TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.03K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈#የመምህራንድምጽ

" የመምህራን ደመወዝ ባለመከፈሉ በዚህ ክረምት ለአቅም ግንባታ ስልጠና የገቡ መምህራኖችና ቤተሰቦቻቸው ለረሀብና ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል " ሲል የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር ገልጸ።

" መምህራኑ በዚህ ሁኔታ በረሀብ ውስጥ ሆነው  መቀጠል አይችሉም የሚመለከተዉ አካል መፍትሄ ያስፈልገዋል " ሲል መልእክቱን አስተላልፏል።

ማህበሩ የሰኔ ወር ደመወዝ እስካሁን ያልተከፈላቸዉ ወረዳዎች 21 መድረሱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከነዚህ 21 ወረዳዎች 13ቱ በፐርሰንት ተቆራርጦ ጥቂት ገንዘቦች እንደገባላቸው ፤ በዚህ ሁኔታ መምህራኑ ህይወት ከባድ እንደሆነባቸው ገልጿል።

" የሚመለከታቸዉ አካላት ለደመወዝ መቆራረጥና አለመግባት እንደምክንያት የሚያቀርቡት የክልል ፋይናንስ ገንዘብ ባለ ማውረዳቸው ነው " የሚል ነው ያለው ማህበሩ " አሁን ላይ መምህራን ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን ፤ ኑሮን መቋቋም እንዳልቻሉ ፤ በዚህም ምክንያት አልፎ አልፎ የመማር ማስተማር ሥራ እየተስተጓጎለ መቆየቱን አሳውቋል።

በቅርቡ በአርባ ምንጭ ከተማ በተደረገው የምክር ቤት ስብሰባ ከምክር ቤት አባላት ይኸው የደመወዝ ጥያቄ ቀርቦ ነበር።

በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር እና በክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች የደመወዝ መዘግየትና በፕርሰንት መከፈል አግባብ እንዳልሆነና የክልሉ መንግስትም ለመምህራን ደመወዝ የቅድሚያ ቅድሚያ በመስጠት ደመወዝና ጥቅማ ጥቅማቸው ወቅቱን ጠብቆ በጊዜ እንዲከፈል መመሪያ ሰጥቶ ነበር።

ነገር ግን አሁንም የሰኔ ወር 2016 ዓ.ም ደመወዝ እስከ ድረስ ሙሉ ያልተከፈላቸውና በፐርሰንት እየተከፈላቸው ያሉ መምህራን መኖራቸውን ማህበሩ አመልክቷል።

ማህበሩ " አሁን ላይ የሰኔ ደሞዝ በመዘግየቱ ምክኒያት  የክረምት የአቅም ግንባታ ስልጠና የገቡ የክልላችን መምህራኖችና ቤተሰቦቻቸው ለረሀብና ለከፋ ችግር ተጋልጠዋል " ብሏል።

" ይህ ሁኔታ ስልጠናውን እንዳያስተጓጉለው አፋጣኝ መፍትሄ ያሻዋል " ም ሲል አሳስቧል።

የመምህራን ከደሞዝ መቆራረጥ ጋር ሲስተዋል የከረመ ከባድ ችግር በ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ሊቀጥል ስለማይገባ መምህሩ የለፋበትንና የሚገባውን ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በወቅቱ እንዲከፈል  የሚመለከታቸው አካላት ሁሉም  የድርሻቸውን እንዲወጡ አጽንኦት ሰጥቶ ጠይቋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ከመምህራን ደመወዝ ጋር በተያያዘ በሰጠን ምላሽ " የደመወዝ ጉዳይ ዲሴንትራላይዝ ሆኗል የሚመለከታቸው የዞንና የወረዳ አመራሮችን ነው " በማለት ችግሩ ካለ የእርምት እርምጃ እንደሚወስድና መምህራን ደመወዝ ሊዘገይም ሆነ ሊቆራረጥባቸዉ እንደማይገባ መግለጹ የሚታወስ ነዉ።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#HawassaUniversity

በህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለጠፈው ማስታወቂያ ምንድነው ? ዩኒቨርሲቲውስ ምን ምላሽ ሰጠ ?

