TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ክፍት የስራ መደብ ማስታወቂያ🔝

#HawassaUniversity #ሀዋሳ_ዩኒቨርሲቲ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#HawassaUniversity #StopHateSpeech

እናት ሀገር ኢትዮጵያ
ኢትዮጵያ የኛ መመኪያ


የTIKVAH-ETH የStopHateSpeech የዩኒቨርሲቲ እንቅስቃሴዎችን በዚህ የዩትዩብ ቻናላችን ማግኘት ትችላላችሁ፦ https://www.youtube.com/channel/UCbHAotwR_yPhyv5lliObk6w
#HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ከቀን 08-12/2012 ዓ/ም ትምህርት አይኖርም በማለት አንድ አንድ ተማሪዎች የተሳሳተ መረጃ እያሰራጩ መሆኑን ደርሼበታለሁ፤ እንዲያህ ያለ ነገር እያሰራጩ ያሉ አካላት ከድርጊታቸው ይቆጠቡ ሲል አስጠንቅቋል። በተሰራጨው የተሳሳተ መረጃ ግቢው ለቀው እየወጡ ያሉ ተማሪዎች እንዳሉ አረጋግጠናል ብሏል ተቋሙ። የትምህርት ስርዓቱ እንደማይቋረጥ የገለፀው ዩኒቨርሲቲው ግቢውን ጥለው የሄዱ ተማሪዎችም በትምህርታቸው ላይ በሚደርስባቸው እክል ሃላፊነቱን እራሳቸው ይወስዳሉ ሲል ገልጿል።

@tikvahethiopiabot @tikvahethiopia
አልፈልግም ማለት አልፈልግም ነው!

• "አቁም" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መሸሽ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "እምቢ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መግፋት/መገፍተር" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ዝግጁ አይደለሁም" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ተወኝ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ዞር በል" ማለት አልፈልግም ነው!
• "መጮህ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "እረፍ" ማለት አልፈልግም ነው!
• "ማልቀስ" ማለት አልፈልግም ነው!

የሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ያንቺ ንቅናቄ ( Yanchi movement ) ለሶስት ቀን በሚቆየው የሴት ልጅ ጥቃትን በመቃወም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ አዘጋጅተዋል፡፡ ዝግጅቱ ትላንት የተጀመረ ሲሆን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የ16 ቀን ንቅናቄ አንድ አካል እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ አዘጋጆቹ ገልጸውልናል፡፡ በዚህ ንቅናቄ በዩኒቨርሲቲው የሚገኙ ሌሎች ክበባትም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በሌላ በኩል በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የሚገኘው "መራሂት ክበብ" አትኩሮቱን ሴት ተማሪዎችን በማብቃት ላይ አድርጎ እየሰራ ሲሆን ለሴት ተማሪዎች የፅዳት መጠበቂያ የሚሆን 88 ካርቶን ሞዴስ በመግዛት ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የሴቶች ህፃናት ወጣቶች እና ኤችአይቪ ኤድስ ዳይሬክትቶሬት አስረክበዋል። የመጀመሪያውን ድጋፋቸውንም የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ቅርንጫፍ በሆነው በአዋዳ ካምፓስ አድርገዋል።

- በቲክቫህ ኢትዮጵያ ስም እየሰራችሁት ላለው መልካም ስራና ለሌሎች ወጣቶች ትምህርት የሚሰጥ ተግባር ላይ በመሳተፋችሁ ያለንን አክብሮት እና ምስጋና እናቀርባለን!

#HawassaUniversity

በርቱልን!
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#AGIIBARIIS #HawassaUniversity

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተሰራ ድራማቲክ ፋንታሲ ዘውግ ያለው ፊልም ሊመረቅ መሆኑን ሰምተናል፡፡ አግባሪስ ከተለመደው የሰው ልጅ አኗኗር መስመር ገለልተኛ የሆኑ ነገሮችን ይቃኛልም ተብሏል። የምረቃት ዝግጅቱ ቅዳሜ 8:00 ሰዓት ላይ የተለያዩ ጥበብ ተኮር ዝግጅቶች ፉሽን ሾው እና ስነ–ፁሁፍ ዝግጅቶችን ጨምሮ ተጋባዥ እንግዶች በተገኙበት በአዲሱ ሀዋሳ ሌዊ ሲኒማ ይመረቃል።

(በኩሉ ኢቨንት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በ2012 ዓ/ም ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ነሐሴ 23 በVirtual Graduation Ceremony ያስመርቃል።

ተመራቂ ተማሪዎች የምረቃት ፕሮግራሙን በቤታቸው ሆነው በዩኒቨርሲቲው ይፋዊ ፌስቡክ (FaceBook) ገፅ በቀጥታ መከታተል እንደሚችሉ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው በላከልን መረጃ መሰረት ነሃሴ 23/2012 ዓ/ም የሚመረቁት 4,800 (አራት ሺህ ስምንት መቶ) ተማሪዎች ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በCOVID-19 ቫይረስ ወረርሺን ምክንያት የተቋረጠውን የ2012 ዓ.ም የሁለተኛ ሴሚስተር ት/ት ለማስጀመር የቅድመ ዝግጅት ማጠቃለያ ውይይት ማካሄዱን ገልጾልናል።

በዩኒቨርሲቲው ባሉ ሁሉም ኮሌጆች የተቋረጠውን ትምህርት ማስቀጠልን በተመለከተ ፦

• ከመግበያ በሮች ጀምሮ በማደሪያ ክፍሎች፤
• በቤተመፃህፍት፤
• ቤተ ሙከራዎች እንዲሁም በካፍቴሪያዎች የተዘጋጀውን የCOVID19 መመሪያ በመከተል አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት የማድረግ ስራው በአብዛኛው ተጠናቋል።

በቀሩት ጥቂት ቀናት ደግሞ የተቀሩትን የዝግጅት ስራዎች በማጠናቀቅ ተማሪዎችን በታቀደው መርሀግብር መቀበል እንደሚቻል ውሳኔ ላይ ተደርሷል፡፡

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ነገ ተማሪዎቹን ያስመርቃል። ዩኒቨርሲቲው ነገ 6,263 ተማሪዎችን እንደሚያስመርቅ የዩኒቨርሲቲው የውጭ ግንኙነት እና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር ወ/ሮ አርማዬ አሰፋ አሳውቀውናል። ከተመራቂዎቹ መካከል 4,119 ወንዶች ሲሆኑ 2,144 ሴቶች ናቸው። • 5,135 - በመደበኛ • 624 - በማታ • 394 - በሳምንት መጨረሻ • 110 - በክረምት መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።…
#HawassaUniversity

ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዩኒቨርሲቲው 6,263 ተማሪዎችን ነው እያስመረቀ የሚገኘው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 4,119 ወንዶች ሲሆኑ 2,144 ሴቶች ናቸው።

ተመራቂዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች፣ የሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ፣ የክብር እንግዶች የስነ ስርዓቱ ተሳታፊ ናቸው።

PHOTO : SRTA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HawassaUniversity

ዛሬ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 270 የህክምና ዶክተሮችን አስመርቋል።

ከተመራቂዎቹ መካከል 48ቱ በተለያዩ የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራም የሰለጠኑ ናቸው።

የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዶክተሮችን ሲያስመርቅ የዛሬው ለ12ኛ ጊዜ ነው።

በሌላ በኩል ፦ ከ12ኛ ዙር ተመራቂዎች መካከል ዶክተር ዮናስ ንጉሴ 3 ነጥብ 87 ውጤት በማምጣት የወርቅ ሜዳሊያ ተሻላሚ መሆን ችሏል።

በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ የህክምና ትምህርት ክፍል እስካሁን ከተመዘገቡ ውጤቶች ውስጥ ከፍተኛው በመሆንም ክብረወሰን ሆኖ ተመዝግቧል።

ምንጭ፦ SRTA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
* Congratulations !

በዛሬው ዕለት ብቻ ከተለያዩት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ከ30,192 በላይ ተማሪዎች ተመርቀዋል።

የትኞቹ ዩኒቨርሲቲዎች ምን ያህል ተማሪ ? በምን ደረጃ እና የትምህርት ዘረፍ አስመረቁ ? ለጥያቄዎቹ መልስ ይህን አጭር ቁጥራዊ መረጃ አስቀምጠናል።

#HawassaUniversity

- አጠቃላይ 6 ሺህ 793 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 2 ሺህ 158ቱ ወይም 32 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ በመደበኛና ተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

#BahirdarUniversity

- አጠቃላይ 5 ሺህ 586 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 714ቱ ሴቶች ናቸው።
- በመጀመሪያ፣ በ2ኛ እና በ3ኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናሰቁ ናቸው።

#JimmaUniversity

- አጠቃላይ 696 ተማሪዎች አሰመርቋል።
- 450 ወንድ እና 246 ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 252 ተማሪዎች በአጠቃላይ ሕክምናና በጥርስ ሕክምና የሰለጠኑ ናቸው።
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ በሶማሊላንድ ሀርጌሳ ካምፓሱ በ 'ኒውትሬሽን' የትምህርት ዘርፍ ያስተማራቸውን 19 የ2ኛ ዲግሪ ተማሪዎችንም አስመርቋል።

#AdamaScience_and_TechnologyUniversity (ASTU)

- አጠቃላይ 1 ሺህ 298 ተማሪዎች አስመርቋል።
- ሰባቱ በሦሥተኛ ዲግሪ (ፒኤችዲ) ተመራቂዎች ናቸው።
- 215ቱ በሁለተኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።
- 1 ሺህ 76 ተማሪዎች በመጀመረያ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

#MettuUniversity

- አጠቃላይ 2 ሺህ 262 ተማሪዎች አስመርቋል።
- 116ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በመደበኛ እና በተከታታይ መርሃ ግብሮች በመቱ እና በበደሌ ካምፓሶች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

#ArsiUniversity

- አጠቃላይ 831 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- በበቆጂ ካምፓስ የሰለጠኑ ናቸው።
- ተመራቂዎቹ በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ በመደበኛና በተከታታይ መርሃ ግብሮች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- በመጀመሪያ እና በ2ኛ ዲግሪ ከተመረቁት መካከል 392ቱ ሴቶች ናቸው።

#AmboUniversity

- አጠቃላይ 4 ሺህ 524 ተማሪዎች አስመርቋል።
- በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ የሰለጠኑ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ 1 ሺህ 980ዎቹ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 450 የሚሆኑት የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂ ሲሆኑ 11 የደቡብ ሱዳን ስደተኛ ተማሪዎች ይገኙበታል።

#JigjigaUniversity

- አጠቃላይ 1 ሺህ 202 ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከጠቅላላ ተመራቂዎቹ 336ቱ ሴት ተማሪዎች ናቸው።
- 233ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን ቀሪዎቹ 969ኙ በመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።

* ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መካከል #AdmasUniversity

- አጠቃላይ ከ10 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አስመርቋል።
- ከተመራቂዎቹ 67 በመቶ ሴቶች ናቸው።
- በቴክኒክና ሙያ፣ በመጀመሪያ ዲግሪ እና 2ኛ ድግሪ በቀንና በማታ ትምህርታቸውን የተከታተሉ ናቸው።
- ከተመራቂዎቹ መካከል 1 ሺህ 532ቱ በ2ኛ ዲግሪ የተመረቁ ናቸው።

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጉዳዮችን በ @tikvahuniversity ተከታተሉ።

@tikvahethiopia