ወልቂጤ⬆️በወልቂጤ ከተማ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራሮች ቅበላ እየተደረገላቸው ይገኛል።
ፎቶ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባላት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
መቐለ⬆️የትግራይ ክልል ምክር ቤት አምስተኛ ዘመን 13ኛ መደበኛ ጉባኤውን #በመቐለ ማካሄድ ጀምሯል፡፡ ምክር ቤቱ ለሶስት ቀናት በሚቆየው ጉባኤው በክልሉ ስራ አስፈፃሚ የበጀት ዓመት አቅድ ላይ ይወያያል፡፡
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ምንጭ፦ etv
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አምነስቲ ኢንተርናሽናል⬆️
ከትላንት በስቲያ የታሰሩት ጠበቃ #ሄኖክ_አክሊሉና አቶ #ሚካኤል_መላከ ያለ ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጠየቀ።
ፖሊስ በምርመራ ጊዜ መጠየቂያ መዝገብ ላይ ለክሱ መነሻ አድርጎ ያቀረበው የመደራጀት ምክንያት “መብት” እንጂ “ወንጀል” አይደለም ሲሉ የአምነስቲ የአፍሪካ ቀንድ ተመራማሪ አቶ ፍሰሃ ተክሌ ለቪኦኤ ገልፀዋል።
ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን ፍርድ ቤት አቅርቦ የ14 ቀን የምርመራ ጊዜ ቀጠሮ ጠይቆባቸው የነበረ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ሰባት ቀን ፈቅዷል።
ጠበቃ አለልኝ ምሕረቱ ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹ #ከፍልስጥዔም ኤምባሲ ጋር ግንኙነት ያደርጋሉ መባሉ እንዳሣዘናቸው ተናግረዋል።
ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ

አዳማ⬆️የኦነግ አመራሮች በአሁን ሰዓት በአዳማ ከተማ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል።
ፎቶ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ፦ የTIKVAH-ETH ቤተሰብ አባል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከሀሰተኛ ወሬዎች ተጠንቀቁ‼️
በአሐዱ ሬዲዮ ከአቶ #ጃዋር_መሃመድ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ተብሎ #በፌስቡክ የተሰራጨው መረጃ #የተሳሳተ መሆኑን አሐዱ ራድዮ በዛሬው ዕለት ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአሐዱ ሬዲዮ ከአቶ #ጃዋር_መሃመድ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ ተብሎ #በፌስቡክ የተሰራጨው መረጃ #የተሳሳተ መሆኑን አሐዱ ራድዮ በዛሬው ዕለት ገልጿል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የማህበራዊ ሚዲያ ህግ እየተዘጋጀ ነው‼️
በማህበራዊ ድረ ገጾች የሚለጠፉ መረጃዎች #ትክክለኛነታቸውንና በህዝቦች መካከል #ግጭት የማይፈጥሩ መሆናቸውን #ለማረጋገጥ መንግስት ህጋዊ አሰራርን ሊተገብር ይገባል ሲሉ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ተናገሩ።
ነዋሪዎቹ አክለውም ህጉ ትክክለኛነታቸው ሳይረጋገጥ በማህበራዊ ድረ ገጽ በሚሰራጩ መረጃዎች ምክንያት የሚከሰቱ ግጭቶችና #አለመግባባቶችን ከማስቀረቱም ባሻገር የዜጎችን #ትክክለኛ መረጃ የማግኘት መብት ለማረጋገጥ እድል ይፈጥራልም ብለዋል።
ከአስተያየት ሰጪዎች መካከል ወይዘሮ ተቋምወርቅ አሰፋ ይህን ብለዋል፦
"ፌስቡክ እውነትም ውሸትም አለው፤ በአሁኑ ሰዓት አልጠቀምም ብትል ከሚዲያ #ትርቃለህ እጠቀማለሁ ስትል ደግሞ #እውነታነቱ የቱ ጋር ነው ፌስቡክ አዘጋጆቹ ራሳቸው እነርሱ ናቸው የሚያውቁት መረጃውን የሚሰጠው አካል እውነታነቱ የቱጋ ነው ብሎ ሲያበቃ ሀሰተኛ መረጃ የሚያስተላልፉትን መንግስት #በህግ ሊከታተላቸው ይገባል˝ ብለዋል።
.
.
በሌላ በኩል...
በኢትዮጵያ ከማህበራዊ ሚዲያዎች አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ስርዓት ያለው አሰራር ለመፍጠር የሚያስችል ህግ #እየተዘጋጀ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር አበይ አህመድ በዚህ ሳምንት በህዝበ ተወካዮች ምክር ቤት ባደረጉት ንግግር ጠቅሰዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “የሚዲያ ነጻነት ሲባል በውሸት ስም ገፅ በመክፈት፣ ማንነትን በመደበቅ፣ ያልተገቡ ተግባራትን በማከናወን አይደለም” ሳይሆን ለአገርና ለህዝብ ግንባታ የሚውሉ ቁምነገሮችን በማሰራጨት መሆን ይገባልም ብለዋል።
ህጉ “በተደራጀ መልኩ ደመወዝ እየተከፈላቸው፤ አንዴ ኦሮሞ ሌላ ጊዜ ደግሞ አማራ፤ አንዱ ቦታ ሴት ፣ ሌላ ቦታ ደግሞ ወንድ ሌላም ሌላም በመሆን የሚሰሩ ሰዎችንም” #ተጠያቂ ለማድረግ ያለመ እንደሆነም ተናግረዋል።
የዚህ ዓይነቱን የማሕበራዊ ሚዲያ የሐሰት ፕሮፖጋንዳ ለመከላከልም ዋነኛው መፍትሔ ዋናዎቹ መገናኛ ብዙኃን ትክክለኛውን መረጃ ፈጥነው ለህዝብ ማድረስ መቻል መሆኑንም በአጽንኦት ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት

#update ጎንደር ጉሙሩክ⬆️
999 #ሽጉጥ እና 30 #የክላሽ_ጠበንጃ ጎንደር ጉምሩክ ላይ ተያዘ። ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ነዳጅ ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ተሳቢ ቦቲ መኪና በውስጡ ህገ ወጥ መሣሪያ ጭኖ ሲጓዝ በደረሠ ጥቆማ በህግ ቁጥጥር ስር መዋሉን የጎንደር ጉምሩክ አስታወቀ፡፡
ጥቅምት 10/2011 ዓ.ም (ጎንደር) የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ በቀን 03/02/2011 ዓ.ም ከሡዳን ወደ ጎንደር ሲጓዝ የነበረ ቤንዚን የጫነ ቦቲ መኪና ኮድ -3 87297 የፊቱ ተሳቢ ኮድ -3 27172 ኢት የሆነ ህገ ወጥ መሣሪያ ጭኖ ሲጓጓዝ ለጎንደር ጉምሩክ ቅርጫፍ ጽ/ቤት በደረሠ ጥቆማ በህግ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
የተያዘው የመሣሪያ ብዛትም ሽጉጥ 999/ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ/ ሲሆን የክላሽ ጠበንጃ ብዛት 30/ሠላሣ/ በመዳበሪያ ተጠቅሎ ከነዳጁ ጋር ተጭኖ መገኘቱን የጎንደር ጉምሩክ አስተውቋል፡፡ እስካሁን ባለው መረጃም እሽከርካሪውና እረዳቱ በህግ ስር ተይዘው የሚገኙ ሲሆን የመኪናው ባለቤት ግን መቅረብ አለመቻሉን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ የጎንደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ዘግቧል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት