TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.48K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኦሮሚያ ክልል⬇️

በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች የሕግ የበላይነትን ለማስከበርና ሕገ ወጥነትን ለመከላከል በተሰራው ስራ የተለያዩ ሕጋዊ እርምጃዎች ተወስደዋል፡፡

#ሱሉልታ

በቄሮ ስም እንቅስቃሴ በማድረግ ሌሊት የግለሰቦችን ቤት በማፍረስና ቆርቆሮ በመውሰድ ላይ የተሰማሩ 4 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር
ውለዋል፡፡

#ሻሸመኔ

ባለፈው ሳምንት በከተማው የተፈጸመው ወንጀል እጃቸው አለበት ተብለው የተጠረጠሩ 7 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ቡራዩ

የቄሮ አመራር ነኝ በማለት መታወቂያ አዘጋጅቶ የተለያዩ ተቋማት በግድ ስፖንሰር እንዲያደርጉት ሲጠይቅ የነበረ፣ ቲተር: ማዕተምና የመታወቂያ ወረቀት በቄሮ ስም አዘጋጅቶ በመሸጥ ሲነግድ የነበረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

#ለገጣፎ_ለገዳዲ

በቄሮ ስም የ62 ወጣቶችን ፎቶ በማሰባሰብና ወረቀት ላይ በመለጠፍ የቄሮ አደረጃጀት ከቀበሌ እስከ ላይ መኖር አለበት በሚል ወጣቶችን
ሲያታልሉና ሲያደረጁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ጅማ

በሕገ ወጥ ስራ ላይ ተሰማርተው ሕገ ወጥ ግንባታ ሲያካሄዱ የነበሩ 42 ሰዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ 8 ሰዎች ላይ ሙሉ መረጃ ተሰባስቦ ለሕግ ሊቀርቡ ነው፡፡
ድንገት በተደረገው ፍተሻም 2ሽጉጥና 180 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

#አዳማ

በቅርቡ በከተማው ለተከሰተው ግጭት መነሻ በመሆን ሰዎችን ሲያነሳሱ የነበሩና ግጭቱ የብሔር መልክ እንዲይዝ አድርገዋል የተባሉ 8 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

#ሞጆ

ጨለማን ተገን በማድረግ ፋብሪካን ለመዝረፍ ሲንቀሳቁ የነበሩ 2 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን፣ በአንደኛው ግለሰብ እጅ ሽጉጥ ተይዟል፡፡

#ሰበታ

በሕገ ወጥ ግንባታ ላይ የተሰማሩ፣ ምግብ ቤት ገብተው በመመገብ ሒሳብ የማይከፍሉና ተደራጅተው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ 14 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ምንጭ:- የኦሮሚያ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ⬇️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ ዙሪያ የተፈናቀሉ ዜጎችን #እየጎበኙ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ ቀትር ላይ በአዲስ አበባ በጉለሌ ክፍለ ከተማ መድሃኃኒያለም ትምህርት ቤት ተገኝተው በአዲስ አበባ ዙሪያ ከተፈናቀሉ ዜጎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ #ቡራዩ አቅንተውም በተመሳሳይ መልኩ በመጠለያ ውስጥ ካሉ ዜጎች ጋር ተመሳሳይ ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ
ይጠበቃል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተፈናቃዮችና ተጎጂዎች የሚያነሷቸውን ጥያቄዎችና የችግሩን ስፋት ለማጤን ነው በአካል ተገኝተው ጉብኝት እያደረጉ ያሉት፡፡

በበጎ ፈቃደኞችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለተፈናቃዮቹ እየተደረገ ያለውን ድጋፍንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተመልክተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ ባሉ አካባቢዎች በተደራጁ ኃይሎች በርካታ ዜጎች ለሞት፣ ለጉዳት፣ ለንብረት ውድመትና መፈናቀል መዳረጋቸው ይታወሳል፡፡

እነዚህን ችግሩን የፈጠሩ ቡድኖችን በቁጥጥር ስር እያዋለ መሆኑንም መንግስት መግለፁ ይታሳል፡፡

©etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሳዛኝ ዜና‼️

በአዲስ አበባ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን #ቡራዩ_ከተማ አስተዳደር መልካ ገፈርሳ ቀበሌ ዛሬ በአንድ መዋዕለ ሕጻናት ትምህርት ቤት ውስጥ የሚገኝ መጸዳጃ ቤት ተደርምሶ የ4 ሕጻናት ሕይወት አልፏል።

በአደጋው ስምንት ሕጻናት ወደ መጸዳጃ ቤቱ #ጉድጓድ ገብተው እንደነበር የዘገበው ኤፍ ቢ ሲ ከእነዚህ ውስጥም የአራቱ ሕይወት #ወዲያውኑ ማለፉን አመልክቷል።

ቀሪዎቹ አራት ሕጻናት ደግሞ በአደጋው ጉዳት ደርሶባቸው በቤተልና አለርት ሆስፒታሎች የሕክምና #ዕርዳታ እየተደረገላቸው መሆኑን የከተማዋ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ወይዘሮ በየኑ ረዳ ተናግረዋል።

በአደጋው ሕይወታቸው ላለፉት ሕጻናት ጥልቅ ሐዘን የተሰማቸው መሆኑን በከተማ አስተዳድሩ ስም የገለጹት ወይዘሮ #በየኑ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶቻቸው መፅናናትን ተመኝተዋል። ትምህርት ቤቶች በግቢያቸው ውስጥ የሚገኙ መጸዳጃ ቤቶች ለተማሪዎች ደኅንነት ምቹ መሆናቸውን ማረጋገጥ ተገቢ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የቡራዩ ከተማ ፖሊስ ምክትል ሳጅን #ሲሳይ_ዓለሙ በበኩላቸው መጸዳጃ ቤቱ የተደረመሰው በነበረበት የጥራት ችግር መሆኑን ተናግረዋል። ጉዳዩን አስመልክቶ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘትም ፖሊስ ምርመራ መጀመሩን ጠቁመዋል።

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ነገ አበበች ጎበና ምን ይዤ ልምጣ?

ፍቅርን፣ አንድነትን፣ መዋደድን፣ ሰውን በሰውነቱ ማክበርን፣ የሀገር ፍቅርን፣ መከባበርን፣ መቻቻልን ከንፁህ ልባችሁ ጋር ይዛችሁ ኑ!!

እንደው እንደው የምትሆኑበት ቦታ የሚያመቻችሁ ከሆነና የትችሉ ከሆነ ደግሞ፦

በህፃናት እንክብካቤና የልማት ድርጅቱ ከ1ኛ ክፍል እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በእናታችን አበበች ጎበና ስር ያሉ ልጆሽ አሉ በመሆኑም ቤት ውስጥ ትንንሽ መጠን ያላቸው ልብሶች፣ እስክርቢቶ/አንድም ቢሆን/፣ የልጆች መፅሃፍ፣ ደብተር/አንድ ነጠላም ቢሆን/ ይዛችሁ መምጣት ትችላላችሁ።

ኑ ከእናታችን ምርቃት እንቀበል!!

ቀጠሮ ይከበር ~ 6:00 ሰዓት

ቦታው፦

R= ቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ቤተክርስቲያን (ከፒያሳ ታክሲ መያዝ ይቻላል)

T1= ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ ሲመጡ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን ያገኛሉ፡፡ አስፓልቱን ትተው ቀጥታ የሚወስደውን ኮብልስቶን መንገድ ይዘው ይጓዙ

T2= ኮብልስቶኑን ተከትለው ቀጥታ ሲጓዙ የአስፓልት መንገድ ያገኛሉ ከዛም ወደ ቀኝ(ወደ ላይ) ይታጠፋሉ፡፡

T3= አስፓልቱን እንደያዙ ወደ ላይ ትንሽ ከፍ እንዳሉ ወደ ድርጅቱ መግቢያ ያገኛሉ፡፡

📌 በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ እለቱን የተመለከቱ ባነሮች መሰቀላቸውን ያረጋግጡ፡፡


በGoogle Map ላይ
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285 ማግኘት ይቻላል፡፡

ስትመጡ መደወል ትችላላችሁ፦

+251913134524/በረከት ጉዲሳ/
+251920486685/አቅለሲያ ሲሳይ/
.
.
#አዲስአበባ #ለገጣፎ #ቢሾፍቱ #ቡራዩ #አዳማ~ቤተሰቦቻችን ተገኙ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#2ኛ_ዓመት #የአፍሪካዋ_ማዘር_ትሬዛ #TIKVAH_ETH

"የላቀ ትውልድ ለላቀች ኢትዮጵያ"

6:00 #እንገናኝ!

ቦታው፦

R= ቅዱስ ዮሐንስ ወልደነጎድጓድ ቤተክርስቲያን (ከፒያሳ ታክሲ መያዝ ይቻላል)

T1= ከዮሐንስ ቤተክርስቲያን ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ ሲመጡ የኢትዮጲያ ንግድ ባንክ ጎጃም በረንዳ ቅርንጫፍን ያገኛሉ፡፡ አስፓልቱን ትተው ቀጥታ የሚወስደውን ኮብልስቶን መንገድ ይዘው ይጓዙ

T2= ኮብልስቶኑን ተከትለው ቀጥታ ሲጓዙ የአስፓልት መንገድ ያገኛሉ ከዛም ወደ ቀኝ(ወደ ላይ) ይታጠፋሉ፡፡

T3= አስፓልቱን እንደያዙ ወደ ላይ ትንሽ ከፍ እንዳሉ ወደ ድርጅቱ መግቢያ ያገኛሉ፡፡

📌 በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ እለቱን የተመለከቱ ባነሮች መሰቀላቸውን ያረጋግጡ፡፡

በGoogle Map ላይ
https://maps.google.com/?cid=14408072496157346285 ማግኘት ይቻላል፡፡

ስትመጡ መደወል ትችላላችሁ፦

+251913134524/በረከት ጉዲሳ/
+251920486685/አቅለሲያ ሲሳይ/
+2519 29 04 41 03/ፀጋዬ/
+2519 09 91 16 68
.
.
#አዲስአበባ #ለገጣፎ #ቢሾፍቱ #ቡራዩ #አዳማ~ቤተሰቦቻችን ተገኙ!!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በዚህ ወር በሀገራችን የተለያዩ አካባቢዎች ያጋጠሙ የእሳት አደጋዎች ፦

#ወልቂጤ_ከተማ (ጉራጌ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በኩር ክ/ከተማ አርሴማ መንደር

• የደረሰው ጉዳት - 14 ቤት ሙሉ በሙሉ 6 ቤት በከፊል ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም ፖሊስ ምርመራ እያደረገ ነው።

#ቤሮ_ወረዳ (ምዕራብ ኦሞ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ሾላ ቀበሌ

• የደረሰው ጉዳት - 1840 መኖሪያ ቤቶች፣ 547 የንግድ ቤቶች፣ 37 የወርቅ ማህበራት ፣ 109 የወርቅ ማሽን በአጠቃላይ 586 ሚሊዮን 142 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እስካሁን አልታወቀም።

#ሆሳዕና_ከተማ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰው በአንድ የገበያ ማዕከል አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያለው ንብረት ወድሟል። በርካታ የኤሌክትሮኒክስ እና አልባሳት ንግድ ድርጅቶች ከነ ንብረታቸው ወድመዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ፖሊስ እያጣራው ነው።

#መካነሠላም_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• በመካነ ሠላም ከተማ በንግድ ቦታ ላይ ድንገት የተከሰተ አደጋ።

• የደረሰው ጉዳት - በሸቀጣ ሸቀጥ ሱቆች፣ በሴቶች የውበት ሳሎን፣ በልብስ ስፌት ቤቶች ላይ ጉዳት ደርሳል። ከ100 ሺህ ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም።

#ወላይታ_ሶዶ_ከተማ (ወላይታ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - መርካቶ ገበያ

• የደረሰው ጉዳት - 1 ቢሊዮን 57 ሚሊዮን 670 ሺህ ብር ወድሟል። 42 ሺህ ገደማ ዜጎች በቀጥታ እና በተዘዋዋሪ ለቀውስ ተጋልጠዋል።

• የአደጋው መንስኤ - አንታወቀም፤ በፖሊስ እየተመረመረ ይገኛል።

#ማሻ_ከተማ (ደቡብ ወሎ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - አዲሱ መናኸሪያ አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 2 ሼዶች በውስጣቸው ካለ ሙሉ ንብረት ጋር ወድመዋል። ሼዶቹ በውስጣቸው ሱቆች፣ ፖስታ ቤት፣ የመንገድ ትራንስፖርት ቢሮ ይገኙበታል። 1 ሚሊዮን 224 ሺህ 936 ብር የሚገመት ሃብት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም፤ እየተጣራ ነው።

#ዌራ_ወረዳ (ሀላባ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ላይኛ በደኔ ቀበሌ በጦሮንቦራ ንዑስ

• የደረሰው ጉዳት - 11 መኖሪያ ቤቶች ተቃጥለዋል። ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እህል የተከመረበት ቦታ ላይ በሶላር ባትሪ ቻርጅ የተሰካ የሞባልይ ስልክ ፈንድቶ።

#ምሻ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ኤራ ጌሜዶ፣ ኩናፋ፣ ጉና ማጋቾ ቀበሌዎች

• የደረሰው ጉዳት - 128 ዶሮዎች፣ 243 ኩንታል የተለያየ እህል፣ 18 የንብ ቀፎ ፣ የተለያዩ የቤት ቁሳቁሶች በድምሩ 23 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - የተፈጥሮ እሳት

#ሶሮ_ወረዳ (ሀዲያ ዞን)

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - በጃቾ ከተማ

• የደረሰው ጉዳት - ከ250 ሺህ ብር በላይ ወድሟል።

• የአደጋው ምክንያት - የመብራት ኮንታክት

#ሐረማያ_ዩኒቨርሲቲ

• የአደጋው የደረሰበት ቦታ - ዋናው ግቢ ህንፃ 3

• አደጋው የኤሌክትሪክ መቆጣጣሪያ ላይ የተነሳ ነው።

• የደረሰው ጉዳት - መጠኑ ያልተገለፀ ንብረት ጉዳት ደርሶበታል።

#ቡራዩ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ገፈርሳ ኖኖ ቀበሌ ገብርኤል አካባቢ

• የደረሰው ጉዳት - 16 ሱቆች ፣ 3 መኖሪያ ቤቶች፣ 3 ባርና ሬስቶራንቶች ቃጠሎ ደርሶባቸዋል። በአጠቃላይ ግምንቱ 10 ሚሊዮን ብር የሆነ ንብረት ወድሟል።

• የአደጋው መንስኤ - እየተጣራ ይገኛል።

#ባህር_ዳር_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 3 ጉዶባህር የሚባለው ሰፈር

• የደረሰው ጉዳት - 22 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል። በገንዘብ 300 ሺህ ብር በላይ የሚገመት ንብረት ተቃጥሏል።

• የአደጋው መንስኤ - እንጀራ ከሚጋገርበት ወቅት ከተቀጣጣይ ነገሮች የተነሳ ነው።

#ጅግጅጋ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ቀበሌ 2 ልዩ ስሙ ድብኡራሾ ሱቅ

• የደረሰው ጉዳት - 7 የምግድ ቦታዎች ላይ ከፍተኛ ንብረት አደጋ ደርሶበታል ይህም 1.2 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም። ከአንድ ቤት ውስጥ ነው የተነሳው ተብሏል።

#ደብረማርቆስ_ከተማ

• አደጋው የደረሰበት ቦታ - ጉልት ገበያ አዳራሽ

• የደረሰው ጉዳት - 48 የንግድ ሱቆች ጉዳት ደርሶባቸዋል። አልባሳት፣ ሸቀጣሸቀጥ፣ ቅመማቅመም፣ አትክልት እና ፍረፍሬ ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል። የንብረት ግምት እየተጣራ ነው።

• የአደጋው መንስኤ - አልታወቀም በፖሊስ እየተጣራ ነው።

በዚህ ወር በደረሱት የእሳት አደጋዎች በርካቶች ጥረው ግረው ያፈሩት ንብረታቸው ፣ ቤታቸው ወድሞባቸው ሜዳ ላይ ወድቀዋል።

በርካቶች ህይወታቸው ተመሰቃቅሏል ፣ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ስራ አጥ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል።

* የአብዛኛዎቹ የእሳት አደጋዎች ትክክለኛ መንስኤ በግልፅ አይታወቅም።

በቲክቫህ ኢትዮጵያ
#TikvahFamily

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia