ምድብ ስድስት ጀምሯል
በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ስድስተኛው ምድብ ኢትዮጵያ በአትሌት ሀብታም አለሙ ተወክላለች።
መልካም እድል 🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe

ሀብታም አለሙ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜ ደርሳለች
በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሀብታም አለሙ አንደኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ሀብታም አለሙ አንደኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሁለት አትሌቶቻችን ግማሽ ፍፃሜ ደረሰዋል !
በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ወርቅነሽ መለሰ እና ሀብታም አለሙ #ሶስተኛ እና #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።
በርቀቱ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ትዕግስት ግርማ ውድድሯን ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች።
የሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን አርብ ምሽት 3:25 ላይ የሚደረግ ይሆናል።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Budapest 🇪🇹
የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሻምፒዮናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በአለም ሻምፒዮናው የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቱን ተከትሎ ከውድድሩ በኋላ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እና በእምባ ታጅቦ ታይቷል።
በተለይም ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የቡድኑ አመራሮች አትሌቶቹን ሲያፅናኑ ታይተዋል። ሰለሞን ባረጋ ሀሳቡ ለሀገሩ ወርቅ ማምጣት እንደነበረ በዕለቱ መናገሩ የሚታወስ ነው።
📽 ሀይሌእግዚአብሔር አድሀኖም
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የቶኪዮ ኦሎምፒክ ሻምፒዮናው አትሌት ሰለሞን ባረጋ በአለም ሻምፒዮናው የነሐስ ሜዳሊያ ማግኘቱን ተከትሎ ከውድድሩ በኋላ በከፍተኛ ሀዘን ውስጥ እና በእምባ ታጅቦ ታይቷል።
በተለይም ከውድድሩ መጠናቀቅ በኋላ የቡድኑ አመራሮች አትሌቶቹን ሲያፅናኑ ታይተዋል። ሰለሞን ባረጋ ሀሳቡ ለሀገሩ ወርቅ ማምጣት እንደነበረ በዕለቱ መናገሩ የሚታወስ ነው።
📽 ሀይሌእግዚአብሔር አድሀኖም
@tikvahethsport @kidusyoftahe
TIKVAH-SPORT
የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ይቅርታ ጠየቁ ! ስፔን የሴቶች ዓለም ዋንጫን ካሳካችበት የፍፃሜ ጨዋታ በኋላ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ጄኒፈር ሄርሞሶ የተባለችውን የቡድኑ ተጨዋች መሳወማቸውን ተከትሎ ቅሬታዎች ቀርበውባቸዋል። አሁን ላይ የሀገሪቱ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ሉዊስ ሩቢያሌስ በዕለቱ ስለተፈጠረው ነገር በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል። ፕሬዝዳንቱ በይቅርታ መልዕክታቸው…
" ፕሬዝዳንቱ ስራውን መልቀቅ አለበት "
የላሊጋው ክለብ ጌታፌ ባለቤት እና ፕሬዝዳንት አንሄል ቶሬስ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ ምክንያት ስራቸውን መልቀቅ አለባቸው ብለዋል።
" የተመለከትነው ነገር እጅጉን የሚያሳዝን ነው " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " ሉዊስ ሩቢያሌስ ስራውን መልቀቅ አለበት ፣ በፕሬዝዳንትነት ለአንድ ደቂቃም ቢሆን መቆየት የለበትም።"ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የላሊጋው ክለብ ጌታፌ ባለቤት እና ፕሬዝዳንት አንሄል ቶሬስ የስፔን እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ ምክንያት ስራቸውን መልቀቅ አለባቸው ብለዋል።
" የተመለከትነው ነገር እጅጉን የሚያሳዝን ነው " ያሉት ፕሬዝዳንቱ " ሉዊስ ሩቢያሌስ ስራውን መልቀቅ አለበት ፣ በፕሬዝዳንትነት ለአንድ ደቂቃም ቢሆን መቆየት የለበትም።"ብለዋል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ5000ሜ ወንዶች የተወዳዳሪ አትሌት ለውጥ ተደርጓል !
የወንዶች 5000ሜ ማጣሪያ አስቀድሞ ኢትዮጵያን እንደሚወክሉ በቋሚነት ተይዘው ከነበሩ አትሌቶች መካከል አትሌት ጥላሁን ሀይሌ #መቀነሱ ታውቋል።
በምትኩም በ10,000ሜ አራተኛ ደረጃን ይዞ ያጠናቀቀው እና የርቀቱ የአመቱ ፈጣን ሰዓት ባለቤት አትሌት በሪሁ አረጋዊ ከሀጎስ ገብረህይወት እና ዮሚፍ ቀጀልቻ ጋር በውድድሩ እንደሚሳተፉ የአለም አትሌቲክስ ይፋ አድርጓል።
ከውሳኔው በኋላ አትሌት ጥላሁን ሀይሌ በከፍተኛ #የሀዘን ስሜት ውስጥ ሆኖ ቅሬታውን ለባህልና ስፖርት ሚንስቴር የስፖርት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ሲገልጽ የተመለከትን ሲሆን ፣ ፌዴሬሽኑ በጉዳዩ ዙሪያ ዛሬ ከሰዓት በኋላ በሚሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ማብራሪያ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።
አትሌት ጥላሁን ሀይሌ የ 5000ሜ ውድድር ለማድረግ ውድድሩ ወደ ሚደረግበት ቡዳፔሽት ከተማ #በትላንትናው ዕለት የመጣ ሲሆን ውሳኔው #ከደቂቃዎች በፊት ሊያውቅ ችሏል።
የ 5000ሜ ወንዶች ማጣርያ ውድድር በነገው ዕለት ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ይካሄዳል።
👉 በልዩ ስፖርት ጋዜጠኛ ሀይለእግዚአብሔር አድሀኖም

ፕርሚየር ሊግ ቀዳሚውን ስፍራ ይዟል !
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ በዘንድሮው የክረምት የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ከየትኛውም ታላላቅ ሊግ በበለጠ ከፍተኛ የዝውውር ገንዘብ ወጪ ማድረጉ ተገልጿል።
የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ክለቦች በዚህ ክረምት የዝውውር መስኮት #ሁለት ቢልዮን ፓውንድ የዝውውር ሒሳብ በማውጣት ቀዳሚ መሆናቸው ተነግሯል።

ሲቲ ተጨዋች ማስፈረም ይፈልጋል !
በአሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የሚመሩት ማንችስተር ሲቲ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ በፊት የዎልቭሱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማቲውስ ኑኔስን የማስፈረም ፍላጎት እንዳላቸው ተገልጿል።
ሲቲ የዌስትሀሙን ተጨዋች ሉካስ ፓኩዊታ ለማስፈረም ያደረጉት ጥረት በኤፍኤ ምርመራ ምክንያት አለመሳካቱን ተከትሎ የመሐል ሜዳውን ለማጠናከር ፊታቸውን ወደ ማቲውስ ኑኔስ ማዞራቸው ተዘግቧል።

ካሪም ቤንዜማ ልምምድ አልሰራም !
በቅርቡ የሳውዲ አረቢያውን ክለብ አል ኢትሀድ የተቀላቀለው ፈረንሳዊ የፊት መስመር ተጨዋች ካሪም ቤንዜማ ከቡድኑ አሰልጣኝ ኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ጋር ያለው ግንኙነት መሻከሩ ተገልጿል።
ይህንንም ተከትሎ የወቅቱ የባሎን ዶር አሸናፊ ካሪም ቤንዜማ በዛሬው የቡድኑ መደበኛ ልምምድ ላይ እንዳልተሳተፈ ተዘግቧል።
አሰልጣኙ በካሪም ቤንዜማ አጨዋወት ደስተኛ አለመሆናቸው እና የቡድኑን አምበልነት ሚና ሀላፊነት ሊሰጡት ፍቃደኛ እንዳልሆኑ ተነግሯል።

" ኦስሜንን ለማስፈረም አስበን አናውቅም "
የሪያል ማድሪዱ ዋና አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ናይጄሪያዊው አጥቂ ቪክቶር ኦሲሜን ጥሩ ተጨዋች ቢሆንም ስእሱ አስበው እንደማያውቁ ተናግረዋል።
" ቪክቶር ኦሲሜን አለም ላይ ካሉ ምርጥ አጥቂዎች አንዱ ነው " ያሉት አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ " ይሁን እንጂ አኛ እሱን ስለማስፈረም አስበን አናውቅም ፣ ቤሊንግሀምን የገዛነው የቤንዜማን መልቀቅ ለማካካስ ነው።"ብለዋል።

ዩናይትድ የወዳጅነት ጨዋታ ተሸንፏል !
ማንችስተር ዩናይትድ በዛሬው ዕለት ከበርንሌይ ጋር የወዳጅነት ጨዋታውን በዝግ ስታዲየም አድርጎ 3ለ0 በሆነ ውጤት ሽንፈት ማስተናገዱ ተገልጿል።
ቀያዮቹ ሴጣኖች ጆኒ ኢቫንስ ፣ ሀኒባል ፣ አንቶኒ ማርሻል ፣ ቫንዴቢክ ፣ ፔሊስትሪ እና ማክ ቶሚናይን በቋሚ አሰላለፍ ውስጥ አካተው እንደነበር ተነግሯል።

የመጀመሪያው ምድብ የ 5000ሜ ሴቶች ማጣሪያ ጀምሯል
የሴቶች 5000ሜ ማጣሪያ ውድድር የመጀመሪያው ምድብ አሁን ላይ የጀመረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በአትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና መዲና ኢሳ ተወክላለች።
ውድድሩን ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በቀጥታ ፍፃሜውን መቀላቀል ይችላሉ።
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የሴቶች 5000ሜ ማጣሪያ ውድድር የመጀመሪያው ምድብ አሁን ላይ የጀመረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በአትሌት ጉዳፍ ፀጋዬ እና መዲና ኢሳ ተወክላለች።
ውድድሩን ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በቀጥታ ፍፃሜውን መቀላቀል ይችላሉ።
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የ5000 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ
ኢትዮጵያዊያኑ ከመሪዎች ተርታ ይገኛሉ
አራት ዙሮች ይቀራሉ
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ኢትዮጵያዊያኑ ከመሪዎች ተርታ ይገኛሉ
አራት ዙሮች ይቀራሉ
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ጉዳፍ ፀጋዬ እና መዲና ኢሳ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ !
በሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና መዲና ኢሳ #ሁለተኛ እና #ስድስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።
ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለተኛው ምድብ የሚወዳደሩ ይሆናል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
በሴቶች 5000 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ጉዳፍ ፀጋዬ እና መዲና ኢሳ #ሁለተኛ እና #ስድስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ለፍፃሜ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።
ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሁለተኛው ምድብ የሚወዳደሩ ይሆናል።
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሁለተኛው ምድብ የ 5000ሜ ሴቶች ማጣሪያ ጀምሯል
የሴቶች 5000ሜ ማጣሪያ ውድድር ሁለተኛው ምድብ አሁን ላይ የጀመረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በአትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ተወክላለች።
ውድድሩን ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በቀጥታ ፍፃሜውን መቀላቀል ይችላሉ።
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe
የሴቶች 5000ሜ ማጣሪያ ውድድር ሁለተኛው ምድብ አሁን ላይ የጀመረ ሲሆን ሀገራችን ኢትዮጵያ በአትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ ተወክላለች።
ውድድሩን ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው የሚያጠናቅቁ አትሌቶች በቀጥታ ፍፃሜውን መቀላቀል ይችላሉ።
መልካም እድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹🇪🇹
@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሶስት ዙሮች ይቀራሉ
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶችን ጨምሮ ስድስት አትሌቶች ተነጥለው ወጥተዋል