#BahirDarUniversity #FacultyPromotions
ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለሦስት ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት ሰጠ።
የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ባደረገው መደበኛ ስብሰባ ለሦስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት አፅድቋል።
የሙሉ ፕሮፌሰርነት ዕድገት ያገኙ ምሁራን፦
1. ዶ/ር አወቀ አንዳርጌ በአፕላይድ ሒሳብ
2. ዶ/ር ገብረእግዚአብሔር ካሕሳይ በ Solid State Physics.
3. ዶ/ር ታደሰ አምሳሉ በ Land Policy and Natural Resource.
ምሁራኑ ባበረከቷቸው የምርምር፣ የማኅበረሰብ አገልግሎት እና የመማር ማስተማር ሥራዎቻቸው ተገምግመው ከተባባሪ ፕሮፌሰርነት ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማደጋቸው ተገልጿል።
@tikvahuniversity

👍126❤12🙏5👏4
#BahirDarUniversity
በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን ለመከታተል ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ሐምሌ 22 እና 23/2016 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ሪፖርት ማድረጊያ ቦታዎች፦
➧ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በፖሊ ካምፓስ
➧ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በግሽ ዓባይ ካምፓስ
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➧ የ12ኛ ክፍል ሰርቲፊኬት ዋናውና ኮፒው
➧ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
➧ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ

👍98👎45😱28❤22😢15👏3🥰1
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 93.3 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።
@tikvahuniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ግዜ ከወሰዱ የቅድመ ምረቃ መደበኛ ፕሮግራም ዕጩ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል 93.3 በመቶ ተማሪዎች የማለፊያ ውጤት ማስመዝገባቸውን ገልጿል።
@tikvahuniversity
👍67❤13👏4
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።
ተመራቂዎቹ በመደበኛው፣ በክረምት፣ በተከታታይ እና በርቀት መርሐግብር ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው፡፡
➭ አጠቃላይ ተመራቂዎች - 8,524
➭ በፒኤችዲ - 82
➭ በማስተርስ ዲግሪ - 1,119
➭ በመጀመሪያ ዲግሪ - 2,589
➭ በስፔሻሊቲ እና ሰብ-ስፔሻሊቲ - 62
➭ በፒጂዲቲ - 4,334
➭ በኤችዲፒ - 96
➭ በአመራር ሰርተፊኬት - 6
➭ በማሪታይም- 234

👍118❤25😢9
#BahirDarUniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ኦሪጅናል ዲግሪ እንዲሠራላችሁ በ45ኛ ዙር የጠየቃችሁ 106 አመልካቾች ኦሪጅናል ዲግሪያችሁ የደረሰ በመሆኑ መውሰድ እንደምትችሉ አሳውቋል፡፡
ኦሪጅናል ዲግሪ ለመውሰድ ስትሔዱ ክሊራንስ እና ቴምፖራሪ ኦርጅናሉን መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
(ኦሪጅናል ዲግሪ የደረሰላችሁ አመልካቾች ስም ዝርዝር ከላይ ተያይዟል፡፡)

👍92❤12😢5👏4🙏4🥰3
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ ለመሆን የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች የሚያከናውን ጽ/ቤት ከፍቷል፡፡
የዩኒቨርሲቲውን የራስ ገዝነት ጉዞን ዕውን ለማድረግ ግብረ-ኃይል ተቋቁሞ ወደ ሥራ መግባቱን የተቋሙ ፕሬዝዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ከዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ክፍል ዲኖች እና ኃላፊዎች ጋር በ2017 የትምህርት ዘመን የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ዘርፍ የትኩረት መስኮች ላይ ውይይት ባደረጉበት ወቅት ነው ይህን የገለፁት፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመቀጠል ራስ ገዝ ከሚሆኑ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች መካካል ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ አንዱ መሆኑ ይታወቃል፡፡

👍59👎6❤5👏2😢1
#BahirDarUniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም በድኅረ ምረቃ ፕሮግራሞች ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር አውጥቶት የነበረውን ማስታወቂያ "በተመዝጋቢዎች ተደጋጋሚ ጥያቄ" እስከ ጥቅምት 8/2017 ዓ.ም አራዝሟል።
መስፈርቱን የምታሟሉና መማር የምትፈልጉ አዲስ አመልካቾች በኦንላይን https://studentportal.bdu.edu.et ወይም በአካል በመገኘት ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። ካልቻሉ ደግሞ በኢሜይል አድራሻ [email protected] ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
አመልካቾች ሀገር አቀፍ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባችሀኋል።

👍112❤10👏7🙏6😱1
#BahirDarUniversity
በ2017 ዓ.ም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ ገቢ የመጀመሪያ ዲግሪ ተማሪዎች እና በ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተከታትላችሁ ወደ Freshman Program የመግቢያ ውጤት ያስመዘገባችሁ ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ከህዳር 16-18/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በሰላም ግቢ
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በፔዳ ግቢ
በተለያየ ምክንያት አንደኛ ዓመት አንደኛ ሴሚስቴር ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ህዳር 19 እና 20/2017 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
በ2017 ዓ.ም ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ወደፊት ይገለፃል ተብሏል።

👍229❤18🥰9👎8👏6😱5🙏4
#BahirDarUniversity
የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በ Health Genomics የማስተርስ ፕሮግራም አስጀመረ፡፡
በ Health Genomics የማኅበረሰብ ጤና ማስተርስ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ሲከፈት ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል፡፡

👍70❤3👏2🙏1
#BahirDarUniversity
በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።
ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

👍250❤28👎26😢26🥰10👏10😱3🙏3
#BahirDarUniversity
በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ሬዚደንት ሐኪሞች የምዝገባ ጊዜ ሚያዚያ 2 እና 3/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በቅጣት ምዝገባ፦ ሚያዚያ 6/2017 ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ፦
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሬጅስትራር ጥበበ ጊዮን ካምፓስ
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ፦
➫ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በፖ.ሣ.ቁ. 79 ማስላከ፣ መድረሱን ማረጋገጥ እና "TRN" ቁጥር ማቅረብ
➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዋናው እና ኮፒው)
➫ አራት ጉርድ ፎቶግራፍ
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፎርም ተሞልቶ በስፖንሰር አድራጊው ተቋም የተፈረመ)
ለሁሉም ትምህርት ክፍሎች ገለጻ (Orientation) ሚያዚያ 7/2017 ዓ.ም ጠዋት 3፡00 ሰዓት ይሰጣል ተብሏል፡፡

👍99❤18👏4😱2🙏1
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የዲጂታል ትምህርት እና ምርምር በተደራጀ መልኩ ለመስጠት የሚያስችል ዘመናዊ የድምጽ እና ምስል ሰቱዲዮ ሥራ አስጀምሯል፡፡
በዩኒቨርሲቲው ጂኦስፓሺያል ዳታ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል ውስጥ የተመረቀው ስቱዲዮው፤ በስትራቴጂክ አጋርነት ከኔዘርላንድሱ ትዌንቴ ዩኒቨርሲቲ ትብብር የተገነባ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ስቱዲዮው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የዲጂታል ትምህርት፣ ምርምር እና ማኅበረሰብ ጉድኝትን ለማስፋት ያስችላል ተብሏል፡፡
የስቱዲዮው ሥራ መጀመር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ የታገዘ ትምህርት በመስጠት ቀዳሚ ከሆኑ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል አንዱ ለመሆን የሚያደርገውን ጥረት የሚደግፍ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

👍134❤27👎9👏7🥰4🙏2
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከመጋቢት 26/2017 ዓ.ም ጀምሮ የኦሪጅናል ዲግሪ ህትመት ማመልከቻ መቀበል ጀምሯል፡፡
ኦሪጅናል ዲግሪ እንዲሰራላችሁ የምትፈልጉ አመልካቾች ለዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ጥያቂያችሁን ማቅረብ እንደምትችሉ ተገልጿል፡፡

👍37❤5👎1
#BahirDarUniversity
ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ TOEFL ምዘና ፈተና መስጠት ሊጀምር ነው፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዓለም አቀፍ ደረጃ የተረጋገጠ የፈተና አስተዳደር አገልግሎቶች በመሰጠት ከሚታወቀው የትምህርት ፈተና አገልግሎት (ETS) ተቋም የ TOEFL iBT ፈተና ማዕከል ሆኖ ፈቃድ አጊኝቷል፡፡
ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የ TOEFL የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና፤ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመቀላቀል፣ ለሙያ እድገት እንዲሁም ለስኮላርሺፕ ዕድሎች አስፈላጊ መሆኑ ይታወቃል፡፡
በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ TOEFL ፈተና ማዕከል ፔዳ ግቢ፣ ፈተናውን ለመውሰድ የአመልካቾች የኦንላይን ምዝገባ በቅርቡ እንደሚጀምር ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
☎️ +251911816361
📧 [email protected]
@tikvahuniveristy

👍217❤25🥰8👎7👏2😱1
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ TOEFL iBT ምዘና ፈተና ለመስጠት የአመልካቾች ምዝገባ ጀምሯል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዓለም አቀፍ ደረጃ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የ TOEFL የእንግሊዘኛ ቋንቋ ምዘና የፈተና ማዕከል ሆኖ በቅርቡ ፈቃድ ማግኘቱ ይታወቃል፡፡
ከሚያዝያ 26/2017 ዓ.ም እስከ መስከረም 21/2018 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ፈተናዎቹ የሚሰጡ መሆኑንን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በመሆኑም አመልካቾች በኦንላይን ምዝገባ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል፡፡
አካውንት ለመክፈት ይህን ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=618B1SLoad0
ለመመዝገብ ይህን ቲቶሪያል ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=tHgeWQMyQS4
ክፍያን በተመለከተና ለተጨማሪ መረጃ 👇
https://www.ets.org/pdfs/toefl/toefl-ibt-bulletin.pdf

👍118👏14❤13👎9🙏3🥰1
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት የሚሰጠው ምንም ምንም ዓይነት ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሌለ ገልጿል፡፡
"ነጻ የትምህርት ዕድል እንሰጣለን በማለት በሐሰተኛ መረጃ ገንዘብ የሚሰበስቡ እንዳሉ ለማወቅ ችለናል" ያለው ዩኒቨርሲቲው፤ ከሐሰተኛ መረጃ እንድትጠነቀቁና በተሳሳተ መረጃ ገንዘባችሁን እንዳታባክኑ በጥብቅ አሳስቧል፡፡

👍112❤18😢1
#BahirDarUniversity
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ መርሐግብሮች ያሰለጠናቸውን 333 ተማሪዎች አስመርቋል።
ተመራቂዎቹ 64 በሁለተኛ ዲግሪ፣ 89 በስፔሻሊቲ፣ 2 በሰብ ስፔሻሊቲ እና 178 በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ መሆናቸው ተገልጿል።

👍49❤12😱1😢1
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመደበኛው መርሐግብር ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተማሪዎች 96.11% ተፈታኞች የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አሳውቋል።
በሁሉም መርሐግብሮች ማለትም በመደበኛ፣ በተከታታይ፣ በክረምት እና በርቀት መርሐግብሮች ለመጀመሪያ ጊዜ ከተፈተኑት ውስጥ 94.4% ተፈታኞች ማለፋቸው ተገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጠባቸው 46 ትምህርት ክፍሎች 100% ተማሪዎችን ማሳለፍ መቻሉን ነው የገለፀው፡፡
የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ካስፈተናቸው ተማሪዎች ውስጥ ከሦስት ተማሪዎች በስተቀር ሁሉም ተማሪዎች ማለፋቸውም ተገልጿል።

👍230❤155👏14👎11🙏5😢2
#BahirDarUniversity
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ Cyber Security እንዲሁም በ Data Science ትምህርት ክፍሎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ተማሪዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ነገ ያስመርቃል።
በሁለቱም የትምህርት መስኮች ተማሪዎች ሲመረቁ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ነው የተገለፀው።
በሁለቱም የትምህርት ክፍሎች የመውጫ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች በሙሉ ማለፋቸውን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

❤280👏66👎8🥰8👍5🙏4
#BahirDarUniversity
#CollegeOfMedicine
#2025Commencement
የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የጤና መስኮች ያስተማራቸውን 166 ተማሪዎች አስመርቋል።
የዩኒቨርሲቲው ኮሌጅ ዛሬ ያስመረቃቸው፦
🎓 93 የሕክምና ዶክተሮች
🎓 አንድ በሦስተኛ ዲግሪ
🎓 37 በሁለተኛ ዲግሪ
🎓 ሁለት በስፔሻሊቲ
🎓 ሁለት በጤና ሳይንስ ዲግሪ
🎓 31 የእንሰሳት ህክምና ዶክተሮች
ከሕክምና ምሩቃን መካከል አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.95 በማምጣት ዶ/ር ቤተልሔም እውነቱ የማዕረግ ተመራቂ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች።
ዶ/ር ቤቴልሄም በኮሌጁ የሚሰጠው "የፕሮፌሰር ዕደማሪያም ፀጋ አካዳሚክ ልህቀት በሕክምና ሽልማት" ተሸላሚም ሆናለች።

❤135👍32👏6👎5🙏1