#TikvahFamilyBulenWoreda
ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ቡለን ወረዳ ከትላንት ሌሊት ጀምሮ እስከ ጠዋት በዘለቀው ጥቃት ከ 96 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን የቡለን ወረዳ በኩጂ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ የቲክቫህ አባላት ገልጸዋል።
እስካሁን ድረስ በግልጽ ስለተፈጸመውም ጥቃት ይህ ነው የሚባል መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት የተሰማ ነገር የለም።
የምን ያህል ሰው ህይወት እንዳለፈም በውል ማረጋገጥ አልቻልንም።
ጉዳቱ ግን "እጅግ በጣም ከባድ" እንደሆነ በበኩጂ ቀበሌ የተፈጸመውን ድርጊት ተመልክተው የፎቶ ማስረጃም የላኩ ቤተሰቦቻችን ገልጸዋል።
በቡለን የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም ከ20 በላይ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።
www.tikvahethiopia.net
@tikvahethiopia @tikvahethmagazine

#SecurityAlert
በመተከል ዞን ቡለን ወረዳ ኤማንጂ፣በኖሽ፣ ዶቢ ቀበሌዎች አሁንም ከፍተኛ የደህንነት ችግር እንዳለባቸውን የቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።
ትላንት ለሊቱን በዶቢ ቀበሌ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ እንደነበረ ጠቁመዋል። ስለደረሰው ጉዳት አጣርተው እንደሚያሳውቁን ገልፀዋል።
በተጠቀሱት አካባቢዎች ነዋሪው ቤት ንብረቱን ጥሎ እየሸሸ መሆኑንም አባላቶቻችን መልዕክት አድርሰዋል።
በ www.tikvahethiopia.net ላይ በየአካባቢው ያለውን የፀጥታ እንዲሁም ደህንነት ስጋት ልታሳውቁን ትችላላችሁ።
#TikvahFamilyBulenWoreda
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

ትላንት ለሊቱን በዶቢ ቀበሌ ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ ሲሰማ ነበር።
በቀበሌው በተፈፀመው ጥቃት የአምስት ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ በቡለን ወረዳ የቲክቫህ ኢትጵያ አባላት አሳውቀዋል።
አሁን በስልክ ያገኘናቸው የዶቢ ቲክቫህ አባላት የሟቾችን ስርዓተ ቀብር በስጋት ውስጥ ሆነው እያከናወኑ እንደሆነ ተናግረዋል።
ጥቃት አድራሾቹ ከበኩጂ ቀበሌ የተበተኑ የታጠቁ ኃይሎች እንደሆኑ የቲክቫህ አባላት በ www.tikvahethiopia.net ላይ ገልፀዋል።
አንድ አባላችን እንደገለፁልን ወደ #ዶቢ የገቡት ታጣቂዎች እስከ 300 የሚደርሱ ናቸው።
የመከላከያ ሰራዊት መረጃው ደርሶት በመግባት ምሽግ ይዞ ጥቃቱን ባይከላከል የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችል ነበር ብለውናል።
አንድ የመከላከያ አባልም መጠነኛ ጉዳት ደርሶበታል።
የመተከል ዞን የቲክቫህ አባላት ለአካባቢው እንዲህ መሆን አመራሮችን ተጠያቂ ያደርጋሉ።
መንግስት ውስጡን እንዲፈትሽም በተደጋጋሚ አሳውቀዋል።
ነዋሪው ተስፋ ቆርጧል ፥ ግፍ እና መከራ አድክሞታል እጅግ በጣም አስቸኳይ መፍትሄ ይፈልጋል ብለዋል።
አሁንም ቢሆን በወረዳው የተለያዩ ቀበሌዎች ውስጥ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት በመኖሩ የሚመመለከተው አካል ንፁሃንን እንዲታደግ አባላቶቻችን እየተማፀኑ ነው።