#Update
ፓኪስታን በዝንጀሮ ፈንጣጣ /Mpox/ በሽታ የተያዘ ሰው መግኘቱን አረጋገጠች፡፡
በበሽታው የተያዘው ሰው በቅርቡ ስሙን ካልገለጸው የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት የመጣ እንደሆነም የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡
በእስያዊቷ ሀገር ፓኪስታን የተገኘው ሰው ከአፍሪካ ውጭ በበሽታው የተያዘ ሰው ሲገኝ ይህ ለ2ኛ ጊዜ ነው።
ሚኒስቴሩ በድንበሮች አካባቢና ኤርፖርቶች ላይ ናሙና በመውሰድ የበሽታው ምልክት የታየባቸው ተጓዦች ወደ ህክምና ቦታ እንዲወሰዱ ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ #irishexaminer
@thiqahEth

👍9❤2😁1😱1
THIQAH
የዝንጀሮ ፈንጣጣ /Mpox/ በሽታን ለመቆጣጠር 50 ሺህ አስቸኳይ ክትባት ያስፈልጋል ተባለ፡፡ በአፍሪካ እየተስፋፋ የመጣውን ይህን በሽታ በፍጥነት ለመቆጣጠር 50 ሺህ ክትባት በአስቸኳይ እንደሚያስፈልግ ድንገተኛ የስነ ህይወት መፍትሄ /Emergent BioSolutions/ የተባለ ተቋም አስታውቋል፡፡ ክትባቱ በሽታው በፍጥነት እየተዛመተባቸው በሚገኙ ሀገራት ማለትም ኮንጎ፣ ቡርንዲ፣ ኬንያ፣ ኡጋንዳና…
በኮንጎ በዝንጀሮ ፈንጣጣ 18,000 ዜጎች ሲጠቁ፣ 629 ሰዎች ሞተዋል።
በበሽታው ክፉኛ በተጠቃችው ኮንጎ 18,000 ዜጎች ሲያዙ፣ 629 ሰዎች ደግሞ ሕይወታቸው አልፏል፡፡
የዓለም ጤና ድርጅት፣ በሽታው ወደ ተቀሰቀሰባት ኮንጎ የሚላከው ክትባት በቅርብ ቀናት ውስጥ እንዲደርስ ይደረጋልም ብሏል።
''በአፍሪካ የተከሰተውን የዝንጀሮ ፈንጣጣ /mpox/ በሽታ በስድስት ወራት ውስጥ እንገታዋለን'' ሲልም ገልጿል።
በሽታው የበለጠ ሳይስፋፋ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት እናቆመዋለን ያሉት ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም (ዶ/ር) ናቸው። #irishexaminer
@thiqaheth

👍14😭8❤3
"በፖላንድ ህገወጥ ስደትን በከፍተኛ ደረጃ እንቀንሳለን" - ዶናልድ ተስክ
ፓላንድ የጥገኝነት ጥያቄዎችን ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሟን ተከትሎ በሩሲያና ቤላሩስ ተቃውሞ ማስከተሉ ተነግሯል።
የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶናልድ ተስክ፣ ውሳኔው የተላለፈው በአዲሱ የኢምግሬሽን ፓሊሲ ምክንያት መሆኑን አስረድተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "በፖላንድ ህገወጥ ስደትን በከፍተኛ ደረጃ እንቀንሳለን" ሲሉ ተደምጠዋል።
የተስክ፣ ውሳኔ ከጎረቤት ሀገራት ሩሲያ እና ቤላሩስ ተቃውሞ አስከትሏል ተብሏል። #irishexaminer

👍11❤3🥰1
THIQAH
በምስራቃዊ ስፔን ቫሌንስያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በትንሹ 63 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል። በሀገሪቱ የቅርብ ጊዜ ታሪክ እንዲህ ያለው አስከፊ የጎርፍ አደጋ አጋጥሞ አያውቅም ተብሏል። @thiqaheth
#Update!
በስፔን የሟቾች ቁጥር ከ95 ማለፉ ተሰማ።
በቫሌንሽያ ከተማ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ
የሟቾች ቁጠር ከ95 ማለፉ ተሰምቷል።
አደጋው በድልድዮችና ህንጻዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የከተማዋ ባለስልጣናት ተናግረዋል፡፡
አደጋውን ተከትሎ በማድሪድና ባርሴሎና ከተሞች ት/ቤቶች እንድዘጉ፤ የባቡር ትራንስፖርት በጊዜያዊነት እንዲቆሙ ተወስኗል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ በጎርፉ የወደሙ መሠረተ ልማቶችን በፍጥነት መልሰን እንገነባቸዋለን ሲሉ ቃል ገብተዋል። #irishexaminer

😢14👍3❤2😁1😭1
በሞዛምቢክ የምርጫ ውጤትን ለመቀወም የወጡ ቢያንስ 10 ሰዎች በፖሊስ ተገደሉ፡፡
የሞዛብቢክ መንግስት በሀገሪቱ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተከትሎ 'ምርጫው ተጭበርብሯል' ባሉ ዜጎች ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
ምርጫው ከጅምሩ ግልጸኝነት የጎደለው እንደሆነ አለማቀፍ ታዛቢ ድርጅቶችም ገልጸዋል፡፡
የምርጫ ውጤቱን ለመቃወም ከወጡ ሰዎች መካከል ቢያንስ 10ሩ በፓሊስ መገደላቸው ተመላክቷል።
ሞዛምቢክ በፈረንጆቹ 1975 ከፖርቹጋል ነጻ ከወጣች በኋላ ላለፉት 40 አመታት በፍረሊሞ ፓርቲ እየተመራች ትገኛለች፡፡ #irishexaminer

👍11😢3❤1🤔1
"ለሰላማዊ መፍትሄ አስተዋጽዖ ለማድረግ እርዳታውን አቁመን እየገመገምን ነው" - አሜሪካ
ትራምፕ ለዩክሬን የሚደረገውን ድጋፍ በጊዚያዊነት አቋረጡ፡፡
ይህም ትራምፕ ከፕሬዝዳንት ዘለንስኪ ጋር በነጩ ቤተመንግስት በሙግትና በክርክር የተሞላ ውይይት ካደረጉ በኋላ የወሰዱት እርምጃ ነው ተብሏል፡፡
አንድ ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የነጩ ቤተመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን፣ ትራምፕ ያስተላለፉት ትዕዛዝ ዩክሬን ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ዝግጁ መሆኗን እስከምታሳውቅ ድረስ ተግባራዊ ሆኖ እንደሚቆይ አረጋግጠዋል፡፡
ዩክሬን ከአሜሪካ የምታገኘው እርዳታ መቋጡን በተመለከተ በተላለፈው ውሳኔ ላይ የሰጠችው ምላሽ የለም። #irishexaminer
@ThiqahEth

👍18🤔1
"ትራምፕ 'ካናዳ ሀገር አይደለችም' በማለት እኛን ከፋፍሎ ሊጠቀልል ያስባል፤ ያ እንዲፈጠር በጭራሽ አንፈቅድም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ
ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ፣ “ሊከበር የሚገባው ሉዓላዊነት የሚባል ነገር አለ“ ሲሉ ተደምጠዋል።
አዲሱ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁነው የተሾሙት ካርኔይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “የካናዳን ሉዓላዊነት ማክበር አለበት“ ነው ያሉት።
“በትራምፕ ኢፍትሃዊ የንግድ እንቅስቃሴ የተነሳ በህይወት ዘመናችን አይተን የማናውቀውን ፈተና እየተጋፈጥን ነው“ ሲሉም ተናግረዋል።
ካርኔይ፣ “ትራምፕ ካናዳ ሀገር አይደለችም በማለት እኛን ከፋፍሎ ሊጠቀልል ያስባል፤ ያ እንዲፈጠር በጭራሽ አንፈቅድም“ በማለት ገልጸዋል፡፡ #irishexaminer #thenational

👍5😁1
"ዋሽንግተን እና የእስያ አጋሮቿ የሚጠነስሱት ሴራ እውን እንደማይሆን ግልጽ ነው" - ዮ ኡንግ
የኪም ጆንግ ኡን እህት የኑክሌር ፕሮግራምን ማስቆም "የቀን ቅዥት" ስትል አጣጣለች፡፡
የሰሜን ኮሪያው ፕሬዝዳንት ታናሽ እህት ኪም ዮ ኡንግ ሀገራቸው የኑክሌር ፕሮግራምን መቼም ቢሆን የማቆም እቅድ የላትም ብለዋል፡፡
ዮ ኡንግ፣ "ዋሽንግተን እና የእስያ አጋሮቿ የሚጠነስሱት ሴራ እውን እንደማይሆን ግልጽ ነው" ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሜሪካ፣ ጃፓንና ደቡብ ኮሪያ ከቀናት በፊት በነበራቸው የሶስትዮሽ ውይይት ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ፕሮግራሟን እንድታቆም የጋራ ስምምነት አድርገዋል፡፡
ከፕሬዝዳንቱ በመቀጠል በሰሜን ኮሪያ ፖለቲካ ተጽዕኖ ፈጣሪ እንደሆነች የሚነገርላት ዮ ኡንግ ስምምነቱን ጸብ አጫሪ በማለት ተችተዋል፡፡ #irishexaminer

👍25❤7😁4😡4🥰1🤔1
"ፑቲን እና ዘለንስኪን ማገናኘት ይሻላል" - አሜሪካ
ጄዲ ቫንስ፣ "ሩሲያ ከመጠን በላይ ነው እየጠየቀች ያለችው" አሉ።
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ፣ ሞስኮ በሰላም ድርድሩ ብዙ ቅድመ ሁኔታዎችን እያስቀመጠች መሆኑን ጠቁመዋል።
"ሩሲያ ጦርነቱ እንዲቆም አትፈልግም ማለት አይደለም ግን ያቀረበችው የ30 ቀን የተኩስ አቁም እቅድ በአሜሪካ ዘንድ ዘላቂ መፍትሄ ስለማይሆን ተቀባይነት የለውም" ብለዋል።
ቫንስ፣ "ፑቲን እና ዘለንስኪን በአካል ማወያየት በአጭር ጊዜ መፍትሄ ሊያመጣ ይችላል" ሲሉ አክለዋል። #irishexaminer

👍15😁3❤2🥰1🤔1😱1
የዓለም አቀፍ ወንጀለኞች ፍርድ ቤት በኒታንያሁ ላይ የተላለፈው የእስር ማዘዣ ጸንቶ እንዲቆይ ወሰነ።
ውሳኔው እንዲቀለበስ የሚያስችል ሁኔታ አለመኖሩን የፍርድ ቤቱ ወንጀል መርማሪ ቡድን አስታውቋል።
ፍርድ ቤቱ እስራኤል በጋዛ ላይ የጦርነት ወንጀል ፈጽማለች በማለት በጠቅላይ ሚኒስትር ኔቲንያሁና በመከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት ላይ የእስር ትዕዛዝ ማውጣቱ ይታወሳል። #irishexaminer

👍36😁5🤔3❤1🔥1🥰1
THIQAH
Photo
"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል። አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" - ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ትራምፕ በአውሮፓ ላይ የጣሉትን የ50% ታሪፍ ለወር አራዘሙ።
ከአውሮፓ ህብረት ፕሬዝዳንት ኦርሱላ ቮንደርሊን ጋር ውይይት ካደረጉ በኋላ ሰኔ ላይ ይተገበራል ያሉት ውሳኔ ወደ ሐምሌ እንዲዛወር መወሰናቸውን ገልጸዋል።
"ቀጥተኛ ድርድር አድርገናል" ያሉት ትራምፕ "አጥጋቢ ስምምነት ላይ ለመድረስ ጊዜ ያስፈልጋል" ሲሉ የተራዘመበትን ምክንያት አብራርተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ከአውሮፓ በሚገቡ ምሬቶች ላይ የጣሉት ቀረጥ ባለፈው ሳምንት ከ30% ወደ 50% ከፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።#irishexaminer

😁8👍2❤1🔥1😱1
"አሜሪካ የንግድ ስምምነቱ የማይቻል መሆኑን ካረጋገጠች፣ የአውሮፓ ህብረት የ21 ቢሊዮን ዶላር ታሪፍ አዘጋጅቷል" አንቶኒዮ ታጃኒ
የአውሮፓ ህብረት በአሜሪካ ላይ 21 ቢሊዮን ዶላር ታሪፍ ለመጣል መዘጋጀቱን አስታወቀ።
ህብረቱ በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረገው የንግድ ውይይት ለውጥ ካላመጣ በአሜሪካ ምርቶች ላይ ቀረጥ እንደሚጀምር ገልጿል።
የቀድሞው የጣሊያን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአውሮፓ ፓርላማ ፕሬዝዳንት አንቶኒዮ ታጃኒ የአውሮፓ ሀገራት የማቅለያ እርምጃ መውሰድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።
ታጃኒ "አሜሪካ ስምምነቱ የማይቻል መሆኑን ካረጋገጠች፣ የአውሮፓ ህብረት የ21 ቢሊዮን ዶላር ታሪፍ አዘጋጅቷል" ሲሉ ተናግረዋል።
ጣሊያናዊዩ ዲፕሎማት አንቶኒዮ ታጃኒ "ቀረጥ ከአሜሪካ ጀምሮ ሁሉንም ይጎዳል" በማለት ገልጸዋል። #irishexaminer

❤8👏5🕊4🤔1🙏1