TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወሎ ዩኒቨርሲቲ🔝

ዛሬ በወሎ ዩኒቨርስቲ (ኮምቦልቻ ካምፓስ) የሚማሩ ተማሪዎች የከተማውን ህዝብ ስላደረጋችሁልን ነገር #እናመሠግናለን በማለት ከተማውን #የማፅዳት ስራ አከናውነዋል።

ከተማሪዎቹ...

ቄጠማ አንጥፋችሁ፣ ቡና አፍልታችሁ፣ ዳቦ ቆርሳችሁ፣ ሻንጣችንን ተሸክማችሁ ለተቀበላችሁን የኮምቦልቻ ከተማ የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች፣ ወጣቶች እና የከተማዋ አመራሮች፦ እኛ የወሎ ዩኒቨርሲቲ ኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች በፍቅር
ተቀብሎ በሰፊ መዳፉ አቅፎ በፍቅር አስመርቆ የሚሸኘንን የኮምቦልቻ ከተማ ማህበረሰብ በማመስገን እሁድ ታህሳስ 7/04/2011 ዓ.ም ውቧን ኮምቦልቻ ውብ አድርገናት ከተማችንን በማጽዳት ምስጋናችንን ለመግለጽ መጥረጊያ፣ አካፋ፣ ዶማ እና ጋሪ ታጥቀን ዘመቻችን በተሳከካ መልኩ ጨርሰን ተመልሰናል ፡፡

ከኮምቦልቻ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች። ወሎ የፍቅርና የጥበብ ምድር!!
©Mekbib

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቤንሻንጉል ጉምዝ‼️

የመከላከያ ሰራዊት ዛሬ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን #የፈንጅ_አደጋ ተከትሎ አካባቢውን #የማፅዳት ስራ እየሰራ ነው።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ #ጀይላን_ከበደ ዛሬ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ በነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ የደረሰውን የፈንጂ አደጋ በተመለከተ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም አደጋውን ተከትሎ የመከላከያ ሰራዊት ስፍራውን በመቆጣጠር አካባቢውን የማጽዳት ስራ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በቀጣይ የፌደራል ፖሊስ ከአደጋው ጋር በተያያዘ ምርመራውን እንደሚያደርግም ነው የተናገሩት።

አደጋው ኮድ 3 በሆነ ተሽከርካሪ ላይ መፈጸሙን ጠቅሰው፥ በአደጋው ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን አንስተዋል።

አደጋው የደረሰበት አካባቢ በርካታ ታጣቂ ሃይሎች የሚንቀሳቀሱበት ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፥ የዛሬው አደጋም ለውጡን በማይቀበሉ ፀረ ሰላም ሃይሎች የተፈጸመ ነው ብለዋል።

የዛሬው አደጋ መንግስት በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን ማንነት ለመለየት ጥረት እያደረገ ባለበት ሰዓት መፈጸሙንም አውስተዋል።

በአደጋው የሞቱ ዜጎች ማንነትም በቀጣይ በምርመራ እንደሚለይም የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

በቀጣይም ህብረተሰቡ በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በመለየትና መረጃዎችን በመስጠት የምርመራ ሂደቱን እንዲያግዝም ጥሪ አቅርበዋል።

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽንም በአደጋው ህይዎታቸውን ባጡ ዜጎች የተሰማውን ጥልቅ ሃዘን ገልጿል።

በዛሬው እለት በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ ተሽከርካሪ ላይ በደረሰ የፈንጂ አደጋ የአስር ሰዎች ህይወት ማለፉ ይታወሳል።

አደጋው የደረሰው ዛሬ ጠዋት 14 ሰዎችን አሳፍሮ ከአሶሳ ወደ ቶንጎ ይጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ፥ ቤጊ መገንጠያ በተባለ ስፍራ ላይ በደረሰ የፈንጂ አደጋ ነው።

በአደጋው በተሸከርካሪው ተሳፍረው ከነበሩት ውስጥ የአስር ሰዎች ህይወት ሲያልፍ፥ አራት ተሳፋሪዎች ደግሞ ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ቤጊ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው ይገኛል።

ምንጭ፦ ፋና ብሮድካስቲንግ
@tsegabwolde @tikvahethiopia