TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
ሁለት ዙሮች ይቀራሉ

ለሜቻ ግርማ መምራት ጀምሯል

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የመጨረሻ ዙር

ለሜቻ ግርማ እየመራ ነው

መልካም ዕድል ለአትሌቶቻችን 🇪🇹🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ለሜቻ ግርማ የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል

ሞሮኳዊው አትሌት በበላይነት አጠናቀቀ

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Budapest 🇪🇹 እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

በ2023ቱ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት ለሜቻ ግርማ ለሀገራችን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችሏል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ታሪክ በአትሌት ለሜቻ ግርማ አማካኝነት 101ኛ ሜዳልያዋን ማስመዝገብ ችላለች።

ውድድሩን ሞሯኳዊው አትሌት ኤል ባካሊ በአንደኝነት ሲያጠናቅቅ ኬንያዊው ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ሁለት የብር ሜዳልያዎች ማስመዝገቧን ተከትሎ በውድድሩ ያላትን የሜዳልያ ቁጥር ወደ ስድስት ከፍ ማድረግ ችላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Photo 🇪🇹

ከደቂቃዎች በፊት ከተጠናቀቀው የ 1500ሜ ሴቶች እና 3000ሜ መሰናክል ወንዶች ፍፃሜ ሀገራችን በሁለቱም ርቀቶች የብር ሜዳሊያ ስታገኝ የተወሰዱ ምስሎች ይመልከቱ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ውጤቱ ከጠበቅኩት በላይ ነው " ድርቤ ወልተጂ

በ 1500ሜ ሴቶች ውድድር ሁለተኛ በመውጣት ለኢትዮጵያ በውድድሩ ታሪክ 100ኛ ሜዳልያ ማስመዝገብ የቻለችው አትሌት ድርቤ ወልተጂ በዚህ ደረጃ መወዳደር ለእሷ ትልቅ ክብር መሆኑን ገልፃለች።

" ውድድሩ በጣም አሪፍ ነበር ፈጣሪ የሰራሁትን ስለሰጠኝ አመሰግነዋለሁ ፣ በአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፍፃሜ ከታላላቅ አትሌቶች ጋር መፎካከር የተለየ ነው።

ወደ ቡዳፔሽት የመጣሁት በደንብ ተዘጋጅቼ ነው ያስመዘገብኩት ውጤት ከጠበቅኩት በላይ እና ወሳኝ ነው።"ስትል የብር ሜዳልያ አሸናፊዋ ድርቤ ትናገራለች።

ከሀያ አመት በታች የአለም ሻምፒዮና ውድድር ላይ ያስመዘገበችው ጥሩ ውጤት ወደፊት ከምርጥ አትሌቶች አንዷ የመሆን ተስፋ እንደሰጣት የምትናገረው ድርቤ " ይህንንም ማረጋገጥ ችያለሁ ነገር ግን ጠንክሬም ሰርቻለሁ።"ብላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
"ለወርቅ መታገሌን ቀጥላለው"

አትሌት ለሜቻ ግርማ የዛሬውን ጨምሮ በተከታታይ የዓለም አቀፍ ውድድሮች በሞሮኮአዊው ሱፊያን ኤል ባካሊ ተቀድሞ የወርቅ ሜዳሊያውን አጥቷል።

ከውድድሩ በኋላ አትሌቱ ለጋዜጠኞች እንደተናገረው  " በተመሳሳይ ውድድሮች ብር ሳመጣ ይህ አራተኛዬ ነው ሆኖም ከኤል ባካሊ ጋር ባደረግኩት ውድድር ሁሉ ደስተኛ ነኝ" ሲል ገልጿል"

"አሁንም በኦሎምፒክም ሆነ በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ወርቅ ለማምጣት አላማ አለኝ" በማለት የተናገረው አትሌት ለሜቻ፥ አሁን ያመጣው ውጤት ለሚቀጥለው አመት ይበልጥ ሞራል እንደሆነው ገልጿል።

"የአለም ክብረ ወሰን በሰበርኩበት ልክ በቴክኒክም ሆነ በአካል ብቃት ከፍተኛ ዝግጅት አድርጌ ነበር" ያለው አትሌቱ "የነበሩ ክፍተቶችን እንመካከራለን፤ ምናልባትም ትኩረት አጥቼ ነበር ያም ሆነ ይህ ለወርቅ መታገሌን ቀጥላለው።" ሲል ተናግሯል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
የጨዋታዎችን ብዛት በመጨመር የሚያሸንፉትን ገንዘብ እስከ 300% ያሳድጉ! ቤቲካ ላይ ይወራረዱ! ያሸንፉ!
ለተሻለ ውርርድ ቤቲካን ይጠቀሙ! አሁኑኑ Betika.et ላይ /በቴሌግራም ቦታችን - @BetikaETBot ይወራረዱ!
🥇WANAW  ወደ ፊት...👉

✔️አድራሻ ፦ ገርጂ መብራት ሃይል የካቲት 
                   ወረቀት ፊትለፊት

👇🏽wanaw
  https://t.iss.one/wanawsportwear

    🤳0901 138 283
    🤳0910 851 535
    🤳0913 586 742
#Budapest 🇪🇹

አምስተኛ ቀኑ ላይ የደረሰው 19ኛው የዓለም ሻምፒዮና በዛሬው ዕለት ሀገራችን በሶስት ማጣርያ ውድድሮች ላይ የሚካፈሉ ይሆናል።

በዚህም መሰረት :-

ከቀኑ 5:05 800ሜ ሴቶች ማጣርያ ( ሀብታሙ አለሙ ፣ ወርቅነሽ መለሰ እና ትዕግስት ግርማ

ከምሽቱ 2:02 5000ሜ ሴቶች ማጣርያ ( ጉዳፍ ፀጋይ ፣ እጅጋየሁ ታዬ ፣ መዲና ኢሳ እና ፍሬወይኒ ሀይሉ

ከምሽቱ 2:45 3000ሜ ሴቶች መሰናክል ማጣርያ ( ሲምቦ አለማየው፣ ዘርፌ ወንድማገኝ ፣ሎሚ ሙለታ እና መቅደስ አበበ )

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ግሪንውድ እንግሊዝ መጫወት አይችልም "

የቀድሞ እንግሊዛዊ ተጨዋች ክሪስ ሱተን ሜሰን ግሪንውድ ከዚህ በኋላ እንግሊዝ ውስጥ መጫወት ከባድ እንደሚሆንበት ተናግሯል።

ክሪስ ሱተን በንግግሩም " ሜሰን ግሪንውድ ዳግመኛ እንግሊዝ ውስጥ መጫወት አይችልም ፣ ከቡድን አጋሮቹ እና ከሚሄድበት ክለብ ያለውን ጫና መቋቋም ይከብደዋል።

እሱ ትልቅ ተሰጥኦ ያለው ተጨዋች ነው ከእንግሊዝ ወጥቶ የእግር ኳስ ህይወቱን በድጋሜ መጠገን አለበት ፣ ትልቅ ስህተት ነው የሰራው ፣ በቀጣይ ወደ ሳውዲ አረቢያ ሊያመራ ይችላል ብዬ አስባለሁ።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌት ወርቅነሽ መለሰ ቀጣዩን ዙር ተቀላቀለች !

በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ወርቅነሽ መለሰ 3ኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏን አረጋግጣለች።

ሌሎች ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች በሌላ ምድብ የሚወዳደሩ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ምድብ አራት ጀምሯል

በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር አራተኛው ምድብ ኢትዮጵያ በአትሌት ትዕግስት ግርማ ተወክላለች።

መልካም እድል 🇪🇹

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አትሌት ትዕግስት ግርማ ቀጣዩን ዙር መቀላቀል አልቻለችም።

ስድስተኛ ደረጃን ይዛ አጠናቃለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe