TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ዩናይትዶች በ ሀትሪክ ታጅበው ድል ቀንቷቸዋል !

የ ራፋኤል ቫራንን ዝውወር ይፋ በማድረግ ጨዋታቸውን የጀመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች የ ማርሴሎ ቤይልሳውን ሊድስ 5 ለ 1 በሆነ ውጤት በ መርታት ጅማሯቸውን የ ሰመረ አድርገዋል ።

• ፖርቹጋላዊው ቁልፍ ተጫዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለ ማንችስተር ዩናይትድ የ መጀመሪያ ሀትሪኩን መስራት ችሏል ።

• ፈረንሳዊው የ መሐል ሜዳ ተጫዋች ፖል ፖግባ አራት ለ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ በ ማቀበል ሀትሪክ ሰርቷል ።

• ሜሰን ግሪንውድ ለ ማንችስተር ዩናይትድ ያስቆጠረውን ግብ ወደ #ሰላሳ ከፍ አድርጓል ።

• ፖል ፖግባ ለ ግብ የሚሆን ኳስ አመቻችቶ በ ማቀበል በ ሊጉ ሀትሪክ ሲሰራ የ መጀመሪያው ነው ።

• የ ሊድስ ዩናይትድን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ሉክ ኤይሊንግ የ መጀመሪያ የ ፕርሚየር ሊግ ጎሉ ሆኗል ።

• ፖል ፖግባ ባለፉት ሁለት የ ውድድር ዓመት ካስመዘገበው ለ ግብ የሚሆኑ ኳሶች የበለጠ በ ዘንድሮው የውድድር ዓመት ከወዲሁ ማስመዝገብ ችሏል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ #ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ሀትሪክ መስራት የቻለ #አስረኛው ተጫዋች ሆኗል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ጨዋታ ሀትሪክ መስራት የቻለ የ መጀመሪያው የ #ክለቡ ተጫዋች ለመሆን በቅቷል ።

• አዲሱ የ ክለቡ ፈራሚ ጀዳን ሳንቾ ተቀይሮ በመግባት የ መጀመሪያ ጨዋታውን አድርጓል ።

• ማንችስተር ዩናይትድ በ #ወቅታዊ ውጤት የ ሊጉን የ ደረጃ ሰንጠረዥ ለመምራት ችለዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ጉዟቸውን በ ድል ጀምረዋል !

የ መርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል አዲስ አዳጊውን ኖርዊች ሲቲ በ ፊርሚንሆ ፣ ጆታ እና ሳላህ ግቦች አሸንፈዋል ።

• ዲያጎ ጆታ ለ ሊቨርፑል በ ፕርሚየር ሊጉ ያስቆጠራቸውን የ ግብ መጠን ወደ አስር አድርሷል ።

• ሞሀመድ ሳላህ በ ጨዋታው ሁለት ለ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ሞሀመድ ሳላህ በ አምስት ተከታታይ የ ውድድር ዓመት በ መክፈቻ ጨዋታ በ #ሊጉ ግብ ማስቆጠር የቻለ ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል ።

• ሳለህ በ ክለቡ ታሪክ በ ሊጉ የመጀመሪያ ሳምንት ሰባት ጎሎችን ከ መረብ በማሳረፍ በ ታሪክ በ #ክለቡ ቀዳሚው ተጫዋች ለመሆን ችሏል ።

• ኖርዊች ሲቲ ዘንድሮ ሊጉን ከተቀላቀሉ ሶስት ክለቦች በ ሳምንቱ ድል ያልቀናው ብቸኛው ክለብ ሆኗል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሰባት ቁጥር ማልያን ይለብሳል ?

ክርስቲያኖ ሮናልዶ ወደ ልጅነት ክለቡ መመለሱን ተከትሎ ስንት ቁጥር ማልያን ይለብሳል የሚለው አጓጊ ሆኗል ።

በ ፕርሚየር ሊጉ ህግ አንቀፅ #አምስት መሰረት ኤዲሰን ካቫኒ ሰባት ቁጥር ለብሶ የ ውድድር ዓመቱን እንዲያጠናቅቅ ይደነግጋል ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ #ሊጉ ሰባት ቁጥር ማልያን ለ መልበስ ኤዲሰን ካቫኒ ከ ቡድን መውጣት #ብቸኛው አማራጭ ነው ።

ሮናልዶ ሰባት ቁጥርን የ መልበስ እድል አለው ?

አዎ ! በ አውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታዎች ላይ #ብቻ ሰባት ቁጥርን ለብሶ የመጫወት ዕድል ይኖረዋል ።

ለ አብነት ያክል በ 2017 / 18 የ ውድድር ዓመት ሚኪታሪያን በ ሊጉ #ሰባት ቁጥርን እንዲሁም በ #ዩሮፓ ሊግ ሰባ ሰባት ቁጥርን ለብሶ መጫወቱ የ ቅርብ ጊዜ ትውስታ ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
አሰልጣኝ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር !

የ ቀያይ ሴጣኖቹ አለቃ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር በ ዛሬው ዕለት 100ኛ ጨዋታውን በ #ሊጉ ማድረግ ችሏል ።

ከዚህም ውስጥ ከ ግማሽ በላይ በሚሆኑት ሀምሳ ሶስት ጨዋታዎች ድል ሲቀናው አስራ ዘጠኝ ጨዋታዎች ላይ ሽንፈት አስተናግደዋል ።

አሰልጣኝ ኦሊ ጎነር ሶልሻየር በዛሬው ዕለት ማሸነፋቸውን ተከትሎ #ከሜዳቸው ውጪ ሀያ ስምንት ጨዋታዎችን ባለ #መሸነፍ አዲስ ታሪክ ፅፈዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ክርስቲያኖ ሮናልዶ አዲስ ሪከርድ አስመዝግቧል !

ማንችስተር ዩናይትድን ዳግም የተቀላቀለው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ከ ወዲሁ አዲስ ሪከርድ ማስመዝገቡ ተገልጿል ።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ አስራ ሁለት ሰዓታት ብቻ 406,250 ማልያዎቹ ሲሸጡ ይህም በ #ሊጉ አዲስ ሪከርድ መሆኑ ተገልጿል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ደረጃቸውን ያሻሻሉበት ውጤት አስመዝግበዋል !

የ መርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ወደ ኤላንድ ሮድ አቅንተው ሊድስ ዩናይትድን አሸንፈው መመለስ ችለዋል ።

• ሞሀመድ ሳላህ ፣ ማኔ እና ፋቢንሆ የ ሊቨርፑልን የ ማሸነፊያ ጎሎች ያስቆጠሩ ተጫዋቾች ናቸው ።

• ሳላህ በ #ሊጉ ያስቆጠራቸውን የ ግብ መጠን ወደ 100 ከፍ ማድረግ ችሏል ።

• ሀርቪ ኢሊዮት ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል ።

• ውጤቱን ተከትሎ ሊቨርፑሎች አራት ደረጃዎችን በ ማሻሻል በ አስር ነጥቦች ሶስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ከግብ የራቀው ሊዮኔል ሜሲ !

አርጀንቲናዊው ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ወደ ፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ፒኤስጂ ካቀና በኋላ በ #ሊጉ ግብ ማስቆጠር ተቸግሮ ይታያል ።

ሊዮኔል ሜሲ በ ፈረንሳይ ሊግ ባደረጋቸው አራት ጨዋታዎች ላይ በ አንድም ግብ ላይ ተሳትፎ ማድረግ ሳይችል ቀርቷል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሙጂብ ቃሲም በ አልጄርያ !

የ ዋልያዎቹ የፊት መስመር አጥቂ ሙጂብ ቃሲም በ አዲሱ ክለብ ጄ ኤስ ካቢሌ በ #ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን #ነገ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ።

ሙጂብ ቃሲም ክለቡ በሊጉ የ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከቀኑ 11:00 "OM MEDA" ሲገጥሙ አስራ ስምንት ተጫዋቾች ብቻ በተካተቱበት ቡድን ስብስብ ውስጥ መካተት ችሏል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
ሙጂብ ቃሲም በ አልጄርያ ! የ ዋልያዎቹ የፊት መስመር አጥቂ ሙጂብ ቃሲም በ አዲሱ ክለብ ጄ ኤስ ካቢሌ በ #ሊጉ የመጀመሪያ ጨዋታውን #ነገ እንደሚያደርግ ይጠበቃል ። ሙጂብ ቃሲም ክለቡ በሊጉ የ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ከቀኑ 11:00 "OM MEDA" ሲገጥሙ አስራ ስምንት ተጫዋቾች ብቻ በተካተቱበት ቡድን ስብስብ ውስጥ መካተት ችሏል ። @tikvahethsport @kidusyoftahe
ሙጂብ ቃሲም የመጀመሪያ ጨዋታውን አደረገ !

የ 2013 የ ቤት ኪንግ ኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ አሸናፊ መጂብ ቃሲም ወደ አልጄርያ ካቀና በኋላ የመጀመሪያ የ #ሊጉ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት አድርጓል ።

ሙጂብ ቃሲም ክለቡ ጄኤስ ካቢሌ ያለ ምንም ግብ አቻ በወጣበት መርሐ ግብር ላይ ተቀይሮ በመግባት መጫወት ችሏል ።

ሙጂብ ቃሲም በ አዲሱ ክለብ ቆይታው ዘጠኝ ቁጥር መለያን በመልበስ ይጫወታል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ ቼልሲ የአሸናፊነት ግስጋሴ !

የ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በ ጀርመናዊው አሰልጣኛቸው ቶማስ ቱሄል እየተመሩ ድንቅ የሚባል ግስጋሴን እያደረጉ ይገኛሉ ።

ቼልሲዎች ባለፉት ዘጠኝ በሁሉም የውድድር መድረክ ባደረጓቸው ጨዋታዎች ያልተሸነፉ ሲሆን ሰላሳ ጎሎችን በ #ሊጉ ማስቆጠር ችለዋል ።

ቼልሲዎች በተጋጣሚዎቻቸው ላይ በርካታ ጎሎችን ሲያስቆጥሩ በተቃራኒው የተቆጠረባቸው አራት ግቦች ብቻ ነው ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሲቲዎች በሜዳቸው ድል ቀንቷቸዋል !

ማንችስተር ሲቲዎች በ ሜዳቸው ኢቲሀድ ባደረጉት የ ሊጉ መርሐ ግብር ኤቨርተንን 3 ለ 0 ማሸነፍ ችለዋል ።

• ስተርሊንግ ፣ ሮድሪ እና በርናርዶ ሲልቫ የ ሲቲን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ አሳርፈዋል ።

• በርናርዶ ሲልቫ በ ሀምሳ የ ሊግ ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ።

• ሮድሪ ለ ማንችስተር ሲቲ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን በ ሊጉ ወደ ሰባት አድርሷል ።

• ሲቲዎች ባለፊት ዘጠኝ ከ ኤቨርተን ጋር ባደረጓቸው ጨዋታ ማሸነፍ ችለዋል ።

• በርናርዶ ሲልቫ በ ኢቲሀድ ስታዲየም 100ኛ ጨዋታውን ለ ሲቲ አድርጓል ።

• ራሂም ስተርሊንግ በ #ሊጉ ብቻ ያስቆጠራቸውን የ ግብ መጠን ወደ ዘጠና ስምንት ከፍ አድርጓል ።

• ጇ ካንሴሎ በውድድር ዓመቱ በ ሁሉም የውድድር መድረኮች ስድስት ለ ግብ የሚሆኑ ኳሶችን አመቻችቶ ማቀበል ችሏል ።

• ራሂም ስተርሊንግ 300ተኛ የ እንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታውን በዛሬው ዕለት አድርጓል ።

• ውጤቱን ተከትሎ ሲቲዎች ሁለተኛ ደረጃን ከ ሊቨርፑል ሲረከቡ ከመሪው ቼልሲ በ ሶስት ነጥቦች ብቻ ርቀው ይገኛሉ ።
የመጀመሪያ አጋማሽ አጫጭር መረጃዎች !

ማንችስተር ዩናይትድ 1 - 1 አርሴናል

ብሩኖ ፈርናንዴዝ ስሚዝ ሮው

• ኤምሊ ስሚዝ ሮው በሊጉ ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ አምስት ከፍ አድርጓል ።

• መድፈኞቹ በ #ሊጉ ያስቆጠሩት ያለፉት ሰባት ጎሎች የተቆጠሩት እድሜያቸው ከ ሀያ ሶስት ዓመት በታች በሆኑ ተጫዋቾች ነው ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ በ ሁሉም የውድድር መድረክ ያስቆጠረውን የግብ መጠን ወደ አምስት አሳድጓል ።

• ስሚዝ ሮው በሁሉም የውድድር መድረኮች ባደረጋቸው ያለፉት አስር ጨዋታዎች ላይ በሰባት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል ።

• ብሩኖ ፈርናንዴዝ ለቀያይ ሴጣኖቹ 100ኛ ጨዋታውን በማድረግ ላይ ይገኛል ።

• ቀያይ ሴጣኖቹ በሜዳቸው በ #ሊጉ አስራ ሁለት ጎሎች ተቆጥረውባቸዋል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ከ ግብ የራቀው ሊዮኔል ሜሲ !

አርጀንቲናዊው የ ፒኤስጂ ኮከብ ሊዮኔል ሜሲ ወደ ፈረንሳዩ ሀያል ክለብ ካቀና በኋላ በ #ሊጉ ላይ ግቦችን ማስቆጠር ሳይችል ቀርቷል ።

የሰባት ጊዜ የባሎን ዶር አሸናፊው ሜሲ በ #ሊጉ ተሰልፎ በተጫወተባቸው 865 ደቂቃዎች አንድ ግብ ብቻ ሲያስቆጥር ስድስት ለግብ የቀረቡ ሙከራዎቹ በ ግቡ አግዳሚ ሲመለሱበት ታይቷል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe