TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ሮማ እና ኤስ ሚላን አቻ ተለያይተዋል !

በጣልያን ሴርያ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሮማ ከ ኤስ ሚላን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

የሮማን ግብ ታሚ አብረሀም ሲያስቆጥር ለኤስ ሚላን የአቻነቷን ግብ ሴሌሜከርስ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኤስ ሚላን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀምሳ ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

ሮማ በተመሳሳይ ሀምሳ ሰባት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኤስ ሚላን ከ ክሪሞኒስ እንዲሁም ሮማ ሞንዛ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ድል አድርጓል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ቶተንሀም ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4ለ3 በሆነ ውጤት አሸንፏል።

የሊቨርፑልን ግቦች መሐመድ ሳላህ ፣ ጆንስ ፣ ሉዊስ ዲያዝ እና ዲያጎ ጆታ ሲያስቆጥሩ ለቶተንሀም ሀሪ ኬን ፣ ሰን ሁንግ ሚን እና ሪቻርልሰን ከመረብ አሳርፈዋል።

ሀሪ ኬን በውድድር አመቱ ሀያ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሞሀመድ ሳላህ በውድድር አመቱ አስራ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሊቨርፑል በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀምሳ ስድስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቶተንሀም በሀምሳ አራት ነጥብ #ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ፉልሀም እንዲሁም ቶተንሀም ከ ክሪስታል ፓላስ የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ አዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናን ሁለት ግቦች መሐመድ ኑር ናስር ሲያስቆጥር ለአዳማ ከተማ አድናን ረሻድ እና ደስታ ዮሀንስ ከመረብ አሳርፈዋል።

- የኢትዮጵያ ቡናው የፊት መስመር ተጨዋች መሐመድ ኑር ናስር በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል

- ኢትዮጵያ ቡና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ አዳማ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ አንድ ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ቡና ከ ባህርዳር ከተማ እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ ወላይታ ድቻ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረክቧል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የሀያ ስምንተኛ ሳምንት ተስተካካይ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ዌስትሀምን 3ለ0 እንዲሁም ሊቨርፑል ፉልሀምን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

- የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ ፣ ናታን አኬ እና ፊል ፎደን ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

- የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግብ ሞሐመድ ሳላህ በፍፁም ቅጣት ምት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ሞሀመድ ሳላህ በውድድር አመቱ አስራ ስምንተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ አምስት ግቦችን በማስቆጠር የአንድ የውድድር አመት የሊጉ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪ መሆን ችሏል።

- ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰባ ዘጠኝ በማድረስ የሊጉን መሪነት ከአርሰናል መረከብ ሲችል ሊቨርፑል በሀምሳ ዘጠኝ ነጥብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ሊድስ ዩናይትድ እንዲሁም ሊቨርፑል ከ ብሬንትፎርድ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ በብሬንትፎርድ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የሊቨርፑልን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ሞሀመድ ሳላህ አስቆጥሯል።

- የሊቨርፑሉ የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ ሳላህ በውድድር አመቱ አስራ ዘጠነኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ #አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ሲችል ብሬንትፎርድ በሀምሳ ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዘዋል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ ሌስተር ሲቲ እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከዌስትሀም የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀዋሳ ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 0 ለ 0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

ሀይቆቹ በተከታታይ ያደረጓቸውን #አራት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም በሶስቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

ሀዋሳ ከተማ እና ሀድያ ሆሳዕና በዚህ አመት በተመሳሳይ ስምንት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተው ስምንት አሸንፈው ሰባት ጨዋታዎች ተሸንፈዋል።

በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሀድያ ሆሳዕና በሰላሳ ሁለት ነጥቦች #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በተመሳሳይ ሰላሳ ሁለት ነጥብ በግብ ክፍያ ተበልጦ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ድል አድርጓል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከሌስተር ሲቲ ጋር ያደረገውን የሰላሳ ስድስተኛ ሳምንት የሊግ መርሐ ግብር 3ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የሊቨርፑልን የማሸነፊያ ግቦች ጆንስ 2x ፣ እና አሌክሳንደር አርኖልድ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

ሊቨርፑል ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቡን ስልሳ አምስት በማድረስ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሌስተር ሲቲ በሰላሳ ነጥብ አስራ ዘጠነኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ሊቨርፑል ከ አስቶን ቪላ እንዲሁም ሌስተር ሲቲ ከኒውካስል ዩናይትድ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሀድያ ሆሳዕና ድል አድርጓል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሀድያ ሆሳዕና ከ ባህር ዳር ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈዋል።

የሀድያ ሆሳዕናን ግቦች ሰመረ ሀፍታይ እና ተመስገን ብርሀኑ ሲያስቆጥሩ ለባህር ዳር ከተማ ቻርለስ ሪቫኖ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ባህርዳር ከተማ ሽንፈት ማስተናደገዱን ተከትሎ የሊጉን መሪነት ከቅዱስ ጊዮርጊስ መረከብ የሚችልበትን ዕድል ሳይጠቀም ቀርቷል።

ሀድያ ሆሳዕና በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ነጥቦቹን ሰላሳ ስድስት በማድረስ #አምስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ባህር ዳር ከተማ በሀምሳ ነጥብ #ሀለተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህር ዳር ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ እንዲሁም ሀድያ ሆሳዕና ከ ኢትዮጵያ ቡና ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቪንሰስ ጁኒየር የወሩ ምርጥ ተጨዋች ተብሏል !

በአሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ የሚሰለጥኑት ሪያል ማድሪዶች የወርሀ ግንቦት የወሩ ምርጥ ተጨዋቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

በዚህም መሰረት ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር የሪያል ማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች በመባል በአብላጫ ድምፅ መመረጥ ችሏል።

ብራዚላዊው የፊት መስመር ተጨዋች ቪንሰስ ጁኒየር ለተከታታይ #አራት ወራት እንዲሁም በውድድር አመቱ ለ #አምስተኛ ጊዜ የሪያል ማድሪድ የወሩ ምርጥ ተጨዋች ክብርን መቀዳጀት ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢንተር ሚያሚ ለውጦችን ማሳየት ችሏል !

አርጀንቲናዊውን የአለም ሻምፒዮን ተጨዋች ሊዮኔል ሜሲ ወደ ቡድኑ የቀላቀለው የአሜሪካው ክለብ ኢንተር ሚያሚ መጠነ ሰፊ ለውጦችን ማስመዝገቡን ቀጥሏል።

የሊዮኔል ሜሲው ክለብ ኢንተር ሚያሚ አሁን ላይ በአሜሪካ በርካታ የኢንስታግራም የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተከታዮች ካሏቸው የስፖርት ክለቦች #አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በርካታ ተከታዮችን በማፍራት ከአንድ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ የአሜሪካ ቅርጫት ኳስ ክለቦች ሲይዙ ኢንተር ሚያሚ በ #ስምንት ሚልዮን ተከታዮች አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ድል አድርጓል !

በአራተኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ የ 2023/24 የውድድር አመት ሪያል ማድሪድ ከጌታፌ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

-የሪያል ማድሪድን የማሸነፊያ ግቦች ጁድ ቤሊንግሀም እና ሆሴሉ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ የጌታፌን ግብ ማዮራል አስቆጥሯል።

- እንግሊዛዊው ተጨዋች ጁድ ቤሊንግሀም በሪያል ማድሪድ ማልያ ባደረጋቸው የመጀመሪያ አራት ጨዋታዎች #አምስተኛ የላሊጋ ግቡን ከመረብ አሳርፏል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

1️⃣ኛ :- ሪያል ማድሪድ ( 1️⃣2️⃣ ነጥብ )

1️⃣3️⃣ኛ :- ጌታፌ ( 4️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ሪያል ማድሪድ ከ ሪያል ሶሴዳድ

ዕሁድ - ጌታፌ ከ ኦሳሱና

( ቀጣይ ጨዋታዎች ከብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ መልስ ከሳምንት በኋላ ይደረጋሉ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#PremiereLeague 🇬🇧

በስምንተኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ2023/24 የውድድር አመት ሊቨርፑል ከብራይተን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

- የሊቨርፑልን ግቦች ሞሀመድ ሳላህ ( 2x ) ከመረብ ማሳረፍ ሲችል ለብራይተን አዲንግራ እና ደንክ አስቆጥረዋል።

- በሌላ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ከዌስትሀም ዩናይትድ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የኒውካስል ዩናይትድን ግቦች አሌክሳንደር አይሳክ ሲያስቆጥር ለዌስትሀም መሐመድ ኩዱስ እና ሱሴክ ከመረብ አሳርፈዋል።

- የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጨዋች ሞሀመድ በውድድር አመቱ #አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ሞሀመድ ሳላህ ከብራይተን እና ማንችስተር ዩናይትድ ጋር ባደረጋቸው ጨዋታዎች አስራ አራት ግቦች ላይ የግብ አስተዋጽኦ በማድረግ በሊጉ ቆይታው ከፍተኛው ነው።

- ሞሀመድ ሳላህ በስምንት ግቦች ብራይተን ላይ ብዙ ግብ ያስቆጠረ የሊቨርፑል ተጨዋች መሆን ችሏል።

በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ስንተኛ ናቸው ?

3️⃣ኛ :- ሊቨርፑል ( 1️⃣7️⃣ ነጥብ )

6️⃣ኛ :- ብራይተን ( 1️⃣6️⃣ ነጥብ )

7️⃣ኛ :- ዌስትሀም ዩናይትድ ( 1️⃣4️⃣ ነጥብ )

8️⃣ኛ :- ኒውካስል ዩናይትድ ( 1️⃣3️⃣ ነጥብ )

ቀጣይ ጨዋታ ምን ይመስላል ?

ቅዳሜ - ሊቨርፑል ከ ኤቨርተን

ቅዳሜ - ማንችስተር ሲቲ ከ ብራይተን

እሁድ - አስቶን ቪላ ከ ዌስትሀም

ቅዳሜ - ኒውካስል ዩናይትድ ከ ክሪስታል ፓላስ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የዩናይትድ የሊጉ ጉዞ ?

በአሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ የሚመሩት ማንችስተር ዩናይትዶች አስረኛ ሳምንት ላይ በደረሰው የሊጉ መርሐ ግብር #አምስተኛ ሽንፈታቸውን በሜዳቸው ለማስተናገድ ተገደዋል።

ማንችስተር ዩናይትዶች በሜዳቸው ካደረጓቸው ስድስት የሊጉ ጨዋታዎች በሶስት መርሐ ግብሮች ላይ ተሸንፈዋል።

ቡድኑ በእነዚህ ጨዋታዎች ላይ ሰባት ጎሎችን በተጋጣሚዎቹ ላይ ሲያስቆጥር በተቃራኒው አስር ጎሎችን አስተናግደዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የእንግሊዝ ሴቶች ሱፐር ሊግ ዛሬ ይጠናቀቃል !

አሸናፊውን ክለብ እስከመጨረሻው ሳምንት መርሐ ግብር ያላሳወቀው የእንግሊዝ የሴቶች ሱፐር ሊግ ውድድር ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜውን ያገኛል።

ሊጉን የቼልሲ ሴቶች ቡድን እና የማንችስተር ሲቲ ሴቶች ቡድን በተመሳሳይ ሀምሳ ሁለት ነጥብ በሁለት የግብ ክፍያ ተበላልጠው አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን እየመሩት ይገኛሉ።

ሁለቱ ክለቦች አስካሁን ካደረጓቸው ሀያ አንድ ጨዋታዎች በተመሳሳይ አስራ ሰባት አሸንፈው ሶስት ተሸንፈው አንድ አቻ ተለያይተዋል።

ሊጉ ዛሬ አሸናፊውን ሲለይ መሪው ቼልሲ ከማንችስተር ዩናይትድ እንዲሁም ማንችስተር ሲቲ ከ አስቶን ቪላ ተጠባቂ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጪ አመሻሽ 11:00 ያደርጋሉ።

የቼልሲ ሴቶች ቡድን ዛሬ የእንግሊዝ ሱፐር ካፕ ዋንጫን የሚያሸንፍ ከሆነ ለ #አምስተኛ ተከታታይ አመታት የሊጉ ሻምፒዮን በመሆን ወርቃማ ታሪክ ይፅፋል።

ሊጉን ማን ያሸንፋል

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የእንግሊዝ ሴቶች ሱፐር ሊግ ዛሬ ይጠናቀቃል ! አሸናፊውን ክለብ እስከመጨረሻው ሳምንት መርሐ ግብር ያላሳወቀው የእንግሊዝ የሴቶች ሱፐር ሊግ ውድድር ዛሬ በተመሳሳይ ሰዓት በሚደረጉ ጨዋታዎች ፍፃሜውን ያገኛል። ሊጉን የቼልሲ ሴቶች ቡድን እና የማንችስተር ሲቲ ሴቶች ቡድን በተመሳሳይ ሀምሳ ሁለት ነጥብ በሁለት የግብ ክፍያ ተበላልጠው አንደኛ እና ሁለተኛ በመሆን እየመሩት ይገኛሉ። ሁለቱ ክለቦች አስካሁን…
ቼልሲ የሴቶች ሱፐር ሊግ ሻምፒዮን ሆነ !

የቼልሲ ሴቶች ቡድን ከማንችስተር ዩናይትድ ሴቶች ቡድን ጋር ያደረገውን የእንግሊዝ የሴቶች ሱፐር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት መርሐግብር 6ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ይህንንም ተከትሎ የቼልሲ ሴቶች ቡድን ሀምሳ አምስት ነጥቦችን ሰብስቦ በማጠናቀቅ የዘንድሮው የእንግሊዝ ሱፐር ሊግ ውድድር ሻምፒዮን መሆኑን አረጋግጧል።

የቼልሲ ሴቶች ቡድን የእንግሊዝ ሱፐር ካፕ ዋንጫን ለ #አምስተኛ ተከታታይ አመታት በማሸነፍ ወርቃማ ታሪክ መፃፍ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲ ሴቶች ቡድን በተመሳሳይ ሀምሳ አምስት ነጥቦችን ይዞ ቢያጠናቅቅም በቼልሲ በግብ ክፍያ ተብልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።

ቼልሲ ፣ ማንችስተር ሲቲ እና አርሰናል በሚቀጥለው የውድድር አመት በሴቶች የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር የሚሳተፉ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#TeamEthiopia 🇪🇹

በ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 5,000ሜ ሴቶች ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ዙር የተሳተፉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋይ እና እጅጋየሁ ታዬ ለፍፃሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።

አትሌት ጉዳፍ ፀጋይ በማጣሪያ ውድድሩ 14:57.84 በሆነ ሰዓት #አምስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

እጅጋየሁ ታዬ በበኩሏ 14:57.97 በሆነ ሰዓት #ስድስተኛ ደረጃን በመያዝ ማጠናቀቅ ችላለች።

የመጀመሪያውን ዙር የማጣሪያ ውድድር ኬኒያዊቷ ኪፕዬጎን አንደኛ ኔዘርላንዳዊቷ ሲፋን ሀሰን ሁለተኛ በመሆን አጠናቀዋል።

በቀጣይ በመጨረሻው ዙር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት መዲና ኢሳ የማጣሪያ ውድድሯን የምታደርግ ይሆናል።

የ 5,000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ሰኞ ሐምሌ 29/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 ሰዓት ይካሄዳል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Paris2024            #TeamEthiopia 🇪🇹

በ 2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣሪያ ውድድር በመጀመሪያው ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሎሚ ሙለታ ለፍፃሜ ማለፏን አረጋግጣለች።

አትሌት ሎሚ ሙለታ በማጣሪያ ውድድሩ 9:10.73 በሆነ ሰዓት በመግባት የግሏን ምርጥ ሰዓት በማስመዝገብ #አምስተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቃለች።

ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ሲምቦ አለማየሁ በሚቀጥለው ምድብ የማጣሪያ ውድድሯን በማድረግ ላይ ትገኛለች።

የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜ ውድድር ማክሰኞ ሀምሌ 30/2016 ዓ.ም ምሽት 4:10 የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የ 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ፍፃሜውን ሲያገኝ ባህሬን በያቪ አማካኝነት የወርቅ ሜዳሊያውን ማሸነፍ ችላለች።

🥇ያቪ ( ባህሬን )
🥈ቼሙታይ ( ዩጋንዳ )
🥉ቼሮቲች ( ኬንያ )

ኢትዮጵያ ሲምቦ አለማየሁ #አምስተኛ እንዲሁም ሎሚ ሙለታ #ስምንተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

ኢትዮጵያ በርቀቱ ሜዳሊያ ያገኘችው እ.ኤ.አ በ 2012 ነበር።