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሚማሩ ተማሪዎች ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ሲልኩ ነበር።

ለዚህ ቅሬታ መነሻቸውም አንድ ተለጥፎ ያዩት ማስታወቂያ ነው።

ማስተወቂያው ፦

° በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት ተማሪዎች ወደቤት መሄዳቸውን ይጠቁማል።

° የገበያው አለመረጋጋት አቅራቢዎች ላይ በፈጠረው ከፍተኛ ጫና እና በቀን ለ1 ተማሪ የተወሰነው 22 ብር ዕለታዊ ወጪ ጋር ተመጣጣኝ ባለመሆኑ ላልተወሰነ ጊዜ የመግቢያ ቀን መራዘሙን ያሳያል።

° ኢንተርን ሽፕ ላይ ያሉ እና ካፌ ተጠቃሚ የነበሩ እጩ ዶክተሮች በምግብ ምትክ የሚሰጠውን የነን ካፌ ፎግም ሞልተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይላል።

° የተማሪዎች መግቢያ እስኪገለጽ ከቀን 29 /11/ 2016 ዓ/ም ጀምሮ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ በመቋረጡ በተለያዩ ምክንያቶች ግቢ ያሉ ተማሪዎች በ4 ቀን ለቀው እንዲወጡ ይላል።

የተማሪዎች ቅሬታስ ምንድነው ?

መልክዕታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የላኩ ተማሪዎች ትልቅ ቅሬታ እንዳላቸው ይገልጻሉ።

ቅሬታቸው ፦

- ላለፉት ስምንት ዓመታት ትምህርት ላይ ብንሆንም አሁንም በተለያየ መልኩ ጊዜያችን እየተቃጠለ ነው።
- የመመረቂያ ጊዜያችን አሳሳቢ ሆኗል።
- መግቢያችን ለሁለተኛ ጊዜ መራዘሙ ትክክል አይደለም።
- በኮቪድ-19 ለአስር ወራት እንዲሁም በ12ኛ ክፍል ፈተና ምክንያት የትምህርት ጊዚያችን ተቃጥሏል። ወሁን የመመረቂያ ጊዚያችን ተራዝሟል።
- በዚህ ዓመት ለ12ኛ ክፍል ፈተና እንድንወጣ ተደርገን ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም ነው የተጠራነው። በኋላም ወደ ሐምሌ 25/2016 ዓ.ም ተገፋ። አሁን ደግሞ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ሰማን። ይህ ትክክል አይደለም።
- የሚመለከተው አካል መፍትሔ ይስጠን።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች ቅሬታን እንዲሁም የተለጠፈውን ማስታወቂያ ይዞ ዩኒቨርሲቲው አለኝ የሚለውን ማብራሪያ ለተማሪ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ተባባሪ  ፕሮፌሰር አለሙ ጣሚሶ ምን አሉ ?

የቀረበዉ መረጃ ትክክል አይደለም።

ኢንተርን ሀኪሞች ከግቢ አይወጡም። ዶርማቸውንም አይለቁም። ይልቁንም ለተወሰነ ጊዜ የዩኒቨርስቲው የምግብ አገልግሎት በመቋረጡ በጀታቸዉን እንዲጠቀሙ ነው የተገለጸው።

ይህ የሆነው አሁን ላይ ለ3 አመት ውል የገቡ ነጋዴዎች በእቃ መወደድ ምክኒያት ምንም አይነት የምግብ ግብአት ሊያቀርቡልን ባለመቻላቸዉና ይህን ችግር  ተወያይተን መፍትሄ እስክንሰጠዉ ነው።

ሌሎች ተማሪዎች ቅድመ ዝግጅት ከተጠናቀቀ በቅርቡ ወደ ትምህርት ገበታቸው ይመለሳሉ። ትክክለኛ ቀኑንም  ለተማሪዎች በይፋ ይነገራቸዋል።

ተማሪዎችን አሁን ላይ መቀበል ያልተቻለው ከምግብ አቅርቦትና አንዳንድ ማስተካከያ የሚፈልጉ ጉዳዮች ስላሉ ነው።

በየጊዜዉ ለ12ኛ ክፍል ፈተና ሲባል ከግቢ መውጣታቸውን ሆነ አሁን ላይ በቶሎ አለመግባታቸው የሚወስድባቸውን ጊዜ  ለማካካስ ዩኒቨርሲቲው መፍትሄዎችን አስቀምጧል። በዛ ይሄዳል።

ተማሪውን የሚያደናግር ማስታወቂያ ያወጣዉ አካል ከኛ እውቅና ዉጭ በመሆኑ ማንነቱን አጣርተን እርምጃ የምንወስድ ይሆናል።

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምና ሳይንስ ተማሪዎች ህብረት ፕሬዝደንቱ ተማሪ ደረጀ መንገሻ ምን አለ ?

👉 ኢንተርን ዶክተሮች ከግቢ ባለመውጣታቸዉ እስካሁን መጉላላት አልደረሰባቸውም። ማስታወቂያውም ያለኛ እውቅና ነው የተለጠፈው።

👉 ተማሪውን ሳይፈልግ ወደነን ካፌ መቀየር አግባብ ስላልሆነ ለዩኒቨርሲቲዉ አመራሮች ውሳኔዉ ልክ አለመሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ አስገብተን ምላሽ እየጠበቅን ነው።

👉 ተማሪዎች ሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ/ም ያልገቡበት ምክኒያት ዩኒቨርሲቲዉ ከበጀት ማስተካከያና ካምፓስ ውስጥ ከሚያስተካክላቸው አንዳንድ ነገሮች ጋር በተያያዘ ምክኒያት ነው።

👉 ተማሪዎች በጊዜ ወደ ግቢ ባለመግባታቸው በቀጣይ ተማሪዎች ላይ የሚከሰተዉን ጫና በተመለከተ ዩኒቨርሲቲው እንዲያስብበት ተነጋግረናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

More - @tikvahuniversity

@tikvahethiopia
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች

° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው ካሉ አርሶ አደሮች ቅሬታ ሲቀበል ውሏል።

አርሶ አደሮቹ ፥ " ' ያቀረብንላችሁን ምርጥ ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ ብቻዉን መውሰድ አትችሉም ' መባላችንን ተከትሎ የሚችል እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ሲገዛ የማይችል የዘር ወቅት እያለፈበት ነው " ብለዋል።

" ወቅቱ የድንች ተከላ ፣ የአደንጓሬ መዝሪያ ፣ የጎመን መትከያ እና የብዙ የክረምት ግዜ አዝመራ ስራ ነው " የሚሉት የአካባቢው አርሶ አደሮች ስለዚህም የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ቢሆንም ይህን ግን ማግኘት አልቻልነም ብለዋል።

በተለይ " ጃለለ የሚባለው ድንች ሞክረነዉ ከኛ አካባቢ ጋር የማይስማማ መሆኑን ተከትሎ ብንተወውም የወረዳው አመራሮች ግን  እንድንዘራዉ እያስገደዱን ነው " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

የአካባቢውን የአርሶ አደሮች ቅሬታ ይዘን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ፍናን አነጋግረናቸዋል።

ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ? ስንል ጠይቀናል።

እሳቸውም ፤ " ግዳጅ የሚባል ነገር የለም " በማለት አርሶ አደሩ ይሆነኛል የሚለውን ዘር በጁ ካለው ማዳበሪያ ብቻ መውሰድ ይችላል ሲሉ መልሰዋል።

" የማዳበሪያ ስርጭቱን በተመለከተ ነጋዴና ደላላ እጅ እንዳይገባ ጥንቃቄ እያደረግን ቢሆንም የትኛውም መሬቱን ዝግጁ ያደረገ ገበሬ የማዳበሪያ ችግር አይገጥመውም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግር ካለም ለመፍታት ዝግጁ ነን " ብለዋል።

አስተዳዳሪው " ዘመናዊ  የግብርና አሰራሮችን መከተልና ምርጥ ዘሮችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን እናምንበታለን " በማለት ይህንም ከወረዳዉ አርሶ አደር ጋር የጋራ መግባባት ተደርሶ እየተሰራበት ነው ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#አበሽጌ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያዊ ክልል ጉራጌ ዞን፣ አበሽጌ ወረዳ ዋልጋና ዳልጌ ከተሞች የሚኖሩ በተለይም የአማራ ወጣቶች ፣ ባለሀብቶችና አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች በጸጥታ ኃይል በአፈሳ እየተያዙ መሆናቸውን ተከትሎ ወጣቶች ከቤት ለመውጣት ፍርሀት ውስጥ መሆናቸው ተሰምቷል።

አካባቢው በተለይ ከኦሮሚያ ጋር የሚዋሰንባቸው መንደሮች ካሁን በፊት ግጭቶች መፈጸማቸውን ተከትሎ በስጋት መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች ከሰሞኑ እየሆነ ያለው ነገር እንዳሳሰባቸው ገልጸዋል።

ምንም እንኳን ወጣቱ በፍርሀት ቤቱ ቢቀመጥም አንዳንዶቹ ቤታቸዉ ባሉበት መያዛቸዉን ተከትሎ ፍርሀቱ ከፍ ሊል ችሏል።

ቃላቸውን የሰጡ አንዳድን ነዋሪዎች አፈሳው እየተደረገ ካለባቸው ምክንያቶች አንዳንዶቹ " እናተ ፋኖን ትደግፋላችሁ፤ ከፋኖ ጋርም ግንኙነት አላችሁ " የሚል ነው ብለዋል።

ሁኔታውን በተመለከተ ማን ማንን ነው እየያዘ ያለው ? ስንል የጉራጌ ዞን ፖሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ገና ደገሞን ጣይቀናል።

እሳቸውም " የተቀናጀ የጸጥታ ኃይል ወንጀለኞችን እየያዙ ነው " ብለዋል።

በተጨማሪም ሰው ፍርሀት ውስጥ ነው ለሚባለው " ወንጀል ውስጥ እጁ ካለበት ሰው ውጭ ንጹሀኑ ፍርሀት ሊገባው አይገባም " ሲሉ መልሰዋል።

" አሁን ላይ የብሄራዊ ደህንነትን ጨምሮ የፌደራል ፖሊስና መከላከያ ሰራዊት በአካባቢዉ ተሰማርተዉ አሰሳ በማድረግ የጥፋት ኃይሎችን እየያዙ ነው " በማለት አካባቢዉ በፍጥነት ወደነበረ ሰላሙ ይመለሳል ብለዋል።

ዋና ኢንስፔክተሩ አክለዉ " እንቅስቃሴዉ በአበሽጌ ወረዳና በኦሮሚያ ወሰን መካከል መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሰዎች ያለስጋት የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸውን እንዲቀጥሉ " ሲሉ ተናግረዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
🔈 #የሰራተኞችድምጽ

° " በየጊዜዉ የደመወዝ መዘግየቱ ህይወትን ከባድ አድርጎብናል " - የደቡብ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ሰራተኞች

° " አሁን ላይ ችግሩ ተቀርፏል ከዚህ በኋላ የደሞዝ መዘግየት ይኖራል ተብሎ አይታሰብም " -ምላሽ የሰጡን አመራር


" የደመወዝ መዘግየት ፈተና ሆኖብናል " ያሉ የደቡብ ሬዲዬና ቴሌቪዥን ሰራተኞች ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ደመወዝ በየወቅቱ ሳይከፈል አይደለም እየተከፈለን እንኳን ኑሮ ከባድ ሆኖብናል " የሚሉት ሰራተኞቹ " በተለያዬ ምክኒያት በ25 ወይም በ26 የሚገባዉ ደሞዝ እስከሁለት ሳምንት እየዘገዬ መግባቱ ችግር እየፈጠረብን ነው " ብለዋል።

