TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.9K photos
1.48K videos
5 files
2.98K links
Download Telegram
አርሰናል አራተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ ምን ያስፈልገዋል ?

የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የመጨረሻ ቀን ጨዋታዎች ሲጠበቁ ከዋንጫ ፉክክሩ በተጨማሪ አራተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ የሚደረገው ፉክክር አጓጊ ሆኖ ይገኛል ።

የሰሜን ለንደኖቹን ክለቦች አርሰናል እና ቶተንሀም አፋጦ የሚገኘው የሻምፒየንስ ሊግ ቦታ ዛሬ ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ምላሽ የሚያገኝ ይሆናል ።

አርሰናል ዛሬ ምሽት ኤቨርተንን ማሸነፍ ከቻለ እና ቶተንሀም በ ኖርዊች ሲቲ ሽንፈትን ካስተናገደ አራተኛ ደረጃን ይዞ የሚያጠናቅቅ ይሆናል ።

ቶተንሀም ከ ኖርዊች ሲቲ ጋር ነጥብ ከተጋራ አርሰናል #አራተኛ ደረጃን ይዞ #ለማጠናቀቅ ኤቨርተንን በ 16 ግቦች ልዩነት #ማሸነፍ ይጠበቅበታል ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ቼልሲ ተከታታይ ሽንፈት አስተናግዷል !

በአሰልጣኝ ኤዲ ሀው የሚመራው ኒውካስትል በአስደናቂ ግስጋሴያቸው ሲቀጥሉ በሜዳቸው ቼልሲን በመርታት የአሸናፊነታቸውን ጉዞ አስቀጥለዋል።

√ ጆ ዊሎክ ብቸኛዋን የማሸነፊያ ግብ በቼልሲ መረብ ላይ አሳርፏል።

√ ጆ ዊሎክ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ለኒውካስትል ወሳኝ ሁለት ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

√ ሚጉኤል አልሚሮን ባለፉት ስምንት ለኒውካስትል ባደረጋቸው ጨዋታዎች ላይ በስምንት ጎሎች ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ችሏል።

√ የለንደኑ ክለብ ቼልሲ ተከታታይ ሽንፈታቸው ሲሆን ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች #ማሸነፍ ተስኗቸዋል።

√ የኤዲ ሀው ስብስብ ባለፉት #አስር ጨዋታዎች በአንዱም ሽንፈት አልገጠማቸውም።

√ ኒውካስትሎች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ ሁለተኛ ላይ ከተቀመጠው ማንችስተር ሲቲ በሁለት ነጥብ አንሰው በሰላሳ ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ይገኛሉ።

√ ቼልሲ ሀያ አንድ ነጥቦችን በመያዝ በፕርሚየር ሊጉ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
#QatarWorldCup 🇶🇦

68,895 ተመልካቾች በአል ባይት ስታዲየም በታደሙት ጨዋታ ጀርመን እና ስፔን ተጠባቂ መርሐ ግብራቸውን አንድ አቻ በሆነ ውጤት አጠናቀዋል።

√ ስፔን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ያስቆጠሩትን የጎል ብዛት ወደ ስምንት ከፍ አድርገዋል።

√ ከተቀያሪ ወንበር እየተነሳ ግብ በማስቆጠር ላይ የሚገኘው አልቫሮ ሞራታ ሁለተኛ ጎሉን በውድድሩ አስቆጥሯል።

√ ስፔን የዓለም ዋንጫውን በ 2010 ባሸነፉበት ዓመት ያስቆጠሩትን የግብ መጠን በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ በሁለት ጨዋታዎች ከመረብ አሳርፈዋል።

√ አልቫሮ ሞራታ በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ በሶስት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ችሏል።

√ ጀርመን በመጀመሪያው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ በአንቶኒ ሩዲገር አማካኝነት ግብ ቢያስቆጥሩም በቫር ተሽሮባቸዋል።

የምድብ አምስት መሪ ማነው?

1ኛ. ስፔን - አራት ነጥብ
2ኛ. ጃፓን - ሶስት ነጥብ
3ኛ. ኮስታሪካ - ሶስት ነጥብ
4ኛ. ጀርመን - አንድ ነጥብ

√ በምድብ አምስት የሚገኙ ሁሉም ሀገራት የማለፍ እድል ሲኖራቸው ቀጣይ የምድቡ ጨዋታዎች በጉጉት ይጠበቃሉ።

√ ጀርመን ከ ኮስታሪካ እንዲሁም ስፔን ከ ጃፓን ቀጣይ የምድቡ ጨዋታዎች ናቸው።

√ የ 2014 የዓለም ዋንጫ አሸናፊዋ #ጀርመን ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ #ኮስታሪካን #ማሸነፍ ይጠበቅባታል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" ማሸነፍ አለብን "

የምድብ የመጨረሻ ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ መካሄዳቸውን ሲጀምሩ ሴኔጋል የጥሎ ማለፉን ለመቀላቀል ኢኳዶርን #ማሸነፍ በቀላሉ ወደ ቀጣዩ ዙር ያሳልፋታል።

አሰልጣኝ አሊዮ ሲሴ ከጨዋታው አስቀድሞ በሰጡት አስተያየት " የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን የትላንቱ ድል ትልቅ መነሳሳትን ይፈጥርልናል ፣ ለጨዋታው ዝግጁ ነን ማሸነፍ ይኖርብናል።

ኢኳዶር ጥሩ ቡድን ነው ይህ መርሐ ግብር የሞት ሽረት ጨዋታ ነው ፣ ኢኳዶር በጣም የምናከብረው ቡድን ነው " ሲሉ አሊዮ ሲሴ ተናግረዋል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ካሜሮን ነጥብ ተጋርታለች !

በአሰልጣኝ ሪጎበርት ሶንግ የሚመመሩት ካሜሮኖች ስድስት ጎሎች በተስተናገዱበት መርሐ ግብር ከ ሰርቢያ ጋር ሶስት አቻ ተለያይተዋል።

√ ካሜሮን በዓለም ዋንጫ ታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በአንድ ጨዋታ ሶስት ጎሎችን አስቆጥራለች።

√ ቪንሰንት አቡበር በእግር ኳስ ህይወቱ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ጎሉን አስቆጥሯል።

√ ኤሪክ ማክሲም ቹፖ ሞቲንግ ባለፉት አስራ ሁለት ጨዋታዎች በሁሉም የውድድር መድረኮች አስራ ሁለተኛ ጎሉ ሆኗል።

√ ቪንሰንት አቡበከር በጨዋታው ተቀይሮ በመግባት በሁለት ጎሎች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን ማድረግ ችሏል።

√ አሌክሳንደር ሚትሮቪች ባለፉት ስድስት #ለሰርቢያ ባደረጋቸው ጨዋታዎች ሰባተኛ ጎሉን አስቆጥሯል።

√ ቪንሰንት አቡበከር ተቀይሮ በመግባት በጎል ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎን በዓለም ዋንጫው ማድረግ የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው #አፍሪካዊ ተጫዋች ሆኗል።

#ካሜሮን ወደ ጥሎ ማለፉ ለመቀላቀል ቀጣይ ጨዋታዋን #ማሸነፍ ሲጠበቅባት ከ #ብራዚል ጋር መርሐ ግብሯን ታካሂዳለች።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ሊቨርፑል ሽንፈትን አስተናግደዋል !

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል ከሜዳቸው ውጪ አቅንተው ከ ብሬንትፎርድ ጋር ያደረጉትን የፕርሚየር ሊጉ ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ተሸንፈዋል ።

- ለብሬንትፎርድ የማሸነፊያ ግቦችን ኢብራሂም ኮናቴ በራሱ ላይ እንዲሁም ዊሳ እና ሙቡዌሞ ከመረብ ሲያሳርፉ የሊቨርፑልን ብቸኛ ግብ ኦክስሌድ ቻምበርሊን አስቆጥሯል።

- ሊቨርፑል ከእረፍት በፊት ሁለት እና ከዛ በላይ ጎል ተቆጥሮባቸው ያለፉትን ሀያ የሊግ ጨዋታዎች #ማሸነፍ አልቻለም ።

- ሊቨርፑል በውድድር ዓመቱ በፕርሚየር ሊጉ አምስተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

- ብሬንትፎርድ በዘንድሮው የውድድር ዓመት ማንችስተር ሲቲ እና ዩናይትድን #ሲያሸንፉ ከ ቼልሲ እና ቶተንሀም ጋር #ነጥብ ተጋርተዋል።

- የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በጊዜያዊነት ከሊጉ መሪ አርሴናል በአስራ አምስት ነጥብ ዝቅ ብለው በሀያ ስምንት ነጥብ #ስድስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

- ሊቨርፑልን ማሸነፍ የቻሉት ብሬንትፎርዶች በአንፃሩ ነጥባቸውን ሀያ ስድስት በማድረስ #ሰባተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችለዋል።

- ሊቨርፑል በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ከ ብራይተን እንዲሁም ብሬንትፎርድ ከ በርንማውዝ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ ስታዲየም ደርሰዋል !

ከሰዓታት በኋላ የሊቢያ ብሔራዊ ቡድንን የሚገጥሙት ዋልያዎቹ ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በ " Stade 19-Mai-1956 " ስታዲየም ደርሰዋል።

ዋልያዎቹ ወደ ቀጣዩ ዙር ለማለፍ #ማሸነፍ እና በምድቡ ሌላኛ ጨዋታ የሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድንን #መሸነፍን ይጠብቃሉ።

@tikvahethsport @kidusyoftahe
እንኳን ደስ አለን 🇪🇹

44ኛው የሀገር አለም አቋራጭ ውድድር በአውስትራሊያ ሲካሄድ ኢትዮጵያ ከ 20ዓመት በታች ውድድር በግል እና በቡድን #ማሸነፍ ችለዋል።

ከ 20ዓመት በታች በተደረገው ውድድር ድንቅ አጨራረስ በታየበት ፉክክር ሰናይት ጌታቸው አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገሯ #ወርቅ አስገኝታለች።

ሌላዋ አትሌታችን መዲና ኢሳ #ሁለተኛ ደረጃን ስትይዝ ኬንያዊቷ ፓሜላ ኮስጌል ሶስተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አጠናቀዋል።

ለመጨረሻ ጊዜ በተደረገው በዚህ የርቀት ውድድር ላይ ኬንያዊያን የበላይነቱን ይዘው አጠናቀው ነበር።

የሌሎች አትሌቶቻችን ውጤት ምን ይመስላል ?

5ኛ :- ለምለም ንብረት
7ኛ :- መሰረት የሻነህ
8ኛ :- ትነበብ አስረስ
11ኛ :- መልኬናት ውዱ

የ 20ዓመት የአለም አቋራጭ ውድድር ስድስት ኪሎ ሜትሮችን የሚሸፍን ውድድር ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
" አላማችን እንደ ባርሴሎና ያሉ ቡድኖችን ማሸነፍ ነው "

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ እና ተከላካዩ ራፋኤል ቫራን በነገው ዕለት ከባርሴሎና ጋር በሚያደርጉት የዩሮፓ ሊግ ጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ዙርያ ከጋዜጠኞች ጋር ቆይታን አድርገዋል።

በቅድሚያ ንግግር ያደረጉት አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሀግ ሲሆኑ በአስተያየታቸውም :-

- በነገው ዕለት የተለየ ነገር እንደምታዩ ተስፋ አለኝ ሀሳብ አለን ያንን ደግሞ በሜዳ ላይ ታዩታላችሁ።

- ሀሪ ማጓየር እና አንቶኒ ለነገው ጨዋታ ዝግጁ ናቸው ፣ አንቶኒ ማርሽያል ግን አሁንም ገና ነው።

- ሁለት ታላላቅ ቡድኖች በኦልድ ትራፎርድ ይፋለማሉ ፣ የስታዲየሙ ድባብ ልዩ ይሆናል።

በመቀጠልም የተከላካይ መስመር ተጨዋቹ ራፋኤል ቫራን ባደረገው ንግግር :-

- ከባርሴሎና ጋር ያደረገውን የመጀመሪያ ጨዋታ ጥሩ ነበር ፣ ለእኛ ጥሩ ውጤት ነበር ብዙ ጎሎችን ማስቆጠር እንችል ነበር።

- የነገውን ጨዋታ በትዕግስት እና በፀባይ መጫወት እንፈልጋለን ፣ ለዚህም ፈተና ዝግጁ ነን።

- ቀጣይ አለማችን እንደ ባርሴሎና ያሉ ክለቦችን #ማሸነፍ ነው ፣ ትልቅ ፈተና እና ጥሩ አጋጣሚ ነው።" ሲል ተደምጧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

45ኛው የአለም አትሌቲክስ ሀገር አቋራጭ ውድድር በሰርቢያ ቤልግሬድ ሲካሄድ ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ከ 20ዓመት በታች 6ኪ.ሜ ውድድርን ተከታትለው በመግባት #ማሸነፍ ችለዋል።

ከ 20ዓመት በታች በተደረገው የሴቶች ውድድር አትሌት ማርታ አለማየሁ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገሯ #ወርቅ ማስገኘት ችላለች።

ሌሎች አትሌቶቻችን አሳየች አይቸው #ሁለተኛ እንዲሁም ሮቤ ዲዳ #ሶስተኛ ደረጃን ይዘው በማጠናቀቅ ታሪካዊውን የአረንጓዴ ጎርፍ ድል አስመዝግበዋል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም ሀገር አቋራጭ ውድድር ታሪክ ከ 20ዓመት በታች ሴቶች ውድድርን ከአንድ እስከ ሶስት ያለውን ደረጃ ይዛ ስታጠናቅቅ ለሶስተኛ ጊዜ መሆኑ ተገልጿል።

በ 8ኪ.ሜ ወንዶች በተደረገ ውድድር ኢትዮጵያዊው አትሌት መዝገበ ስሜ ሁለተኛ ደረጃን ይዞ በማጠናቀቅ ለኢትዮጵያ የብር ሚዳልያ አስገኝቷል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe