TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች

° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ


ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ ከሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው ካሉ አርሶ አደሮች ቅሬታ ሲቀበል ውሏል።

አርሶ አደሮቹ ፥ " ' ያቀረብንላችሁን ምርጥ ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ ብቻዉን መውሰድ አትችሉም ' መባላችንን ተከትሎ የሚችል እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ሲገዛ የማይችል የዘር ወቅት እያለፈበት ነው " ብለዋል።

" ወቅቱ የድንች ተከላ ፣ የአደንጓሬ መዝሪያ ፣ የጎመን መትከያ እና የብዙ የክረምት ግዜ አዝመራ ስራ ነው " የሚሉት የአካባቢው አርሶ አደሮች ስለዚህም የአፈር ማዳበሪያ አማራጭ ሳይሆን ግዴታ ቢሆንም ይህን ግን ማግኘት አልቻልነም ብለዋል።

በተለይ " ጃለለ የሚባለው ድንች ሞክረነዉ ከኛ አካባቢ ጋር የማይስማማ መሆኑን ተከትሎ ብንተወውም የወረዳው አመራሮች ግን  እንድንዘራዉ እያስገደዱን ነው " ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል።

የአካባቢውን የአርሶ አደሮች ቅሬታ ይዘን የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ አሰፋ ፍናን አነጋግረናቸዋል።

ለምን እንዲህ ታደርጋላችሁ ? ስንል ጠይቀናል።

እሳቸውም ፤ " ግዳጅ የሚባል ነገር የለም " በማለት አርሶ አደሩ ይሆነኛል የሚለውን ዘር በጁ ካለው ማዳበሪያ ብቻ መውሰድ ይችላል ሲሉ መልሰዋል።

" የማዳበሪያ ስርጭቱን በተመለከተ ነጋዴና ደላላ እጅ እንዳይገባ ጥንቃቄ እያደረግን ቢሆንም የትኛውም መሬቱን ዝግጁ ያደረገ ገበሬ የማዳበሪያ ችግር አይገጥመውም " ሲሉ ገልጸዋል።

" ችግር ካለም ለመፍታት ዝግጁ ነን " ብለዋል።

አስተዳዳሪው " ዘመናዊ  የግብርና አሰራሮችን መከተልና ምርጥ ዘሮችን መጠቀም አስፈላጊ መሆኑን እናምንበታለን " በማለት ይህንም ከወረዳዉ አርሶ አደር ጋር የጋራ መግባባት ተደርሶ እየተሰራበት ነው ሲሉ መልሰዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
TIKVAH-ETHIOPIA
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ ° " ' እኛ ያቀረብነውን ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አትወስዱም ' በመባላችን የእርሻ ወቅት እንዳያልፍብን እስከ 8 ሺህ ብር ማዳበሪያ ለመግዛት ተገደናል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ ሻመና ከተማና አካባቢው አርሶአደሮች ° " ያቀረብነውን ምርጥ ዘር ካልወሰዳችሁ ብሎ ያስገደደ የለም ማዳበሪያ ብቻ የሚፈልግ መውሰድ ይችላል " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አስተዳዳሪ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዛሬ…
🔈 #የአርሶአደሮችድምጽ

ሲዳማ !

" የማዳበሪያ ችግር የለም ተብሎ በሚዲያ ቢነገርም በቂ ማዳበሪያ እየደረሰን አይደለም " - የሀዋሳ ዙሪያ ወረዳ አርሶ አደሮች

ከሰሞኑ " ዘር ካልገዛችሁ ማዳበሪያ አይሰጣችሁም ተባልን " ያሉ የሀዋሳ ዙሪያ አርሶ አደሮች ቅሬታ ማቅረባቸዉን ዘግበን ነበር።

በወቅቱ  የማዳበሪያ ችግር እንደሌለና ወደግብርና ቢሮ በመምጣት መዉሰድ እንደሚቻል ከምርጥ ዘር ጋር በተያያዘ አርሶአደሩን የሚጠቅም አካሄድ መሆኑን ይሁንና ገበሬዉ የራሱ ዘር ካለዉ እንደማይገደደ ተገልጾም ነበር።

ይሁንና ከመረጃዉ በኋላ " የማዳበሪያ ችግር የለም " ተብሎ በሚዲያ ምላሽ ከመሰጠቱ በላይ በስብሰባ ወቅት " መጋዝናችን ሙሉ ነዉ " ብንባልም በአግባቡ እየተሰጠን አይደለም ሲሉ በድጋሜ የአካባቢዉ አርሶአደሮች ቅሬታ አቅርበዉልናል።

" አሁን ላይ የዘር ወቅት እያለፈ በመሆኑ ከፍተኛ ስጋት ዉስጥ ገብተናል " የሚሉት አርሶ አደሮቹ " አራትና አምስት  ኩንታል ለሚያስፈልገዉ አምስት ሄክታር የለሰለሰ ማሳ አንድ ኩንታል ብቻ ስለምን እንደሚሰጠን አይገባንም " በማለት ቅሬታቸውን ገልጸዋል።

" ማዳበሪያዉ በቂ አለመሆኑን የአካባቢዉ የግብርና ባለሙያዎች ያውቃሉ። እንደኛ ከማዘን ዉጭ መፍትሄ መስጠት አልቻሉም " ሲሉ ገልጸዉ ጉዳዩ በአመራሩ እጅ መያዙን አስረድተዋል።

ከዚህ በተጨማሪም ፥ " ቀኑን ሙሉ ስራ በመፍታት መጋዝን በር ላይ የሚዉለዉ አርሶ አደር ሀያ ሰላሳ ሰዎች ከተስተናገዱ በኋላ ወደቤታችሁ ሂዱ ይባላል በማለት መጋዝኑን የሞላዉ ማዳበሪያ ለማን ነዉ ? " በማለት ጠይቀዋል።

ከሳምንት በፊት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ " የማዳበሪያ ችግር የለም ከአካባቢዉ አርሶ አደር ጋርም የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል " ያሉት የወረዳዉ አስተዳዳሪ  " መሬቱን ያዘጋጀ ገበሬ የፈለገዉን ያክል ማዳበሪያ መዉስድ ይችላል " በማለት አንዳች ቅሬታ ያለበት አርሶ አደር ካለ ሊያናግረን ይችላል ማለታቸዉ ይታወሳል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🔈#የአርሶአደሮችድምጽ

" እኛ ተጠቃሚ ነን አንልም ሚጠቀመው ሌላ አካል ነው " - ቡና አምራች አርሶአደሮች

በሲዳማ ክልል 170 ሺህ ሄክታር በቡና የተሸፈነ ሲሆን ከዚህም ውስጥ 143 ሺህ ሄክታሩ ምርት የሚሰጥ ነው ከዛ 159 ሺህ ቶን ይጠበቃል። አጠቃላይ 401 ሺህ ቡና አምራች የሆነ አርሶ አደርም በክልሉ በዚሁ ዘርፍ ተሰማርቶ ይገኛል።

ሆኖም ቡና አምራች አርሶአደሮች ከተጠቃሚነት አንጻር ቅሬታ ሲያቀርቡ ይደመጣል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች ቡናን የሚያመርቱ አርሷደሮችን ጠይቋል።

ቡና አምራች አርሷደሮች ምን አሉ ?

የቡና ተክል ተክለን ፍሬ ለማግኘት ከ3 እስከ 5 ዓመት እንደሚፈጅባቸው የነገሩን አንድ አርሶአደር፥ ቡና በማምረት ውስጥ ያለው ድካም ቀላል እንዳልሆነና ነገር ግን ፍሬው ሲታይ ድካሙ ሁሉ እንደሚጠፋ ይገልጻሉ።

" ሆኖም ለገቢያ ሲወጣ የሚቀርብበት የሽያጭ ዋጋ ልብ ሰባሪ ነው" ሲሉ ነው የተናገሩት።

" ልክ ካመረትን በኋላ ለነጋዴዎች ነው ምናስረክበው ለማህበራት ሚያስረክቡም አሉ። አምና መጨረሻው 30 ብር ነበር ዘንድሮ 35 ብር ነበር የጀመረው አሁን 45 ብር ደርሷል በኪሎ ይህ ደሞ ከልፋታችን አንጻር በጣም የወረደ ሂሳብ ነው " ሲሉ ያስረዳሉ።

" እኛ ተጠቃሚ ነን አንልም ሚጠቀመው ሌላ አካል ነው (በስም ያልገለጿቸው) እንደውም አንዳንዴ መሬቱን ሽጠን ወደሌላ ዘርፍ እንግባ ብለንም እናስባለን፣ በዚህ ሰዓት ቡና ብቻ አምርቼ ኖራለው ብሎ ማሰብ ከባድ ነው " ሲሉም ጉዳቱን ያነሳሉ።

" በአሁን ገበያ አንድ ሰራተኛ ቡና ሊለቅም እንኳን ሚገባ በ120 ብር ነው ሚሰራው አሁን ላይ የሚሸጠው በ45 ብር ነው ምናልባት 10 ሰው ሊለቅም ከገባ ገንዘቡ ለዛ ብቻ ነው ሚውለው ማለት ነው። እንደውም አምና ለሰራተኛ ብቻ ሰጥተን ነው የገባነው ዘንድሮም ያው ነው " በማለት ቅሬታቸውን ያቀርባሉ።

ለመሆኑ ዋጋውን የሚወስነው ማነው ?

" ዋጋውን እራሳቸው ይወስናሉ እኛ ማን እንደሚወስን የምናውቀው ነገር የለም በዚህ ያህል ተከፈተ ሲባል ነው የምናውቀው ህብረቱም በዚህ ዋጋ ከፈተ ሲባል ነው ምንሰማው፣ ምናልባት ባለሀብቱ አንድ ብር እንኳን አሳልፎ ከገዛ እንኳን ያንን ባለሀብት ተረባርበው እንዴት እንዲህ አደረክ ብለው ወዲያው ይጣሉታል የትኛው አካል እንደዚህ እንደሚያደርግ ግን አናውቅም " ሲሉ አርሶ አደሮቹ ይናገራሉ።

አክለውም፥ " እነሱ እኮ (ቡናውን የሚረከቡት ለማለት ነው) ስራውን በጀመሩ ሦስት እና አራት ዓመት ነው በብልጽግና ማማ ላይ የሚወጡት በጣም አልፈው ነው ሚሄዱት፤ አርሷደሩ እንደለፋ አላገኘም ባለስልጣናቱም ጭምር በእኛ ዘንድ ይታማሉም " ብለውናል።

" የሚመለከተው አካል ቢደርስልን እየተንገዳገድን ነው ወደ መውደቅ እየደረስን ነው ታች ተወርዶ ምን እየተካሄደ ነው ሚለውን አይቶ የቡናን ነገር ቢያይልን የዋጋውን ነገር ቢመለከትልን " ሲሉም ጠይቀዋል።

" ቡናችን ለአርሷደሩ ብቻ ሳይሆን ለሀገር የሚጠቅም ነገር ነው ህብረተሰቡ በዋጋ ማነስ ምክንያት ወደሌላ ምርት ፊቱን ካዞረ ጉዳቱ እንደ ሀገር ስለሆነ የገቢ ምንጭም ስለሚቀንስ መንግስት አርሷደሩን ወርዶ ቢመለከት ቢያወያዩ አርሷደሩ እንዳይጎዳ ቢያደርግ መልካም ነው " ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

በጉዳዩ ላይ የክልሉ ቡና ፍራፍሬና ቅመማ ቅመም ባለስልጣንን ጠይቀናል ምላሹን የምናቀርብ ይሆናል።

#TikvahEthiopia

Via @tikvahethmagazine