TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update የእንግሊዝ የልማት ተራድኦ ድርጅት (DFID) የኢትዮጵያ ተወካይ ክርስቲያን ሮግ የሶማሌ ክልልን ጎብኝተዋል። መንግስትቸው ለክልሉ ልዩ ፖሊስ #ድጋፍ አድርጓል መባሉንም #አስተባብለዋል። ከክልሉ ፕሬዝዳንት #ሙስጠፋ_ዑመር ጋርም መልካም ውይይት ማድረጋቸውን ሀላፊው ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ዋዜማ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማርያም ተስፋዬ‼️ የታዳጊዋ የህክምና ተማሪ #ማርያም_ተስፋዬ ሰርጀሪ በዛሬው ዕለት #በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል።

ሁላችሁም ወደ ሙሉ ጤንነቷ እንድትመለስ በየእምነታችሁ ፀልዩላት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
#Update በአዲስ አበባ ከተማ ሁከት እና ብጥብጥ ለመፍጠር ወጣቶችን በማደራጀት #ጠርጥሪያቸዋለሁ ሲል ፖሊስ ሦስት ሰዎችን ዛሬ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

ምንጭ፦ የአሜሪካ ድምፅ ራድዮ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የመረጃ መደራረብ እና መሰልቸት እንዳይኖር ቻናላችን ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ብቻ ይህን ገፅ አዘጋጅቷል! ገፁ ለቀጣይ 1 ወር ብቻ የሚቆይ ነው!

https://telegram.me/TIKVAHUNIVERSITY
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
ይህ የተስተካከለ የመግቢያ ቀን የሚመለተው የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢኒስቲትዩት ተማሪዎችን ብቻ ነው። ሪፖርት የምታደርጉበት ቀን ከላይ ተቀምጧል።

@tsegabwolde @tikvahuniversity
#update በሀገሪቱ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ቄያቸው #መመለስ መቻሉን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በተለያዮ ጊዜያት በኢትዮጵያ በተፈጠረው ግጭት አያሌ ዜጎች ህይወታቸው አልፏል፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች ከቄያቸው ተፈናቅለው ለእንግልት #መዳረጋቸው ይታወቃል፡፡

ግጭቶቹም በዋናነት በኦሮሚያና ሶማሌ ክልል፣ በምዕራብ ጉጂና ጌዲዮ፣ በኦሮሚያና ቤንሻንጉል ጉሙዝ ባሉ አዋሳኝ አካባቢዎች እንዲሁም በሶማሊያ ክልልና በቡራዮ ከተማ የተከሰቱ ናቸው፡፡

በእነዚህም ግጭቶች ከተፈናቀሉ ዜጎች መካከል እስካሁን 930 ሺህ 150 ገደማ ሰዎች ወደ ነበሩበት አካባቢ መመለስ መቻሉን በብሔራዊ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አይ ኤስ አይ ኤስ 700 የሚደርሱ #የአሜሪካ እና #የአውሮፓ ሀገራት ዜግነት ያላቸውን ሰዎች በሶሪያ አግቷል፡፡ ከታጋቾቹ ውስጥም 10 የሚደርሱትን እንደገደላቸው ታውቋል፡፡ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በአካባቢው ያለውን የአሜሪካ ጦር ‹‹አስፈሪ ውድቀት›› ሲሉ ተችተውታል፡፡

ምንጭ፦ አር ቲ ኒውስ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ህወሓት⬇️

የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ ማዕከላዊ ኮሚቴ የድርጅቱን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥር ከ11 ወደ ዘጠኝ #ዝቅ አደረገ።

ማዕከላዊ ኮሚቴው ትናንት ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው ነው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥሩን ቀደም ሲል ወደነበረበት የቀነሰው።

በድርጅቱ ህገደንብ መሰረት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ቁጥርን የመጨመርም ሆነ የመቀነስ የድርጅታዊ ጉባኤ ስልጣን ነው።

ቀደም ሲል ማዕከላዊ ኮሚቴው ከዘጠኝ ወደ 11 ቁጥሩን ከፍ ሲያደርግ በድርጅታዊ ጉባኤ ውሳኔ አለመሆኑም የማስተካከያ ውሳኔው መነሻ እንደሆነ ተመልክቷል።

ድርጅቱ በቅርቡ ባካሄደው ድርጅታዊ ጉባኤ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መምረጡ ይታወሳል።

በምርጫው መሰረትም፦

1. ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል
2. ወይዘሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር
3. አቶ ጌታቸው ረዳ
4. አቶ አስመላሽ ወልደስላሴ
5. ዶክተር አብረሃም ተከስተ
6. ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም
7. አቶ ጌታቸው አሰፋ
8. ዶክተር አምባሳደር አዲስዓለም ባሌማ
9. አቶ ዓለም ገብረዋህድ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል ሆነው መመረጣቸው የሚታወስ ሲሆን፥ እነዚህን ጨምሮ አቶ በየነ መክሩ እና ዶክተር አክሊሉ ሀይለሚካኤል የተካተቱበት የህወሃት ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትንም መርጦ ነበር።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
"የታጠቁ ወታደሮች ወደ ቤተመንግስት የመጡበት ሁኔታ ኢ-ህገመንግስታዊ ብቻ ሳይሆን ፍላጎቱ የተጀመረውን ሀገራዊ ለውጥ #ማጨናገፍ
ነበር"

▪️ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ▪️
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች‼️

"የፀጥታ እና የደህንነት ስጋት እንዳይኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል።"
*
*
*
ነባርና አዲስ ተማሪዎች ተቀብሎ ለማስተናገድ የሚያስችል በቂ ቅድመ ዝግጅት ማድረጉንና የተማሪ ቤተሰቦችና ተማሪዎች #ከጸጥታና #ደህንነት ሥጋት ነጻ ለማድረግ #ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

የተማሪችን አቀባበል አስመልክቶ በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የምክክር መድረክ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲጎለብት የድርሻቸውን
ሚና እንደሚወጡ ባለድርሻ አካላት ጠቁመዋል፡፡
*
*
*
የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ባለፉት አስራ አንድ አመታት ሰላም የሰፈነበት የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀናጅቶ በመስራቱ በሃገር አቀፍ ደረጃ ሠላማዊ ዩኒቨርሲቲ መባሉ ይታወሳል፡፡ በዚህም በበርካታ ተማሪዎችና የተማሪ ወላጆች ዘንድ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ እየሆነ መጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በ2020 ከሃገሪቱ ምርጥ አምስት እንዲሁም በምስራቅ አፍሪካ ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ለመሆን የሚያስችለውን ተግባር በማከናወንና የተማሪዎች ቅበላ አቅሙን በማሳደግ የትምህርት መርሃግብሮቹን መጠን ከጊዜ ወደ ጊዜ በማሻሻል ፍላጎትን መሰረት አድርጎ እየሰራም ይገኛል፡፡

ዩኒቨርሲቲው የ2011 ዓ.ም የተማሪዎች ቅበላን አስመልክቶ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተወካዮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግስት ተጠሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና የሚመለከታቸው አካላትን በማሳተፍ ምክክር በማድረግ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በምክክር መድረኩ ተገኝተው መግለጫ የሰጡት የዩኒቨርቲው አካዳሚክ ጉዳዩች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ወንድሙ ወልዴ እንደገለጹት ዩኒቨርሲቲው ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን በማስፈንና የተማሪ ቅበላ አቅሙን 29ሺህ በማድረስ በትጋት እየሰራ መቆየቱን ነው የተናገሩት፡፡

ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት ለማስፈን እንዲቻል ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በቅርበት ሲሰራ መቆየቱን የተናገሩት ም/ፕሬዝዳንቱ፣ ከወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታዎች ጋር ተያይዞ የተፈጠረውን ስጋት ለመቆጣጠር የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ስራ ከሚመለከታቸው ባለከድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱንም አውስተዋል፡፡

ሠላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲሰፍን ከአካባቢው ማህበረሰብ፣ ከሃይማኖት አባቶች፣ መንግስትና ተቋሙ ልዩ ክትትል የሚያደርግና የተማሪ ቤተሰቦችና ተማሪዎች ከጸጥታና ከደህንነት ስጋት ነጻ ለማድረግ የሚያስችል ስራ መሰራቱንም ም/ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተናገድ እንዲቻል አስፈላጊው ዝግጅት ሁሉ በበቂ ሁኔታ መደረጉን የተናገሩት ዶ/ር ወንድሙ፣ የአካባቢው ማህበረሰብ በተለይም የጸጥታ አስከባሪዎች፣በጎ አድራጎት ማህበራት፣የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በሙላት ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተናገዱ ሂደት በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በመድረኩ በመሳተፍ መግለጫ ከሰጡት መካከል የሃገር ሽማግሌዎችን በመወከል አቶ ሚልኪያስ ኦሎሎ እና የሃይማኖት ተቋማትን በመወከል አቶ ሰይፉ ለታ እንደገለጹት ሠላም የሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተናገዱ ሂደት ሁሉም ባለድርሻ በባለቤትነት ሊሳተፍ ይገባል ብለዋል፡፡

ወላይታና አካባቢው እንግዳ ተቀባይ መሆኑንና አሁን ላይ ከተማሪ ቅበላ ጋር በተያያዘ አንዳች የሚያሰጋ የጸጥታና የደህንነት ስጋት እንደሌለ ጭምር ተሳታፊቹ አውስተዋል፡፡

የወላይታ ሶዶ ከተማ ፍትህና ጸጥታ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አንዱዓለም አዳነ አካባቢውን ከደህንነትና ከጸጥታ ስጋት ነጻ በማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማጠናከር ከአቀባበል ጀምሮ በዘላቂነት ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል ተግባር ዘርፉ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡

በዩቨርሲቲው የሰላም ፎረም ጽ/ቤት ፕሬዝዳንት ተማሪ በረከት አፈወርቅ ከዚህ ቀደም ከነበረው የተሻለ አቀባበል እንዲኖር ለማስቻል በተማሪዎች አደረጃጀት ዘርፍ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት መደረጉንና አዳዲስ ተማሪዎችን ከዩኒቨርሲቲውና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ለማላመድ መዘጋጀታቸውን ተናግሯል፡፡

በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የህግ ት/ቤት ዲን እና የወላይታ በጎፈቃደኞች ማህበር አባል መምህር ተከተል ለቤና አዲስና ነባር ተማሪዎችን የመቀበሉን ተግባር ከማሳካት ረገድ ማህበሩና የማህበሩ አባላት ጉልህ ተሳትፎ እንደሚኖራቸው ጠቁሟል፡፡

ተማሪዎችን በበጎ ፈቃድ ለማገልገል የማህበሩ አባላት ከምንጊዜውም በበለጠ ዝግጅት ማድረጋቸውንና አቀባበሉንም ደማቅ ለማድረግ
ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርበው እየሰሩ መሆናቸውን መምህር ተከተል አውስቷል፡፡

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2011 የትምህርት ዘመን ከ 15 ሺህ የሚበልጡ ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 3 ሺህ 4 መቶ ያህሉ አዲስ ገቢ ተማሪዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡

የመደበኛ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከጥቅምት 10 እስከ 14 ባሉት ጊዜያት ውስጥ እንደሚካሄድ የዩኒቨርሲቲው ሬጅስተራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት መግለጹም ይታወቃል፡፡

ምንጭ፦ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የቀድሞ የሱዳን ፕሬዘዳንት ሞቱ⬆️

የሱዳን የቀድሞ ፕሬዚዳንት አብዱልራህማን ሞሃመድ ሀሰን በሳዑዲ ዓረቢያ ዋና ከተማ #ሪያድ ወታደራዊ ሆስፒታል ውስጥ መሞታቸውን የሱዳን ዜና ኤጀንሲ ዘግቧል።

ከቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ሞት ምክንያት ጋር በተያያዘ ዝርዝር መረጃዎች አልተነገሩም። አብዱልራህማን ሞሃመድ ሀሰን ሲዋር አል ዳሃብ ከፈረንጆቹ 1985 እስከ 1986 ሱዳንን በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል።

ከዚያ ቀደም ብሎ የመከላከያ ሚኒስትር የነበሩ ሲሆን በ1985 ጃፋር ኒሜሪን ከፕሬዚዳንትነት የማውረድ ሂደትን መርተዋል።

የሱዳን መንግስት በቀድሞ ፕሬዚዳንቱ ህልፈት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update የውጪ ሀገራት ጉዞ⬇️

"ስምምነት ከተደረገባቸው አገራት ውጪ የሚደረግ ሕገወጥ ጉዞ መቆም አለበት" ም/ጠ/ሚ/ ደመቀ መኮንን
*
*
*
ባለድርሻ አካላት ኢትዮጵያ ስምምነት ካደረገችባቸው 3ቱ የአረብ ሀገራት የውጭ ሀገር ጉዞ ውጪ የሚደረገውን ሕገወጥ ጉዞ በማስቆም የድርሻቸውን እንዲወጡ የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን አሳሰቡ፡፡

ም/ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሕገወጥ የሰዎች ዝውውርን በመከላከል ኃላፊነት ለተሰጣቸው የፌዴራል ፖሊስ፣ ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት፣ ኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳዮች መምሪያ፣ ሲቪል አቪየሽን ባለሥልጣንና ኢትዮጵያ አየር መንገድ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡

አቶ ደመቀ መንግሥት መስራት ለሚችሉ ዜጎች በሀገር ውስጥ ምቹ የሥራ ዕድሎች የሚስፋፊበት ሁኔታ ለመፍጠር የሚያደርገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ ወደ ውጭ ሀገር በመሄድ ለመሥራት ፍላጎት ያላቸው ኢትዮጵያውያን መብታቸው ደህንነታቸው እና ክብራቸው ተጠብቆ ባላቸው ችሎታና አቅም ሰርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል የኢትዮጵያ የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2ዐዐ8 ማውጣቱን ለተቋማቱ በፃፉት ደብዳቤ አመልክተዋል፡፡

በዚሁ መሠረት አሁን ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈርሞ ሰራተኞችን ለመላክ ቅድመ ዝግጅት የተደረገባቸው ሀገራት #ሳዑዲ_አረቢያ#ኳታር
እና #ጆርዳን ብቻ መሆናቸውንም በደብዳቤያቸው ተጠቅሷል፡፡

ሆኖም ግን የሁለትዮሽ ስምምነት ካልተደረገባቸው ሀገራት መካከልም ኩዌት፣ ባህሪን፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ፣ ቤይሩት እና ኦማን በተለያዩ የቪዛ አይነቶች ማለትም በቱሪስት በዘመድ ጥየቃ፣ በጉብኝት፣ በንግድ በመሳሰሉት ምከንያቶች ከሀገር እየወጡ ሕገወጥ የሥራ ስምሪት የሚያደርጉ ግለሰቦች እንዲሁም በዚህ መልኩ ዜጎችን ወደ ውጭ የሚልኩ ኤጀንሲዎች መኖራቸውንም ጠቅሰዋል፡፡

በመሆኑም በዜጎች ላይ የሚደርሰውን የመብት ጥሰት ለመታደግ የሁለትዮሽ ስምምነት ወዳልተደረገባቸው ሀገራት በተለያዩ የቪዛ አይነቶች ለሥራ የሚሄዱ ዜጎች እና በዚህ ሁኔታ ዜጎችን የሚልኩ ኤጀንሲዎች ድርጊታቸው ሕጋዊ መሠረት የሌለው መሆኑ ታውቆ ጉዳዩ የሚመለከታቸው እነዚህ ተቋማት በሙሉ ሀገራዊ የሥራ ስምሪቱ በይፋ ከተከፈተበት ከመስከረም 30/2011 ጀምሮ ሕገወጥ አሠራሩ በአስቸኳይ እንዲቆም ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እንዲያደርጉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ጾታዊ ተዋፅዖውን የጠበቀ ካቢኔ ካዋቀረች ከሁለት ቀናት በኋላ #ሩዋንዳም የአዲስ አበባን ፈለግ በመከተል ግማሹን የካቢኔ አባላቷን ሴቶች ማድረጓ ተሰምቷል፡፡ ከ26ቱ አዲስ ተመራጭ የሀገሪቱ ካቢኔ አባላት መካከል 13ቱ #ሴቶች መሆናቸው ተገልጿል። ከሀገሪቱ የፓርላማ አባላት መካከልም 61 በመቶው ሴቶች መሆናቸውን አሶሺዬትድ ፕሬስ በዘገባው አስነብቦናል፡፡

@tseabwolde @tikvahethiopia
#update የወጣቶቹ አስተያየት⬆️

የወሰዱት የተሃድሶ ስልጠና በቀጣይ የአገራቸውን #ሰላም ለመጠበቅ ትልቅ መሰረት እንድሚሆናቸው በጦላይ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ስልጠና የተከታተሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ገለጹ።

ወጣቶች ባለፈው በአዲስ አበባ ተከስቶ በነበረው ሁከትና ብጥበጥ ተሳትፋችኋል ተብለው ነው ወደ ማሰልጠኛው የገቡት።

ከአዲስ አበባ ሁሉም አካባቢዎች ተይዘው ወደ ማሰልጠኛው የገቡት 1ሺ174 ወጣቶች ስለ ህገመንግስትና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ለተከታታይ አንድ ወር የተሃድሶ ስልጠና ሲዎስዱ ቆይተው ትናንት ወደ የመጡበት አካባቢ ተመልሰዋል።

ከቆየታቸው በኋላ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የሰጡ ወጣቶች እንዳሉት በአዲስ አበባ በነበረው ሁከትና ብጥብጥ ተሳትፋችኋል በሚል ተይዘን ነው ወደ ማሰልጠኛው የገባነው።

ተይዘው ወደ ማሰልጠኛ ከገቡ ጀምሮ የነበረውም እንድ ወንጀለኛ ሳይሆን ልክ እንደሌሎች ወታደራዊ ስልጠና እንደሚወስዱት ሰልጣኞች በበቂ ሁኔታ ስልጠናውን መውሰድ መቻለላቸውን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update አብዲ ኢሌ ከእስር ለማምለጥ ሞክረው ነበር‼️

የሶማሌ ክልል የቀድሞው ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሐመድ ከእስር ቤት #መስኮት ሰብረው ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ሲል ፖሊስ ገለጸ።

አቶ #አብዲ_መሐመድ ከሐምሌ 26 ቀን እስከ ሃምሌ 30 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ፥ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ በተፈጠረው ሁከትና ብጥብጥ ሳቢያ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።

አቶ አብዲ ዛሬ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የቀጠሮ ችሎት በቀረቡበት ወቅት፥ ለደህንነታቸውና ለጤናቸው ሲባል የፖሊስ ቢሮ ውስጥ ታስረው መቆየታቸውን ፖሊስ ገልጿል።

ይሁንና አቶ አብዲ የታሰሩበትን ቢሮ መስታወት በመስበርና አንድ የጥበቃ አባልን ጉሮሮ በማነቅ ለማምለጥ ሙከራ አድርገዋል ብሏል ፖሊስ በማብራሪያው።

አቶ አብዲ መሐመድ በበኩላቸው ድርጊቱን አለመፈጸማቸውን በመጥቀስ፥ ሆን ተብሎ ስሜን ለማጥፋትና እኔን ለመምታት የተደረገ ሴራ ነው ብለዋል።

ድርጊቱን ፈጽመዋል መባሉ ውሸት መሆኑንና በእርሳቸው ላይም ከፍተኛ ጫና እየተደረገባቸው እንደሆነም ተናግረዋል።

ምቹ ባልሆነ እስር ቤት መታሰራቸውን፣ የአዕምሮ ህመምተኛ የሆነ ታሳሪ የታሰሩበትን ክፍል በር ገንጥሎ በመግባት ሁለት ቀን ጉዳት ሊያደርስባቸው እንደሞከረና ይህም በደህንነታቸው ላይ ስጋት እንደፈጠረባቸውም ገልጸዋል።

በአንድ አጋጣሚም አንድ እስረኛ የሽንት ቤት በር ገንጥሎ እሳቸው ላይ በመጣል ጉዳት ሊያደርስ መሞከሩንም ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል።

የታሰሩበት እስር ቤትም የማይመችና በጤናቸው ላይ እክል እንደፈጠረባቸውም ነው አቶ አብዲ የተናገሩት።

መርማሪ ፖሊስ በበኩሉ አቶ አብዲ መሐመድ ማንኛውም እስረኛ በሚቆይበት እስር ቤት እንደታሰሩ ጠቅሶ፥ በእርሳቸው ላይ ምንም አይነት ጫና አለመደረጉን ገልጿል።

በተጨማሪም ፖሊስ ከእርሳቸው ጋር ውይይት ባደረገበት ወቅት ለግጭቱ መቀስቀስ ተጠያቂ መሆናቸውንና በዚህም ተጸጽተው ይቅርታ መጠየቃቸውንም አስረድቷል።

ፖሊስ በአብዲ መሐመድ የክስ መዝገብ ተጨማሪ መረጃ ለማሰባሰብ የ10 ቀን የምርመራ ጊዜ እንዲሰጠው ፍርድ ቤቱን ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱም ምርመራውን እያካሄደ ያለው ፖሊስ የምርመራውን ውጤት ለጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም ይዞ እንዲቀርብ በማሳሰብ ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ተያዘ⬇️

በአዲስ አበባ መስመር ወደ አዳማ ከተማ ሊገባ የነበረ 17 ሽጉጥና 45 ጥይት ዛሬ በተደረገ ድንገተኛ #ፍተሻ መያዙን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የአዳማ ከተማ አስተዳደር ልዩ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ዋና ሳጅን #ወርቅነሽ_ገልሜቻ እንደገለፁት ዛሬ ከጠዋቱ 1፡30 አካባቢ በአሰላ መስመር ወደ አዳማ መግቢያ ልዩ ስሙ ሶደሬ መንገድ ተብሎ በሚጠራው ቦታ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ 2 ሹጉጦች ተይዘዋል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ከቀኑ 10 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ከአዲስ አበባ ቃሊቲ መነሃሪያ የተነሳው ኮድ 3 – 42617 ኦሮ ሃይሩፍ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ አዳማ ከተማ መግቢያ ላይ ልዩ ስሙ መልከአዳማ በተባለው ስፍራ በተደረገው ድንገተኛ ፍተሻ ደግሞ 15 ሽጉጦችና 45 ጥይቶች ተይዘዋል፡፡

የጦር መሳሪያው ባለቤት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ህብረተሰቡ ተመሳሳይ ጥርጣሬ የሚያጭሩ የተለዩ ሁኔታዎች ሲያጋጥመው ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት #እንዲተባበር ዋና ሳጅን ወርቅነሽ መልእክት አስተላለፈዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢዜአ
@tsegabwolde @tikvahethiopia