ኦንላይን ትምህርት በቅርብ ጊዜ ተጀምሮ አሁን ላይ በስፋት በብዙ ሰዎች ተመራጭ መሆን የቻለ መስክ ነው። በተለይ የጊዜ እና የቦታ ገደብ አለመኖሩ፣ ለትምህርት የሚሆኑ ማቴሪያሎች በብዛት እና በቀላሉ መገኘታቸው እንዲሁም ከወጪም አንጻር ዝቅተኛ መሆኑ ተመራጭ አድርጎታል። ስታቲስታ በተባለው ኢንተርናሽናል ድርጅት የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ትምህርታቸውን በኦንላይን የተማሩ ተማሪዎችን እስከዛሬ ከተማሩበት እና ከተለመደው የአካል የክፍል ትምህርት ጋር በማወዳደር የትኛው የተሻለ ጥራት እንዳዩበት በመረጡበት ጥናት የኦንላይን ትምህርት ስኬታማ መሆኑን የሚያሳዩ ምላሾች ተገኝተዋል። የተማሪዎቹ ምላሽ በዝርዝር በግራፍ በምስሉ ላይ ተካቷል።
#Ashewa_technology_solutions
#Ashewa_Elearning
#Online_learning
#Ashewa_technology_solutions
#Ashewa_Elearning
#Online_learning