TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"አቶ በረከት #ለፍርድ መቅረብ አለበት"፡ አና ጎሜዝ - BBC⬇️

📌ጥያቄ፡- ሰሞኑን አቶ በረከትን ቃለ መጠይቅ አድርገንላቸው ነበር። 'ወ/ሮ አና፣ 'እባክዎ አርፈው ይቀመጡ' ብለዎታል፡፡ እንዲያውም እኚህ ሴትዮ ‹‹የፖርቹጋል #ቅኝ ግዛት #አስተሳስብ አልለቀቃቸውም››፤ ሲሉ ነው አስተያየት የሰጡት።

▪️ወይዘሮ አና ጎሜዝ፡- ለእንዲህ ዓይነት የወረደ ሐሳብ መልስ መስጠት አልሻም ነበር። አገሬን መስደባቸው ግን ትክክል አይደለም። እኔን እና አገሬን ከቅኝ ግዛት ጋር ማያያዛቸውም #አሳፋሪ ነው። በፖርቹጋል እኔ የምታወቀው በጸረ ቅኝ አገዛዝ ተጋድሎዬ ነው። ያውም ቅኝ ግዛትን መጻረር ፈታኝ በሆነበት ዘመን ነው የምልህ። ሕይወቴንም አደጋ ላይ ጥዬ ነው ይሄን ያደረገኩት። ተማሪ እያለሁ ጀምሮ ነው ይሄን ተጋድሎ የፈጸምኩት። ታሪኬ የሚያስረዳውም ይህንን ነው።

📌ጥያቄ፡- ሁለታችሁን እንዲህ የቃላት ጦርነት ውስጥ የሚከታችሁ እኛ የማናውቀው ነገር አለ?

▪️አና ጎሜዝ፡- ነገሩ በ2005 እኔ የአውሮፓ ምርጫ ታዛቢ ቡድንን መምራት በጀመርኩበት ጊዜ የሆነ ነው። እሱ ያኔ የመንግሥት ተወካይ ነበር። ከእኔና እኔ ከምመራው የምርጫ ታዛቢ ቡድን ጋር እሱ ነበር በየጊዜው የሚገናኘው። የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትርም ነበር። በዚያ የታዛቢ ቡድን አማካኝነት እኔና የቡድኔ አባላት የተደረገውን ማጭበርበር ስላጋለጥን ነው በእኔ ላይ ቂም ይዞ የቆየው። ከበረከት ስምኦን ጋር በጁን 8፣ 2005 የነበረንን ንግግር መቼም አልረሳውም። በመሐል አዲስ አበባ የተደረገውን ግድያ ሰምቼና ሆስፒታሎችን ጎብኝቼ ወዲያውኑ አገኘሁት። የጎበኘኋቸው ሐኪሞችና ነርሶች እያለቀሱ ነበር [በጥይት የተመቱትን] የሚያክሙት፡፡ ሁኔታው አስቆጥቷቸው ነበር። ባየሁት ጉዳይ ላይ መግለጫ እንደምሰጥ በረከትን ነገርኩት። እርሱ በዚህ ውሳኔዬ ተበሳጨ፡፡ ይባስ ብሎ
ለተፈጠረው ግድያ ተጠያቂው የአውሮፓ ኅብረት ነው አለኝ። ይህ ብሽቅ የኾነ ሐሳብ ነው።

📌ጥያቄ፡- በቀደም ለታ የትዊተር ገጽዎ አቶ በረከትን ‹‹ርህራሔ የሌለው፣ ዋሾና፣ ጨካኝ›› ብለውታል። አልበዛም? የተጠቀሟቸው ቃላቶች የዲፕሎማት ቋንቋ አይመስልም።

▪️አና ጎሜዝ፦ #እውነት ስለሆነ ነዋ፣ እውነት ስለሆነ ነው፥ እርሱ ጨካኝና #ውሸታም ነው። በ2005 በደንብ አውቀዋለሁ ሰውዬውን። ባህሪው እንደዚያ ነው። እኔ ከአገሪቱ ጋር ምንም ችግር የለብኝም። የኔ ችግር ሁልጊዜም ከአምባገነኖች ጋር ነው።

📌ጥያቄ፡- አሁን ነገሩ ረዥም ጊዜ ሆነው እኮ፤ ለምን አይረሱትም ግን እርስዎ?

