TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ: በተከሰከሰው አውሮፕላን ውስጥ የነበሩ #ተሳፋሪዎች ቤተሰቦች፣ አውሮፕላኑ ከተከሰከሰበት #ቢሾፍቱ አካባቢ በመሄድ ሀዘናቸውን በመግለፅ ላይ ናቸው፡፡

Via VOA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ: #ቢሾፍቱ አካባቢ በመሄድ #ሀዘናቸውን የገለፁ የተሳፋሪ ቤተሰቦች የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባሰራው አዲሱ ህንፃ #አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ፎቶ፦ OBANI
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምባሳደር መለስ አለም...

ዛሬ #በናይሮቢ መድኃኒያለም ቤተ ክርስትያን ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ ሳለ #ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦንግ 737 ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች የመታሰቢያ ፀሎት ስነ ስርዓት ላይ አምባሳደር #መለስ_አለም ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በፀሎት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር #መለስ የአውሮፕላኑ አደጋ በደረሰበት ዕለት ወደ ናይሮቢ እንደመጡና #በተከሰከሰው አውሮፕላን #ሊሳፈሩ እንደነበርም ተናግረዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ አበበች ጎበና ምን ይዤ ልምጣ?

ፍቅርን፣ አንድነትን፣ መዋደድን፣ ሰውን በሰውነቱ ማክበርን፣ የሀገር ፍቅርን፣ መከባበርን፣ መቻቻልን ከንፁህ ልባችሁ ጋር ይዛችሁ ኑ!!

እንደው እንደው የምትሆኑበት ቦታ የሚያመቻችሁ ከሆነና የትችሉ ከሆነ ደግሞ፦

በህፃናት እንክብካቤና የልማት ድርጅቱ ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በእናታችን አበበች ጎበና ስር ያሉ ልጆሽ አሉ በመሆኑም ቤት ውስጥ ትንንሽ መጠን ያላቸው ልብሶች፣ እስክርቢቶ/አንድም ቢሆን/፣ የልጆች መፅሃፍ፣ ደብተር/አንድ ነጠላም ቢሆን/ ይዛችሁ መምጣት ትችላላችሁ።

ኑ ከእናታችን ምርቃት እንቀበል!!

ቀጠሮ ይከበር ~ 6:00 ሰዓት

ቦታው፦

R= ቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ቤተክርስቲያን (ከፒያሳ ታክሲ መያዝ ይቻላል)

T1= ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ ሲመጡ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን ያገኛሉ፡፡ አስፓልቱን ትተው ቀጥታ የሚወስደውን ኮብልስቶን መንገድ ይዘው ይጓዙ

T2= ኮብልስቶኑን ተከትለው ቀጥታ ሲጓዙ የአስፓልት መንገድ ያገኛሉ ከዛም ወደ ቀኝ(ወደ ላይ) ይታጠፋሉ፡፡

T3= አስፓልቱን እንደያዙ ወደ ላይ ትንሽ ከፍ እንዳሉ ወደ ድርጅቱ መግቢያ ያገኛሉ፡፡

📌 በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ እለቱን የተመለከቱ ባነሮች መሰቀላቸውን ያረጋግጡ፡፡


በGoogle Map ላይ
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285 ማግኘት ይቻላል፡፡

ስትመጡ መደወል ትችላላችሁ፦

+251913134524/በረከት ጉዲሳ/
+251920486685/አቅለሲያ ሲሳይ/
.
.
#አዲስአበባ #ለገጣፎ #ቢሾፍቱ #ቡራዩ #አዳማ~ቤተሰቦቻችን ተገኙ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#2ኛ_ዓመት #የአፍሪካዋ_ማዘር_ትሬዛ #TIKVAH_ETH

"የላቀ ትውልድ ለላቀች ኢትዮጵያ"

6:00 #እንገናኝ!

ቦታው፦

R= ቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ቤተክርስቲያን (ከፒያሳ ታክሲ መያዝ ይቻላል)

T1= ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ ሲመጡ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን ያገኛሉ፡፡ አስፓልቱን ትተው ቀጥታ የሚወስደውን ኮብልስቶን መንገድ ይዘው ይጓዙ

T2= ኮብልስቶኑን ተከትለው ቀጥታ ሲጓዙ የአስፓልት መንገድ ያገኛሉ ከዛም ወደ ቀኝ(ወደ ላይ) ይታጠፋሉ፡፡

T3= አስፓልቱን እንደያዙ ወደ ላይ ትንሽ ከፍ እንዳሉ ወደ ድርጅቱ መግቢያ ያገኛሉ፡፡

📌 በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ እለቱን የተመለከቱ ባነሮች መሰቀላቸውን ያረጋግጡ፡፡

በGoogle Map ላይ
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285 ማግኘት ይቻላል፡፡

ስትመጡ መደወል ትችላላችሁ፦

+251913134524/በረከት ጉዲሳ/
+251920486685/አቅለሲያ ሲሳይ/
+2519 29 04 41 03/ፀጋዬ/
+2519 09 91 16 68
.
.
#አዲስአበባ #ለገጣፎ #ቢሾፍቱ #ቡራዩ #አዳማ~ቤተሰቦቻችን ተገኙ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ ቀዳማዊ እመቤት ዝናሽ ታያቸው እና የኦሮሚያ ክልል ምክትል ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሣ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ቢሾፍቱ ከተማ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን አስጀምረዋል፡፡ በዚህ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም በርካታ የፌደራልና የኦሮሚያ ክልል ባለስልጣናት ተገኝተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎችም ይህን መርሃ ግብር በማስኬድ ላይ ይገኛሉ፡፡ ሁለት መቶ ሚሊዮን ችግኝ በአንድ ጀምበር የመትከል ፕሮግራም በመላው ሀገሪቱ እየተካሄደ ነው፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ጀግኒት

ተማሪ SELAMAWIT KASSAHUN #በዘንድሮው የዩኒቨርሲቲ/የከፍተኛ ትምህርት ተቋም መግቢያ ፈተና 616 ያስመዘገበች ጀግኒት! #ኢትዮጵያዊት

#616 #ቢሾፍቱ

🗓የሌሎች #ጀግኒቶች ውጤት ይቀጥላል🔄
#ቢሾፍቱ

"በትላንትናው ዕለት የአምባ ፋርማሲዩቲካልና አኳርየስ አቪየሽን በመተባበር ለ2ኛ ጊዜ በቢሾፍቱ ሀይቅ ዳርቻ ከአካባቢው ሕብረተሰብ ጋር ዝናቡ ሳያመልጠን ችግኞች ስንተክል፤ የዛሬ ወር ገደማ የተከልናቸውንም ስንንከባከብ ዉለናል።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን ደመራ እንዳልተደመረ ገልፀዋል። ለምን? የሚለውን በቦታው የነበሩ የቤተሰባችንን አባላት ያዩትን ተናግረዋል ይቀርባል። የሚመለከታቸውን አካላት ለማናገርም ጥረት እናደርጋለን

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከቢሾፍቱ የአይን እማኝ...

"ከኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን መንገድ ላይ ስንደርስ ያልተፈቀደ አርማ ያለበትን ልብስ ለብሳችኃል/ይዛችኃል/ በሚል አታልፉም አሉን/የፀጥታ አካላት/። አረንጓዴ ቢጫ ቀይ የለበሱም ነበሩ እሱን እንዲህ ሆነን ማለፍ እንደማንችል ተነገረን። መዘምራንም ጭምር። ይሄን አርማ ይዛችሁ እና ለብሳችሁ ማለፍ አትችሉም አሉን። እዛው የነበርነው ሰዎች እንደዛ ከሆነ እዛው ኪዳነ ምህረት እናበራለን ብለን ተመለስን። ወደኪዳነ ምህረት ስንመለስ ወደአዳባባይ የሄዱት ሰዎች አንድ ደብር ጎሎ #አናበራም ብለው ሁሉም ተሰብስቦ ወደ ኪዳነ ምህረት እየተመለሰ ነበር #አደባባይ ያለውን ሳያበሩ ቀርተው። ግማሹ ኪዳነ ምህረት ከሄደ በኃላ እላይ ያለውን ወደታች እንዳይወርድ ታች ያለውን ወደ ላይ እንዳይወጣ ከለከሉ። ሰዎች ወደቤት አንሄድም አሉ። ሰዎችን አሳምነውም ወደአደባባይ ለመውሰድ እና ደመራው እንዲበራ ለማድረግ ጥረት አድርገው ነበር ግን ሰው አልተስማማ። እየዘመርን ወደቤታች እንመለሳለን ብሎ እኛ ወደቤታችን ሄደናል።"

ቢሾፍቱ ስለተፈጠረው ጉዳይ ምላሽ ለማግኘት ጥረት አድርጌ ነበር አልተሳካም። #BISHOFTU #ቢሾፍቱ
@tsegabwolde @tikvahethiopia