TIKVAH-SPORT
246K subscribers
46.8K photos
1.48K videos
5 files
2.97K links
Download Telegram
የኒውካስል ተጨዋቾች ቃል ተገብቶላቸዋል !

የኒውካስል ዩናይትድ ባለቤቶች ክለቡ በካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ማንችስተር ዩናይትድን አሸንፎ ሻምፒዮን የሚሆን ከሆነ የ #አንድ ሚልዮን ፓውንድ የማበረታቻ ሽልማት ለተጨዋቾቹ እንደሚሰጡ ተገልጿል።

የውድድሩ አሸናፊ ክለብ 100,000 ፓውንድ የሚያገኝ ቢሆንም የኒውካስል ባለቤቶች ክለቡ ከ 48ዓመታት በኋላ የመጀመሪያ ዋንጫውን የሚያገኝ ከሆነ አስር እጥፍ የሚሆን ገንዘብ ለተጨዋቾቹ እንደሚሰጡ ገልጸዋል።

ማንችስተር ዩናይትድ ከ ኒውካስል ዩናይትድ የሚያደርጉት የካራባኦ ካፕ ፍፃሜ ጨዋታ ዕሁድ ምሽት 1:30 በዌምብሌይ ስታዲየም ይደረጋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
መድፈኞቹ ድል አድርገዋል !

የሰሜን ለንደኑ ክለብ አርሰናል ከኒውካስል ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የሊግ መርሐ ግብር 2ለ0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የመድፈኞቹን የማሸነፊያ ግቦች ማርቲን ኦዴጋርድ እና ፋብያን ሻር በራሱ ግብ ላይ ከመረብ ማሳረፍ ችለዋል።

የአርሰናል የመሐል ሜዳ ተጨዋች ማርቲን ኦዴጋርድ በውድድር አመቱ አስራ አምስተኛ የሊግ ግቡን ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

አርሰናል ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ሰማንያ አንድ በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው የሊጉ መሪ ማንችስተር ሲቲ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አንድ ማጥበብ ችሏል።

የአሰልጣኝ ኤዲ ሆው ቡድን ኒውካስል ዩናይትድ በስልሳ አምስት ነጥቦች #ሶስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር አርሰናል ከብራይተን እንዲሁም ኒውካስል ዩናይትድ ከሊድስ ዩናይትድ ይገናኛሉ።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዶርትመንድ ድል አድርጓል !

በጀርመን ቡንደስሊጋ ሰላሳ ሁለተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዶርትመንድ ከ ምንቻግላድባች ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 5ለ2 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችሏል።

የዶርትመንድን የማሸነፊያ ግብ ማለን ፣ ቤሊንግሀም ፣ ሀለር 2x እና ሬይና ከመረብ ማሳረፍ ሲችሉ ስቲንድል እና በንሰባይኒ የምንቻግላድባችን ግቦች አስቆጥረዋል።

ዶርትመንድ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን ስልሳ ሰባት በማድረስ ከሊጉ መሪ ባየር ሙኒክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አንድ ማጥበብ ችሏል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ቦርስያ ዶርትመንድ ከኦግስበርግ ጋር የሚገናኙ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባህርዳር ከተማ ወሳኝ ድል አስመዝግቧል !

በቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ ሀያ አራተኛ ሳምንት መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከአዳማ ከተማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት ማሸነፍ ችለዋል።

የባህርዳር ከተማን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አደም አባስ ተቀይሮ በመግባት ከመረብ ማሳረፍ ችሏል።

ባህርዳር ከተማ ማሸነፉን ተከትሎ ነጥቡን #ሀምሳ በማድረስ አንድ ጨዋታ ከሚቀረው የሊጉ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ #አንድ ማጥበብ ችሏል።

አዳማ ከተማ በሊጉ ደረጃ ሰንጠረዥ ሰላሳ ሁለት ነጥቦችን በመሰብሰብ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

በቀጣይ የሊጉ መርሐ ግብር ባህርዳር ከተማ ከ ሀድያ ሆሳዕና እንዲሁም አዳማ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ ጋር የሚጫወቱ ይሆናል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዋልያዎቹ በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ ዝቅ ብለዋል !

የፊፋ የወንዶች የአለም ሀገራት እግር ኳስ ደረጃ ሰንጠረዥ ይፋ ሲደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ( ዋልያዎቹ ) #አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው ለመቀመጥ ተገደዋል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በፊፋ ወርሀዊ ደረጃ ባለፉት ወራቶች ከነበሩበት 142ኛ አንድ ደረጃ ዝቅ ብለው 143ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።

ዋልያዎቹ በካፍ የአፍሪካ ሀገራት የደረጃ ሰንጠረዥም አንድ ደረጃ ዝቅ በማለት አርባ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ለመቀመጥ ተገደዋል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ቼልሲ በቶድ ቦህሊ ስር ለዝውውር ስንት አወጣ ?

የምዕራብ ለንደኑ ክለብ ቼልሲ በአዲሱ አሜሪካዊ ባለቤት ቶድ ቦህሊ ስር በሶስት የዝውውር መስኮቶች ለተጨዋቾች ግዢ በርካታ ገንዘብ ወጪ ማድረጋቸው ተነግሯል።

ሰማያዊዎቹ በቶድ ቦህሊ ስር በአስራ አምስት ወራቶች ውስጥ #አንድ ቢልዮን ዶላር የዝውውር ሒሳብ ወጪ ሲያደርጉ ሀያ ሶስት ተጨዋቾችን ወደ ቡድናቸው ማዘዋወር ችለዋል።

ቼልሲ በተጨማሪም በዚህ የዝውውር መስኮት ተጨማሪ ተጨዋቾችን እንደሚያስፈርሙ ሲጠበቅ ሮሚዮ ላቪያን ከሳውዝሀምፕተን በ50 ሚልዮን ዩሮ ለማስፈረምም መቅረባቸው ይታወቃል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ዩናይትድ የጋላታሳራይን ጥያቄ ውድቅ አደረገ !

የቱርኩ ክለብ ጋላታሳራይ የማንችስተር ዩናይትዱን የመሐል ሜዳ ተጨዋች ዶኒ ቫን ዴቢክ በውሰት ለማስፈረም #አንድ ሚልዮን ፓውንድ ቢያቀርብም ማንችስተር ዩናይትድ ውድቅ ማድረጉ ተገልጿል።

ሁለቱ ክለቦች በተጨዋቹ ዝውውር ዙሪያ ከስምምነት ለመድረስ ንግግር ማድረጋቸውን መቀጠላቸው ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ሰርጅዮ ራሞስ ሲቪያን መቀላቀል መርጧል !

ስፔናዊው የቀድሞ የሪያል ማድሪድ ተጨዋች ሰርጅዮ ራሞስ ከሳውዲ አረቢያ እና ቱርክ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያስገኝ ጥያቄ ቢቀርብለትም ውድቅ በማድረግ ሲቪያን ለመቀላቀል ከስምምነት ደርሷል።

ሰርጅዮ ራሞስ ከአል ኢትሀድ በአመት 20 ሚልዮን ዩሮ እንዲሁም ከጋላታሳራይ 11 ሚልዮን ዩሮ ክፍያ ቢቀርበለትም ሲቪያን በአመት #አንድ ሚልዮን ዩሮ እየተከፈለው ለማገልገል መወሰኑ ተገልጿል።

የልጅነት ክለቡን ሲቪያ ለመቀላቀል ወደ ስፍራው ያመራው ራሞስ " ወደዚህ ለመመለስ ለረጅም ጊዜ ስጠብቅ ነበር ፣ ወደዚህ የተመለስኩት የአያቴን እና ቤተሰቤን እንዲሁም የክለቡን ደጋፊዎች እዳ ለመክፈል ነው።"ብሏል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
#Ethiopia 🇪🇹

በአለም አትሌቲክስ አዘጋጅነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረገው የዓለም የጎዳና ላይ ሩጫ ውድድር በዛሬው ዕለት በላቲቪያ ሪጋ በይፋ ጅማሮውን ያደርጋል።

በውድድሩ ሀገራችን ኢትዮጵያን የሚወክሉ አትሌቶች ዛሬ ከረፋድ 5:50 ሰዓት ጀምሮ በሁለቱም ፆታዎች በሶስት ርቀቶች የሚሳተፉ ይሆናል።

ኢትዮጵያ በእነማን ትወከላለች ?

👉 የሴቶች 5ኪ.ሜ ውድድር ጠዋት 5:50 ሰዓት

- እጅጋየሁ ታዬ
- መዲና ኢሳ

👉 የወንዶች 5ኪ.ሜ ውድድር ቀን 6:15 ሰዓት

- ዮሚፍ ቀጄልቻ
- ሀጐስ ገ/ሕይወት

👉 የሴቶች #አንድ ማይል ውድድር ቀን 7:00 ሰዓት

- ድርቤ ወልተጂ
- ፍሬወይኒ ኃይሉ

👉 የወንዶች #አንድ ማይል ውድድር ቀን 7:10 ሰዓት

- ታደሰ ለሚ

👉 የሴቶች ግማሽ ማራቶን ውድድር ቀን 7:30 ሰዓት

- ጽጌ ገ/ሰላማ
- ያለምጌጥ ያረጋል
- ፍታው ዘርዬ

👉 የወንዶች ግማሽ ማራቶን ውድድር ቀን 8:15 ሰዓት

- ጀማል ይመር
- ንብረት መላክ
- ፀጋዬ ኪዳኑ ሀገራችንን ወክለው ይወዳደራሉ፡፡

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ኢትዮጵያ ተጨማሪ ወርቅ አገኘች !

በሪጋ እየተካሄደ በሚገኘው የአለም የጎዳና ላይ የአለም ሻምፒዮና አትሌት ድርቤ ወልተጂ ኬንያዊቷን የ 1500ሜ የአለም ሪከርድ ባለቤት ፌዝ ኪፕዬጎን በመርታት ለሀገሯ ወርቅ አምጥታለች።

ድርቤ ወልተጂ ከማሸነፍ ባለፈም የአለም የአንድ ማይል ሪከርድን 4:21.00 በመግባት በመስበር ልታሸንፍ ችላለች።

በርቀቱ የተካፈለችው ሌላኛዋ አትሌት ፍሬወይኒ ኃይሉ ሁለተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቅ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳልያ ማስመዝገብ ችላለች።

ድርቤ ወልተጂ በቡዳፔሽት የዓለም ሻምፒዮና በ 1500ሜ በፌዝ ኪፕዬጎን ተቀድማ ለሀገሯ የብር ሜዳሊያ ማምጣቷ የሚታወስ ነው።

ፌዝ ኪፕዬጎን በ 2023 የውድድር ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ ልትሸነፍ ችላለች።

የዚህ ውድድር አሸናፊዎች ምን ያህል ያገኛሉ ?

1️⃣ኛ. አስር ሺህ ዶላር

2️⃣ኛ. ስድስት ሺህ ዶላር

3️⃣ኛ. ሶስት ሺህ አምስት መቶ ዶላር

ሀገራችን ኢትዮጵያ እስከአሁን በተደረጉ ሶስት የፍፃሜ ውድድሮች #ሁለት ወርቅ ፣ #ሁለት ብር እና #አንድ የነሀስ ሜዳልያ በማስመዝገብ የሜዳልያ ሰንጠረዡን በመምራት ላይ ትገኛለች።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe
ባርሴሎና የተጫዋቹን ውል አድሷል !

የካታላኑ ክለብ ባርሴሎና የወጣቱን ስፔናዊ የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል ኮንትራት ለተጨማሪ አመታት ማራዘማቸውን ይፋ አድርገዋል።

የ 16ዓመቱ ወጣት የፊት መስመር ተጨዋች ላሚን ያማል በባርሴሎና ቤት እስከ 2026 የሚያቆየውን የሶስት አመት ኮንትራት መፈረሙ ይፋ ሆኗል።

የተጨዋቹ ውል ማፍረሻ ገንዘብ #አንድ ቢልዮን ዩሮ ሆኖ በኮንትራቱ ውስጥ መካተቱ ተዘግቧል።

@tikvahethsport     @kidusyoftahe