TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update በኦሮሚያ ክልል የሰብዓዊ መብት ፎረም #መመስረቱ ተገለጸ። በፎረሙ አደረጃጀቶች መመሪያና የማስፈጸሚያ ስልት ላይም በባለ ድርሻ አካላት ውይይት ተካሂዷል። ፎረሙ በህገ መንግስት መብቶችና ግዴታዎች ላይ የግልና የቡድን መብቶች አጠባበቅ ስርዓት መዘርጋትን ያለመ ነው። የሰብዓዊ መብት ጉዳይ ከተቋማት በላይ የህዝቡ የጋራ አጀንዳ እንዲሆንና ህዝቡም ሰብዓዊ መብት ማክበርና ማስከበር ላይ ንቃተ ህሊናውን ማሳደግ ሌላው የፎረሙ ዓላማ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ከጣሊያን ታላላቅ የአልባሳት አምራች ኩባንያዎች አንዱ የሆነው #ካልዜዶንያ በአፍሪካ የመጀመሪያው የሆነውን ፋብሪካውን በትግራይ ከፈተ። ኢታካ ቴክስታይል በመባል የሚታወቀው ይህ ኩባንያ ምርቱን ከትግራይ #በምፅዋ ወደብ በኩል ወደ ውጪ ለመላክ ያለመ ነው። የትግራይ ክልል ባለስልጣናት በተገኙበት ፋብሪካው ተመርቋል። በምረቃው ላይ ያልተገኙት ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር #አብይ_አህመድ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ልከዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹የላልይበላን ቅርስ አስጠብቆ ማስቀጠል ካልተቻለ ለዚህ ትውልድ ታሪካዊ #ኪሳራ ነው፡፡››

◾️ምክትል ጠ/ሚ አቶ ደመቀ መኮንን◾️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Donate Blood for #Cancer Patients @ National Blood Bank(Red Cross) - Ocutober 21,2018 * 10:00 AM - 5:00 PM
@Tsegabwolde @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#update ከላልይበላ ከተማ እና ከቅዱስ ላልይበላ ደብር የተወከሉ ልዑካን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ #ደመቀ_መኮንን ጋር በቅርሱ ጥገና ዙሪያ ባደረጉት ውይይት ቅርሱን ከጉዳት ለመከላከል የተሰራው መጠለያ በዚህ ዓመት እንደሚነሳ ቃል እንደተገባላቸው ተናግረዋል፡፡

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያ የሆነውና በአይነቱ የተለየ #የመልእክት እና #የገንዘብ መላላኪያ የስልክ መተግበሪያ በትላንትናው እለት በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተመርቆአል። ይህ 'ሜዳ ቻት' የተሰኘ መተግበሪያ #360_ግራውንድ በተባለ ሀገራዊ ድርጅት የተሰራ ሲሆን በአማርኛ, በኦሮምኛ, በትግርኛ እና በኢንጊሊዘኛ ቻት ማድረግ ያስችላል። የገንዘብ መላላኪያው አዲሱን የዳሽን ባንክን አሞሌ ኦንላይን ገንዘብ የሚጠቀም ሲሆን Wechat እንደተሰኘው የቻይናዊውያን መተግበሪያ ገንዘብን ልክ እንደመልክት እጅግ በቀለለ መልኩ መላክ እና መቀበል ያስችላል። ሜዳ ቻት በየቀኑ የሚያሸልም ጨዋታ, በርካታ ሀገራዊ ስቲከሮች እና ሌሎችም አገልግሎቶችን የያዘ ሲሆን መተግበሪያውን ለመስራት ከሶስት አመት በላይ ፈጅቷል።

ምንጭ፦ ብሩክ(ከሜዳ ቻት)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ወረራን ጨምሮ #ህገ_ወጥ ተግባራት እየተበራከቱ መምጣታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን እና ደንብ ማስከበር ጽህፈት ቤት አመራሮች እና ባለ ድርሻ አካላት ዛሬ ተወያይተዋል።

በውይይቱ ወቅት የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሜጀር ጄኔራል #ደግፌ_በዲ፥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ ህገ ወጥ የመሬት ወረራና ተግባር እየተበራከተ መምጣቱን ተናግረዋል።

ከመሬት ወረራው ባሻገርም የኮንትሮ ባንድ ንግድ እና ህገ ወጥ የመንገድ ላይ ንግድ መበራከቱንም ነው የተናገሩት።

ይህን ለመከላከልና የህግ የበላይነትን ለማስፈንም ህብረተሰቡን በማሳተፍ ውጤታማ ስራ ሊያሰራ የሚያስችል እቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር መግባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

ለወንጀሉ መስፋፋት መንስኤ በሆኑ ጫት ማስቃሚያ፣ ሺሻ ማስጨሻ እና ቁማር ማጫወቻዎች ላይ ልዩ ትኩረት ይሰጣል ያሉት ኮሚሽነሩ፥ የተደራጁ ወንጀለኞች ላይ እየተወሰደ ያለው እርምጃም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

የአስተዳደሩ ደንብ ማስከበር አገልግሎት ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ ኮሚሽነር ፍስሃ ጋረደው በበኩላቸው፥ ደንብን የማስከበር ስራ ለተቋማት ብቻ የሚተው ስራ አለመሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ አንጻርም ህብረተሰቡና ባለ ድርሻ አካላት ህግን ከማስከበር አኳያ ሁለቱ ተቋማት እያደረጉት ላለው ጥረት እገዛ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ኮሚሽኑ እና ጽህፈት ቤቱም በከተማዋ እየተስተዋለ ያለውን ህገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው እንደሚቀጥሉ መግለጻቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ለጣቢያችን የላከው መግለጫ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Track 15
New Artist (35)
#ሼር
ያቅታል እንጂ ቁምነገር መስራት
በጣም ቀላል ነው ሰውንስ #ማማት
ለሚመለከተው አካል‼️
(በተለይ ለሰሞነኞቹ....)
.
.
ስለማይረዱ #ማንነታቸውን
ከስራቸው ይልቅ ያምናሉ አፋቸውን
.
.
እየቀላቀሉ #ተንኮል እና #ክፋት
እየሸፋፈኑ እውነትን በሀሰት
#የሚደክመውን ሰው ቁጭ ብሎ በማማት
ትልቅ ኩነኔ ነው ላወቀው ሰው በእውነት
.
.
ያቅታል እንጂ ቁምነገር መስራት
በጣም ቀላል ነው ሰውንስ #ማማት
.
.
ስለማይረዱ ማንነታቸውን
#ከስራቸው ይልቅ ያምናሉ #አፋቸውን
.
.
ካልታገሉ በቀር አይሳካም #ምኞት
#ለየብቻ ናቸው መስራት እና ማውራት
እግዜር ከፈጠረው በዚህች ምድር ዓለም
ሆን ብሎ እንደማውራት #ቀላል ነገር የለም።
.
.
ያቅታል እንጂ ቁምነገር መስራት
በጣም ቀላል ነው ሰውንስ ማማት

©ክቡር ዶክተር አርቲስ ጥላሁን ገሰሰ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሳውዲ አረቢያ አመነች‼️ሳውዲ አረቢያ ከ17 ቀናት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጠኛ #ጀማል_ካሾጂ በኢስታንቡል ቆንስላዋ ውስጥ በተፈጠረ አምባጓሮ #መገደሉን አመነች። ከዚህ ጋር በተያያዘ የደህንነት መስሪያ ቤቷን ም/ኅላፊ ማባረሯን አስታውቃለች።

©BBC
@tsegawolde @tikvahethiopia
#update የከፍተኛ አመራሮች ስልጠና⬆️

ለመንግስት ከፍተኛ አመራሮች ስልጠና #በመሰጠት ላይ ነው::

ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ስልጠናውን ሲከፍቱ:-

▪️አመራሩ ለውጡን ለማስቀጠል የማያቋርጥ የመማርና የማድረግ ሂደት ውስጥ መግባት እንዳለበት።

▪️አመራሩ ለሚመራው ሰራተኛ/ ህዝብ ምሳሌ መሆን እንዳለበት:- ሰዓት በማክበር: በትጋት በመስራት: ውጤታማ በመሆን እንዲሁም በሌሎች ህዝቡን በሚጠቅሙ መልካም ተግባራት ምሳሌ ሆኖ ማሳየት እንዳለብት።

▪️እያንዳንዱ ሚንስትር የመጀመሪያ 100 ቀናት ዕቅድ በማዘጋጀት ፈጣና የህዝቡን ፍላጎት የሚመጥን ለውጥ ለማምጣት እንዲረባረብ አሳስበዋል።

ስልጠናው ቁልፍ በሆኑ ርዕሶች በተመረጡ የዘርፉ ምሁራን በመካሄድ ላይ ይገኛል። ስለጠናው ዛሬ እና ነገ (እሁድ) ሙሉ ቀናት የሚቀጥል
ይሆናል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia