተለዋውጠዋል። ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለችውን ለውጦች በተለይም የኢኮኖሚ ዘርፉ ላይ በማተኮር ሚኒስትሩ ለምክትል ኃላፊዋ ገለጻ አድርገውላቸዋል።

ምክትል ሃላፊ ካራ ሞሮው በበኩላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ለውጥ እንደሚያደንቁ በመግለጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የ2019 የኖቤል ተሸላሚ በመሆናቸውም ለሚኒስትሩ ደስታቸውን ገልዋል። ኢትዮጵያ የአለም የንግድ ድርጅት አባል ለመሆን በምታደርገው ሂደት አሜሪካ ድጋፍ እንደምታደርግም ም/ሀላፊው አረጋግጠዋል፡፡

ምንጭ፡- በዋሽንግተን የኢትዮጵያ ኤምባሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሻሸመኔና ሆለታ ከተሞች መንገዶች እንደተዘጉ ነው። በቢሾፍቱ ከተማም ውጥረቱ ሙሉ በሙሉ አረገበም። አዳማ ከተማ ከትላንት የተሻለ የተረጋጋ ሁኔታ አለ ነገር ግን ጥዋት በገንብ ገበያ አካባቢ የእሳት አደጋ ተነስቶ እንደነበርና መቆጣጠርም እንደተቻለ ቤተሰቦቻችን ጠቁመዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ADAMA

በአዳማ ከተማ የገበያ ማዕከል የተነሳ የእሳት ቃጠሎ በንብረት ላይ ጉዳት አደረሰ። በከተማዋ በተለምዶ ፍራንኮ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኝ የገበያ ማዕከል ላይ ዛሬ ንጋት ላይ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ 30 በላይ አነስተኛ ሱቆች ላይ ጉዳት አደረሰ። የከተማ አስተዳደሩ የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ኃላፊ አቶ ጉታ ኃይሌ እንደገለጹት ዛሬ ንጋት ላይ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ 24 አነስተኛ ሱቆች ሙሉ በሙሉ የወደሙ ሲሆን 10 የሚሆኑት ደግሞ መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

እንደ ኢዜአ ዘገባ የአደጋውን መከሰት ተከትሎ ሁለት የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች ተሰማርተው በአካባቢው ከሚገኙ የጸጥታ አካላትና ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ቃጠሎውን በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን አስረድተዋል። አደጋው በሰዎች ላይ ምንም ጉዳት እንዳላስከተለ የገለጹት ኃላፊው በንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠንና የቃጠሎው ምክንያት እየተጣራ መሆኑን ጠቁመዋል።

Via ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

በዶዶላ ከተማ ትላንት የጀመረው አለመረጋጋት ዛሬም መቀጠሉን የቲክቫህ ዶዶላ ቤተሰቦች ገልፀዋል። ሁኔታዎች ወደከፋ ሁኔታ እየሄዱ ነው መንግስት ልዩ ትኩረት ይስጠው ብለዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋጋ ጭማሪ ቅሬታ!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ይፋ ያደረገው የአገልግሎት ዋጋ ተመን ማሻሻያ የሕብረተሰቡን የኑሮ ደረጃና አቅም ያገናዘበ አይደለም ሲሉ ተጠቃሚዎች ቅሬታ አቀረቡ።

መንግሥት በኤሌክትሪክ አገልግሎት ተመን ላይ ለአራት አመት የሚቆይ የታሪፍ ማሻሻያን በ2011 ይፋ ማድረጉና በየዓመቱ እየጨመረ የሚሔድ መሆኑን መግለፁ ይታወሳል፡፡

ይህን ተከትሎም በአገልግሎቱ ቅሬታ የሚበዛበት ተቋሙ ሁለተኛው ዙር የዋጋ ጭማሪን ከታኅሣሥ 2012 ጀምሮ እንደሚተገብር መናገሩ አይዘነጋም፡፡

ይሁንና ከአገልግሎቱ መቆራረጥ ባሻገር የኑሮ ውድነቱ ጫና ውስጥ ያስገባቸው የኤሌክትሪክ አገልግሎቱ ደንበኞች ጭማሪው የህብረተሰቡን የኑሮ ደረጃና አቅም ያገናዘበ አይደለም ሲሉ ቅሬታቸው ያሰማሉ።

የዋጋ ተመን ማሻሻያው ቀደም ሲል ይከፍሉት ከነበረው ታሪፍ እስከ ሶስት እጥፍ እንዲከፍሉ ማድረጉንም ይጠቅሳሉ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በበኩሉ አገራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎትና የደንበኞች ብዛት እንዲሁም ካለው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ፍላጎት አንጻር ጥራት ያለው አገልግሎት ለመስጠትና ለማስፋፋት የሚያስችል ገቢ ማግኝት ባለመቻሉ የታሪፍ ጭማሪው ማስፈለጉን ያስረዳል፡፡

ምንጭ፦ አሐዱ ቴቪ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DODOLA

በባሌ ዶዶላ ዛሬ በነበረ ግጭት አራት ሰዎች ሞተው ወደ ዶዶላ አጠቃላይ ሆስፒታል መምጣታቸውን የሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ቶላ ቢዮ ለቢቢሲ ተናገሩ። ትናንት በአካባቢው ከጠዋት ጀምሮ ሠልፍ እንደነበር የተናገሩት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ከሰዓት በኋላ ግን ይህ ሠልፍ መልኩን መቀየሩን ይናገራሉ። በአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ግለሰብ ለቢቢሲ እንደገለፁት የዛሬው ግጭት ሊቀሰቀስ የቻለው "ከሁለት ወር በፊት አንድ ወጣት መሳሪያ በመተኮሱ ለእርሱ በቀል ነው" ሲሉ ይናገራሉ።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-10-24

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#attention

በድሬዳዋ ከተማ ትላንት ጀምሮ የተፈጠረው አለመራጋጋት ዛሬም በአንዳንድ አካባቢዎች ቀጥሏል። የደረሱ ጉዳቶችን እያጣራን ነው። የሀገር መከላከያ ሰራዊት ችግሩን ለመቆጣጠር ጥረት እያደረገ ይገኛል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia