THIQAH
13.3K subscribers
2.6K photos
29 videos
1 file
23 links
ይህ ቲቃህ (ታማኝ) ኢትዮጵያ በቲክቫህ ኢትዮጵያ ሥር የሚተዳደር የኢትዮጵያን ጨምሮ ወቅታዊ ዓለም አቀፋዊ መረጃዎች የሚቀርቡበት ገጽ ነው።
Download Telegram
ፕሬዝዳንት ማዱሮ በምርጫ ማሸነፋቸውን ተከትሎ በቬኒዝዌላ አመጽ ተቀስቅሷል፡፡

ቬኒዝዌላውያን ከፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ውጤት ይፋ መሆን በኋላ ወደ ዋና ከተማዋ ካራካስ ለተቃውሞ አደባባይ ወጥተዋል።

በዚህም ከፀጥታ ሃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተዋል።

የፕሬዚዳንት ኒኮላስ ማዱሮን መመረጥ የተቃወሙት የተፎካካሪ ፓርቲዎች በበኩላቸው፣ የምርጫው ውጤት እንዲቀየር ጠይቀዋል።

ቬንዙዌላ በተካሄደው ምርጫ ፕሬዝዳንት ማዱሮ 51 በመቶ በሆነ ድምጽ ማሸነፋቸውን የማዕከላዊ ምርጫ ባለስልጣን አስታውቋል፡፡
#thenational

@thiqahEth
👍181🥰1
"በሶስተኛው ዓለም ጦርነት ቁማር እየተጫወትክ ነው፤ አንተ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ፍላጎት የለህም፣ በሚሊዮኖች ህይወት እየቀለድክ ነው" - ትራምፕ

"ፑቲንን መቼ አወራኸው ? ምን አለህ ? 25 ጊዜ የፈረመውን ስምምነት የጣሰው ራሱ" - ዘለንስኪ

"በሚዲያ ፊት ከምትከራከር ስህተትህን አምነህ ተቀበል" - ጄይዲ ቫንስ

የትራምፕና የዘለንስኪ ውይይት ያለስምምነት ተጠናቀቀ።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ በሩሲያ ጋር ስለሚደረገው ስምምነት ለመነጋገር ወደ አሜሪካ ያደረጉት ጉዞ ውጤታማ አለመሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዘለንስኪን "የሚሰማንን ስሜት አንተ አትነግረንም" በማለት ከተለመደው የመሪዎች ንግግር ወጣ ባለ መልኩ ኃይለ ቃል ሲለዋወጡ ተደምጠዋል።

ይህን ተከትሎ ዘለንስኪ የማዕድን ስምምነት ፊርማ አለመፈረማቸው ተዘግቧል።

ትራምፕ፣ "በሶስተኛው የአለም ጦርነት ቁማር እየተጫወትክ ነው: አንተ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ ፍላጎት የለህም፡ በሚሊዮኖች ህይዎት እየቀለድክ ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

ዘለንስኪ በበኩላቸው፣ "ፑቲንን መቼ አወራኸው ? ምን አለህ ? 25 ጊዜ የፈረመውን ስምምነት የጣሰው ራሱ" ሲሉ ተደምጠዋል።

በነጩ ቤተመንግሥት በተደረገው ውይይት የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄጂ ቫንስ ዘለንስኪን፣ "ለአሜሪካ ህዝብ አክብሮት ሊኖርህ ይገባል" በማለት በስሜት ተናግረዋል።

"በሚዲያ ፊት ከምትከራከር ስህተትህን አምነህ ተቀበል" ሲሉም ተደምጠዋል። #startribune#kyivpost#thenational#scotsman#buenosairestimes

@ThiqahEth
👍41😁5👌3😱21
"ትራምፕ 'ካናዳ ሀገር አይደለችም' በማለት እኛን ከፋፍሎ ሊጠቀልል ያስባል፤  ያ እንዲፈጠር በጭራሽ አንፈቅድም" - ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ

ጠቅላይ ሚኒስትር ማርክ ካርኔይ
“ሊከበር የሚገባው ሉዓላዊነት የሚባል ነገር አለ“  ሲሉ ተደምጠዋል።

አዲሱ የካናዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሁነው የተሾሙት ካርኔይ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ “የካናዳን ሉዓላዊነት ማክበር አለበት“ ነው ያሉት።

“በትራምፕ ኢፍትሃዊ የንግድ እንቅስቃሴ የተነሳ በህይወት ዘመናችን አይተን የማናውቀውን ፈተና እየተጋፈጥን ነው“ ሲሉም ተናግረዋል።

ካርኔይ፣ “ትራምፕ ካናዳ ሀገር አይደለችም በማለት እኛን ከፋፍሎ ሊጠቀልል ያስባል፤ ያ እንዲፈጠር በጭራሽ አንፈቅድም“ በማለት ገልጸዋል፡፡
#irishexaminer   #thenational

@ThiqahEth
👍5😁1
THIQAH
"ጠላት አየር መንገዳችን ላይ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት አድርሶብናል" - የሰነዓ አየር መንገድ ዳይሬክተር እስራኤል በሰነዓ አየር መንገድ ላይ ፈጸመችው በተባለ ጥቃት ሦስት የየመን አውሮፕላኖችና ስድስት የጦር ጄቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ተባለ። ዝርዝሩን ይጠብቁ @ThiqhEth
"አየር መንገዱን ለመጠገን ሰፊ ጊዜ ይወስድብናል" - አል ሻይፍ

"ጠላት አየር መንገዳችን ላይ 500 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ውድመት አድርሶብናል" ሲሉ ሰነዓ አየር መንገድ ዳይሬክተር ተናግረዋል።

እስራኤል በሰነዓ አየር መንገድ ላይ ፈጸመችው በተባለ ጥቃት ሦስት የየመን አውሮፕላኖችና ስድስት የጦር ጄቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል ተባለ።

የሰነዓ አየር መንገድ ጄነራል ዳይሬክተር ካሊድ አል ሻይፍ፣ "ጠላት አውሮፕላኖቻችንን ከነ መቀያየሪያዎቹ፣ መጋዘኖች እና ተርሚናሎች አውድሞብናል" ሲሉ ተናግረዋል።

"በጊዚያዊነት ስራ ለመጀመር አማራጮች አሉ"  ያሉት አል ሻይፍ፣ ነገርግን "አየር መንገዱን ለመጠገን ሰፊ ጊዜ ይወስድብናል" ብለዋል።

ጥቃት መፈጸሙን ያመነው የእስራኤል ጦር በሁቲ አማካኝነት ለተፈጸመበት ጥቃት የወሰደው የአጸፋ እርምጃ መሆኑን አስታውቋል።

በኢራን ይደገፋል የሚባለው በየመን የሚንቀሳቀሰው የሁቲ አማፂ ቡድን ከሁለት ቀን በፊት በእስራኤል ቤን ጉሪን አየር መንገድ ላይ ጥቃት ማድረሱ ይታወሳል። 
#thenational

@ThiqahEth
👍302🔥1🙏1
"50% ፍልስጤማውያን ጋዛን ለቀው ይወጣሉ" - ኔታንያሁ

ጠቅላይ ሚኒስትር ቢኒያም ኔታንያሁ "ፍልስጤማውያንን ለመቀበል ፍላጎት ያላቸውን ሀገራት እየፈለግን ነው" ብለዋል።

እስራኤል ወደጋዛ ለመግባት "ሙሉ ሃይሏን አዘጋጅታለች" ያሉት ኔታንያሁ "ሀማስን ሳናጠፋና ታጋቾችን ሳናስለቅቅ አንመለስም" ሲሉ ተናግረዋል።

"ሀማስ ታጋቾችን እለቃለሁ ሊል ይችላል፣ ጥሩ ነው ይመለሱ፣ እንቀበላለን ነገርግን ወደ ጋዛ መግባታችን የማይቀር ነው" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ "ጦርነት ልናቆም የምንችልበት ሁኔታ አይኖርም" ያሉ ሲሆን "ጊዚያዊ የተኩስ አቁም ግን ሊኖር እንደሚችል ጠቁመዋል።
#thenational

@ThiqahEth
😡48🔥13👍10😭6🥰1🤔1😱1
"ዛሬ ብቻ ከ100 የሚበልጡ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት ተገድለዋል"  - የጋዛ ጤና ሚኒስቴር

በዛሬው እለት ብቻ "ከ100 የሚበልጡ ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት" መገደላቸውን የጋዛ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጦር አውሮፕላኖች ጥቃት ያደረሱት ተፈናቃዮች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ መሆኑ የጉዳቱ መጠን እንዲጨም ር ማድረጉን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የጋዛ ከተማ አስተዳደር ቃል አቀባይ ሙሀመድ ባዙል በበኩላቸው፣ ንጹሐሃኑ የተገደሉት በአስከፊ
#የቦምብ_ጥቃት ነው ብለዋል። #thenational

@ThiqahEth
😢67😡6👍5😭4🤔3🥰2
"ሁሉም ክሶቹ ማንነታቸው በማይታወቁ ሀሰተኛ ምስክሮች የታጀበ ማስረጃ የሌለው የሴራ ውሳኔ ነው"  - ፓርቲው

የቱኒዝያ ተፎካካሪ ፓርቲ መሪ ራችድ ጋኖቺ የ14 አመት እስራት ተፈረደባቸው።

የእንሃዳ ንቅናቄ ፓርቲ መሪው ጋኖቺ፣ "በብሔራዊ ደህንነት ላይ በማሴር" ወንጀል ተከሰው ከቀረቡ በኋላ ነው የቱኒዚያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የእስር ውሳኔውን ያሳለፈባቸው።

ፓርቲያቸው እንሃዳ "ሁሉም ክሶቹ ማንነታቸው በማይታወቁ ሀሰተኛ ምስክሮች የታጀበ ማስረጃ የሌለው የሴራ ውሳኔ ነው" በማለት የፍርድ ውሳኔውን እንደማይቀበለው ገልጿል።

ጋኖቺ የሀገሪቱ ፖርላማ አፈጉባኤ በመሆን አገልግለዋል። ከ6 አመት ቀፊት የወቅቱ ፕሬዝዳንት ካዒስ ስዒድ ወደ ስልጣን ሲመጡም እስር ቤት ገብተው ነበር ተብሏል።
#thenational

@ThiqahEth
8🤔3🕊2👏1
በሱዳን ከ1.3 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ወደ መኖሪያ ቤታቸው ተመልሰዋል ተባለ።

320,000 ዜጎች ሀገራቸውን ለቀው ወደ ጎረቤት ሀገራት መሰደዳቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

በሱዳን ጦር እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ጦርነት ምክንያት በድምሩ 7.7 ሚሊዮን ሱዳናውያን መፈናቀላቸውን የድርጅቱ ሪፖርት አመላክቷል።#thenational

@ThiqahEth
13🕊5👏2🙏1