▪️አና ጎሜዝ፡ - ለምን እረሳለሁ?! በ2005ቱ ምርጫ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን ሞተዋል። የነርሱ ቤተሰቦች ይህን የሚረሱ ይመስልኻል? ስለዚህ እኔም አልረሳም። የሰው ሕይወት ነው የጠፋው፤ ለግድያው ኃላፊነት መውሰድ ያለባቸው ሰዎች አሉ፤ አንዱ አቶ በረከት ነው። ይህን ጉዳይ የግለሰቦች ጉዳይ ለምን ታደርገዋለህ። እኔ በግል ከሰውየው ጋር ምንም ችግር የለብኝም እኮ። ፖለቲካዊ ነው ጉዳዩ። በርካታ ሰዎችን የጨፈጨፈውን ሥርዓት ሲያገለግል የነበረ ሰው ነው። እኔ ለማወቀውና ለፈጸመው ወንጀል ተጠያቂ ይሁን ነው እያልኩ ያለሁት። ብቸኛው ተጠያቂ እንዳልሆነ አውቃለሁ። ሆኖም አንዱና ዋንኛው ነው።

📌ጥያቄ፡- ለማለት የፈለኩት ከእርስዎ ጋር ምርጫውን የታዘቡ፣ የኾነውን የተመለከቱ ብዙ ዲፕሎማቶች ነበሩ፤ አንዳቸውም በእርስዎ መጠን መንግሥት ላይ ትችት ሲሰነዝሩ አልሰማንም። እርስዎ ለምንድነው አንዲህ ነገሩን ለዓመታት የሙጥኝ ያሉት?

▪️አና ጎሜዝ፡ - ዲፕሎማቶች የተፈጠሩት እንዲዋሹ አይመስለኝም። ዝም አልልም፤ ለምን ዝም እላለሁ፤ በመለስና በአቶ በረከት ትእዛዝ የተገደሉ ሰዎችን አይቻለሁ፤ #ስለምን ዝም እላለሁ? አሁንም ላረጋግጥልህ የምፈልገው፤ አሁንም ወደፊትም ዝም አልልም። ሌሎች ዝም ብለዋል ላልከው እኔ ያኔም ያስተጋባሁት የ200 የቡድኔን አባላት በመላው ኢትዮጵያ ተዘዋውረው ያዩትን ነው። ያወጣነው ሪፖርት ደግሞ ከካርተር ሴንተር ካወጣው ሪፖርት ጋር የሚመሳሰል ነው። ነገር ግን ሁሉም ሰው ለአንድ ጉዳይ የሚሰጠው ምላሽ ተመሳሳይ ላይሆን ይችላል። እኔ ባየሁት ነገር እጅግ ተቆጥቻለሁ። የመለስና የበረከት መንግሥት የሕዝብን ድምጽ ያጭበረበረበት መንገድ አናዶኛል። የአውሮፓ አገራት ይህንን መንግሥት እሹሩሩ ያሉበት መንገድ አበሳጭቶኛል። አሁንም ዝም አልልም፤ ወደፊትም ዝም አልልም፤ በእጃቸው የሰው ደም ያለባቸውን እንደ አቶ በረከት ያሉ ሰዎችን በዝምታ አላልፋቸውም።

📌ጥያቄ፡- አቶ በረከት ወንጀለኛ ናቸው ለፍርድ ይቅረቡ እያሉ ነው?

▪️አና ጎሜዝ፡- ይሄ ምን ጥያቄ አለው፤ አቶ በረከት ለፍርድ ነው መቅረብ ያለበት። እርግጥ ነው ብቻውን አይደለም፤ ግን ዋናው ሰው ነው፤ ለፍርድ የማይቀርበው ለምንድነው? አሁን ለውጥ ላይ ያለው መንግሥት ወደዚህ ድምዳሜ ላይ ይመጣል የሚል ተስፋ አለኝ።

📌ጥያቄ፡- የአቶ በረከት ስምኦንን ጉዳይ ለጊዜው ገሸሽ እናድርገውና፤ ሌላ ጥያቄ ላንሳ፤ በ2012 አቶ መለስ ዜናዊ በብራስልስ መሞታቸውን #ለኢሳት መረጃ ያቀበሉት እርስዎ ኖት እንዴ?

▪️አና ጎሜዝ፡- ሊሆን ይችላል። መረጃው ነበረኝ። ያኔ ማንም መለስ ዜናዊ መታመሙን ቀርቶ አገር ውስጥ አለመኖሩንም የሚያውቅ ብዙ ሰው
አልነበረም። #መሞቱንም ብዙ ሰው አያውቅም ነበር። የነበረኝ መረጃ እጅግ #አስተማማኝ የሚባል ነበር። ያን መረጃ ኢሳት የተጠቀመበት ይመስለኛል። ቀደም ብሎ መሞቱን የነገረኝ ምንጭ እጅግ የምተማመንበትና አስተማማኝ ነበር።

📌ጥያቄ፡- ስለዚህ አቶ #መለስ የሞቱት በመንግሥት #ከተገለጸው ቀን ቀደም ብሎ ነው ብለው በእርግጠኝነት መናገር ይችላሉ?

▪️አና ጎሜዝ፡- ያለምንም ጥርጥር። መጀመርያ ብራዚል ለሕክምና ተወስዶ ነበር። ከሐኪሞቹ ጋር በብራዚል ተገናኝቷል። የሕመሙ ሁኔታ
የተገመገመው ብራዚል በሚገኙ ስፔሻሊስቶች ነበር። ምንም ማድረግ እንደማይችሉ ተነገረው። ከዚያ በኋላ ነው ብራስልስ እንዲመጣ የተደረገው። እኔ መረጃውን ባገኘሁበት ቅጽበት ራሱ ከቀናት በፊት መሞቱ ነው የተነገረኝ። ሆኖም በምሥጢር ተይዞ ነበር።

📌ጥያቄ፡- ትክክለኛ ቀኑን ያስታውሱታል?

▪️አና ጎሜዝ፡- አላስታውስም

📌ጥያቄ፡- የትኛው በሽታ ለሞት እንደዳረጋቸውስ ያስታውሳሉ?

▪️አና ጎሜዝ፡- እ…አንዳች የካንሰር ዓይነት ሕመም ሳይሆን አይቀርም፤ በትክክል ምን እንደነበር እርግጠኛ አይደለሁም።

📌ጥያቄ፡- መንግሥት ለምን መሞታቸውን ዘለግ ላለ ጊዜ መደበቅ የፈለገ ይመስልዎታል?

▪️አና ጎሜዝ፡- እነርሱን ነው መጠየቅ ያለብህ። ነገር ግን በአምባገነን መንግሥታት ውስጥ የጠንካራ መሪ ሞት መደበቅ የተለመደ ነው፤ #የመለስን ሞት #ቀደም ብዬ አውቅ ነበር እያልኩህ አይደለም። እንደሰማሁት መረጃውን ሰጠሁ። ብዙም ሳይቆይ መንግሥትም መሞታቸውን አረጋገጠ። ከዚያ በፊት ግን ስለመታመማቸው እንኳን ለኢትዯጵያ ሕዝብ አልተነገረም ነበር።

📌ጥያቄ፡- እርስዎ መች ነው ግን ለመጀመርያ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚለውን ስም የሰሙት?

▪️አና ጎሜዝ፡- በልጅነቴ ነው። በቅኝ ግዛትና ከቅኝ ግዛትም በፊት በነበረው የአገሬ ታሪክ ወስጥ የኢትዮጵያ ስም ገናና ነው። ፖርቹጋሎች ለረዥም ዓመት ኢትዮጵያ በእግር ተጉዘው ለመድረስ ይሞክሩ ነበር። የፕሪስት ጆን አገር ተብላ ትታወቅ ነበር። የፖርቹጋል አሳሾች ትልቅ ጉጉት ነበራቸው፤ ይቺን አገር ለማየት። እኔ አገሪቱን የረገጥኩት በ97 ምርጫ ጊዜ ነው።
.
.
ይቀጥላል🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአፍሪካ ህብረት አስቸኳይ ጉባኤ‼️

የአፍሪካ ኅብረት ከሕዳር 8-9 ቀናት 2011ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚያደርገው አስቸኳይ ጉባኤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዝግጅት #ማጠናቀቁን አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ 11ኛው የርዕሳን ብሔራት እና ርዕሳነ መንግሥታት አስቸኳይ ጉባኤዎችን በውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ደረጃ ከሕዳር 5-6 ቀናት 2011ዓ.ም እና በመሪዎች ደረጃ ደግሞ ከሕዳር 8-9 ቀናት 2011 ዓ.ም ለምታዘጋጀው ጉባኤ ሙሉ ዝግጅት ማጠናቀቋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ #መለስ_ዓለም እንዳስታወቁት የጉባኤው ዓላማ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን አዲስ ማሻሻያን የሚመለከት ነው ተብሏል፡፡

በጉባኤው ከ45 በላይ ሀገራት እንደሚሳተፉ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ ለዝግጅቱ ከ40 በላይ መሥሪያ ቤቶች ከኤርፖርት ጀምሮ እስከ ሆቴል እና መሰብሰብያ ጉበኤው ድረስ ያሉ አሠራሮችን ቀላል ለማድረግ እየሠሩ እንደሆነም ታውቋል፡፡

ከ79 በላይ ደረጃቸውን የጠበቁ ሆቴሎችም ለእንግዶች ማረፊያ ዝግጁ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ አየር መንገድ✈️

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኤርትራ አየር ክልል መጠቀሙ ባንድ በረራ ብቻ እስከ 100 ሺህ ዶላር ኪሳራ እንደሚያስቀርለት የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ #መለስ_ዐለም መናገራቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግቧል፡፡ ከኤርትራ ጋር ሰላም ስምምነት ከመፈረሙ በፊት አየር መንገዱ ለተጨማሪ ወጭ ይዳረግ የነበረው ወደ መካከለኛው ምስራቅ በሚያደርጋቸው በረራዎች ነበር፡፡

ምንጭ፦ wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኬንያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር #መለስ_ዐለም የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አቅርበዋል፡፡

Via FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አምባሳደር መለስ አለም...

ዛሬ #በናይሮቢ መድኃኒያለም ቤተ ክርስትያን ባለፈው ሳምንት ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ በመብረር ላይ ሳለ #ቢሾፍቱ አቅራቢያ በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ቦንግ 737 ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች የመታሰቢያ ፀሎት ስነ ስርዓት ላይ አምባሳደር #መለስ_አለም ተገኝተው ንግግር አድርገዋል። በፀሎት ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ሰፋ ያለ ንግግር ያደረጉት አምባሳደር #መለስ የአውሮፕላኑ አደጋ በደረሰበት ዕለት ወደ ናይሮቢ እንደመጡና #በተከሰከሰው አውሮፕላን #ሊሳፈሩ እንደነበርም ተናግረዋል።

Via BBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ግንቦት

ታሪክን መለስ ብለን ስናይ፦

√የውጫሌ ውል የተፈረመው በግንቦት ወር ነው።

√ለንግስና ያልበቁት ልጅ እያሱ በሚኒሊክ የተሾሙት በግንቦት ወር ነው።

√በደረሰባቸው የመኪና አደጋ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት ልዑል መኮንን ኃይለስላሴ በግንቦት 1949 ነው።

√ኮ/ሌ #መንግስቱ_ኃይለማርያም የተወለዱት ግንቦት 19 ነው፤ መፈንቅለ መንግስት የተሞከረባቸው ግንቦት 8 ሆኖ ግንቦት 13/1983 ደግሞ ሀገራቸውን ጥለው የተሰደዱበት ቀን ነው።

√ግንቦት 11/1982 ዓ.ም 12 ከፍተኛ ጀኔራሎች #የተገደሉበት ቀን ነው።

√ግንቦት 20 ኢህአዴግ አዲስ አበባን የተቆጣጠረበት ቀን ነው።

√የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ #መለስ_ዜናዊ የተወለዱት ግንቦት 1 ነበር።

√ግንቦት 7/1997 በኢትዮጵያ የብዙሃን ፓርቲ ምርጫ የተካሄደበት ነበር።

√ግንቦት 18/1999 በደርግ ከፍተኛ አመራሮች ላይ ሞት የተፈረደበት ቀን ነው፤ ግንቦት 24/2003 የሞት ፍርዱ ወደ እድሜ ልክ የተለወጠበት ቀን ነው።

ግንቦት ታሪካዊ ናት!

Via ሌ/ኮሎኔል ፍስሃ ደስታ/አብዮቱና ትዝታዬ/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ግንቦት 20, 1983 ዓ/ም👆

ከላይ ባለው ፎቶ የሕወሓት ሊቀመንበር #መለስ_ዜናዊ እና የደኅንነቱ ሹም #ክንፈ_ገብረ_መድኅን ወደ ግዮን ሆቴል ሲገቡ ይታያሉ።

የሚሊተሪ ለብሶ የሚታየው የቀድሞው ጦር (ደርግ) መኮንን የነበረው ኮሎኔል አስራት ነው። ኮሎኔል አስራት በሕወሓት ከተማረከ በኋላ ከኢህአዴግ ጋር ተሰልፎ በብሔራዊ መረጃና ደህንነት መምሪያ ሀላፊነት ደረጃ ድረስ ሲሰራ የነበረ፤ በኋላም የግርማዊ ዐፄ ኃይለሥላሴ አስከሬን ከኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ጽ/ቤት ለማውጣት የተዋቀረውን ግብረ ኃይል ያስተባበረ ነው።

አብዮት ልጇን ትበላለችና ኮሎኔል አስራት የቀይ ሽብር ተዋናይ ነበር ተብሎ ወደ ወህኒ ቤት የወረደ ሲሆን፤ በወህኒ ቤትም እያለ "በህመም" ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ መሆኑ ታውቋል።

ግንቦት 20 ዛሬ 28ኛ አመቱ ሲታሰብ በፎቶው ላይ የምናያቸው ሶስቱም አመራሮች በሕይወት የሉም።

Via #PetrosAshenafi
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ለማስተዋወቅ እንደሚሰሩ የእውቁ ኬንያዊ ፎቶ ጋዜጠኛ መሐመድ አሚን ልጅ ሳሊም አሚን ገለፁ። ሳሊም አሚን በናይሮቢ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተገኝተው ከሚሲዮኑ ጋር በመተባበር “የኢትዮጵያን በጎ ገፅታ′ በፎቶግራፊ ሙያ ለዓለም ማስተዋወቅ በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ከአምባሳደር #መለስ_ዓለም ጋር መክረዋል።

Via #ENA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ማስታወሻ

"... የዚህ ታላቅ ፕሮጀክት ጥቅም በኢትዮጵያ ብቻ የተወሰነ አይደለም፤ሁሉንም ጎረቤቶቻችን በተለይም የታችኛው ተፋሰስ ሀገሮች የሆኑትን ሱዳን እና ግብፅን በእጅጉ የሚጠቅም ነው።

ፕሮጀክቱ ሲጠናቀቅ ወንዙ ተሸክሞት ይሄድ የነበረው ደለል ስለሚቀር በግብፅ እና በሱዳን ያሉ ግድቦች በተለይም በደለል እየተሞላ የሚሰጠው ጥቅም በከፍተኛ መጠን የቀነሰው የሱዳን የሮሰሪስ ግድብ ከዚህ አደጋ ነፃ ይሆናል።
.
.
ጥቅሙ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለጎረቤት ሀገሮች በተለይ ለሱዳን እና ግብፅ ጭምር በመሆኑ ፍትህ የሰፈነበት ሁኔታ ቢኖር የግድቡን ወጪ 3ቱም ሀገራት ሊሸፍኑት በተገባ ነበር።

እያንዳንዱ ሀገር ከግድቡ በሚያገኘው ጥቅም ልክ ወጪውን ይሸፍን ቢባል ሱዳን የወጪውን 30%፣ግብፅ የወጪውን 20% መሸፈን በተገባቸው ነበር።

ይሁንና በአባይ ወንዝ አጠቃቀም ዙሪያ እንዲህ አይነቱ ገንቢና ፍትሃዊ አሰራር ሊሰፍን አልቻለም፤በመሆኑም ወጪው በሙሉ ኢትዮጵያ ለመሸፈን ተገዳለች።

ይባስ ብሎ ግድቡን ለመስራት ብድር እና እርዳታ እንዳናገኝ የተለያዩ ኃይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ምክንያት የፕሮጀክቱን ወጪ ለመሸፈን የሚተባበረን ሀገር ወይም ተቋም ማግኘት አልቻልንም።

ስለሆነም ወጪውን ብቻችንን ከመሸፈን አልፈን ከራሳችን ቁጠባ ለመሸፈን የምንገደድበት ሁኔታ ተፈጥሯል።
.
.
ያለን አማራጭ አንድም ግድቡን አለመስራት ፥ አለበለዚያ እንደምንም ወጪውን በራሳችን መሸፈን ነው።

ከነዚህ ሁለት ከባድ አማራጮች መካከል የኢትዮጵያ ህዝብ ምርጫ የቱ እንደሚሆን ግልፅ ነው።

በተለመደው ወኔው ምንም ያህል ድሃ ብንሆንም ድህነታችንን ለማስወገድ ማንኛውም መስዋዕነት ለመክፈል ዝግጁ ነን፤ ስለዚህ ፕሮጀክቱ መሰራት አለበት እንደሚል ለአፍታም ያህል አልጠራጠርም። "

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠ/ሚኒስትር አቶ #መለስ_ዜናዊ - መጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ከተናገሩት የተወሰደ።

@tikvahethiopia