TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NewsAlert

ሰሞኑን በሲዳማ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች እና ከተሞች በተከሰተው ግጭት ሀኪም ቤት ሳይደርሱ በየአካባቢው የተቀበሩትን ሳይጨምር 53 ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች 54 ሰዎች ደግሞ መጎዳታቸውን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አረጋገጠ። በወቅቱ ከተከሰተው ግጭት ጋር በተያያዘም እስካሁን 935 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥራ ማዋሉን የሲዳማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።

የመምሪያው ዋና አዛዥ ምክትል ኮማንደር ዳኛው ደምሴ ዛሬ በተለይ ለጀርመን ራድዮ እንደገለፁት የግጭቱ መነሻ ሐምሌ 11 ቀን 2011ዓ,ም በሐዋሳ ከተማ የሲዳማ ብሔር በክልል የመደራጀት ጥያቄን እናውጃለን የሚሉ ወጣቶች ከፀጥታ አካላት ጋር መጋጨታቸው ነው። በመቀጠልም ግጭቱ ሲዳማ ዞን ውስጥ ወደሚገኙት ሁላ፣ ይርጋዓለም፣ ማልጋ፣ ሞሮቾ እና አለታ ወንዶ ወረዳ እና ከተሞች መዛመቱን ተናግረዋል። በተጠቀሱት ከተሞች እና ወረዳዎች ከሞቱት እና ከቆሰሉት ወገኖች በጠጨማሪ፤ የዱቄት ፋብሪካዎች እና የመዝናኛ ሎጆችን ጨምሮ በሚሊየን ብሮች የሚገመት ንብረት በቡድን ሲንቀሳቀሱ በነበሩት ወጣቶች መውደሙን እና መቃጠሉንም ዘርዝረዋል።

በወጣቶቾ የተፈጸመው ድርጊት ከሲዳማ ባሕል እና ወግ ያፈነገጠ ብቻ ሳይሆን ከጥያቄው ጋር አይገናኝም ያሉት ምክትል ኮማንደሩ በአሁኑ ወቅትም ድርጊቱ በሲዳማ ማኅበረሰብ እና በየወረዳው በሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች እየተወገዘ እንደሚገኝም አመልክተዋል።

Via #DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ደቡብ ክልል

በደቡብ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተው ችግር ምክንያቱ ፖለቲካዊና የአመራር ስርዓቱ አለመጠናከር መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ገለፁ። የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ለማስከበር የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት በሚያከናውናቸው ተግባራት ላይ ከዞን እስከ ወረዳ ካሉ የሰላምና ጸጥታ አመራሮች ጋር ትላንይ በሃዋሳ ከተማ ተወያይተዋል። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኤልያስ ሽኩር እንዳሉት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በክልሉ ውስጥ ሀገራዊ መልክ ያላቸው የተለያዩ ችግሮች እየተከሰቱ ነው።

https://telegra.ph/D-07-31
Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጃፓን

የባህር ዳር ከተማን የውኃ አቅርቦት ለማሻሻል የሚያስችል ስምምነት በ425 ሚሊየን ብር ተፈረመ፡፡ ስምምነቱ በአማራ ክልል የውኃ፣ መስኖና ኢነርጂ ልማት ቢሮ አና በኮኖይኬ ኮንስትራክሽን መካከል በጃፓን ተፈርሟል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በሐዋሳ ተቀስቅሶ ወደ ሌሎች የሲዳማ ወረዳዎች በተዛመተው ኹከት ሳቢያ 935 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ምክትል ኮማንደር ዳኛቸው ደምሴ ገልጸዋል። የፖሊስ አዝዡ በቁጥጥር ሥር ስለዋሉት ሰዎች በዝርዝር ያሉት ነገር የለም።

Via #EsheteBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Fake "የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት #ተለቀቀ" በሚል TIKVAH-ETHን በመጥቀስ ሀሰተኛ መረጃዎች እየተሰራጩ እንደሆነ ተመልክተናል። መረጃው ፍፁም ከእውነት የራቀና በፎቶሾፕ የተቀነባበረ ነው።

🏷የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ማድረጊያ ቀንን በተመለከተ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት ጥያቄ አቅርበን ምላሽ እየጠበቀን ስለሆነ የምናገኘውን ምላሽ ወደናተ እናደርሳለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዘምዘም ባንክ በመስከረም ወር ስራ ይጀምራል!

በኢትዮጵያ ወለድ አልባ ባንክ እንዲመሠረት ለማድረግ ቀዳሚ ሚና የነበረው ዘምዘም ባንክ አክሲዮን ማኅበር (በምሥረታ ላይ) በ2012 ዓ.ም. የመጀመርያው እንደሚሆን የሚታሰውበውንና ሙሉ በሙሉ ወለድ አልባ የሚሆውን ባንክ በአንድ ቢሊዮን ብር ካፒታል ለመመሥረት የሚያስችለውን ዝግጅት እንዳጠናቀቀ አስታወቀ፡፡

#ዘምዘም_ባንክ ቅዳሜ፣ ሐምሌ 20 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ እንዳደረገው፣ ወለድ አልባውን ባንክ ለማስጀመር የሚያስፈልገውን ካፒታል በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝና እስካሁንም ከሚፈልገው ካፒታል ከ70 በመቶ በላይ ማሟላቱን አስታውቋል፡፡

Via #ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ሰመራ

"...አብዛኛዎቹ #የመንግስት ቤቶች በህገ ወጥ መንገድ የተያዙ ናቸው"
.
.
#በሰመራ_ሎግያ ከተማ አስተዳደር ከሚገኙ 200 የመንግሰት ቤቶች መካከል በህጋዊ ውል የተያዙት ከ35 እንደማይበልጡ የአስተዳደሩ ቤቶች ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ። የሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር የቤቶች ልማት ፅህፈት ቤት በበኩሉ ከ2 እስከ 10 ዓመት ድረስ የቤት ኪራይ ባልከፈሉና የመንግስት ቤት በህገ ወጥ መንገድ በያዙ ግለሰቦች ላይ ክስ ለመመስረት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ኢንጂነር ራሁባ ሙሀመድ እንደገለጹት በመንግስት ቤት ከሚኖሩ 200 አባውሯዎች መካከል ህጋዊ ውል ያላቸው 35ቱ ብቻ ናቸው። “ቀሪዎቹ 165 አባወሯዎች ከፅህፈት ቤቱ እውቅና ውጪ ቁልፍ ገዝተውና በህገወጥ መንገድ ቤቶቹን በእጃቸው ያስገቡ ናቸው” ብለዋል። ህጋዊ ውል ያላቸውም ቢሆኑ በመንግስት የክትትልና ቁጥጥር ድክመት ምክንያት ከ2 እስከ 10 ዓመት ድረስ ያልከፈሉት ከ300 ሺህ ብር በላይ #ውዝፍ የቤት ኪራይ ዕዳ ያለባቸው ከ100 በላይ ሰዎች እንዳሉ በቅርቡ በተደረገው የማጣራት ስራ መረጋገጡን ኢንጂነር ራሁባ ገልፀዋል። የመንግስት ቤቶችን በህገወጥ መንገድ  ባስተላለፉ፣ ቤቶቹን በያዙና ለረጅም ዓመታት የቤት ኪራይ ባልከፈሉ ግለሰቦች ላይ እስከ መጪው መስከረም ወር ድረስ ክስ እንደሚመሰረትም ኃላፊዋ አስታውቀዋል።

Via #ena
ፎቶ፦ ፋይል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተጨማሪ...

የአፋር ክልል ርዕሰ ከተማ #ከአይሳኢታ ወደ #ሰመራ ሲዘዋወር የመንግስት ሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመፍታት መንግስት ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ቤቶች ሰርቶ ማስረከቡ ይታወሳል፤ ይሁን እንጂ አብዛኛዎቹ ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በአሁኑ ወቅት የግል መኖሪያ ቤት የሰሩ ቢሆንም የራሳቸውን ቤት እያከራዩ በመንግስት ቤት በነፃ እየኖሩ መሆናቸውን ተረጋግጧል። በመሆኑም ቤቶቹ ከአመራሮቹ ተቀምቶ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሠራተኞች እንዲተላለፉ የሚደረግ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር፣ UCodeGirl እና አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በትብብር ከሐምሌ 24 እስከ ሐምሌ 28 /2011 ዓ.ም ያዘጋጁት የኮዲንግ ስልጠና የመክፈቻ ስነስርዓት ትናንት ሐምሌ 23 ቀን 2011 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ተካሂዷል፡፡

ከ23 የመንግስት ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪ የሆኑ 100 ሴት ተማሪዎች የሚሳተፉበት ስልጠና የመክፈቻ ፕሮግራም ሲካሄድ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ እንዳሉት በውጭ አገራት ያሉ ዲያስፖራዎች በተሰማሩበት መስክ ያካበበቱትን እውቀትና ክህሎት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በመነጋገር ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚኖሩ ወገኖች የማስተላለፍ ስራ ቢሰሩ መልካም ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም በታዳጊ ሴቶች ላይ ከልጅነታቸው ጀምሮ በመስራት በቴክኖሎጂ ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡ ፕሮፌሰር አፈወርቅ እንዳሉት በተለይ ሴቶች በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ፣ ኢንጂነሪንግና ሂሳብ (STEM) ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግና ውጤታማነታቸውን ለማጠናከር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ስቲም ሴንተሮችን በመክፈት እየሰራን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው አክለውም ወጣቶች ወደ ትምህርት አለም ሲገቡ ከዓለም አገሮች አንፃር ሲታይ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ በማገናዘብ ለአገሬ አንድ ነገር አበረክታለሁ በሚል መነሻነት ሊሆን እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡ UCodeGirl በአሜሪካን አገር በትውልደ ኢትዮጵያዊት የተቋቋመ ታዳጊ ሴቶችን በኮዲንግ የሚያሰለጥን ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ነው፡፡

https://telegra.ph/SH-07-31

Via #EPA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#የችሎትወሬዎች

/ሳምራዊት ለማ/

እነ #በሪሁን_አዳነ ዳኛ ይቀየርልን በሚል ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ሆኗል፤ ያለበቂ ምክኒያት ዳኛው እንዲነሳ በመጠየቃቸው 300 ብር ተቀጥተዋል፡፡ "ጉዳያችንን የያዙት ዳኛ ከመርማሪው አካል እና ከፖለቲካ ተፅዕኖ ውጭ ሆነው በገለልተኝነት ጉዳያችንን በማየት ትክክለኛ ፍትህ ይሰጡናል ብለን ስለማናምን ከመዝገቡ ይነሱልን" በማለት ከዚህ ቀደም አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡

አንድ ዳኛ በምን ምክኒያቶች ከተሰየመበት መዝገብ ሊነሳ እንደሚችል በ ፌደራል ፍርድቤቶች አዋጅ ቁጥር 25/88 አንቀፅ 27 የተቀመጠ ሲሆን በቂ ምክኒያት ሳይኖር የሚቀርብ ማመልከቻ ስለሚያስከትለው ቅጣትም በዛው አዋጅ አንቀፅ 30 ከላይ እንደሚታየው ተቀምጧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የደኢህዴን ስብሰባ ተጠናቋል!

በሐዋሳ ሲካሔድ የቆየው የደኢሕዴን ስብሰባ መጠናቀቁን ንቅናቄው አስታውቋል። ደኢሕዴን «በክልሉ እየተነሱ ያሉ የአደረጃጀት ጥያቄ ላይ በተደረገው የጥናት ግኝት ላይ ከሐምሌ 18 ጀምሮ» ስብሰባ ላይ ከርሟል፤ ከደቂቃዎች በኋላ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ኮማንድ_ፖስት

በደቡብ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች ተፈጥሮ ከነበረው የፀጥታ ችግር ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑን በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስት አስታወቀ። ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ በዛሬው እለት ዝርዝር ተግባራትን እና የአፈጻጸም ሁኔታዎችን ይፋ አድርጓል።

በዚህም በክልሉ በተለይም በሲዳማ ዞን እና አካባቢው ከተፈጠረው የፀጥታ ችግር በተያያዘ በደረሰው ጉዳት የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር እየዋሉ መሆኑን አስታውቋል።

በቁጥጥር ስር የዋሉ ግለሰቦች ላይ የመለየትና የማጣራት ስራ እየተሰራ ነው ያለው ኮማንድ ፖስቱ፥ ህብረተሰቡም ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ተጠርጣሪዎችን አሳልፎ የመስጠትና ንብረቶችን የማስመለስ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልጿል።

ከህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ጋር በተያያዘም ጥብቅ ቁጥጥር እየተደረገ መሆኑን ጠቅሶ፥ የፍተሻ ኬላዎችን አልፈው በግለሰቦች እጅ የሚገኙ መሳሪያዎች ተይዘዋልም ነው ያለው።

ጊዜያዊ ኮማንድ ፖስቱ ከ12 ቀናት በፊት በክልሉ አንዳንድ አካባቢዎች የፀጥታ ችግር መከሰቱን ተከትሎ መቋቋሙ የተገለጸ ሲሆን፥ ክልሉ ወደ ቀደመ ሰላሙ እስከሚመለስ ድረስ እንደሚሰራ ተጠቅሷል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CMP-07-31
#SEPDM

ላለፉት ሰባት ቀናት ሲካሄድ የቆየው የደቡብ ኢትዮጰያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ደኢህዴን) ከፍተኛ አመራሮች መድረክ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታና ድርጅቱ ባስጠናው የክልልነት ጥያቄ ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ተጠናቀቀ።

በምክክር መድረኩ የሰባት ቀናት ቆይታ ዙሪያ የደኢህዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሞገስ ባልቻ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳሉት ለአመራር መድረኩ በቀረቡ አጀንዳዎች ዙሪያ የተደረገው ውይይት ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ነበር።

በሀገሪቱ ተጀመረውን ለውጥ በድርጅት ውስጥም ሆነ በውጪ ሊያደናቅፍ የሚያስችል የአመለካከት መዛባት ያለበት በመሆኑ ይህን በማረም የህዝብን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ስምምንት ላይ መደረሱን ገልጸዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/D-07-31-2
#ኮማንድ_ፖስት

ሀምሌ 11 ቀን 2011 ዓም #በሲዳማ_ዞን እና #በሀዋሳ ከተማ የተከሰተውን የጸጥታ ችግር አስመልክቶ በክልሉ የተቋቋመው ኮማንድ ፖስት መደበኛውን የህግ ማስከበር ስርዓት ተከትሎ የህብረተሰቡን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑ ተገለጸ፡፡

ኮማንድ ፖስቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ የተከናወኑ ዝርዝር ተግባራትን አስመልክቶ ዛሬ በሀዋሳ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/CM-07-31
#ኮማንድ_ፖስት

√መደበኛ ህጎችን መጣስ
√ያልተፈቀዱ ሰልፎችን ማድረግ፣
√በዜጎች ላይ ሰብዓዊ ጥቃት መፈጸም፣
√የተለየ እና የሰላም ማደፍረስ እንቅስቃሴ ማሳየትና ማድረግ በኮማንድ ፖስቱ ተከልክለዋል።

ከዚህ ባለፈም...

በሃዋሳ ከተማ ክልከላው እስከሚነሳ ድረስ ሞተር ብስክሌት ማሽከርከር አይቻልም። ከዚህ ጋር ተያይዞ ሞተር ብስክሌታቸው የተያዘባቸው ግለሰቦች ባለቤትነታቸውን አሳውቀው መውሰድ ይችላሉ ነው ብሏል ኮማንድ ፖስቱ።

በቀጣይም ከሃዋሳ ውጭ ባሉ ሌሎች ከተሞች ከሞተር ብስክሌት አጠቃቀም ጋር ተያይዞ ለፀጥታ ችግር ሊሆኑ የሚችሉ እንቅስቃሴዎች ከተስተዋሉ ክልከላ ይደረጋል።

ከላይ ከተጠቀሰው ውጭ በኮማንድ ፖስቱ የሰዓት እላፊም ሆነ የተለየ ክልከላ አልተደረገም፤ ኮማንድ ፖስቱ፥ ወደፊት ከዚህ ጋር ተያይዞ የተለዩ አካባቢዎች ካሉ ይፋ ይደረጋል።

🏷አሁን ላይ በክልሉ ሁሉም መንገዶች ክፍት መሆናቸውን ተጠቅሷል፥ ህብረተሰቡ ከፀጥታ አካላት ጋር በመሆን ላሳየው ትብብር ምስጋና ቀርቧል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
በኦሮሚያ ክልል በ319 ወረዳዎች እና በ19 ከተሞች ከ7 ሺሕ 426 ቀበሌዎች የተውጣጡ ከ57,000 በላይ የቀበሌ አመራሮች ከዛሬ ጀምሮ የ10 ቀናት የአመራር ስልጠና መጀመራቸውን የኦሮሚያ ኮምዩንኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ አድማሱ ዳምጠው ተናግረዋል።

Via #EshetBekele
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#መቐለ

ሁለተኛው የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል በመቐለ መካሄድ ጀመረ፡፡ ፌስቲቫሉን የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ደብረፂዮን ገብረሚካኤል በተገኙበት ተከፍቷል፡፡ ይህ የትግራይ አለም አቀፍ የዳያስፖራ ፌስቲቫል የክልሉን ህዝብ ከድህነት ለማላቀቅ በሚያስችል ጉዳዮች ላይ በማተኮር የሚካሄድ መሆኑን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

Via #fbc
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#አዲስ_አበባ

#የብርሃን_ኢንተርናሽናል_ባንክ አ.ማ ለመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች 350ሺ ደብተር እና 150 ሺ እስክርቢቶ ድጋፍ አደረገ፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማም የብርሃን ባንክ አ.ማ ለተማሪዎች ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን እንዳቀረቡ ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአለርት ሆስፒታል አልባሳር ኢንተርናሽናል ከተሰኘ ሳኡዲ በቀል በጎ አድራጎት ድርጅት ጋር በመተባበር የፊታችን ሐምሌ 27 እና 28 የሞራ ግርዶሽ የአይን ህክምና በነጻ ለመስጠት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"...የፌስቡክ አርበኞች እና የከሠሩ የፅንፈኛ ፖለቲካ አቀንቃኞች.."

የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት በሀገራዊ አንድነት እና የሕግ ማስከበር ሥራ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ አስታወቀ፡፡ የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዓመት 5ኛ የሥራ ዘመን 9ኛ መደበኛ ጉባኤውን ከትናንት ጀምሮ እያካሄደ ነው፡፡ በሁለት ቀን ቆይታውም እስከ ሐምሌ 24/2011 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ድረስ የ23 ተቋማትን የ2011 በጀት ዓመት የሥራ አፈፃጸም ገምግሞ አጽድቋል፡፡ ምክር ቤቱ በተለይም በሀገራዊና ክልላዊ የሠላም ጉዳይ ላይ ሰፊ ጊዜ ወስዶ መክሯል፡፡

በሀገራዊ ለውጡ በክልሉ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶች ተከስተዋል፡፡ በእነዚህ ግጭቶች የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ ንብረትም ወድሟል፡፡ ይህ ይሁን እንጂ በክልሉ መንግሥት ቁርጠኝነት፣ ከአጎራባች ክልሎች እና ከፌዴራል መንግሥት ጋር በመሆን በተሠራው የሕግ ማስከበር ሥራ በፍጥነት ከግጭቶች በመውጣት ሠላማዊ እንቅስቃሴ እንዲኖር ማድረግ መቻሉ ተጠቅሷል፡፡

ምክር ቤቱ በአሶሳ ዞን አሶሳ ከተማ፣ ማኦ እና ኮሞ ልዩ ወረዳዎች፣ ካማሼ እና መተከል ዞኖች ላይ የተፈጠሩት ግጭቶች መሠረታቸው ሕዝባዊ ሳይሆኑ የፌስቡክ አርበኞች እና የከሠሩ የፅንፈኛ አቀንቃኞች ሥራ መሆኑን መገምገሙን የክልሉ ምክር ቤት የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ተኪቶ ታደሰ ለአብመድ ተናግረዋል፡፡

አቶ ተኪቶ ታደሰ ምክር ቤቱ የቤኔሻንጉል ጉሙዝ ክልል መንግሥት እና ሕዝብ መሠል ችግሮች እንዳይፈጠሩ እንደቀደመው ሁሉ በሀገራዊ አንድነት እና የሕግ ማስከበር ሥራ ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ነው የተናገሩት፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/BNG-07-31

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ችሎት

ትናንት ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት የወሰነላቸው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላትና አመራሮች አልተፈቱም፡፡ ምክንያቱ ዐቃቤ ሕግ ይግባኝ በመጠየቁ ነው- ብሏል አብን በፌስቡክ ገጹ፡፡

በተያያዘ ዜና...

ፖሊስ የአማራ ተማሪዎች ማኅበር ጸሃፊ #ሮዛ_ሰለሞንን ፖሊስ ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧታል፡፡ ዐቃቤ ሕግ በሽብርተኝነት እከሳታለሁ በማለቱ ችሎቱ 28 የምርመራ ቀናት ፈቅዷል፡፡ ፍርድ ቤት በሌላ ችሎት “በመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ” የተከሰሰው የአሥራት ቴሌቪዥን ባልደረባ ጋዜጠኛ በሪሁን አዳነ፣ ዳኛ ይነሱልኝ ሲል ያቀረበውን አቤቱታ ችሎቱ ዛሬ ውድቅ ያደረገበት ሲሆን፣ ያለ አሳማኝ መነሻ አቤት ብሏል በማለትም የ300 ብር መቀጮ እንደጣለበት አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል፡፡

Via #AddisStandard/#ዋዜማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia