TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.4K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ⬇️

በኢትዮጵያ እና ኤርትራ ድንበር ላይ የሰፈረው የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ወደ #ጦር ሰፈሩ መሰብሰብ እንደሚጀምር ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አስታወቁ።

በሁለቱ ሀገራት ድንበር አካባቢ ያለው ውጥረት የተሞላበት የጦርነት ስሜት ከአሁን በኋላ “በከፍተኛ ሁኔታ” #እንደሚቀንስም ተናግረዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ በቡሬ እና በዛላምበሳ ግንባሮች ያሉ የኢትዮጵያ እና የኤርትራ የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ጎብኝተው ከተመለሱ በኋላ በቦሌ አየር ማረፊያ በሰጡት መግለጫ ነው።

“የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከዛሬ ጀምሮ ድንበር አካባቢ ላይ #ውጥረት የነበረውን #የጦርነት ስሜት በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ ወደ ካምፕ በመሰብሰብ የሚያገግምበት፣ የሚሰለጥንበት፣ ራሱን የሚያበቃበት ሁኔታ ይፈጠራል” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ።

ምንጭ፦ Dw Amharic
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል‼️

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል በበርካታ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል፡፡ ጅማ፣ መቱ፣ አምቦ፣ ባኮ፣ ጉደር፣ ባሌ ሮቤ፣ ሆለታ፣ በደሌ፣ ቡራዩ፣ ወሊሶ እና ጊምቢ በርካታ ሰልፈኞች አደባባይ ከወጡባቸው ከተሞች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ በጅማ ዩኒቨርስቲም ተመሳሳይ ሰልፍ ተደርጓል፡፡

ሰልፈኞቹ በክልሉ ምዕራባዊ አካባቢዎች የዜጎች ግድያ እና መፈናቀል #ባስቸኳይ ይቁም፤ ወንጀለኞችም ተይዘው ለፍርድ ይቅረቡ በማለት ጠይቀዋል፡፡ በሕዝባዊ አመጹ ጊዜ የክልሉ ሕዝብ ላነሳቸው ጥያቄዎች መንግሥት መፍትሄ ይስጥ የሚሉ መፈክሮችም ተንጸባርቀዋል፡፡

የክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ጥቃቱን በሕዝቡ ላይ የከፈቱት አካላት በተቀናጀ #ሥልጠና እና #ጦር_መሳሪያ ተደግፈው ስለሆነ ባጭር ጊዜ ማስቆም አልተቻለም፡፡

በሌላ በኩል...

#በወልድያ ከተማ ታች አምና በዛሬዋ ዕለት የመንግሥት ጸጥታ ሃይሎች የገደሏቸውን ንጹሃን ዜጎች ለማሰብ ሰልፍ ተካሂዷል፡፡ ልጆቻቸው በግፍ የተገደሉባቸው ወላጆች በሰልፉ ላይ ንግግር አድርገዋል፤ የልጆቻችን ገዳዮች ለፍርድ ይቅረቡልን የሚል ጥያቄ ከሰልፈኞቹ ተሰምቷል፡፡

©wazemaradio
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰኔ 15 ጦር ሀይሎች አካባቢ ምን ተከሰተ?
/ከአሶሼትድ ፕሬስ ጋዜጠኛ #ኤልያስ_መሰረት/

ሰኔ 15 ቀን አመሻሽ ላይ በአማራ ክልል እንዲሁም በአዲስ አበባ ውስጥ ቦሌ አካባቢ የተከሰተው ግርግር እና ግድያ ብዙ ትኩረት ቢስብም #ጦር_ሀይሎች በተለምዶ ሲግናል (በድሮ አጠራሩ #መኮ) የተከሰተው ሁነት ግን እስካሁን ይፋ አልሆነም።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ቢያንስ ሶስት ምንጮች አረጋገጡልኝ እንዳለው ጦር ሀይሎች አካባቢ በነበረው ግጭት ሁለት ወይም ሶስት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። እስከ ለሊቱ ስድስት ሰአት ገደማም የጥይት ተኩስ ይሰማ ነበር። ይህ ክስተት በእለቱ ከነበሩት ሌሎች ግድያዎች ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ግልፅ አይደለም።

በቅርቡ ስለ ጉዳዩ በAPው ጋዜጠኛ የተጠየቁ አንድ የመንግስት የስራ ሀላፊ "ስለ ጉዳዩ መረጃ የለኝም። አጣርቼ መልስ ልሰጥህ እሞክራለሁ" የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

በጉዳዩ ዙሪያ መረጃ አለኝ ያለ አንድ ግለሰብ ለጋዜጠኛው ተከታዩን መረጃ አቀብሎ ነበር፦

"ስለ ሰኔ 15ቱ (የጦር ሀይሎች አካባቢ ጉዳይ) የተወሰነ መረጃ አለኝ። መረጃውን ላገኝ የቻልኩት ደግሞ በዛ ምሽት ከሞቱት ሶስት የፌዴራል ኮማንዶዎች አንዱ የአክስቴ ልጅ ስለነበር ሬሳ ለመቀበል ከቤተሰብ ጋር በሄድንበት ጊዜ የአሟሟቱ ጉዳይ ስለተነገር ነው። እናም ጉዳዩ ከጀነራሎቹ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠረ አንድ ኮሎኔል ለመያዝ በሄዱበት ጊዜ በተፈጠረው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት ነው። ግን እስካሁን አንድ የመንግሥት አካል ስለ ጉዳዩ ምንም ነገር አለማለታቸው እጅግ በጣም አሳዝኖኛል።"

Via #EliasMeseret
@tsegabwolde @tikvahethiopia