TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
ተጠናቀቀ | አስቶን ቪላ 3-0 ኒውካስል ዩናይትድ

ራምሴይ
ዋትኪንስ

- በአሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ የሚመሩት አስቶን ቪላዎች በሊጉ ተከታታይ #አምስተኛ ድላቸውን ማስመዝገብ ችለዋል።

- የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ስብስብ ኒውካስል ዩናይትድ ከአምስት ተከታታይ ጨዋታዎች ድል በኋላ ሽንፈት አስተናግደዋል።

- አስቶን ቪላ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን #ሀምሳ በማድረስ #ስድስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- ኒውካስል ዩናይትድ በሀምሳ ስድስት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ናፖሊ 0-0 ሄላስ ቬሮና

- ናፖሊ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰባ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ ከተከታዩ ላዝዮ በአስራ አራት ነጥቦች ርቆ ሊጉን በበላይነት እየመራ ይገኛል።

- የአሰልጣኝ ሉሲያኖ ስፓሌቲው ስብስብ በውድድር አመቱ #ሶስተኛ የሊግ ጨዋታውን አቻ ወጥቷል።

- የሊጉ መሪ ናፖሊ በቀጣይ ከጁቬንቱስ ጋር ተጠባቂ የሊግ መርሐ ግብሩን አልያንዝ ስታዲየም ላይ የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኒውካስል ወሳኝ ሶስት ነጥብ አስመዝግቧል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኒውካስል ዩናይትድ ከቶተንሀም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 6ለ1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የኒውካስል ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች መርፊ 2x ፣ አሌክሳንደር አይሳክ 2x ፣ ጆኢሊንተን እና ካሉም ዊልሰን ከመረብ ሲያሳርፉ የቶተንሀምን ብቸኛ ግብ ሀሪ ኬን አስቆጥሯል።

በሀያ አንድ ደቂቃዎች አምስት ግቦችን ማስቆጠር የቻለው ኒውካስል ዩናይትድ በፕርሚየር ሊጉ ታሪክ በፍጥነት ይህንን ያህል ግብ ያስቆጠረ ሁለተኛው ፈጣን ክለብ መሆን ችሏል።

ኒውካስል ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሀምሳ ዘጠኝ በማድረስ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቶተንሀም በሀምሳ ሶስት ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኒውካስል ዩናይትድ ከኤቨርተን እንዲሁም ቶተንሀም ከ ማንችስተር ዩናይትድ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አንደኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል።

- የባህር ዳር ከተማን ግቦች ሀብታሙ ታደሰ እና አደም አባስ ከመረብ ሲያሳርፉ ለኢትዮጵያ መድን ሳይመን ፒተር እና ሀቢብ ከማል ማስቆጠር ችለዋል።

- የኢትዮጵያ መድኑ ተጨዋች ሀቢብ ከማል በውድድር አመቱ #ዘጠነኛ ግቡን ሲያስቆጥር ሌላኛው ተጨዋች ሳይመን ፒተር ስድስተኛ ጎሉን ከመረብ አሳርፏል።

- የባህርዳር ከተማው ተጨዋች ሀብታሙ ታደሰ በውድድር አመቱ ሰባተኛ ግቡን ማስቆጠር ችሏል።

- ባህርዳር ከተማ በአርባ ሶስት ነጥቦች #ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ መድን በሰላሳ ስምንት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ እንዲሁም ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲቲ የሊጉን መሪነት ተረክቧል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ሰላሳ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ፉልሀምን 2ለ1 እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ አስቶንቪላን 1ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የማንችስተር ሲቲን የማሸነፊያ ግቦች ኤርሊንግ ሀላንድ እና ጁሊያን አልቫሬዝ ሲያስቆጥሩ ቪንሰስ የፉልሀምን ግብ ከመረብ አሳርፏል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግብ ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

በሌላ ጨዋታ ኒውካስል ዩናይትድ ከ ሳውዝሀምፕተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ 3ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ሲቲው የፊት መስመር ተጨዋች ኤርሊንግ ሀላንድ በውድድር አመቱ ሰላሳ አራተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ማንችስተር ሲቲ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰባ ስድስት በማድረስ አንድ ጨዋታ እየቀረው የሊጉን መሪነት ከአርሰናል መረከብ ችሏል።

ኒውካስል ዩናይትድ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

ማንችስተር ዩናይትድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ ሶስት በማድረስ #አራተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

በቀጠይ የሊጉ መርሐ ግብር ማንችስተር ሲቲ ከ ዌስትሀም እንዲሁም ማንችስተር ዩናይትድ ከ ብራይተን ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ጁቬንቱስ ነጥብ ጥሏል !

በጣልያን ሴርያ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐግብር ጁቬንቱስ ከ ቦሎኛ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

የቦሎኛን ግብ ኦርሶሊኒ ሲያስቆጥር ለጁቬንቱስ የአቻነቷን ግብ ሚሊክ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ጁቬንቱስ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ስልሳ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቦሎኛ በአርባ አምስት ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐግብር ጁቬንቱስ ከሊቼ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ መድን አሸንፏል !

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

- የኢትዮጵያ መድንን የማሸነፊያ ግቦች ሐቢብ ከማል እና ብሩክ ሙሉጌታ ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ለኢትዮ ኤሌክትሪክ አብዱልራህማን ሙባረክ አስቆጥሯል።

- የኢትዮጵያ መድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ሀቢብ ከማል በውድድር አመቱ አስረኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- ኢትዮጵያ መድን ማሸነፉን ተከትሎ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮ ኤሌክትሪክ በአስራ አንድ ነጥብ አስራ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ሲዳማ ቡና እንዲሁም ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከ ድሬዳዋ ከተማ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ድል አድርገዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲን ኦዴጋርድ እና ፋብያን ሻር በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የአርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ በውድድር አመቱ አስራ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰማንያ አንድ በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አንድ ማጥበብ ችሏል።

የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ቡድን ኒውካስል ዩናይትድ በስልሳ አምስት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከብራይተን እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሲዳማ ቡና ድል አድርጓል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ ሶስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ መድን ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የሲዳማ ቡናን የማሸነፊያ ግብ ፍሊፕ አጃህ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሲዳማ ቡና ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሀያ ሰባት በማድረስ አስራ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ኢትዮጵያ መድን በአርባ አንድ ነጥቦችን #ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ድሬዳዋ ከተማ እንዲሁም ሲዳማ ቡና ከ መቻል የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ተጠናቀቀ | ሊድስ ዩናይትድ 2-2 ኒውካስል ዩናይትድ

አይሊንግ ካሉም ዊልሰን
ክሪስቴንሰን

- የኒውካስል ዩናይትዱ የፊት መስመር ተጨዋች ካሉም ዊልሰን በውድድር አመቱ አስራ ሰባተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

- የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ቡድን ኒውካስል ዩናይትድ በስልሳ ስድስት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

- ሊድስ ዩናይትድ በሰላሳ አንድ ነጥቦች በወራጅ ቀጠናው አስራ ስምንተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሪያል ማድሪድ ሽንፈት አስተናግዷል !

ሪያል ማድሪድ ከቫሌንሽያ ጋር ያደረገውን የስፔን ላሊጋ ሰላሳ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር 1ለ0 በሆነ ውጤት ተሸንፏል።

የቫሌንሽያን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ ዲያጎ ሎፔዝ ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ሪያል ማድሪድ በውድድር አመቱ ስምንተኛ ሽንፈታቸውን አስተናግደዋል።

ሪያል ማድሪድ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰባ አንድ ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቫሌንሽያ በአርባ ነጥብ አስራ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#BKEthPL 🇪🇹

በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አምስተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ሀዋሳ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 2ለ2 በሆነ አቻ ውጤት ማጠናቀቅ ችለዋል።

የኢትዮጵያ መድን ግቦች ሲሞን ፒተር 2x ሲያስቆጥር ለሀዋሳ ከተማ የአቻነት ግቦችን ሰዒድ ሀሳን 2x ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

የኢትዮጵያ መድኑ የፊት መስመር ተጨዋች ሲሞን ፒተር በውድድር አመቱ ስድስተኛ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ኢትዮጵያ መድን በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ አርባ አምስት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ሀዋሳ ከተማ በሰላሳ አራት ነጥብ #ሰባተኛ ደረጃን ይዟል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ መድን ከ ወልቂጤ ከተማ እንዲሁም ሀዋሳ ከተማ ከ መቻል ጋር ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ማንችስተር ዩናይትድ ድል አድርጓል !

በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ተስተካካይ መርሐ ግብር ማንችስተር ዩናይትድ ከ ቼልሲ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የማንችስተር ዩናይትድን የማሸነፊያ ግቦች ካሴሚሮ ፣ ማርከስ ራሽፎርድ ፣ አንቶኒ ማርሻል እና ብሩኖ ፈርናንዴዝ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የሰማያዊዎቹን ብቸኛ የማስተዛዘኛ ግብ ጇ ፌሊክስ ከመረብ አሳርፏል።

ቀያዮቹ ሴጣኖች ማሸነፋቸውን ተከትሎ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ ውድድር ተሳትፎ ቦታን ማረጋገጥ ችለዋል።

ማንቸስተር ዩናይትድ በሰባ ሁለት ነጥብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጥ ቼልሲ በአርባ ሶስት ነጥብ አስራ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

በሊጉ የመጨረሻ ጨዋታ ማንችስተር ዩናይትድ ከፉልሀም እንዲሁም ቼልሲ ከኒውካስል ዩናይትድ የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ብርቄ ኃየሎም ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች 🇪🇹

የ1,500 ሜትር ሴቶች የማጣሪያ ውድድር እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን በውድድሩ ሶስተኛ ምድብ የተካፈለችው ኢትዮጵያዊት አትሌት ብርቄ ኃየሎም #ሶስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሁለት አትሌቶቻችን ግማሽ ፍፃሜ ደረሰዋል !

በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ ውድድር የተካፈሉት ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ወርቅነሽ መለሰ እና ሀብታም አለሙ #ሶስተኛ እና #አንደኛ ደረጃን በመያዝ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ችለዋል።

በርቀቱ የተሳተፈችው ሌላኛዋ ኢትዮጵያዊት አትሌት ትዕግስት ግርማ ውድድሯን ስድስተኛ ደረጃን ይዛ ማጠናቀቋን ተከትሎ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል ሳትችል ቀርታለች።

የሴቶች 800 ሜትር ግማሽ ፍፃሜ ውድድር የፊታችን አርብ ምሽት 3:25 ላይ የሚደረግ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
አል ናስር ድል አድርጓል !

በሳውዲ አረቢያ ሊግ ስምንተኛ ሳምንት መርሐ ግብር የክርስቲያኖ ሮናልዶው ክለብ አል ናስር ከአል ታኢ ጋር ያደረገውን ጨዋታ 2ለ1 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

ክርስቲያኖ ሮናልዶ በጨዋታው አንድ ግብ በፍፁም ቅጣት ምት ሲያስቆጥር የአል ናስርን የመጀመሪያ ግብ ላስቆጠረው ታሊስካ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል።

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በ2023 አርባ ሶስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል።

- አል ናስር በሊጉ አስራ ስምንት ነጥቦችን በመሰብሰብ #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

- ክርስቲያኖ ሮናልዶ በሰባት የሉጉ ጨዋታዎች #አስር ግቦችን ከመረብ በማሳረፍ የሳውዲ አረቢያ ሮሸን ሊግ ከፍተኛ ግብ አስቆጣሪዎች ደረጃን በመምራት ላይ ይገኛል።

- ሮናልዶ አጠቃላይ በሊጉ በዘንድሮው የውድድር ዘመን በአስራ አምስት ግቦች ላይ ቀጥተኛ ተሳትፎ ማድረግ ሲችል ይህም በሊጉ ከፍተኛው ነው።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe