TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ነገ ጳጉሜ 2 በስራ ገበታው ላይ ያልተገኘ ሰራተኛ ስራውን በገዛ ፈቃዱ እንደለቀቀ ተቆጥሮ ድርጅቱ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን ገልጿል። #DIREDAWA

#ድሬዳዋ_ናሽናል_ሲሚንቶ

#TIKVAH_ETHIOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
አዳምጡ⬆️

ዛሬ በተካሄደው የቅዱስ ሲኖዶስ ምላዓተ ጉባኤ ስብሰባ ላይ 95 በመቶ መግባባት ላይ መሰረደረሱን #ሁለቱም ወገኖች አስታውቀዋል።

በዛሬው ስብሰባ ላይ ባልተቋጩ ጉዳዮች ነገ ጥዋት ይመክራል! ዝርዝር መግለጫም ይሰጣል!

Via VOA AMAHARIC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለሚመለከተው አካል‼️ የአምና ወይም 2010 #የወርቅ_ሜዳሊያ ተሸላሚ ተመራቂዎች እስካሁን ስኮላርሺፕ እንዳላገኙ ለTIKVAH-ETHIOPIA በላኩት መልዕክት ገልፀዋል። የወርቅ ሜዳሚያ ተሸላሚ ተመራቂዎቹ እንዳሉት፦ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር #ዐብይ ቃል በገቡልን መሰረት ውጪ ሀገር scholarship እንደ ሚሰጠን በሁሉም የሚዲያ የተነገረ ነበር። ፕሬዘዳንት ዶክተር #ሙላቱ_ተሾመ በበኩላቸዉ የውጪ ሐገር…
የ2010 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች!

የ2010 የውርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚዎች የውጭ የትምህርት እድል እንደምናገኝ ተገልፆ ህዝቡም ስምቶት የነበረ ቢሆንም ምንም የትምህርት እድል አላገኘንም አሁንም እዚሁ ነው ያለነው አንዳንዶች በስራ ፍለጋ፡ አንዳንዶችም ተቀጥረን እየሰራን ነው ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ አስተያየቱን የሰጠው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል እና የዓምና የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ይህን ብሏል፦

"መቅረቱ ምንም አይደለም ሄዶ የለፋው ተማሪ ፓስፖርት ብሎ ብዙ ነገር ብሎ፤ ያንን ፕሮሰስ ለመጨረስ ብሎ ከስራውም የተባረረ እና የተስተጓጎለ ሰው እንዳለ ነው የሰማሁት። ያንን ፕሮሰስ ለማድረግ በሌክቸርነት የተቀጠሩ 20 እና 30 ቀን አ/አ ተቀምጠው ብዙ ከተለፋ በኃላ #የለም ማለት ያሳዝናል። አዳንዶች የሚሰሩበትም ዩኒቨርሲቲ አላውቃችሁም ብሎ አባሯቸዋል። ሙሉ በሙሉ ስኮላርሺፕ ጠብቆም አልነበረም ሰዉ፤ ያው የፖለቲካ ጉዳይ ነው ብሎ ተማሪውም አስቦበት ነበር፤ ማለቅ ከነበረበት አምና ነው ማለቅ የነበረበት እንኳን 400 ተማሪ ሌላም መውሰድ ይቻላል። ተማሪውን ያሳዘነው መቅረቱ አይደለም መንከራተቱ ነው። ቢያንስ እውነተኛ መረጃ ሊሰጥ ይገባ ነበር። ተስፋ መስጠቱም ተገቢ አይደለም። ቀጣይም እንዲህ ያሉነገሮች መደረግ የለባቸውም።"

የነበረው ሁኔታ ያብራራላችሁ አካል አልነበረም?

"አንድም ይሄ ነገር ሆኗል ፣ እንደዚህ ነገር ሆኗል ያለን አካል የለም። ለትምህርት የተላከ የሄደ አንድም ሰው የለም። አዲስ አበባ ሄዶ ለተንገላታው ተማሪ መልስ የሰጠ የለም። አንድም የመንግስት አካል ያናገረን የለም።"

ይህ ጉዳይ እስካሁን ተዳፍኖ መቅረቱ እንዳሳዘናቸው የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል የሆኑ የ2010 የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ የሆኑ ተማሪዎች ተናግረዋል!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአራዳ ልጅ ደም ይለግሳል!

በትዊተር የተሰባሰብን 100 የምንጠጋ ሰዎች ዛሬ ከጠዋት 4 ሰዓት ጀምሮ በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ውስጥ የደም መለገስ ፕሮግራም አሰናድተናል። ይህ ፕሮግራም የግሪን ሲቲስ (#ግሪንግ_አዲስ) የትዊተር እንቅስቃሴ አንዱ አካል ሲሆን ከወር በፊት በዚህ ግቢ ውስጥ 400 ችግኞች ተክለናል። አራዳነት ወይም ማወቅ ለሌሎችም መትረፍ ነው በሚል አላማ ነገ የመጀመርያ ዙር ደም ልገሳ ፕሮግራማችን ይካሄድል።

ሳሙኤል
ከግሪን ሲቲስ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የጅማ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ልገሳ!

ጅማ ዩኒቨርሲቲ “ኑ በጋራ የልጆቻችንን ተስፋ ብሩህ እናድርግ” በሚል መሪህ ቃል ከነሃሴ 6 እስከ 10/2011 ዓ.ም. ባደረገዉ የልገሳ ሳምንት የተለገሰዉን የትምህርት ቁሳቁስ ለ13 ትምህርት ቤቶች በዛሬዉ እለት (ጳጉሜ 1/2011 ዓ.ም) አስረክቧል፡፡

በልገሳዉ ዝግጅት ላይ የዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ የከተማ አስተዳደር አካላት፣ የከተማዉ ትምህርት ቢሮ፣ የ13 ትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች፣ የወላጅ ኮሚቴ አባላት እና ተማሪዎች የተገኙ ሲሆን ለ1014 ተማሪዎች ለእያንዳንዱ 1ደርዘን ደብተር እና 10 እስክሪፐቶ በትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች በኩል የተለገሰ ሲሆን ለ300 ተማሪዎች ደግሞ ዩኒፎርም ማሰፊያ ተበርክቷል፡፡ በዚህ የልገሳ ሳምንት ከዩኒቨርሲቲዉ፣ ከዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ እና ከተለያዩ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ በገንዘብ ሲተመን ግማሽ ሚሊዮን እንደሚደርስ በዝግጅቱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

የልገሳ ዝግጅቱን የከፈቱት የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጀማል አባፊጣ፣ የለገሱትን እና ያስተባበሩትን አካላት አመስግነዉ፣ በቀጣይ ዩኒቨርሲቲዉ የበጎ አድራጎት ማዕከል በመክፈት የበጎ አድራጎት ስራን በተሳለጠ መልኩ እንደሚያካሂድ ገልጸዋል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የታደሙት አባገዳዎች፣ የከተማዉ ት/ት ቢሮ እና የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች ለዩኒቨርሲቲዉ ማህበረሰብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Via #JimmaUniversity

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከጋምቤላ ሆስፒታል የተሰረቀች የአንድ ቀን ተኩል ዕድሜ ያላት ህፃን ከሁለት ቀናት ክትትል በኋላ ከነሙሉ ጤንነቷ ተገኘች። የጋምቤላ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡቲያንግ ኡቻን እንደገለፁት በጋምቤላ ሆስፒታል ነሀሴ 28 ቀን 2011 ዓም አንዲት ህፃን በሰላም ወደ ዓለማችን ተቀላቅላለች።
ከምጥ ጋር ታግላ ጤናማ ህፃን በሰላም የተገላገለችው እናት ድካሙ አልለቀቃትም ነበርና በማግስቱ አገር አማን ነው ብላ ጨቅላዋን አጠገቧ እንዳስቀመጠች እንቅልፍ ሸለብ ያደርጋታል። ከእንቅልፏ ስትነሳ ግን የአንድ ቀን ተኩል እድሜ ያላት የአብራኳን ክፋይ እንዳስቀመጠቻት ከጎኗ የለችም። እናት በድንጋጤ ተውጣ የድረሱልኝ ጥሪ በማሰማቷ የሆስፒታሉ ማህበረሰብ ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ስለ ጉዳዩ ማውረድ ማውጣት ይጀምራል። ዋነኛው መፍትሔ ሆኖ የተገኘው ግን ጉዳዩን ለፖሊስ ማሳወቅ ነበር። የክልሉ ፖሊስም ነሀሴ 29 ቀን 2011 ዓም ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ጠፋች የተባለችውን ጨቅላ ህፃን ለማግኘት ፍለጋውን ይጀምራል።

ይህን ተጭነው ተጨማሪ የንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-07

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በጋምቤላ የዓለም ሰብዓዊ አገልግሎት ተቋረጠ!

ሁሉም የሰብዓዊ ዕርዳታ ተቋማት በጋምቤላ ክልል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለጊዜው #ማቋረጣቸውን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ አስታወቁ፡፡ እዚሁ ውሳኔ ላይ የተደረሰውም በጋምቤላ ክልል በተፈፀመው ጥቃት ሁለት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሰራተኞች መገደላቸውን ተከትሎ፣ መሆኑን በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት ተጠባባቂ የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ ስቲቨን ዌር ኦማሞ ለአሜሪካ ድምፅ አስረድተዋል።

Via #VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህርዳር

በኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በህገ ወጦች ሲንቀሳቀስ የነበረ ንብረትን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል፡፡የተለያዩ አልባሳት እና ህገ ወጥ የአሳ ማስገሪያ መረቦች ናቸው በፖሊስ የተያዙት፡፡ በሁለት አይሱዙ መኪናዎች ተጭነው ከሁመራ ወደ ጎንደር ከተማ ሊገቡ እያለ ትክል ድንጋይ ላይ እንደተያዙ ጽህፈት ቤቱ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዛሬ በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

የንብረቶቹ ግምታዊ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን 170 ሺህ ብር በላይ እደሚሆንም ነው የተገለጸው፡፡ ንብረቶቹን የያዙት የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ናቸው ብሏል ጽህፈት ቤቱ፡፡ ንብረቶቹም ለጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ገቢ እንደተደረጉ ነው የተገለጸው፡፡ ከተያዙት ንብረቶች ውስጥ 3 ሺህ 480 ህገ ወጥ የአሳ ማስገሪያ መረብ ይገኝበታል፡፡ ይህም መጠኑ ለማስገሪያነት ከሚያገለግለው መረብ ያነሰ በመሆኑ የአሳ ጫጩቶች ለምግነብነት ከመድረሳቸው እና ከመራባታቸው በፊት እንዲያዙ፣ የአሳ ምርትም እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Art and #Architectural Exhibition

አዲስ አበባ የምትገኙ ኦሮሚያ ባህል ማዕከል ብቅ በሉ ብለዋችኃል አዘጋጆቹ!! #UTOPIA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#New⬆️ "...ወደ ክቡር ስራችሁ ትመለሱ ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን!!" #ድሬዳዋ_ናሽናል_ሲሚንቶ #DIREDAWA

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA ሰራተኞቹ አሁንም ወደስራ አልተመለሱም። በተለጠፈው ማስታወቂያ ላይ ቀነ ገደብ አልተገለጠም፤ መቼ ተፈፃሚ እንደሚደረግ ድርጅቱ ያለው ነገር የለም በማለት አሁንም ወደስራ ገበታቸው እንዳልተመለሱ ለማወቅ ተችሏል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#DIREDAWA ከሰራተኞች ጋር መግባባት ላይ በመደረሱ ሁሉም ሰራተኛ በዓሁን ሰዓት ወደስራ ገበታው እየተመለሰ ይገኛል።

#ናሽናል_ሲሚንቶ

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#NEW

ASTU/AASTU የመምዝገቢያ መስፈርቶች!

በ2012 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ2011 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱና ከታች የተጠቀሱትን ዝርዝር መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋሉ፡፡

የምዝገባ ጊዜ፡-

ከጳጉሜ 2 / 2011 ዓ.ም እስከ መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም

ምዝገባው የሚጠናቀቀው፡-

💫መስከረም 5 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ይሆናል፡፡

የምዝገባ ቦታ፡

💫የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ www.aastu.edu.et www.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን፡-

💫መስከረም 9 ቀን 2012 ዓ.ም ( ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 11፡00 ድረስ ይሆናል)

ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ፡-

💫በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ👇
https://telegra.ph/ETH-09-07-2

#ሼር #share

 @tsegabwolde @tikvahethiopia
#SUDAN

በሱዳን የዳቦ ዋጋ መናርን ተከትሎ በተቀሰቀሰው የፖለቲካ ቀውስ ምክንያት የቀድሞውን ፕሬዘዳንት ኦማር ሃሰን አልበሽርን ከስልጣን በማውረድ ብቻ አልተጠናቀቀም ነበር።

ተቃውሞን ተከትሎም የአገሪቱ ወታደራዊ ጦር ስልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ በሱዳን ድጋሚ የፖለቲካ ቀውስ ተከስቶ ነበር። በዚህ ምክንያት ነበር የአፍሪካ ህብረት በወቅቱ የአገሪቱን ስልጣን ተቆጣጥሮ የነበረው ወታደራዊ የሽግግር መንግስት ስልጣኑን ለሲቪል እንዲያስረክብ ያዘዋል። ይሁንና የሽግግር መንግስቱ ስልጣኑን በተባለው ጊዜ ባለማስረከቡ ምክንያት ህብረቱ ሱዳንን በጊዜያዊነት አገደ።

አሁን ላይ የሽግግር መንግስቱና #የተቃዋሚ ሃይሎች በመስማማታቸው የፕሬዘዳንትነቱን ስልጣን ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤት የጠቅላይ ሚኒስትርነትና የተወሰኑ የሚኒስትርነት ቦታዎችን ከተቃዋሚዎች በሚመረጡ ሹመኞች እንዲያዝ ተስማምተዋል።

የቀድሞው የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ምክትል ሃላፊ የነበሩት ኢኮኖሚስቱ ዶክተር አብደላ ሃምዶክ የሱዳን ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው የተሾሙ ሲሆን ካቢኔያቸውን ከትናንት በስቲያ አዋቅረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን የፖለቲካ ታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርም ሾመዋል። በሱዳን የነበረው የፖለቲካ ቀውስ እየረገበ በመምጣቱና ወታደራዊ ጦሩ ስልጣኑን በከፊል በማስረከቡ የአፍሪካ ህብረት በሱዳን ላይ ጥሎት የነበረውን እገዳ ማንሳቱን አስታውቋል።

Via #ETHIO_FM
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ!

የኦሮሚያ ቤተክሀነት ፅ/ቤት እንዲቋቋም በመጠየቅ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሂዶ ቤተ ክተርስትያን ቅዱስ ሲኖዶስን በመጠየቅ የሰጠው መግለጫ ጥፋት ነው በማለት የኮሚቴው አባላት ይቅርታ እንዲጠይቁ ብፁሃን አባቶች ለማስገደድ ብሞክሩም የኮሚቴው አባላት ያጠፋነው ነገር የለም በማለት ይቅርታ መጠየቅ አይገባንም በማለት ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ምክኒያቱም መግለጫ የተሰጠው፡-

1ኛ. የቤተ ክርስትያኗን ቀናኢ ልጆችን ብሶትና ፍላጎትን ለመግለፅ ነው

2ኛ. ላለፉት 27 አመታትና ከዚያ በፊት ባሉ ጊዜያት ለህዝቡ በተለይም ለኦሮሞ ህዝብ ተደራሽ ያልሆነ መዋቅርና የአገልግሎት አሰጣጠት ችግር ፋታ የማይሰጥ በመሆኑ

3ኛ. ቋሚ ሲኖዶሱ መግለጫ እንዳይሰጥ ከልክሏል ብለን ስለማናምን

4ኛ. ህዝቡ መግለጫውን በከፍተኛ ተነሳሽነት የሚጠብቅ ስለሆነ መግለጫው በመቅረቱ ምክኒያት የሀገሪቱ ሰላም እንዳይደፈርስ

5ኛ. እንዲያውም ይቅርታ መጠየቅ ተገቢ ከሆነ መጠየቅ ያለባቸው ላለፉት አመታት ስር የሰደደውን የቤተ ክርስትያኗን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ ቤተ ክርስትያኗን የፖሊትካዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎቶቻቸው ሎሌ ያደረጉ ብፁሃን አባቶች በመሆናቸው ህዝቡን ይቅርታ በይፋ ጠይቀው ህዝቡን እንዲክሱ በትህትና በዚህ አጋጣሚ እንጠይቃለን:: በአጠቃላይ በእነዚህና አያሌ አሳማኝ ምክኒያቶች ያለጥፋታችን ይቅርታ ጠይቁ የተባልነውን አስገዳጅ ኣካሄድ አልተቀበልንም፡፡

የኦሮሚያ ቤተክህነት ኣደራጅ ኮሚቴ
ጳጉሜ 2፣ 2011 ዓ.ም

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ተጠናቆ ጋዜጣዊ መግለጫ እየተሰጠ ይገኛል!

ዝርዝር መረጃ ከደቂቃዎች በኋላ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መግለጫው ተጠናቋል!