" አሁን ላይ የሀምሌ ወር ደሞዛችን ባለመግባቱ ቤት አከራዮቻችን ሽሽት ላይ ነን " የሚሉት ሰራተኞቹ " ኑሮን ደግሞ የምታዉቁት ነው " በማለት የሚመለከታቸዉ አካላት ለችግራቸው ዘላቂ መፍትሄ እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

በጉዳዩ ላይ ስሜ አይጠቀስ ብለዉ አስተያየታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንድ የድርጅቱ አመራር " አሁን ላይ ከሶስቱ ክልሎች ማለትም ከደቡብ ኢትዮጵያ ፣ ከደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያና ከመእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች ጋር መግባባት ላይ ተደርሶ የበጀት መልቀቅና ገንዘብ የማዘዋወር እንቅስቃሴ ተጀምሯል " ሲሉ ተናግረዋል።

ከሶስቱ ክልሎች በተጨማሪ የሲዳማ ክልል ገና ዉሳኔ ላይ አለመድረሱን የገለጹት ኃላፊው ከነሱም ጋር ያለው ሁኔታ ቀስ ብሎ በውይይት መፍትሄ እንደሚፈለግለትና ከዚህ በኋላ ችግር ይኖራል ብለው እንደማያስቡ ገልጸዋል።

ከዚህ ቀደም የዚሁ ተቋም ሰራተኞች ከደመወዝ ጋር በተያያዘ ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ማሰማታቸው ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የነዋሪዎችድምጽ

ሰሞኑን " ዶላር በጣም ጨምሯል " በሚል የዋጋ ጭማሪ እያደረጉ የሚገኙ የንግዱ አካላት እጅግ እያማረሯቸዉ መሆኑን የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቤት ብለዋል።

" አሁን ላይ ነጋዴው እቃውን በሌሎች ነጋዴዎች ሱቅና በራሱ መጋዘን ሲያስቀምጥ አይናችን እያዬ እቃዉ የለም በሚል ዋጋ ሊጨምር ሲሞክር ማየት ያማል " ሲሉ ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ፥ " እስከ 1,080 ብር የነበረዉ ዘይት 1380 ብር ሲገባ ዶላር ነው " አሉን " እሺ የቲማቲምና ሽንኩርቱስ ዋጋ መናር ከየት መጣ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

1 ኪሎ ሽንኩርት ከ40 ብር ተነስቶ 90 ብር ቲማቲም 20 ብር የነበረው 40 እና 45 መግባቱን ጤፍም በኪሎ ከ10 ብር በላይ እንደጨመረ ጠቁመዋል።

ስሚንቶ ላለፉት ወራት ጥሩ ቢሆንም አሁን ላይ " የለም " እየተባለ እንደሆነ ገልጸዋል።

የነዳጅ ጉዳይ ግን በፊትም አንስቶ ፈተና ነበር አሁን ብሶበት ራስ ምታት ሆኖ ቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ሀዋሳ ላይ የገበያውን ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የተቋቋመ ግብረሀይል መኖሩን በመስማታችን  የነዋሪዎችን ቅሬታ ይዘን የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ አዛዡ ኢንስፔክተር መልካሙ አየለን አነጋግረናል።

እሳቸውም ፥  " አሁን ላይ እቃ በሚደብቁ እና አላግባብ ዋጋ በሚጨምሩ ህገወጥ ነጋዴዎች ላይ ግብረሀይሉ  ጠንካራ እርምጃ እየወሰደ ነው " ብለዋል

ግብረሀይሉ  በሰራዉ ስራ ሁለት ማደያዎች እና 62 የሸቀጣሸቀጥ ሱቆች የምግብ ግብአትና የብረታብረት አቅራቢዎች በ8ቱ ክፍለ ከተሞች  መታሸጋቸዉንና እቃዎችም ተወርሰዉ ህገወጦቹ ግለሰቦች  በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን ገልጸዋል።

ክትትሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚገልጹት አዛዡ ማህበረሰቡም ህገወጦችን በመጠቆም የፖሊስን ስራ እንዲያግዙ ጥሪ አቅርበዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የመምህራንድምጽ

° " ግንባታው እንዲቆም ተደርጎብናል " - መምህራን

° " ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደውታል፤ ምርመራ ተጀምሯል " - የሀዋሳ ፖሊስ

ከሰሞኑን " በማህበር ተደራጅተን የምንገነባውን የመኖሪያ ቤት ግንባታ በማስቆም እንዲገነባልን ውል የገባውን ተቋራጭ አሰሩብን " ያሉ የሀዋሳ ከተማ መምህራን ቅሬታቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አቅርበዋል።

መምህራኑ " አመራሩ ሊደግፈን ሲገባ እየገፋን ነው " ብለዋል።

" በሀገሪቱ ጠ/ ሚኒስትር ሳይቀር ለመምህራን ድጋፍ ተደርጎ የቤት ባለቤት የምንሆንበት መንገድ ይመቻች በተባለበት በዚህ ወቅት መምህራን የሚገነቡትን ቤት አስቁሞ ተቋራጭን ማሰር መንግስትና መምህራንን ለማጋጨት የታሰበ ሴራ እንጅ ሌላ ምንም አይደለም " ብለዋል።

" ድርጊቱ አሳፋሪ ነው " ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።

መምህራኑ፤ ከሳምንት በፊት አመራሩ በመምጣት " በርቱ " እንዳላቸውና ከፌደራል ሳይቀር እንግዳ ጋብዞ ፣ እገዛ ልናደርግ ዝግጁ ነን " እንዳላቸው ተናግረዋል።

በድንገት ግን ተገልብጦ ስራው ህጋዊ አይደለም ማለቱን ጠቁመዋል።

" ችግሮች ቢኖሩ እንኳን በውይይት ማስተካከል ይቻላል " የሚሉት መምህራኑ ለ9 አመታት የቆመ ቤት ድንገት መሰራት ሲጀምር ለማስቆም መሯሯጥ ከጀርባው ሌላ ዓላማ ያነገበ እንዳይሆን ስጋታቸውን ገልጸዋል።

መምህራኑ ህጋዊ በሆነ መንገድ የሚያሰሩትን የህንጻ ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 መቀየራቸውን የከተማው ማዘጋጃ ቤት የማህበራት ማደራጃ እና የከንቲባ ጽህፈት ቤት የሚያውቀው እንደሆነ ጠቁመዋል።

ይህ ሆኖ እያለ ግንባታው #እንዲቆም መታዘዙን ገልጸው ፤ " ወቅቱ መምህራን የሚደገፉበት እንጅ ጥሪታቸውን ያፈሰሱበትን የሚቀሙበት አይደለምና እንቅፋት የሆኑብን አካላት ሊተዉን ይገባል " ብለዋል።

" በህግ አምላክ እጃችሁን ከድሀው መምህራን ላይ አንሱልን ፤ ይህ ባይሆን ግን አደባባይ በመውጣት ጩኸታችንን ለማሰማት ዝግጁ ነን " ሲሉም ተናግረዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የከተማው አስተዳደር ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ በአጠቃላይ ለስድስት የመምህራን መ/ቤቶች ህብረት ስራ ማህበራት የጻፈውን ደብዳቤ ደርሶት ተመልክቷል።

በዚህም ደብዳቤው ፦

- የነበረው ዲዛይን ከG+3 ወደ G+4 ማስተካከያ እንዲደረግ ተጠይቆ የG+4 ዲዛይን መሰጠቱ ፤

- ነገር ግን ይህ ዲዛይን የመምህራን መ/ቤቶች ማህበራት ከተደራጁበት አላማ አንጻር ተጻራሪ ዓላማ እንዳለው ስለተደረሰበት የG+4 ዲዛይን መሰረዙን ሌላ ደብዳቤ እስኪላክላቸው ድረስ ቀድሞ በነበረውም G+3 ዲዛይን ግንባታ ማካሄድ እንደማይችሉ ያዛል።

የመምህራኑን ጥያቄ ይዘን ጥያቄ ያቀረብንለት የከተማው ፖሊስ ጉዳዩን የጸረሙስና አካላት ወደ ፍርድ ቤት ወስደዉ ምርመራ እንደጀመሩበት በመግለጽ ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥቧል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
#Gamo : ሰሞኑን ለሶስት ተከታታይ ቀናት በጣለ ከባድ ዝናብ በተፈጠረ የመሬት መንሸራተት በጋሞ ዞን በገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካምአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል። መረጃው  የገረሴ ዙሪያ ወረዳ ኮሙዩኒኬሽን ጉ/ጽ/ቤት ነው። @tikvahethiopia
#Update

" አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል ናቸው " - በጋሞ ዞን የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ

በጋሞ ዞን፣ ገረሴ ዙሪያ ወረዳ ካማአለ ባርኤ ኦሮ ቀበሌ በደረሰ የናዳ አደጋ የ4 ሰዎች ህይወት ማለፉ ይወቃል።

ከዚህ ባለፈ ደግሞ ከሰላሳ ሰባት በላይ የቤት እንስሳት ላይ ጉዳት ደርሷል ፤ 15 ቤቶችም መፍረሳቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተረድቷል።

የገረሴ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ካሳሁን ካማ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፥ " የሟቾችን ቀብር ከአካባቢዉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን በክብር አስፈጽመናል " ብለዋል።

በአካባቢዉ ችግር ይከሰታል የሚል ቅድመ ትንበያም ይሁን ግምት ፈጽሞ እንዳልነበር ይልቁኑ በቀርከሀ የተሞላ ደን እያለ አደጋዉ መከሰቱ ሁኔታዉን አስደንጋጭ አድርጎታል ሲሉ ገልጸዋል።

አራቱ ሟቾች የአንድ ቤተሰብ አባል መሆናቸዉን የገለጹት አስተዳዳሪው በአንድ ቤት ዉስጥ ከነበሩት ሰባት ሰዎች ውስጥ በጓዳ የነበሩት አራቱ ሞተው ሶስቱ ከጓዳ ወጭ የነበሩት መትረፋቸውን ነግረውናል።

የሟቾች ስርዓተ ቀብር ከተፈፀመ በኃላ ወደ ቀጣይ ተግባር ተገብቷል ሲሉም ገልጸዋል።

አሁን ላይ የዝናቡ መጠን ከፍ እንደሚል መረጃ ማግኘታቸውን ተከትሎ ሌላ አደጋ እንዳይከሰት እንቅስቃሴ መጀመሩንና የአካባቢውን ሰው በማሸሽ በአጎራባች ቀበሌዎች ውስጥ ባሉ ትምህርት ቤቶች የጤና ኬላዎችና የእምነት ቦታዎች ማሳረፍ መጀመሩን አመልክተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ወንድም እና እህቱን በቁጥጥር ስር አድርገን ምርመራ እያካሄድን ነው " - የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የባህር ዳር ከተማ የመሀል ሜዳው ተጫዋች አለልኝ አዘነ ለህልፈት መዳረጉን ተከትሎ ቤተሰቦቹ  በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል። የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል ፥ " አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ የቅርብ ግንኙነት…
የእግር ኳስ ተጫዋቹ አለልኝ አዘነ ጉዳይ የት ደረሰ ?

የባህር ዳር ከነማው የመሀል ሜዳ ተጫዋች አለልኝ አዘነ ከወራት በፊት አሟሟቱ ድንገተኛና አሰቃቂ መሆኑን ተከትሎ " የቅርብ ግንኙነት ያላቸውን አካላት ይዤ ምርመራ ጀምሪያለሁ " ያለው የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ " ጉዳዩን በፍጥነት በማጣራት በቅርብ ለኢትዮጵያ ህዝብ የደረስኩበትን አደርሳለሁ " በማለት ቃል ገብቶ ነበር።

ይሁንና በጉዳዩ ላይ ሀምሌ ወር ውስጥ መግለጫ ይሰጣል መባሉ በተጨማሪ ለእስር የተዳረጉት የተጫዋቹ የቅርብ ሰዎች መሆናቸውን ተከትሎ ጉዳዩ የት ደረሰ ? የሚለው ትልቅ ጥያቄ ነው።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥያቄ ያቀረበለት የጋሞ ዞን ፍ/ቤት ጉዳዩ ወደ ፍ/ቤት አለመመራቱንና ክስ ባልተከፈተበት በጉዳዩ ላይ መረጃ መስጠት እንደማይችል ገልጾልናል።

ይህንንም ተከትሎ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወቅቱ ጉዳዩን እንደያዙትና ከምርመራ በኋላ የተደረሠበትን ጉዳይ ለህዝብ እንደሚያደርሱ ቃል የገቡልን በወቅቱ የአርባ ምንጭ ከተማ ፖሊስ አዛዥ የነበሩትን ኢንስፔክተር አብርሀምን አነጋግረናቸው ነበር።

አዛዡ በወቅቱ የሟችን ቤተሰቦች በቁጥጥር ስር አድርገው ምርመራ እያካሄዱ እንደነበር አስታውሰው አሁንም ጉዳዩ ምርመራ ላይ እንደሆነ በመግለጽ ከቦታው በመነሳታቸው እንዲሁም የፖሊስ አሰራር በዚህ ሰአት መረጃ መስጠትን ስለሚከለክል ዝርዝር መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ጉዳዩን አሁንም ይከታተላል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
🔈 #የመምህራንድምጽ

" መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " - የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን

" በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል " - የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊ

ከሰሞኑ በተደጋጋሚ በደረሰን የቅሬታ መልእክት በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የደቡብ ኦሞ ዞን መምህራን ላለፉት ሁለት ወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸዉ በመግለጽ በተለያዩ ፕሮግራሞች ውስጥ መሳተፍ እንዳልቻሉ ነግረዉናል።

መምህራኑ እንደሚሉት አሁን ላይ ከፊሉ በመንግስት አቅም ማሻሻያ ፕሮግራሞች ግማሹ ደግሞ በራሱ ፍላጎት ወደተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ቢያቀናም ደሞዝ አለመለቀቁን ተከትሎ ግን ችግር ላይ ወድቀዋል።

አሁን ላይ በገቡባቸዉ ዩኒቨርሲቲዎች ዉስጥ አላማቸዉን ካለማሳካታቸዉ ባለፈ ጥለዋቸዉ የመጡ ቤተሰቦቻቼዉ ረሀብ ላይ መዉደቃቸዉን ተከትሎ የሄዱበትን የትምህርትና ስልጠና ፕሮግራሞች ጥለዉ ለቀን ስራ መዳረጋቸዉን ይገልጻሉ።

ከዚህ በተጨማሪ በትራንስፖርት ችግር ምክኒያት ብዙ መምህራን በሚያስተምርበት አካባቢ ቢቀሩም በእንቅርት ላይ እንዲሉ ባሉበት አካባቢም የወባ ወረሽኝ አስቸጋሪ ሆኖባቸዋል።

ችግሩን የመንግስት አካላት ያዉቁታል የሚሉት የጎሪጌሻ የሜኒት ማጅና ቱም የጎልዲያና ሻሻ እንዲሁም የጋቺት እና ሱርማ ወረዳ  ቅሬታ አቅራቢዎች " መምህራን እየተራቡ ስለትምህርት ጥራት ማዉራት አግባብ አይደለም " ብለዋል።

በጉዳዩ ላይ ከቀናት በፊት ያነጋገርናቸዉ የዞኑ ትምህርት መምሪያ ሀላፊዉ አቶ  በበኩላቸዉ በዚህ ደረጃ ክፍያ ይዘገያል ብለን ባናስብም ችግሩ ካለ በቅርብ ይፈታል ብለዋል።

ሀላፊዉ አክለዉም ምናልባትም ችግሩ የበጀት ከሆነ አሁን ላይ በየወረዳዉ ግብር እየተሰበሰበ በመሆኑ በተቻለ ፍጥነት ችግሩ  ይፈታል በማለት የደሞዝ ችግሮ በቅርቡ እንደሚፈታ ገልጸዉልናል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM